Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ዘመን ጳጉሜ 3 ቀን 2016 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK
👍2🙏1
ኮንስትራክሽን ክሌም

         
💫የኮንስትራክሽን ክሌም ለመስራት የውሉ የክፍያ መንገድ ላምፕ ሰም ወይስ አድሜዠርመንት የሚለውን መለየት ግድ ነው።

🚧የውሉ አይነትም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(DBB) ወይም ዲዛይን ቢዩልድ(DB) ስለመሆኑ  መለየት ይገባል።

⭐️DBB እና DB የተለያየ ጀኔራል ኮንዲሽን ይጠቀማሉ።

❇️ለምሳሌ FIDIC 2017 Red Book ለ DBB እና Yellow Book ለ DB መጠቀም ይቻላል።

▶️የክፍያ መንገዱ ላምፕ ሰም ወይም አድሜዠርመንት መሆኑ ግን የጀኔራል ኮንዲሽን እንድትቀይር አያስገድድም።

🏷ለምሳሌ ፒፒኤ 2011 ቨርሽን ለሁለቱም የክፍያ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

▶️ስፔሻል ኮንዲሽን ላይ የተለወጠ የጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ ያለ እንደሆነ ማረጋገጥም ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት።

⏺ከዚህ በኋላ ለክሌሙ አግባብነት ያለውን የውል ድንጋጌ፣የህግ ድንጋጌ እና የጀኔራልና ስፔሻል ኮንዲሽን ድንጋጌ መለየትና መስፈርቱን የሚያሟላ ክሌም ማዘጋጀት ይቻላል።

▶️ከዚያም ክሌሙ ለአማካሪ፣ለዲስፒውት ሪቪው ቦርድ፣ለአርቢትሬሽን ወይስ ለፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባው ለመለየት ጀኔራል ኮንዲሽኑን እና በዋናነት ስፔሻል ኮንዲሽኑን ማየት ይገባል።

Via ጉባዔ አሰፋ

@etconp
👍8
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

ተማሪዎች እና ወላጆች የፈተናውን ውጤት ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ።

ውጤት የሚታየው ፦

► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et

► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

► በቴሌግራም ቦት 👉 https://t.me/EAESbot ላይ ነው።

ከፍተኛ የኔትዎርክ መጨናነቅ ስለሚኖር በትዕግስት ይሞክሩት።

በ2016 ዓ / ም ለፈተናው ከተቀመጡት ከ684 ሺህ በላይ ተማሪዎች 36,409 ተማሪዎች (5.4 በመቶ) ናቸው በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን 50% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡት።

ምንም እንኳን በተማሪ ቁጥር ደረጃ ከአምናው የቀነሰ ቢሆንም በቀጣይ የትምህርት ዘመንም የሬሜዲያል ፕሮግራም ይኖራል።

via TIKVAH

@etconp
👍2🙏2
👉የዛሬው ክፍል፦ ምክር ነው።

🚧የኮንስትራክሽን ሠራተኛ (አርክቴክት፣ መሐንዲስ፣ ሙያተኛ) በሙሉ ሁለተኛ ፈጣሪ ነው፣ የከበረ ሙያ፣ የጥበብ ቁንጮ ነው። በተሰማራንበት ፕሮጀክት ሁሉ የሚያስከብር ንግግር፣ የሚያሳምን ሀሳብ፣ ምክንያታዊ የሆነ መልስ መስጠት አለብን።

🏷ምንም ነገር ከመሥራታችን በፊት ማሰብ፣ መለካት፣ ደጋግሞ ለራስ ማዳመጥ፣ ትክክለኛ መሆናችንን በማስረጃ ማመን፣ ... እነዚህን ካለፍን በኋላ ለሌሎች ማስተላለፍ ወይም በሥራው ላይ የተግባር ውሳኔ ማስተላለፍ አለብን።

💫የግንባታ ሠራተኛ የሚያስተውል፣ የተረጋጋ፣ የሚያውቅ፣ የሚያሳምን፣ የማይጮህ፣ የሚለካ ደርባባ መሆን ይገባዋል።

⭐️ስለኮንስትራክሽን ሕግ እና አንዳንድ የሥራ ሂደቶች ጠቃሚ መረጃዎች ማድረሳችንን እንቀጥላለን።

@etconp
👏27👍4
ጥያቄ፦ አንድ ተቋራጭ ግንባታውን አጠንቅቆ ባስረከበው ሕንጻ ላይ በሥራ ጉድለት (ግድፈት) ወይም በመሬቱ የአፈር አለመርጋት የተነሳ በሕንጻው ላይ ለሚደርስ ጥፋት ተቋራጩ ተጠያቂ የሚሆነው እስከስንት ዓመት ድረስ ባለው ጊዜ ችግሩ ከተፈጠረ ነው? @etconp
Anonymous Quiz
47%
ሀ) እስከ አንድ ዓመት
16%
ለ) እስከ አምስት ዓመት
32%
ሐ) እስከ አሥር ዓመት
5%
መ) እስከ ሃያ ዓመት
👍19👏5😭4
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
👉ውድ ቤተሰቦቻችን

⭐️የዚህ ጥያቄ መልስ ዋናው ቻናላችን ለቀነዋል👇👇

https://t.me/ETCONp/11520
🙏2👍1
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮጵያን ሄራልድ ጳጉሜ 4  ቀን 2016 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONp
❤2😭1
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮጵያን ሄራልድ ጳጉሜ 4  ቀን 2016 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONp
🙏2❤1👍1
Ethiopian Construction Vacancy & Tender pinned «👉ውድ ቤተሰቦቻችን ⭐️የዚህ ጥያቄ መልስ ዋናው ቻናላችን ለቀነዋል👇👇 https://t.me/ETCONp/11520»
👉NEW VACANCY

❇️የስራው መጠሪያ: Architects and Interior Designers

🚧የስራው አይነት: በተመደቡበት የሚሰራ - ቋሚ

🏷የስራው ዘርፍ: #አርክቴክቸር_እና_የከተማ_ፕላን

💫የስራው ቦታ: አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

⭐️የትምህርት ደረጃ: የመጀመሪያ ዲግሪ

⏺የልምድ ደረጃ: መካከለኛ

▶️የተፈላጊ ሰው ብዛት: 2

▶️ደሞዝ/ክፍያ: ወርሃዊ

🔰የማመልከቻ ማብቂያ ቀን: September 24th, 2024

📜የስራው ዝርዝር:
Are you an architect or interior designer with a passion for creativity and a keen eye for detail? Do you excel in transforming spaces with innovative designs and breathtaking visualizations? If so, we want you on our team!

🎲Who We’re Looking For:

- Architects and Interior Designers with a strong portfolio showcasing exceptional design and visualization skills.
- Proficiency in Revit, 3ds Max Vray, and Lumion is a must.
- Creative problem solvers with the ability to turn ideas into reality.
- Detail-oriented professionals who thrive in a collaborative environment. 

📩Send your portfolio👇

adaptivedesignset@gmail.com

__

@etconp
👍3🙏2
🌼🌼 እንኳን አደረሳችሁ🌼🌼

➡️ውድ ቤተሰቦቻችን አዲሱ አመት የሰላም፤ የፍቅር፤ የአንድነት፤ የብልፅግናና የደስታ ይሆንላቹ ዘንድ ልባዊ ምኞታችን ነው!

🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት 🌼🌼

@ETCONpWORK
❤6👍1
👉ኢትዮጵያ አየር መንገድ በ50 ሚሊዮን ዶላር የሚያስተዳድራቸውን ሪዞርቶች ሊያዘመን ነው

🚧የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አካል በሆነው ስካይላይት ሆቴል አስተዳደር ክፍል እንዲከናወን የተላለፉትን አራት ሪዞርቶች ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ የ50 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት እንደሚጠይቅ ታወቀ።

የስካይላይት ሆቴል አስተዳደር በሁለት ክፍሎች ተከፍሎ፣ የአየር መንገዱን ባለአምስት ኮከብ ሆቴል የሚያስተዳድረው ክፍል፣ እንዲሁም የተረከባቸውን ሪዞርቶች ለማስተዳደር የተመደበውን ክፍል በሌላ በኩል የሚመሩ የየራሳቸው ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጆች ተሹመውላቸዋል።

እነዚህ ሁለት የሥራ ክፍሎች ሪፖርት የሚያቀርቡላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የወንጪ፣ የጎርጎራ፣ የሀላላ ኬላ እንዲሁም የጨበራ ጩርጩራ ሪዞርቶችን አጠናቆ ወደ ሥራ ለማስገባት በአጠቃላይ 50 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀን ገደብ ባልተቀመጠለት የማስተዳደርና የዕለት ተዕለት ሥራዎችንም የማስፈጸም ኃላፊነቱ፣ ሪዞርቶቹ የሚያስፈልጓቸውን ያላለቁ ግንባታዎች ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ወጪ በአየር መንገዱ እንደሚሸፈን ኃላፊው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በበላይነት በሚመሩት በ‹ገበታ ለአገር› እና በ‹ገበታ ለትውልድ› ፕሮጀክቶች ተሠርተው፣ የአስተዳደር ሥራቸው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተላለፉት መካከል የወንጪ ሪዞርት የማስታዋወቅ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ (Soft Opening) መከናወኑን፣ ሀላላ ኬላም በተመሳሳይ ባለፈው በነሐሴ ወር ሥራ መጀመሩን አሳውቀው፣ በጨበራ ጩርጩራ ግን የቀሩ የሚሠሩ ሥራዎች መኖራቸውንና ጎርጎራም በተመሳሳይ ሒደት ውስጥ እንደሚገኝ አሳውቀዋል።

አቶ ለማ ‹‹ሆቴሎች ሥራ ሲጀምሩ ምንጊዜም እስከ ሦስት ወር ያለው የመጀመርያ ጊዜ ያለው የሥራ ጫና የሚታይበት፣ የሥራ ሒደት ፍሰቱ ልከኝነት የሚገመገምበትና በሙሉ አቅሙ እስኪሠራ ድረስ በዚህ ሁኔታ እየሠራን ነው፤›› ብለዋል።

በአራቱም ሪዞርቶች ያልተጠናቀቁ ሥራዎች ለመጨረስና ሙሉ ለሙሉ በይፋ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚፈጀው የገንዘብ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ አቶ ለማ ‹‹ይህንን በምንገመግምበት ጊዜ ሪዞርቶቹ የሦስት ኮከብ ደረጃ ነው ያላቸው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስካይላይት ሆቴል ደግሞ ባለ አምስት ኮከብ ደረጃ ነው ያለው፡፡

ስለዚህ እኛ እነዚህን እንድናስተዳድር ከመንግሥት የሚጠበቅብን በባለአምስት ኮከብ ደረጃ ነው ይህም እያንዳንዱ ሆቴል የተለያዮ የኢንቨስትመንት ደረጃዎችን እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል በዚህ ደረጃ ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር የሚፈጁ ይሆናል፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ገንዘቡ በአንድ ጊዜ ወጪ የሚደረግ እንደማይሆን የገለጹት የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ወጪው ምንም ያህል ቢሆን አየር መንገዱ ሪዞርቶቹን ወደ አምስት ኮከብ ደረጃ ለማምጣት የሚያስፈልገውን ኢንቨስትመንት እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።

የስካይላይት ሆቴል አስተዳደር አሁን ከመንግሥት ከተረከባቸው በተጨማሪም፣ መንግሥት አፈጻጸማቸውን ገምግሞ፣ አሁን በግንባታ ላይ ያሉትን በገረዓልታ፣ ሐይቅና ጅግጅጋ ላይ የሚሠሩትን ሪዞርቶችም እንዲያስተዳድሩ ዕጩ እንዲያደርጋቸው ፍላጎት እንዳላቸውም ጠቅሰዋል።

አሁን የተረከባቸውን በሚያስተዳድራቸው ሪዞርቶች ሰዎች በመኪና ከመሄድ ይልቅ በአየር ትራንስፖርት ሐሳብ ካላቸው በሚል፣ አንዳንዶቹ ሪዞርቶች በውኃ የተከበቡ መሆናቸውንም ታሳቢ በማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስካይላይት ሆቴልስ የተለዩ በውኃና በየብስ ላይ ማረፍ የሚችሉ ትንንሽ አውሮፕላኖች (Amphibious Aircraft) አስገብቶ ለማሰማራት የዋጋ ጥናቶችን አከናውኖ የግዥ ሒደቱ ላይ ውሳኔ ለመስጠት የመጨረሻ ክፍል ግምገማ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ለማ ሦስት ዓይነት የአውሮፕላን ዓይነቶች ተለይተው ለግምገማ መቅረባቸውንና ግዥውም እንደሚፈጸም ገልጸዋል።

ምን ያህል ገንዘብ ይፈጃል? የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚወሰነው በሚመረጠው የአውሮፕላን ዓይነት መሆኑን ገልጸው፣ ‹‹ትንሽ ገንዘብ አይደለም የሚሆነው፣ ግን ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዕድገት የምናበረክተው አስተዋጽኦ ስለሆነ፣ እኛ አሁን ስለገንዘቡ ብዙም ችግር የለብንም፤›› ብለዋል።

አየር መንገዱ እ.ኤ.አ. በ2035 በዓመት 100 ሚሊዮን ደንበኞች ማስተናገድ የሚያስችለውን በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚያስገነባው የኤርፖርት ከተማ ከሚፈጥራቸው ዕድሎች አንዱም፣ አየር መንገዱ 15 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስቀመጠውን ዕቅድ እንዲያሳካ ማስቻሉ ነው ብለዋል።

በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ መንገደኞች ከ65 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑት ተላላፊ (Transit) መንገደኞች መሆናቸውንና ወደ አገሪቱ ገብተው ኢንቨስት እንደማያደርጉ ሪፖርተር ከአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ባለሙያዎች ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

@etconp
👍8❤1
👉የጨረታ ማስጠበቂያ (Bid Security Bond)

🚧የጨረታ ማስጠበቂያ ለተቋራጮች የወጣ ጨረታ (በተለይ ክፍት ጨረታ /open tender/) የጨረታ ማስጠበቂያ መያዣ በማረጋገጫ ሰነድ ላይ በቴክኒካል ሰነድ (Technical Documents) እንዲካተት ይጠበቃል።

ይህ የጨረታ ማስጠበቂያ (Bid Security Bond) በ’ PPA (section 1)  “instruction to bidder (ITB) አንቀጽ አሥራ ስድስት (article 16) ላይ እንደተመለከተው አንድ ተጫራች የወጣውን ጨረታ ሞልቶ ካስገባ በኋላ ጨረታውን ቢያሸንፍ እና አሸናፊነቱን የሚገልጽ የቅቡልነት ደብዳቤ (Acceptance Letter) ከተጻፈለት በኋላ ሀሳብ ቀይሮ “የተወዳደርኩበትን ጨረታ ትቼዋለሁ፣ የግንባታ ውል መፈራረምም ይሁን ግንባታውን ማከናወን አልፈልግም” ቢል ጨረታውን ለማከናወን የወጣውን ወጪ ለመሸፈን እና በደረጃ ቅደም ተከተል መሰረት ለሌሎቹ አሸናፊዎች ጥሪ ለማድረግ አልያም እንደገና ውድድሩን ለማከናወን የሚያስችል ገንዘብ ተደርጎ ይታሰብና ጨረታውን ላወጣው አካል የሚሰጥ የባንክ ማረጋገጫ ደረሰኝ (Certified Payment Order - CPO) ነው።

የጨረታ ማስከበሪያ(Bid Security Bond) በ'PPA ITB 16.2 መሰረት በካሽ ወይም በተፈረመበት ቼክ ወይም በክፍያ ማዘዣ ወይም በተቀናሽ ሂሳብ ደብዳቤ ወይም በየትኛውም የባንክ ዋስትና ማረጋገጫ ሊገለጽ የሚችል ሆኖ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን መጠን ያህን የሆነ ገንዘብ ወይም ግምቱ ከዚያ የማያንስ ንብረት/ዋስትና ሊሆን ይችላል።

በውጪ ባንኮች የተሰጠ ዋስትና ከሆነ በሀገር ውስጥ ባንኮች በኩል ዋስትናውን የማረጋገጫ ሰነድ መቅረብ አለበት እንጂ የውጪ ባንኮች ዋስትና በቀጥታ ተግባራዊ ሊደረግ አይችልም።

ማንኛውም አስተማማኝ የጨረታ ማስከበሪያ የሌለው የጨረታ መልስ ሰነድ (Bid response) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውድቅ መደረግ ይኖርበታል።

ከአንድ በላይ የሆኑ ማኅበራት ላቀረቡት የጨረታ ሙሌት ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ በጋራ ሲያስገቡ የሁሉም ድርጅቶች ስም በጨረታ ማስከበሪያው ላይ መዘርዘር ይኖርበታል።

የገንዘቡ መጠን በጨረታ ሰነዱ Bid Data Sheet ITB Article16ን ተመርኩዞ በወጣው የጨረታ ሰነድ Bid Data Sheet section ሥር ባለው Preparation of Bids በሚለው ሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰው መጠን የተገለጸው መሆን አለበት።

መጠኑ እንደፕሮጀክቱ ስፋት፣ እንደፕሮጀክቱ ወሳኝነት እና እንደተገመተው የጨረታ ማፍረስ ስጋት ታይቶ በጨረታ አውጪው አካል ሊወሰን ይችላል ነገር ግን አሸናፊው ተጫራች የአሸናፊነቱን ደብዳቤ ተቀብሎ ሥራውን መጀመር የሚችል ከሆነ በጨረታ ሰነዱ Bid Data Sheet & ITB 16.5 መሰረት ሙሉ ለሙሉ ተመላሽ ይሆናል።

የጨረታ ማስጠበቂያ (ማስከበሪያ) ገንዘብ ለተጫራቹ የሚመለስበት ጊዜ በ’ITB, article 16 (16.2) መሰረት ለ28 ቀናት በባንክ ከቆየ በኋላ መሆን አለበት።

በህግ ረገድ ስለዋስተና አይነቶች የሚያብራራው የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 646/2001 ዝርዝር አንስቷል።

የጨረታ ማስከበሪያ ለተጫራቹ የማይመለስባቸው ምክንያቶች፦

[1ኛ] ተጫራቱ ጨረታውን ቢያሸንፍም ሥራውን ተዋውሎ ለመሥራት ፍቃደኛ ካልሆነ ወይም ሀሳብ ከቀየረ፣

[2ኛ] ተጫራቹ የዋጋ ማስተካከያ በPPA ITB clause 27 (በታወቁ ስህተቶች መሰረት የተሞላ አግባብነት የሌለውን ዋጋ ስለማውጣት የተደነገገ አንቀጽ) መሰረት የተደረገ የዋጋ ማስተካከያ ርምጃዎችን አልቀበልም ካለ::

[3ኛ] አሸናፊው ተጫራች ሥውል ፈጽሞ ራውን ለመሥራት ፈቃደኛ ቢሆንም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ውል መፈረም ካልቻለ ወይም ሌሎች የውል ማስከበሪያዎችን ማቅረብ ካልቻለ ነው።

🔰የቴሌግራም ቻናላችንን ስለሚከታተሉ እጅግ እናመሰግናለን።

🌟መሐንዲሶችን እና አርክቴክቶችን ይጋብዙልን! ቤተሰብ እንሁን።

Link: t.me/ETCONp

ማንኛውንም ሀሳብዎን ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/ETCONpBOT ላይ ይጻፉልን።

@ETCONpWORK
👍8❤1
👉ተቋራጩ የሚጠበቅበት ሥለሥራ ሪፖርት ማድረግ ግዴታ

በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3025 (1) እና (2) መሰረት ተቋራጩ የተከናወኑ ሥራዎች የደረሱበትን ሁኔታና እንዲሁም የሥራውን ዋጋ፣ ለሥራ የተጠቀማቸውን ነገሮች (ግብአቶችን የሰው ኃይል እና ማሽኖች/እቃዎች) ታሳቢ ያደረገውን ወጪ ላሠሪው አካል የማሳወቅ ግዴታ አለበት።

በውሉ ላይ የተገለጸ ተቃራኒ ቃል የሌለ እንደሆነ ተቋራጩ በየወሩ መጨረሻ ለአሠሪው ማስታወቅ (ሪፖርት ማቅረብ) እንዲኖርበት ይገደዳል።

[ስንቶቻችሁ ሥራ ቦታ ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ነው?]


የቴሌግራም ቻናላችንን ስለሚከታተሉ እጅግ እናመሰግናለን። መሐንዲሶችን እና አርክቴክቶችን ይጋብዙልን! ቤተሰብ እንሁን።

ክብር ለአርክቴክቶች እና መሐንዲሶች!

🎲ሌላኛው የ ስራ ቅጥር እና ጨረታች ሚወጡበት ቻናል ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
❤2👍2
👉ሞሮኮ የዓለማችን ግዙፍ ስታዲየም ግንባታ ዲዛይን ይፋ አደረገች

ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ የ2030ን ፊፋ ዓለም ዋንጫ ከስፔን እና ፖርቹጋል ጋር በቅንጅት የማዘጋጀት እቅድ አላት።

48 ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚሳተፉበት የሚጠበቀው ይህ የዓለም ዋንጫ በ20 ስታዲየሞች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ስፔን ለዚህ ውድድር 11 ስታዲየሞችን እንደምታዘጋጅ ስትገልጽ ቾርቹጋል ሶስት እንዲሁም ሞሮኮ ደግሞ ስድስት ስታዲየሞችን እንደሚያዘጋጁ አስታውቀዋል።

ሞሮኮ ለዚህ ውድድር ከምታዘጋጃቸው ስድስት ስታዲየሞች መካከል አንዱ "ሀሰን ሁለተኛ" የተሰኘ ስታዲየም የግንባታ ዲዛይን ይፋ አድርጋለች።

ይህ ስታዲየም ሲጠናቀቅ 115 ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ይኖረዋል የተባለ ሲሆን በግዝፈቱ ከዓለም ትልቁ እንደሚሆን ተገልጿል።

የሞሮኮ ብዙሀን መገናኛዎች እንደዘገቡት ከሆነ አዲሱ ስታዲየም ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ካዛብላንካ 38 ኪሎ ሜትር ላይ ይገነባል።

በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ግንባታው ይጀምራል የተባለው ይህ ስታዲየም በ2028 ይጠናቀቃል ተብሏል።

ዓለም አቀፉ የስፖርት ፌዴሬሽን ወይም ፊፋ የ2030 ዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ ሀገራትን እስካሁን በይፋ አላሳወቀም።

ውድድሩን ለማዘጋጀት እየተፎካከሩ ካሉ ሀገራት መካከል ሞሮኮ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል።
ይሁንና ሶስቱ ሀገራት የፍጻሜውን ውድድር ማን ያስተናግድ የሚለውን እስካሁን አልተስማሙም።

@etconp
👍4👏1
👉የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት የላቀ ብቃት ያካበቱ ባለሙያዎችን ለማፍራት ማስቻሉ ተገለጸ

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት በሲቪልም ሆነ በሃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች የላቀ ብቃት ያካበቱ ባለሙያዎችን ማፍራት መቻሉ ተገለጸ።

የግድቡ ግንባታ ፕሮጀክት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኤፍሬም ወልደኪዳን (ኢ/ር)፤ ለፕሮጀክቱ ስኬት ከዲዛይን ጀምሮ እስከ ግንባታው የኢትዮጵያውያን ሚና የላቀ መሆኑን አስታውሰዋል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጀመር በአንድ ጊዜ እስከ 15 ሺህ ዜጎች በግንባታው ሂደት ላይ በተለያዩ ሙያዎች ይሳተፉ የነበሩ ባለሙያዎች ሌት ከቀን በመትጋት ለግድቡ እውን መሆን ዘላለማዊ አሻራቸውን በማሳረፍ የሚያኮራ ተግባር ፈፅመዋል ብለዋል።

በግንባታው የረጅም ዓመት ልምድ በቀን ሰራተኝነት የጀመሩ በርካታ ወጣቶች አሁን ላይ ከፎርማን እስከ ሱፐርቫይዘርነት መድረሳቸውን አብራርተዋል።

በዚህም በሲቪልም ሆነ በሃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች የላቀ ብቃት ያካበቱ በርካታ ባለሙያዎችን ማፍራት ስለመቻሉ መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ግድቡ 13 ተርባይኖች እንዳሉት ገልጸው፤ የጀነሬተር አካል እስከ 12 ሜትር ዲያሜትርና ከ460 ቶን በላይ ክብደት ስላለው በትራንስፖርት አጓጉዞ ለማድረስ ፈታኝ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ነገር ግን በፕሮጀክቱ ግንባታ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አቅማቸውን በማጎልበት ዛሬ ላይ ግብዓቶችን በስፍራው እንዲገጣጠሙ ማድረግ የሚችሉበት አቅም ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
በመሆኑም በቀጣይ ኢትዮጵያ

ለምትገነባቸው የሀይድሮ ፓወር ፕሮጀክቶች የሙያ ብቃትና ዝግጁነት እንዲኖር አስችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

የግድቡ ግንባታ ሲጀመር ተቀጥረው ይሰሩ እንደነበር ያስታወሱት የኬ.ቲ ኢንዱስትሪያል ሶሉሽን ሥራ አስኪያጅ ሞላ አስማረ፤ በሂደት የራሳቸውን ድርጅት ከፍተው ለተርባይን ማቀዝቀዣ ክፍል አካል የሆነውን ራዲያተር በራሳቸው መስራት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

አብዛኛውን የፕሮጀክቱን ግብዓት በራሳቸው መሥራት እንደሚችሉ ገልጸው፤ ከአቅም ግንባታ ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ያስችላልም ብለዋል፡፡

በግድቡ ላይ በተለያዩ ሙያዎች ላይ የተሳተፉ በርካታ ወጣቶች በየዘርፉ የተሻለ የሙያ ደረጃ ላይ የደረሱ እንዳሉም ተናግረዋል።

Via FBC

@etconp
❤6👍3
👉የከተማ መሬት መረጃ አያያዝ ስርአት / ካዳስተር/ ምንነትና የሚያስገኘው ጠቀሜታ

🚧ካዳስተር ማለት የመሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡

ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) አንዱ ሲሆን የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እንዲሁም አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ይሆናል፡፡

ሁለተኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል ይታወቃል ይህም የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ. እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን የሚያካትት ሲሆን እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

ካዳስተር ህጋዊ ካዳስተር ፤ፊስካል ካዳስተር እና ሁለገብ ወይም ሁሉን አቀፍ ካዳስተር ተብሎ በሦስት ይከፈላል፡፡  

ህጋዊ ካዳስተር ተብሎ የሚጠራው ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም የትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታው የይዞታ ዋስትና የሚረጋገጥበት ይሆናል፡፡

ሁለተኛው ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡

ሦስተኛው የካዳስተር ዓይነት ሁለገብ ወይም ሁሉን አቀፍ ካዳስተር የሚባለው ሲሆን በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ-ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡

የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡

በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፤ የተሞከረውም ሁለ-ገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር፤ ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡

በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለ-ገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን በመገንዘብ በአገራችን በሚገኙ ከተሞች ተግባራዊ ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል፡፡

መሬት በቁጠባ ሊተዳደር የሚገባው አላቂ ሃብት በመሆኑ በአጠቃቀም እንዳይባክን ብክነት የሚወገድበትን አሰራር መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

የመሬት መረጃ አያያዝ እንደ ወቅቱ የቴክኖሎጂ ደረጃ መንግስታት መሬትን ለማስተዳደር እንደሚከተሉት የመሬት አስተዳደር እንዲሁም መረጃን ዘመናዊ ለማድረግ ካላቸው ቁርጠኝነት ጋር ተያይዞ የሚወሰን ሲሆን ይህም በፖሊሲዎች እና በህግ ማዕቀፎች ላይ የሚንጸባረቅ ይሆናል፡፡

በዋናነት ካዳስተር መረጃ ላይ በመመርኮዝ በከተሞች የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ የቋሚ ንብረት ሃብት ወደ ገበያ እንዲገባ ከማስቻል ባለፈ ዜጎች የኢኮኖሚው እድገት እንቅስቃሴ አካልና ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፤ ይህ ደግሞ መልካም አስተዳደርን እውን ከማድረግና ልማታዊነትን ከማረጋገጥ አንፃር ትርጉም የሚሰጠው ሆኖ እንዲተገበር ተከታታይነት ያለው ሥራ በእቅድ ይዞ መስራት ያስፈልጋል፡፡

ዘመናዊ እና የተደራጀ የከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባ ስርዓት ዝርጋታ እውን መሆን፤ ውስን የሆነውን የከተማ መሬት በተገቢው መንገድ ለተገቢው አገልግሎት ለማዋል ብሎም በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ መስጠት እንዲቻል ከማድረጉም በላይ የህብረተሰቡን የመሬት ይዞታ ባለቤትነት ዋስትናን በማረጋገጥ የከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ያስችላል፡፡

የከተማ መሬት መረጃ ሥርዓትን በከተሞች ተግባራዊ ማድረግ በዘርፉ የሚስተዋሉትን የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮች ለማድረቅ፤ ለልማት የተመቻቸ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ለመፍጠር፤ ህገ-ወጥነትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል፤ የከተሞችን የገቢ አቅም ለማሳደግ፤ በይዞታ የመጠቀም መብትንና የንብረት ባለቤትነት ዋስትናን ለማረጋገጥ፤ ቀልጣፋ፤ ግልፅና ተጠያቂነት ያለበት የመሬት አስተዳደርን ለማረጋገጥ እንዲሁም የከተማ መሰረተ-ልማትን ለማስፋፋትና በአግባቡ ለማስተዳደር ትልቅ አቅም ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ በአገራችን የህጋዊ ካዳስተር ዝርጋታ በአተገባበር ሂደት እየጋጠሙ የሚገኙ ዋና ዋና ችግሮችን ለመቅረፍና አፈጻጸሙን ከፍ ለማድረግ  የመሬት ይዞታ መዝጋቢ ተቋማት፣ የመሬት ልማት ማኔጅመንትና የከተማ ፕላን ወጥና ተናባቢ የመሬት ዕቅድ በማውጣት ለዕቅዱ መሳካት በጋራ ሊረባረቡ ይገባል፡፡

እነዚህን ሥራዎች ለማከናወን የሚያስችል የፋይናንስ አቅም መፍጠር፣ ይሄን ስራ ለማቀላጠፍና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግና ፈፃሚውና አስፈፃሚው፣ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ነዋሪው በአሰራሩ ላይ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ እና በስራው ላይ ሙሉ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

@etconp
👍9
👉ሩዋንዳ በ300 ሚሊዮን ዶላር "Kigali Innovation City" ተብሎ የሚጠራ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም እየገነባች ነው።

🚧ይህ ተቋም የአፍሪካ ሲልከን ቫሊ (Silicon Valley of Africa) ተብሎ ሊገለጽ የሚችል ነው ተብሏል።

🏷በ61 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው ይህ ተቋም በውስጥ አራት ምርጥ ዩኒቨርስቲዎች፣ ለቢሮ የሚሆኑ ቦታዎች፣ የስታርት አፕ ቢዝነስ ማበልጸጊያ ክፍሎች ይኖሩታል።

💫በዚህ ተቋም ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሥራ ዕድል የሚያገኙ ሲሆን፣ የተቋሙ ዓመታዊ የቴክኖሎጂ ኤክስፖርት 150 ሚሊዮን ይደርሳል።

@etconp
👏2❤1👍1