Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
ዝምተኛው ጀግና - አርክቴክት ምናሴ አይተንፍሱ

[ ከትልልቅ ፕሮጀክቶች ጀርባ ያለ ሰው ]

በእስክንድር መርሐጽድቅ

1. ‹‹የመጨረሻው እራት››

#Ethiopia | ከትንሣኤ ዕለት በፊት ያለው ‹‹ፀሎተ-ሐሙስ›› ጌታችን፣ አምላካችን እና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለ12ቱ ሐዋሪያት ከሥጋው እና ከደሙ ጋር መስሎ የመጨረሻውን እራት የመገበበት እለት እንደሆነ በሉቃስ 22*ከ14-18፣ በማቴዎስ 22*ከ17-30፣ በማርቆስ 14*ከ12-18 እና በሉቃስ 22*ከ7-13 መጠቀሱ ይታወቃል፡፡ ይህን በመመሰል አንዳንድ ሰዎች የመጨረሻ የሆነ ድርጊት ሲፈጽሙ ‹‹The last supper›› እያሉ ወጋቸውን ለማጣፈጥ ከጌታ እራት ጋር ያያይዙታል፡፡ ያለፈው ሐሙስ (የደመራው እለት መስከረም 16/2017 ዓ.ም.) ምሽትም ከጌታ የመጨረሻ እራት ጋር በሐሙስነቱ ተመሳስሎ ሊታሰብ የአንድ ትጉህ ሰው የመጨረሻ እራት ሆኖበታል፡፡

2. የ2017 ዓ.ም. ደመራ

አርክቴክት ምናሴ አይተንፍሱ የዘንድሮውን የደመራ ምሽት ያሳለፈው የባለቤቱ ቤተ-ሰቦች ቤት ነው፡፡ ሞቅ ባለው የአማቾቹ ቤት ችቦ አብርቶ እና ቤት ያፈራውን የዓመት በዓል ድግስ ተቋድሶ ቤተ-ሰቡን እዚያው በመተው ሆላንድ ኤምባሲ ፊትለፊት ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ምሽት ላይ ተመልሶ በሰላም አድሯል፡፡

3. ትውልድ እና ትምህርት

ምናሴ አይተንፍሱ የተወለደው ከሻለቃ አይተንፍሱ መንገሻ እና ከሲስተር ፀሐይ አክሊሉ ሰኔ 6/1967 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በልደታ ካቴድራል የወንዶች ትምህርት ቤት፤ የሁለተኛ ደረጃውን ደግሞ በጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ባመጣው ከፍተኛ ውጤት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻ ኮሌጅ ተመድቦ በአርክቴክቸርና ከተማ ፕላን /Arctecher & urban plan/ በ1990 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡ በ2000 ዓ.ም. ደግሞ በከተማ ዲዛየን እና ፕላኒንግ /Urban design & planning/ ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ (ማስትሬት) ዲግሪውን ተቀብሏል፡፡

4. የሥራ ልምድ

ላለፉት 26 ዓመታት በሙያው የካበተ ልምድ ባለቤት የሆነው አርክቴክት ምናሴ፤ በበርካታ ታዋቂ ድርጅቶች ውስጥ በአርክቴክቸርነት የተሳተፈ ሲሆን ከዲዛየን ፕሮጀክቶቹ መካከል በዋናነት እነዚህ ይጠቀሳሉ፡-

- የአማራ ብሐራዊ ክልላዊ መንግሥት ቢሮ፤
- የአማራ ብሐራዊ ክልላዊ መንግሥት የስብሰባ ማእከል
- የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ሕንጻ
- የትግራይ መረዳጃ ማህበር ዋና መ/ቤት ሕንጻ፤
- የፌዴራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት፤
- የባህር ትራንዚት ዋና መ/ቤት፤
- የቤተ-መንግሥት ማስተር ፕላን እና የፕሬዜዳንቶች እንግዳ ማረፊያ እንዲሁም
- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት የዲዛየን ውድድር፡፡

‹‹ቢጋር ገንቢዎችና አልሚዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር››ን እ.ኤ.አ. በ2002 ከሙያ አጋሮቹ ጋር በመመሥረት እስካሁን በሥራ አስኪያጅነት መርቷል፡፡

- በለገሀር ባቡር ጣቢያ እና በአካባቢው በግንባታ ላይ የሚገኘውን ኤግል ሂልስ ሪል ስቴት /La Gare central core/ የዲዛየን ሀሳብ ከማመንጨት እስከ ፍጻሜው በሚኖረው ሒደት በዋናነት በመሳተፍ እና በመምራት ላይ ነበር፡፡ ተጨማሪ ፕሮጀክቶቹ ደግሞ፡-
- ሞሐ ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ ዋና መ/ቤት፤
- ኢሊቬሽን የዲፕሎማቶች መኖሪያ፤
- የዓለም ባንክ የአዲስ አበባውን ዋና መ/ቤት፤
- ጊፍት ሪል ስቴት እና
- ከፍታ አፓርትመንት ነበሩ፡፡

5. ማህበራዊ ኃላፊነት

አርክቴክት ምናሴ አይተንፍሱ በሙያውም፣ ከሙያው ውጪም በርካታ ቦታዎች ላይ በአባልነትም፣ በመሪነትም በትርፍ ጊዜው ብቻ ሳይሆን የሥራ ጊዜውንም በመሰዋት ቅን አገልግሎት ሰጥቷል፡፡

6. መንፈሳዊ አገልግሎት

የሃይማኖት ሰዎች አንዱ ግዴታቸው አሥራት ማውጣት መሆኑን ጠንቅቆ የተረዳው አርክቴርት ምናሴ አሥራቱን አንድም ሳያስቀር ለቤተ-ክርስቲያን ሲሰጥ እንደነበር የሃይማኖት አባቶች መስክረዋል፡፡ ከዚህ በላቀ ደግሞ እውቀቱን፣ ጊዜውን፣ ገንዘቡን እና ጉልበቱን እንዲሁም ባለሙያዎቹን በመጠቀም የተለያዩ ቤተ-ክርስቲያኖችን የዲዛየን እና የግንባታ ሥራዎች በኃላፊነት ጭምር በነጻ የሠራ ሲሆን በተለይ ከመኖሪያ ቤቱ ጀርባ ከሚገኘው የገነተ-ኢየሱስ ገዳም ጀምሮ የቀራኒዮ መድሐኒዓለም እና የደብረ-ሊባኖስ ገዳም ላይ ያስቀመጠው አሻራ ለየት ያለ ነው፡፡

በ2003 ዓ.ም. ተጀምሮ አሁን ግንባታው 85 በመቶ የደረሰውን የገዳመ-ኢየሱስ ሕንጻ ዲዛየን ከመሥራቱ ባሻገር የሕንጻ አሠሪ ዐቢይ ኮሚቴ አባል በመሆን እያገለገለ ነበር፡፡ የገዳሙ አስተዳዳሪ ምስክርነታቸውን ሲሰጡ፣ ‹‹የግንባታ ሒደቱን ይከታተል የነበረው ከወለዳቸው ልጆች አስበልጦ ነበር›› ነው ያሉት፡፡

በቀራኒዮ መድሐኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ በቅዱስ ሚካኤል ስም የተቋቋመው የሰንበቴ ማሕበር አባል ሲሆን ከተለመደው የሰንበቴ አባልነት ተግባር አልፎ ማሕበሩ ሲያከናውናቸው በነበሩ የልማት ሥራዎች ላይ እቅድ እና ፕሮግራም በማውጣት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

በደብረ-ሊባኖስ የአቡነ ተክለ-ሃይማኖት ገዳም የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትሪያርክ የነበሩት ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ያቋቋሙት የብሉይ እና የሐዲስ የሊቃውንት ት/ቤት አለ፡፡ ለዚህ ት/ቤት በዘመናዊ መልክ መታደስ አርክቴክት ምናሴ አይተንፍሱ ያለምንም ክፍያ ከአፈር ምርመራ ጀምሮ በዲዛየን እና ገቢ በማሰባሰብ ተሳትፎ 800ሺ ብር የተገመተ ወጪን አድኗል፡፡

እነዚህ መንፈሳዊ አገልግሎቶቹ የታወቁት ሲሆኑ በስውር የፈጸማቸው በጎ አድራጎቶች በርካታ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠባዩን የሚያውቁ ይመሰክሩለታል፡፡

7. ማህበራዊ አኗኗር

ከላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት የሚፈጽም ሰው ለቤተ-ሰቡም ሆነ ለወዳጅ ዘመዶቹ ጊዜ እንደማይኖረው ይታወቃል፡፡ አርክቴክት ምናሴ ግን ከአቅም በላይ ጉዳይ ካልገጠመው በስተቀር የሰዎች ደስታና ሀዘን ላይ የማይቀር፣ ለቤተ-ሰቡም ጊዜ የሚሰጥ፣ የሀገሩንም ጉዳይ በቸልታ የማያልፍ እና በሀገሩ ጥቅም ቀልድ የማያውቅ፣ ባገኘው ትርፍ ጊዜ የሚያነብ፣ ለሰዎች ሥራ ክብር የሚሰጥ እና አድናቂ እንዲሁም ተጫዋች እና የምንም ሱስ ተገዢ ያልሆነ ነበር፡፡

8. ቤተ-ሰብ ምስረታ

አርክቴክት ምናሴ አይተንፍሱ ከባለቤቱ ከወ/ሮ ምሕረት መርናቸው ጋር ትዳር የመሠረተው ሚያዝያ 4/1999 ዓ.ም. ሲሆን የአንዲት ሴት እና የሁለት ወንዶች አባት ነበር፡፡

9. ከፕሮጀክቶቹ ቀድሞ ያለቀ ፕሮጀክት

ምድር ላይ ከኖረበት 49 ዓመታት በላይ ጊዜን ወደፊት ገፍቶ የተበደረን ያህል የሠራው አርክቴክት ምናሴ ከተጠናቀቁት ሌላ ከላይ የተዘረዘሩትንም ሆነ ያልተጠቀሱትን ጅምር ፕሮጀክቶች መጨረሻ ሳያይ አምላክ የተመነለት በዚህ ምድር የመቆያው ተጠናቆ ብክነት ካላሳየባት ዓለም የ2017 መስቀል እለት (መስከረም 17) በመኖሪያ ቤቱ እንደተቀመጠ ያለምንም ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
👍14❤3
10.  የመጨረሻው ስንብት

የአርክቴክት ምናሴ አይተንፍሱ አስከሬን ካረፈባት ዕለት ጀምሮ ከቆየበት ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መስከረም 19 ወጥቶ በገዳመ-ኢየሱስ አመሻሽ ላይ በልዩ ሥነ-ሥርዓት አውደ-ምሕረት ላይ መንፈሳዊ መርሐ-ግብር ከተከናወነለት በኋላ ቤተ-መቅደስ ገብቶ ሌሊቱን ፀሎተ-ፍትሐት ሲደረግለት አድሯል፡፡ በነጋታው ደግሞ ካደረበት የቀድሞው ሕንጻ ቤተ-ክርስቲያን ወጥቶ የግንባታ ሒደቱን ከፍተኛ ክትትል ወደሚያደርግበት አዲስ ሕንጻ ቤተ-ክርስቲያን አውደ-ምሕረት ላይ ከተወሰደ በኋላ የካህናት ወረብ እና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች ተከናውነውለት በመንፈሳዊ አባቶች እና መዘምራን ዝማሬ ታጅቦ ወደ መኖሪያ ቤቱ ተወስዷል፡፡

ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ደግሞ ከመኖሪያ ቤቱ በከፍተኛ እጀባ የሰንበቴ ማሕበር አባል ወደነበረበት ቀራኒዮ መድሐኒዓለም ተወስዶ እዚያም ለአንድ ከፍተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት ለሰጠ ምዕመን በሚፈጸም ክብር የአውደ-ምሕረት መርሐ-ግብር ተከናውኖለታል፡፡

በብዙ ሺ ወዳጅ ዘመዶቹ የታጀበውን የአርክቴክት ምናሴ አይተንፍሱ ሥርዓተ-ቀብር ለመሳተፍ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የሰሜን ሸዋ እና ሰላሌ ፍቼ ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ተገኝተው ነበር፡፡ ሊቀ-ጳጳሱ፤ የአርክቴክት ምናሴ የሕይወት ታሪክ እና የማፅናና ስብከት እንዲሁም ከገዳመ-ኢየሱስ እና ከደብረ-ሊባኖስ ገዳም አስተዳዳሪዎች ምስክርነት ከቀረበ በኋላ ቃለ-ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተው ግብዓተ-መሬቱ ተፈጽሟል፡፡

11. የነምናሴ እና የኛ ቤት መመሳሰል

11.1. ከሻለቃ አይተንፍሱ ልጆች መካከል ምናሴ እና ኤፍሬም የሚባሉ ልጆች እንዳሉ ሁሉ እኛም ቤት ምናሴ እና ኤፍሬም አሉ፤
11.2. ምናሴ በድንገት እንደሞተ ሁሉ ወንድማችን ሳሙኤል መርሐጽድቅም የዛሬ ዓመት የሞተው እንደርሱ በድንገት ነው፤
11.3. የነምናሴም፣ የእኛም እናቶች ከዚህ ዓለም የተለዩት፤ ያደረባቸው ህመም ካንሰር ደረጃ ደርሶ ነው፡፡

12. ምኞት እና አደራ

ለአርክቴክት ምናሴ አይተንፍሱም ሆነ ለሳሙኤል መልካም እረፍትን እና መንግሥተ-ሰማያትን፤ ለመላው ቤተ-ሰብ፣ ዘመድ እና ወዳጅ ደግሞ መጽናናትን እመኛለሁ፡፡

መልካም የሠራ ሰው በቁሙ ብቻ ሳይሆን ሞቶም ሕይወቱ ያስተምራልና አርክቴክት ምናሴን ሸኝቶ መመለስ ብቻ ሳይሆን ከርሱ ተግባራት ተምሮ እንደርሱ መሆንን መልመድ ተገቢ ነው፡፡

13. ስለምናሴ ከተጻፉት

13.1. ‹‹ስው በሞቱ ሀገር ሲያጎድል ባንተ አየሁ

አዎ፤ ሰው በሞቱ ቤተሰብ ሲያጎድል አይቻለሁ፡፡ ያንተ ግን ከዛም በላይ ነው፡፡ ሀገር አጉድለሀል፤ ሥራዎችህን ለሚያውቅ ‹ሀገር ጎደለባት› ቢል ያንስዋልን?

በሥራህም፣ በዝናህም ያልተኩራራህ፣ እራስህን ከፍ ከፍ የማታደርግ፣ ትሁት እና ተጫዋች፣ ማህበራዊ ሕይወት የሚያስደስትህ፣ ሀገርህን የምትወድ፣ ቅን እና በጎ በሆኑ ነገሮች ላይ ሁሉ የምትገኝ ነበርክ፡፡ አዎ፤ ምን ሀገር ብቻ…

ቤተክርስቲያንም ልጇን አጥታለች፤ አማኝ ብቻም አልነበርክምና!
ለቅርሶቿ እና ለገዳማቷ የምትጨነቅ፤ ለደብሯ የዲዛይን ሥራን በነፃ ትሠራ የነበርክ፤ እምነት እና ሥራን ሆነህ እና ኖረህ ያሳየህም ነበርክ:: ለቤተስብህ ብቻ ሳይሆን ለኛም ለዘመዶችህ ትልቅ ኩራትና ምሳሌም ነበርክ::

ዋናውና ትልቁ ደሞ የጥሩ ቤተ-ሰብ ምሳሌም ነበርክ፤ ጥሩ ባልና አባትም ነበርክ፡፡ የሚያውቁህ ብዙ ብዙ እያሉልህም ነው፡፡ በአጭሩ፤ ጥሩ ዜጋ ነበርክ፡፡ ሞት ክፉ ቢሆንም ሞትህ ግን የፃድቅ ሞት ነው፡፡ የምድሩን ብቻ ሳይሆን የሰማዩንም ሠርተሀልና ሥራህ ከመቃብር በላይ ነው:: እግዚአብሔር ባለቤትህንና ልጆችህን ይባርክልህ፤ ያንተን ፈለግ የሚከተሉ፣ ሀገርና ወገን የሚኮራባቸው፣ ጥሩ ዜጎች ያርግልህ፤ በመልካሙ ስፍራ ነህና በሱ እንፅናናለን::››
ቢኒያም ሥዩም

13.2. ‹‹Minassiyee, it's now been 4 days since you left us. It's so hard to type this right now. We were cousins but i have always seen you like my brother. The things you did for me were endless and the memories we share i will never forget. My heart is broken knowing you are gone. Just two weeks ago we were celebrating new years and now we are saying goodbye. You asked me when I was coming back so we can spend more time together, not knowing that was our last. We had so many plans for the future and your kids that we will never get to see. Minassiyee, thank you for being the selfless and kind person you were to me and everyone around you. To know you is to love you. I will never forget you. I know God has put you in a better place, May you rest in peace my brother i love you forever.››
ቤተልሔም ሥዩም

13.3. ‹‹የተከበራችሁ የማህበራችን አባላት

እጅግ የተወደዱት የማህበራችን አባል አቶ ምናሴ አይተነፍሱ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም ማለፋቸውን ማህበራችን ሲያሳውቅ ከታላቅ ሀዘን ጋር ነው።

አቶ ምናሴ ማህበሩን በተለያዩ ኃላፊነት ቦታዎች ከማገልገላቸውም በላይ ማህበሩ በፈለጋቸው ጊዜና ቦታዎች ሁሉ ያለመታከት ሲረዱ የቆዩ ባለሙያ ነበሩ። ነብሳቸውን በአፀደ-ገነት እንዲያሳርፍልን እየተመኘን ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው መፅናናትን ይመኛል።››

የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር

13.4. ‹‹In moments like these, words are insufficient.It’s hard to believe that he is gone May God give strength and comfort to his kids, wife, and the entire family .››
ቤዛ ጌታቸው

በ ጌጡ ተመስገን በኩል

@etconp
😭11👍8❤1
ጥያቄ፦ አንድ ተቋራጭ በ63,930,000 ብር ቅድመ ግምት የተሰራለትን ፕሮጀችት ከባለቤቱ ጋር በ "ወጪ የሚሸፈንበት  (Cost-reimbursement)" ውል አይነት ተዋውሎ ግንባታውን በቀጥተኛ ዋጋ ብር 59,322,550.60 እና በተዘዋዋሪ ወጪዎች ብር 7,250,000 (ትርፍና የአገልግሎት ወጪ) ቢያጠናቅቅ የዋጋ ልዩነት የመጣውን 2,642,550.60 ብር የመሸፈን ግዴታ የማን ነው? @etconp
Anonymous Quiz
60%
የአሰሪው /ባለቤት/ (Client/owner)
35%
የሥራ ተቋራጩ (Contractor)
5%
የፕሮጀክት አማካሪ (Consultant)
👏22👍2
እንኳን ለደማቁ የእሬቻ በአል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

Baga Irreecha Baranaa Geenye!

መልካም በአል!

@etconp
❤6👍3
👉የዕለቱ የውጭ ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@etconp
👉የንድፍ ውድድር እድል

💫የተገነቡ ህንጻዎች ንድፍ ውድድር

🏷አጠቃላይ ሽልማት መጠን 1 ሚሊዮን ዳላር

📜ዝርዝሩን ከታች ይመልከቱ

The Holcim Foundation has launched the Awards 2025 competition this week The USD 1 million competition is free to enter, open to client-supported projects intended for real-world execution. Projects already under construction are eligible, provided they are not completed before February 11, 2025.

⏺The competition is open for registration until February 11, 2025, and winners will be honored at the Awards Ceremony during the Foundation’s Venice Forum event on November 20, 2025.

⭐️Detailed information, inspiring stories of previous winners and the entry form are available at
http://awards.holcimfoundation.org/

@etconp
👍2🙏2❤1👏1
👉URGENT VACANCY

⭐️Job Vacancies at Wossen Ayal Construction PLC (GC-3)

🚧Position 1: Office Engineer
🚧Position 2: Senior Accountant

🏷Company Overview

Wossen Ayal Construction PLC is a Grade 3 General Contractor (GC-3) specializing in Building Construction, Road and Bridge Works, Water Works, and Electromechanical Works. We are seeking qualified professionals to join our team at our office located in CMC, Addis Ababa.

💫1. Office Engineer

⏺Requirements:

▶️Bachelor’s Degree in Civil Engineering or Construction Technology Management.

⏺Minimum of 3 years of relevant work experience.

⏺Proficiency in project management software (AutoCAD, Microsoft Project, etc.).

⏺Excellent organizational and communication skills.

❇️Responsibilities:

Prepare project schedules, reports, and documentation.

⏺Coordinate with project managers, site engineers, and other departments.

⏺Monitor project progress and provide technical support.

⏺Ensure compliance with project specifications and standards.

🚧2. Senior Accountant

🏷Requirements:

⏺Bachelor’s Degree in Accounting or Finance.

⏺Minimum of 5 years of experience in accounting, preferably in the construction sector.

⏺Proficiency in accounting software (Peachtree, QuickBooks).

⏺Strong analytical and problem-solving skills.

⏺Knowledge of Ethiopian tax laws and regulations.

❇️Responsibilities:

⏺Prepare financial statements and manage budgets.

⏺Handle tax filings and ensure compliance with regulations.

⏺Oversee day-to-day financial transactions and audits.

⏺Manage payroll, invoicing, and financial reporting.

🔰Application Information

⏺Work Location: CMC, Addis Ababa

⏺Application Deadline: 3 days from today (starting October 5, 2024)

📩How to Apply:Send Your CV
Email: leulbase@gmail.com Or
Telegram: 0911245698

@etconp
👍13🙏1
የስራው መጠሪያ: Junior Architect and Urban designer | 3D design

የስራው አይነት: ባሉበት የሚሰራ - የትርፍ ጊዜ

የስራው ዘርፍ: #አርክቴክቸር_እና_የከተማ_ፕላን

የስራው ቦታ: አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

የትምህርት ደረጃ: የመጀመሪያ ዲግሪ

የልምድ ደረጃ: ጀማሪ

የተፈላጊ ሰው ብዛት: 3

ደሞዝ/ክፍያ: የአንድ ጊዜ

የማመልከቻ ማብቂያ ቀን: October 19th, 2024

የስራው ዝርዝር:
We seek a talented Junior Architect and Urban Designer skilled in 3D rendering and corridor project design. If you deliver high-quality designs quickly, we want to hear from you!

Project Details:
- Task: 10 corridor site plans need rendering; one urgent 3D design plan with the XYZ coordinator.
- Submission Deadline: October 5 - 7 (2 working days)

Incentives:
- Exceptional submissions may lead to ongoing opportunities.
- We will select 3 designers for this project, each receiving $1,000.
- The winner earns additional payment and consideration for 9 upcoming corridor projects.

Please contact @Tot2034 on telegram

______

https://t.me/ETCONpWORK
❤4👍1
የስራው መጠሪያ: Sanitary Engineer

የስራው አይነት: በተመደቡበት የሚሰራ - ቋሚ

የስራው ዘርፍ: #ሲቪል_ምህንድስና_እና_ኮንስትራክሽን

የስራው ቦታ: አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

የትምህርት ደረጃ: የመጀመሪያ ዲግሪ

የልምድ ደረጃ: መካከለኛ

ደሞዝ/ክፍያ: ወርሃዊ

የማመልከቻ ማብቂያ ቀን: October 19th, 2024

የስራው ዝርዝር:
Job Title: Sanitary Engineer

Location: Bole, Addis Ababa

Company: Luxury-Con

About Us: Luxury-Con is a forward-thinking company with sole proprietorship that is engaged in developing deluxe and complex infrastructure to the utmost quality standard. It offers exqusite services in collaboration with its international partners along the lines automation of construction systems. It is committed to excellence and innovation.

Key Responsibilities:
- Design and develop water supply and wastewater treatment systems.
- Create plans and specifications for sanitation projects.
- Oversee construction and installation of sanitation infrastructure.
- Manage project timelines, budgets, and resources effectively.

Qualifications:
- Bachelor’s degree in civil engineering, environmental engineering, or a related field (master’s degree preferred).
- 2-3 years relevant experience in sanitary or environmental engineering.
- Professional Engineer (PE) license is a plus.
- Strong analytical and problem-solving skills.
- Excellent communication and teamwork abilities.
- Proficiency in engineering design software and modeling tools.

Salary:
Competitive salary according to company scale, plus profit sharing.

We are seeking a skilled Sanitary Engineer to design, develop, and oversee sanitary systems and components for various projects. The ideal candidate will have a strong technical background, excellent problem-solving skills, and the ability to work collaboratively in a team environment.

How to Apply:
*If you fulfill the above requirements send your CV via email address
info@luxuryconworld.com with the subject line “Sanitary Engineer Application – [Your Name].”

______

https://t.me/ETCONpWORK
👍6👏2
👉ሸገር አዱ ገነት

ውብ ምሽት ተመኘን❤🙏

@etconp
❤8👍2
👉NEW VACANCY

🚧Graduate Civil Engineer

#fiseha_arega_general_contractor

#Addis_Ababa

⭐️Bachleor's Degree in Civil Engineering or in a related field of study Graduate Civil Engineer,

🏷Only Female Applicants of 2016 graduates.

🔰Duties & Responsibilities

- Design, plan, and develop technical and engineering specifications for infrastructure and construction projects

💫Quanitity Required: 1

🌟Minimum Years Of Experience: #0_years

⏹Deadline: November 1, 2024

📩How To Apply: Send Your CV @hahujobs_bot

https://t.me/ETCONp
👍9❤1🙏1