Co.Market / ኮ-ገበያ
537 subscribers
5.06K photos
81 videos
3 files
2.47K links
  📲+251 9 11 81 16 72
https://ermitheethiopia.com

👉
Download Telegram
🌙እንኳን አደረሳችሁ ለመላው
🕌
እስልምና ተከታዮች በሙሉ
መልካም በአል
.....ያልተማረ ይግደልህ.....

"ትናንትን አፈቀርኩት"ዛሬን ግን ጠላሁት
አፌን ለሆድ ብቻ ሲጮህ አገኘሁት፡፡
ትንሽ መግፋት ቢቻል ጊዜን ወደ ኋላ
እኔስ በተሰየምኩ ካባቴ ፊት ለፊት ከአያቴ በኋላ
ወይ ታሪኬ ሊፃፍ ወይ ግፌ ሊሰላ፡፡

አባባ ገድልህን ለምን ነው የነገርከኝ?
ለትናንት አሻቅለህ ዛሬ አስጠላኸኝ
ብትከፍተው ገለባ
ሕይወት ትግል አልባ፣ ትግሉም ሕይወት አልባ
የተማረ ይግደለኝ ብለህ አጓግተኸኝ
ፊደል ከቆጠረ ቁጥርን ከደመረ ለሆዱ ካደረ መንጋ መሀል ጣልከኝ

"እኔም ተማከርኩልህ" ተመራመርኩልህ
የመብት አቡጊዳ ትግሌን ጀመርኩልህ
መብሌን አትንኳት ብዬ ፎከርኩልህ
ኧረ በሞትኩልህ
ይልቅስ ልንገርህ" ሞትክን በተማረ መመኘትክን እርሳው
ጽድቁን ከፈለግከው
ፊደል ያልቆጠረው ያገሬ ገበሬ ተኩሶ ይጣልህ፣
ይግደልህ ከማሳው፡፡

(ቼበለው መኩሪያ፣ ማለዳ፣ 1993)

ሃሳብ መስጫ ቻናሉን ለማጋራት
➷ ➷
@ermitheEthiopia
ድሮ ➡️“አውደ አመት አመት-ድገምና፣
የአባብዬን ቤት-ድገምና፣
የእማምዬን ቤት-ድገምና፣
ወርቅ ይፍስስበት፡፡ ዘንድሮ➡️የወንዜው ነብር፣
ሊሰጠኝ ነው ብር ሳይመነዘር፣
ያውም በዶላር፡፡
የወንዜው ሳቢሣ፣
ሊሰጠኝ ነው አምሳ፡፡ ያማረ ቆንጆ በዓል ተመኘሁ ለሁላችሁም @ermitheethiopia
🌿🌿 አስተማሪ ታሪክ 🌿🌿

ዛፍ➱ ቆራጩ
📜
ከዕለታት በአንዱ ቀን በጣም ጠንካራና ጎበዝ ዛፍ ቆራጭ እንጨት ነጋዴ ጋር ሄዶ እንዲቀጥረው ጠየቀው እሱም ተቀበለው። ደሞዙም በጣም ጥሩና የስራውም ሁኔታ ተስማሚ ነበር።
በዚህ ምክንያት ዛፍ ቆራጩ ጥሩ ነገር እንደሚያደርግ አስቆራጩ ነጋዴ ተማምኗል። አለቃውም መጥረቢያ ከሰጠው በኋላ ዛፎቹን እየቆረጠ የሚያጋድምበትን ቦታ አመለከተው።

በመጀመርያው ቀን ቆራጩ 15 ዛፎችን ቆርጦ አመጣ። አለቃውምᐸᐸእንኳን ደስ አለህ በዚህ ስራህ ቀጥልበት።>>አለው።
እሱም በአለቃው ቃል እጅግ ተነሳሳ በቀጣይም ቀን በጣም በርትቶ ለመስራት ሞከራ ነገርግን 10 ዛፎችን ብቻ ይዞ ለመምጣት ቻለ። በቀጣይም ቀን የበለጠ ቢሰራም ይዞ ሊመጣ የቻለው 7 ዛፎችን ብቻ ነበር።

ከቀን ወደ ቀን ጥቂትና ያነሰ ዛፍ ብቻ ያመጣ ጀመር፤ እሱም ᐸᐸጉልበቴ ደክሟል ማለት ነው..>> ብሎ አሰበ። እሱም ወደ አለቃው ይቅርታ ለመጠየቅ አመራ፣ ምን እየሆነ እንዳለ ሊገባው እንዳልቻለ ነገረው ...
አለቃውም ᐸᐸመቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ መጥረቢያህን የሳልከው(የሞረድከው?>>) በማለት ጠየቀው። ᐸᐸ የሳልከው? መጥረቢያውን ለመሳል ጊዜ አልነበረኝም፣ በጣም በስራ ተወጥሬ ነበር.. ዛፎችን በመቁረጥ ሲበዛ ተጠምጄ ነበር።>> ብሎ መለሰለት።

የታሪኩ መልዕክት 💌💌💌
አብዛኞቻችን ክህሎታችንን (skill) አናዳብርም(update) ወይም አናሳድግም። የምናውቃትን ነገር ብቻ
የሙጥኝ ይዘን በቂዬ ነው እንላለን ።
ከደህና ጥሩ ይሻላል ከጥሩም ደግሞ በጣም ጥሩ አለ ስለዚህ ችሎታችንን ወይንም ክህሎታችንን በየጊዜው መሳላችን ወይም መሞረዳችን ለስኬታችን ቁልፍ ነው።

@ermitheethiopia


ምንጭ @ ethio fiction