Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉አንድን ጨረታ የሚያሸንፈው ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢ ተጫራች ወይስ ከመሐንዲሱ ግምት ተቀራራቢ የሆነ ዋጋ ያስገባ ተጫራች?

💫ጨረታ ለተቋራጮች በሁለት አይነት መንገድ ሊፈጸም ይችላል።

⭐️አንደኛ ግልጽ ጨረታ ሲሆን ማንኛውም ብቁ የሆነ፣ ህጋዊ ፍቃድ ያለው እና ፍላጎት ያለው ተቋራጭ መሳተፍ የሚችልበት በጋዜጣ ወይም በአካባቢው ባሉ የማታወቂያ መንገዶች ወይም በማህበራዊ መገናኛ ድረገጾች (website) ላይ በሚለቀቅ የተጫራችነት ግብዣ ጥሪ (Invitation to Tender) አማካኝነት ተጫራቾች ኩል ዕድል ተሰጥቷቸው እንዲሳተፉ የሚጋበዙበት ሂደት ሲሆን

⭐️ሁለተኛው ውስን ጨረታ የሚባል ነው። ውስን ጨረታ አንድ ተጋባዥ ወይም ውስን ቁጥር ያላቸው ልዩ መስፈርት የተሰጣቸው ተጫራቾች ጋር በሚደረግ ድርድር ወይም የመለያ ጨረታ አማካኝነት የሚከናወን የጨረታ አይነት ነው።

📜በግልጽ ጨረታ ሂደት ደግሞ አጫራቹ አካል ሁለት አይነት መንገድን ሊጠቀም ይችላል።

🏷[አንደኛው] ፖስት ኳሊፊኬሽን (Post Qualification) የሚባል ሲሆን ሥራው ቀለል ያለ እና ማንኛውም ተጫራች ሊያከናውነው የሚችል ከሆነ ቅድሚያ ኢኮኖሚያው (የገንዘብ) መጠናቸውን መመዘን ነው።

⏺በዚህ ሂደት ቅድሚያ ቅንሽ ዋጋ ያስገቡ ተጫራቾች ተለይተው እነዚያ ደግሞ በቴክኒካዊ ልኬት ተመዝነው አሸናፊ የሚለይበት መንገድ ነው።

🏷[ሁለተኛው] ፕረ ኳሊፊኬሽን (Pre-Qualification) የሚባለው ደግሞ ማንኛውም ተጫራች ቅድሚያ በቴክኒካዊ ልኬት ተመዝነው በኋላ በገንዘብ ዝቅተኛ ያስገባው አሸናፊ የሚሆንበት የጨረታ ምዘና መንገድ ነው።

⏺በመሆኑ ይህ ሂደት በፌደራል የግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የወጣው መመሪያ ክፍል አምስት (5) ንዑስ ክፍል (1), (2) እና (3) ላይ በዝርዝር የተብራራ ነው።

🚧በመሆኑም በጨረታ ሰነዶች ምዘና (Bid Response Document Evaluation) ሂደት ላይ ተጫራቾት እንደጨረታ ሰነዱ አወጣጥ ተመስርቶ በቅድሚያ ዝቅተኛ ዋጋ ያስገቡትን በመምረጥ (Post Qualification ሂደትን በመከተል) በቴክኒካል ሰነዳቸው አXእናፊውን የሚለይበትን መንገድ ሊከተል ይችላል።

▶️አልያም ደግሞ Pre-Qualification ሂደትን በመከተል ቅድሚያ የቴክኒካል ሰነዳቸው ታይቶ ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ብቻ ተለይተው ዝቅተኛ ገንዘብ ባስገባ (Lowest bidder) የሚለዩበት መንገድ ነው።

▶️ይህ ሁለቱም መንገድ በግል ፕሮጀክቶችም ይሁን በመንግሥት ፕሮጀችቶች ላይ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉና ህጋዊ እውቅና ያላቸው መንገዶች ናቸው።

▶️የጨረታውን አከፋፈት በተመለከተ በ ክፍል 2 (2.2.1.5) ላይ እንደተብራራው ቃለጉባኤ ተይዞ፣ የጨረታውን አከፋፈት ሂደት ላይ ውይይት ከተካሄደባቸው ጉዳዮች በተጨማሪ ጨረታው ሲከፍተ የተገኙ ተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው ስለጨረታው አከፋፈት ሂደት የሚያብራራ ቃለጉባኤ ላይ ስማቸውን እና ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይገባቸዋል። etconp

❇️አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመሐንዲስን ግምት ያማከለ የጨረታ ሰነዶች ምዘና የሚካሄድበት አጋጣሚ አለ።

⏺ይህም Federation Internationale Des Ingenieurs Conseil – FIDIC አንቀጽ 14 ላይ እንደተገለጸው ተጫራቾች መሐንዲሱ ገምቶ ያስቀመጠውን የግንባታ ዋጋ (Engineering Estimation of Construction Cost) እንደመነሻ በመቁጠር ተጫራቾች ከግምቱ በታች ከ20% በታችን የቀነሰ ዋጋ እንዳያስገቡ ወይም ከግምቱ በላይ ከ20% በላይ እንዳይጨምሩ ገደብ በማስቀመጥ ከዚህ እሳቤ ውጪ የሆኑትን የተጫራቾች ሰነዶች በመጣል በዚህ ክፍተተ (interval) ውስጥ ያሉትን ብቻ የማወዳደር ሥራ የሚሰሩበት መንገድ ነው። etconp

⏹ቢሆንም ግን ይህ አካሄድ ግምቱን ባወጣው መሐንዲስ (ግለሰብ) ጥንቃቄ እና እውቀት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ብዙ ክፍተቶች የሚፈጠሩበት ቢሆንም  የፌደራል መንግስት የግዢ መመሪያ ቀድሞ በነበረው በዚህ አሰራር ላይ ግልጽ ማብራሪያ ሳያስቀምጥ አልፎታል።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍13👏4❤1
👉በ መቐለ ከተማ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተጀመረ

🚧በ መቐለ ከተማ በ2 ነጥብ 1ቢሊዮን ብር በጀት የአስፋልት መንገድ ግንባታ መጀመሩን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመቐለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

💫የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የመሰረተ ልማት አማካሪ አቶ ሀፍቱ መብራህቱ እንደገለፁት፤ በከተማዋ በ2017 በጀት ዓመት 9 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ለመገንባት የተያዘውን እቅድ ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል።

Via EBC

@etconp
👍5
👉NEW VACANCY

🏷Site Engineer

#iddo_wood_work_and_trading_plc

#Addis_Ababa

💫Master's or Bachelor's Degree in Civil Engineering, COTEM or in a related field of study with relevant work experience in furniture work company is advantageous.

Duties & Responsibilites

- Studies carefully contract documents and drawings relevant to the site verify their correctness and reports errors omissions clarification if required & recommend changes, if necessary,
- Prepares daily and weekly work plans and resource schedules
- Prepare monthly budget for the project

Quanitity Required: 1

Minimum Years Of Experience: #2_years
Maximum Years Of Experience: #3_years


Deadline: October 21, 2024

📩How To Apply: Submit your application letter, updated CV and credentials via email: Hr@elhadar.com

Note: Mention the position in the subject line of your email

@etconp
👍6
2017 1st QUARTER CONSTRUCTION WORKS ONLY DIRECT COST.pdf
22.3 MB
🏷በ2017 ዓ.ም የ አንደኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (1St Quarter Construction Works of Direct Cost)

🔑በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

💫በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።

@etconp
👍11
👉የበለስ - መካነ ብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 75.2 በመቶ ደረሰ

🚧በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ እና ጃናሞራ ወረዳዎችን የሚያገናኘው የበለስ - መካነ ብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 75.2 በመቶ ደርሷል።

🏷የመንገድ ፕሮጀክቱ 36.42 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲኾን፥ ግንባታው በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እየተካሄደ ይገኛል።

💫በለስ ኮንሰልቲንግ የግንባታውን ጥራት የመቆጣጠር እና የማማከር ሥራ ይሠራል።

💫አሁን ላይ እየተሠሩ ከሚገኙ ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የሰቤ ቤዝ፣ የውሃ መፋሰሻ ቱቦ እንዲሁም የጠጠር ማምረት ሥራዎች ይጠቀሳሉ።

🚧በተጨማሪም የአስር አነስተኛ እና ከፍተኛ ድልድዩች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል።

⏺ለግንባታው የተመደበው ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በፌደራል መንግሥት ነው የሚሸፈነው።

🌟በአካባቢው የሚስተዋለውን ተደጋጋሚ የጸጥታ ችግር ተከትሎ የግንባታ ጥሬ እቃ እና ማሽነሪዎች በቀላሉ ማቅረብ አለመቻል እንዲሁም የሥፍራው አስቸጋሪ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ የፕሮጀክቱ ፈተና መኾናቸው ተመልክቷል።

❇️የመንገዱ መገንባት በተለይም በመንገድ እጦት ተራርቆ የቆየውን ሕዝብ በቅርበት እና ደረጃውን በጠበቀ መንገድ የሚያገናኝ ነው። በመንገዱ ክልል እና በዙሪያው የሚገኙ የበለስ፣ ወይና፣ ሚጊራ እና መሰል ከተሞች ዕድገት ያፋጥናል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ቀድሞ ይወስድ የነበረውን 8 ሰዓት የጉዞ ጊዜ ወደ 1 ሰዓት ያሳጥረዋል።

🔰የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መዳረሻ እንደመኾኑም የቱሪዝም ዘርፉን በማነቃቃት በኩል የጎላ ሚና ይጫወታል።

@etconp
👍4
የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 22 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ገንብቶ ከሚያስተላልፋቸው መደበኛ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ በካፒታል ፕሮጀክት እየገነባ ለሽያጭ የሚያቀርባቸው የመኖሪያና ንግድ ቤቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ግንባታቸው የተጠናቀቁና መሠረተ ልማት የተሟላላቸውን 545 ባለ አራትና ባለአስራ አንድ ወለል ከፍታ ያላቸውን መኖሪያ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ለጨረታ ያቀረባቸውን መኖሪያ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከ04/02/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27/02/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ምሽት 12፡30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ በመክፈል ከዚህ በታች በተገለፁት ቦታዎች መግዛት ይችላሉ፡፡

@etconp
👍8
👉አቤት ሆስፒታል የማስፋፍያ ፕሮጀክቱን ቦታ በፍርድ ቤት ክርክር አሸንፎ መረከቡን አስታወቀ

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሕክምና ኮሌጅ ሥር የሚተዳደረው አቤት ሆስፓታል፤ ከሊዝ ነፃ ባገኘው 8926 ሜትር ካሬ ቦታ ላይ በ500 ሚሊዮን ብር ወጪ ባለ አሥራ አምስት ወለል ሕንፃ ለማሠራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ፤ ቦታው ላይ የፍርድ ቤት ዕግድ ወጥቶበት ጉዳዩ በክርክር ላይ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡

ቦታው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አዲሱ ገበያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፤ ለሌላ አግልግሎት ሲውል እንደነበር ተገልጿል፡፡

በፍርድ ቤቱ ክርክር ወቅት ተከራካሪው አካል ስምንት ሚሊዮን ብር እንዲያሲዚ ቢጠየቅም፤ ይህን ገንዘብ ለፍርድ ቤት ማስያዝ ባለመቻሉ ለሆስፓታሉ እንደተፈረደለት ተነግሯል።

እግዱን አውጥቶ የነበረው አካል ማረጋገጫ ካርታ የሌለው መሆኑ የፍርድ ቤቱን ክርክር እንዲያሸንፉ ዕድል እንደሰጠው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የግንባታ ክፍል ባለሙያው ገብረጊዮርጊስ ዘሩ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በዚም መሰረት ጳውሎስ ሆስፓቲል የማረጋገጫ ካርታ እንደተሰጠው ተገልጿል።

ተቋሙ አሁን ላይ የሕንፃው ግንባታ እንዲጀመር የጨረታ ሰነዱን አዘጋጅቶ ማስረከቡ የተነገረ ሲሆን፤ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥም የግንባታ ሥራውን ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙን አቶ ገብረጊዮርጊስ ለአሐዱ ገልጸዋል።

አቤት ሆስፒታል ሊያስገነባው ያሰበው አዲስ ሕንፃ ሲጠናቀቅ፤ ደረጃቸውን የጠበቁ 18 የቀዶ ሕክምናና 40 የማገገሚያ ክፍሎች፣ እንዲሁም ከ700 በላይ አልጋዎች የሚኖሩት ሲሆን፤ ለአስተዳደርና ለልዩ ልዩ ሥራዎች ማከናወኛ የሚውሉ በርካታ ክፍሎችን እንደሚይዝም ተገልጿል፡፡

@etconp
👍6
👉ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት

በገበታ ለትውልድ እየተገነቡ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች በሶማሌ ክልል በመገንባት ላይ ያለው የሸቤለይ ሪዞርት ግንባታ ሂደት

@etconp
👍6
👉ዓለም ዐቀፍ የውል ሰነዶች (መደበኛ ውሎች)

🚧ከ 'FIDIC' በተጨማሪ በእኛ ሀገር ብዙም አይታወቁም እንጂ ሌሎች ተቋሞች ያዘጋጇቸው ስታንዳርድ ውሎችም አሉ።

💫ለምሳሌ፦ Joint Contract Tribunal (JCT) የሚባል ዘርፉ የሚመለከታቸው ቡድኖች ተሰባስበው ያዘጋጁት ከ1909 ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሰነድ አለ።

📜ሰነዱ በ2005 ተሻሽሎ የወጣ ሲሆን JCT Standard Building Contract የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

💫የአሜሪካ አርክቴክቶች ማኅበር (AIA) ያዘጋጀውም  General Conditions አለ።

💫Institute of Civil Engineers (ICE) ደግሞ በ2005 ያወጣው The New Engineering Contract (NEC 3) በጣም ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱንና በእንግሊዝ ሀገር በባሕር ሥር የሚያልፈውን የባቡር ሐዲድ ውል የተፈራረሙበት መሆኑን Murdoch and Huges የተባሉ ጸሐፊዎች የኮንስትራክሽን ውሎች በሚል ርእስ በጻፉት መጽሐፍ ጠቅሰዋል።

ይህ ተቋም ቀደም ብሎ በ1945 ለመጀመሪያ ጊዜ ስታንዳርድ ውል አዘጋጅቶ ነበር።

⭐️በየጊዜው እየተሻሻለ መጥቶ ሰባተኛው እትም በ1999 ICE 7 Condition of Contract – measurement Version በሚል ርእስ ታትሟል።

💫FIDIC ያዘጋጀው ስታንዳርድ ውል ከዚህ ICE ካዘጋጀው ስታንዳርድ ውል ከ4ኛ እትም የተወሰደ ወይም የተቀዳ እንደሆእነ መርዶክ የተባለ ጸሕፊ እና ዘውዱ ተፈራም ጠቅሰውታል።

🏷ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች (ለምሳሌ የዓለም ባንክ) Standard Biding Docuement for Procurement በሚል በ1995 ባዘጋጀው ሰነድ ውስጥም ጠቅላላ አናቅጽ ሰፍረው እናገኛለን።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ዋናው ቻናላችን ለመቀላቀል @ETCONp

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍4🙏2❤1
የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር አዋሽ አካባቢ መጠነኛ ጉዳት አጋጠመው

15 ሜትር ርዝመት ያለው የባቡር ሃዲዱ ብረት ወደ መሬት መስጠሙን እና አንዳንድ የሃዲዱ ማሰሪያዎች (ማያያዣዎች) መቆራረጣቸውም ተገልጿል፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) የጉዳት መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተፈጠረውን መጠነኛ ጉዳት በፍጥነት በማስተካከል መስመሩን ወደ ሙሉ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

@etconp
👍4❤1
👉አዲስ የ ስራ ቅጥር

🏷አዲስአበባ መንገዶች ባለስልጣን

@etconp
👍4