Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
አዲስ አበባ መንገዶች ለወሰን ማስከበር ሥራ ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ካሳ ከፈለ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት ባከናወናቸው የመንገድ ግንባታ ሳቢያ ለተነሱ መሠረተ ልማቶች እና የመኖሪያ ቤቶች 1.8 ቢሊዮን ብር የካሳ ክፍያ መፈጸሙን ገለጸ።

መስሪያ ቤቱ በዘንድሮው በጀት ዓመት በሚገነባቸው መንገዶች እና ከሁለተኛው ዙር የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ 546 የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች እንደሚነሱ አስታውቋል።

መስሪያ ቤቱ በ2016 ዓ.ም 1,140 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አከናውኗል።

በመንገድ ግንባታ እና ጥገናው ሳቢያ 682 ቤቶች እንዲነሱ መደረጋቸውን የገለጸው መስሪያ ቤቱ፤ ከ1,200 በላይ በሆኑ የመብራት እና የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ላይም ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል።

ቤቶቹ እና መሰረተ ልማቶቹ እንዲነሱ የተደረጉት፤ መንገዶች በሚገነቡበት “ወሰን ውስጥ የሚገኙ” በመሆናቸው ምክንያት ነው።

ባለስልጣኑ በመንገድ ሥራው ተነሺ ለሆኑ ነዋሪዎች እና መሠረተ ልማቱን ለገነቡ ተቋማት ተገቢውን ካሳ መከፈሉ ታውቋል።

ባለፈው ዓመት ለካሳ የከፈለው የገንዘብ መጠን 1.1 ቢሊዮን ብር መሆኑ ተገልጿል።

ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ተግባራዊ ማድረግ በተጀመረው የኮሪደር ልማት ለተከናወኑ የመንገድ ግንባታዎች፤ መስሪያ ቤቱ በተጨማሪነት 795 ሚሊዮን ብር ካሳ መክፈሉ ተጠቅሷል።

ይህ የካሳ ክፍያ የተፈጸመው “ለንግድ እና ለመኖሪያ ቤቶች ብቻ” መሆኑ ታውቋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መስሪያ ቤቱ በዚህ ዓመት ሊገነባቸው ካቀዳቸው መንገዶች ጋር በተያያዘ፤ 546 የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ከ1,800 በላይ የመብራት እና የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች እንደሚያነሳ ታውቋል።

@etconp
👍3❤1
👉"ተለዋጭ መጓገድ ለመገንባት ጥረት እያደረግን ነው" - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

🚧ከአዲስ አበባ - ጅማ - መቱ - ጋምቤላ መስመር በቡኖ በደሌ ዞን ደዴሳ ወረዳ ከጅማ ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለው መጓገድ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት መንገዱ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል።

⏺ችግሩ ለመቅረፍ በኢትዮጵያ መንገዶ አስተዳደር የጅማ መጓገድ ጥገና ዲስትሪክት ጊዜያዊ ተለዋጭ መጓገድ ለመገንባት ጥረት እያደረገ እንደሆነ አመልክቷል።

▶️በመኾኑም ተለዋጭ መንገድ በጥቂት ቀናት ውስጥ ተጠናቅቆ ለትራፊክ ክፍት እስኪደረግ ድረስ አሽከርካሪዎች በትዕግስት እንይጠባበቁ ጠይቋል።

💫ከመሃል ሃገር ለሚነሱ _ አሽከርካሪዎች የአዲስ አበባ - ነቀምት - በደሌ - መቱ - ጋምቤላ መሥመርን በአማራጭነት እንዷጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

Via ERA

@etconp
👍4
👉ከኖህ ሪል እስቴት ቤት ገዝተው የነበሩ ግለሰቦች ከውላችን ውጪ መሠረተ ልማት ያልተሟላለት ቤት ተረክበን ከፍተኛ ችግር ላይ ነን አሉ

⭐️ከኖህ ግሪን ፓርክ ሳይት መኖርያ አፓርታማ ገዝተው ከተረከቡ ከሁለት አመት በላይ እንደሆናቸው የሚናገሩት እነዚህ ግለሰቦች አሁን ድረስ መብራት እና ዉሀ እንኳን ስላልተሟላ ለመኖር አልቻልንም ብለዋል።

🚧በተደጋጋሚ ለድርጅቱ ጥያቄዎች ቢቀርብም አጥጋቢ መልስ አላገኘንም የሚሉት ነዋሪዎቹ ጉዳዩን ወደ ህግ ለመውሰድ እንደተገደዱ ለመሠረት ሚድያ አስረድተዋል።

💫በዚህ ምክንያት ቤታቸው መግባት ሳይችሉ አሁን ድረስ በቤት ኪራይ እንደሚገኙ የሚናገሩት ግለሰቦቹ ኖህ ሪል እስቴት ከዚህ ቀደም መሠረተ ልማቱን በወር ከ15 ቀን ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ በሚዲያ በኩል ቃል ገብቶላቸው እንደነበር አስታውሰው ግን ምንም ሳይሰራ ወራቶች እንደጠቆጠሩ ተናግረዋል።

🏷በዚህ ዙርያ ምላሽ ለማግኘት ቢሮው ድረስ ሄደው ቢጠይቁም አጥጋቢ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው አስረድተው አሁንም መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

📜መሠረት ሚድያ የኖህ ሪል እስቴት ባለቤቶችን በተደጋጋሚ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

Via Meseret Media

@etconp
🙏3
👉Canadian company PLAEX is introducing an innovative construction method inspired by LEGO, utilizing bricks that resemble construction sets

🚧These blocks are made from 90% recycled plastic, making them an environmentally friendly alternative to traditional building materials.

⭐️The PLAEX bricks offer several advantages:

📍Weight: They are 35% lighter than concrete.
📍Cost: They are 15-30% cheaper than traditional building materials.
📍Strength: Despite their lightweight nature, the bricks are stronger and more durable.
📍Flexibility: The bricks do not require mortar, allowing structures to be easily disassembled and reassembled.

📜Currently, these bricks are approved only for non-residential buildings.

⏺However, PLAEX aims to secure the necessary permits to use them for residential construction by next year.

@etconp
👍1
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት ጽ/ቤት ተወካይ ሃላፊ የነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ፀጋዬ #በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ሲፈለጉ የነበሩት በዛሬው ዕለት በእስካይ ላይት ሆቴል በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ተጠርጣሪው በኮሪደር ልማት ሽፍን በማድረግ ከመንግስት አሰራር እና ውሳኔ ውጪ በመደራደር ባልተገባ መንገድ ለግል ጥቅም ለማግኘት ሲል የካሳ ግምት በማናር ውስን የሆነዉን የህዝብ ና የመንግስትን መሬት ከአሰራር ውጪ በማሰተላለፍ ለግለሰቦች አላስፈላጊ ጥቅም በማዋል ፤ ተጠርጥረው በዛሬው ዕለት ከተሸሸጉበት እስካይ ላይት ሆቴል በቁጥጥር ሰር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪ ከሀገር ውጪ ወተዋል በማስባል የህግ ማስከበሩን እንዲስተጓል በማድረግ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል::

በተጨማሪም በክ/ከተማው ወረዳ 4 ዉስጥ በኮሪደር ልማት ኘላን ልማት ውስጥ የማይካተት ከመመሪያ እና አሠራር ዉጪ 6 መኖሪያ እና አንድ የንግድ ቤት የሆነውን ከዋይልድ አፓርትመንት የተባለ ህንፃ ባለቤት ጋር ተመሳጥረው ቤቶቹን እንዲፈርሱ በማድረግ እና ለህንፃው ማስፋፊያ እንዲሆን የሰጡ እና የመንግስት ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ግለሰቦች የእቃ የማጓጓዥያ ሳይከፈል እንዲነሱ በማድረጉ እንዲሁም ምትክ ቦታ እስጣቿለው በማለት አንደኛ ቦታ አስቀይርላቿለው ና የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀሎችን በማድረግ ህብረተሰቡ ሲያደናግር ና ያልተገቡ ጥቅሞችን ሲያደርግ እንደነበረ የአዲስ አበባ የፀረ ሙስና ግብረ ሃይል አስታውቋል::

@etconp
👍1
መመርያ_ቁጥር_1023_2016_ወደ_ኣገር_በሙገቡ_እቃዎች_ላይ_ከተጣለው_ማህበራዊ_ልማጥ_ቀረጥ_ነፃ_ይውሆኑ.pdf
984.8 KB
ወደ ሀገር በሚገቡ እቃዎች ላይ ከተጣለው ማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ የተደረጉ ዕቃዎችን ለመወሰን የወጣ መመርያ ቁ.1023/016


@etconp
👉"የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚያስገነባቸው ግንባታዎች ላይ ትዕዛዝ መሥጠት ይችላል ወይስ አይችልም? "

🚧“አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት በሚያስገነባቸው ግንባታዎች ላይ በግንባታ ሒደት ውስጥ ለተቋራጩ የስራ ትዕዛዞችን እየሰጠ፣ የስራዎቹን አካሄድ የመወሰንና ስራው በሚፈቅደው አይነት እንዲፈፀም የስራ ተቋራጩን የማዘዝ ሥልጣን ያለው ሲሆን፣ ተቋራጩ በበኩሉ በአሠሪው የመንግሥት መሥሪያ ቤት በተሰጡት ፕላኖች አይነቶችና የዋጋና የስራ ማስታወቂያ መሰረት ጠንቅቆ የግንባታ ሥራውን የመስራት ግዴታ እንዳለበት።” በፍ/ብሔር ህግ ቁጥር 3252 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ንዑስ አንቀጽ 2 በግልፅ ተደንግጓል።

🏷ከዚህ ጋር ተያይዞ የጨረታ ሰነዱ በሚወጣበት ጊዜ በግንባታ ዲዛይኑ ላይ ከተመለከተው ልኬት በታች ሆኖ በኋላ በዲዛይኑ መሰረት ለሚሰራ ግንባታ የሥራው ባለቤት በግንባታው ሥራ ውል ሰነዱ ላይ ከተመለከተው ክፍያ ውጪ በተጨማሪነት በባለቤቱ ፈቃድና ትዕዛዞች መሠረት ለተሠሩ ሥራዎች ክፍያ ለመክፈል የሚገደድ ሲሆን በህጉ አግባብ በባለቤቱ የተሰጡ ተጨማሪ የሥራ ትዕዛዞች የሥራ ውሉ አካል ተደረገው የሚወሰዱ ይሆናል። የፍ/ብ/ህ/ቁ.3244, 3225,(1)(2), 3152(1), 3266(1), 3263, 3265(3)

#ConstructionLaw

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ዋናው ቻናላቻን ለመቀላቀል👉 @ETCONp

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👉ዓለም ዐቀፍ የውል ሰነዶች (መደበኛ ውሎች)

🚧ከ'FIDIC በተጨማሪ በእኛ ሀገር ብዙም አይታወቁም እንጂ ሌሎች ተቋሞች ያዘጋጇቸው ስታንዳርድ ውሎችም አሉ።

🏷ለምሳሌ፦Joint Contract Tribunal (JCT) የሚባል ዘርፉ የሚመለከታቸው ቡድኖች ተሰባስበው ያዘጋጁት ከ1909 ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሰነድ አለ።

⭐️ሰነዱ በ2005 ተሻሽሎ የወጣ ሲሆን JCT Standard Building Contract የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

⭐️የአሜሪካ አርክቴክቶች ማኅበር (AIA) ያዘጋጀውም  General Conditions አለ።

📜Institute of Civil Engineers (ICE) ደግሞ በ2005 ያወጣው The New Engineering Contract (NEC 3) በጣም ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱንና በእንግሊዝ ሀገር በባሕር ሥር የሚያልፈውን የባቡር ሐዲድ ውል የተፈራረሙበት መሆኑን Murdoch and Huges የተባሉ ጸሐፊዎች የኮንስትራክሽን ውሎች በሚል ርእስ በጻፉት መጽሐፍ ጠቅሰዋል።

🔰ይህ ተቋም ቀደም ብሎ በ1945 ለመጀመሪያ ጊዜ ስታንዳርድ ውል አዘጋጅቶ ነበር።

▶️በየጊዜው እየተሻሻለ መጥቶ ሰባተኛው እትም በ1999 ICE 7 Condition of Contract – measurement Version በሚል ርእስ ታትሟል።

▶️FIDIC ያዘጋጀው ስታንዳርድ ውል ከዚህ ICE ካዘጋጀው ስታንዳርድ ውል ከ4ኛ እትም የተወሰደ ወይም የተቀዳ እንደሆእነ መርዶክ የተባለ ጸሕፊ እና ዘውዱ ተፈራም ጠቅሰውታል።

▶️ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች (ለምሳሌ የዓለም ባንክ) Standard Biding Docuement for Procurement በሚል በ1995 ባዘጋጀው ሰነድ ውስጥም ጠቅላላ አናቅጽ ሰፍረው እናገኛለን።

#ConstructionLaw

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ዋናው ቻናላቻን ለመቀላቀል👉 @ETCONp

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍2
👉የኮንስትራክሽን ደህንነት ሄልሜቶች በቀለማት ሲለዩ

⭐️ነጭ ሄልሜት:-ለኢንጂነሮች፣ ለማናጀሮች፣ ለፎርማኖች፣ ለሱፐርቫይዘሮች

⭐️ሰማያዊ ሄልሜት፦ ለኤሌክትሪሺያኖች ለአናፂዎችና ለቴክኒክ ሠራተኞች

⭐️ቀይ ሄልሜት፦ ለእሳት አደጋ ሠራተኞች

⭐️አረንጓዴ ሄልሜት፦ ለሴፍቲ ሠራተኞች

⭐️ግሬይ ሄልሜት፦ ለሳይት ጎብኚዎች

⭐️ቢጫ ሄልሜት፦ ለጉልበት እና ለግንባታ ማሽን ኦፕሬተር ሠራተኞች

⭐️ብራዎን ሄልሜት፦ ለበያጆችና ከፍተኛ ሙቀት ባለበት ቦታ ለሚሰሩ ሠራተኞች

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ዋናው ቻናላቻን ለመቀላቀል👉 @ETCONp

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etcono
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ዘመን መስከረም 11 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ዘመን መስከረም 11  ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ዘመን መስከረም 11  ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ዘመን መስከረም 11  ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK
👉This is the 1,813-kilometer-long Haoji Railway Bridge in China. It is the longest railway bridge in the world, the bridge is used for the transportation of coal.

The total cost was around 28 billion US dollars. It was built to transport 200 million tons of coal from Inner Mongolia and Shanxi to the southern provinces of China.

It is a heavy rail system with 1435 gauge tracks The railway is also China's first north-south railway that is dedicated to coal, and is built to avoid existing coal transportation routes that pass through coastal cities by boat.

The line reduces transit time from 20 days by sea to just 3 days by rail. The line connects with existing railways at several points to share maintenance facilities.

The design speed of the railway is 120 kilometers per hour. It is operated by China Railway. The line was approved in 2014 at a cost of 27 billion USD. It was financed by China Railway and several large national coal mining companies. The railway was inaugurated on September 28, 2019.

@etconp