Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉አቤት ሆስፒታል የማስፋፍያ ፕሮጀክቱን ቦታ በፍርድ ቤት ክርክር አሸንፎ መረከቡን አስታወቀ

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሕክምና ኮሌጅ ሥር የሚተዳደረው አቤት ሆስፓታል፤ ከሊዝ ነፃ ባገኘው 8926 ሜትር ካሬ ቦታ ላይ በ500 ሚሊዮን ብር ወጪ ባለ አሥራ አምስት ወለል ሕንፃ ለማሠራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ፤ ቦታው ላይ የፍርድ ቤት ዕግድ ወጥቶበት ጉዳዩ በክርክር ላይ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡

ቦታው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አዲሱ ገበያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፤ ለሌላ አግልግሎት ሲውል እንደነበር ተገልጿል፡፡

በፍርድ ቤቱ ክርክር ወቅት ተከራካሪው አካል ስምንት ሚሊዮን ብር እንዲያሲዚ ቢጠየቅም፤ ይህን ገንዘብ ለፍርድ ቤት ማስያዝ ባለመቻሉ ለሆስፓታሉ እንደተፈረደለት ተነግሯል።

እግዱን አውጥቶ የነበረው አካል ማረጋገጫ ካርታ የሌለው መሆኑ የፍርድ ቤቱን ክርክር እንዲያሸንፉ ዕድል እንደሰጠው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የግንባታ ክፍል ባለሙያው ገብረጊዮርጊስ ዘሩ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በዚም መሰረት ጳውሎስ ሆስፓቲል የማረጋገጫ ካርታ እንደተሰጠው ተገልጿል።

ተቋሙ አሁን ላይ የሕንፃው ግንባታ እንዲጀመር የጨረታ ሰነዱን አዘጋጅቶ ማስረከቡ የተነገረ ሲሆን፤ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥም የግንባታ ሥራውን ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙን አቶ ገብረጊዮርጊስ ለአሐዱ ገልጸዋል።

አቤት ሆስፒታል ሊያስገነባው ያሰበው አዲስ ሕንፃ ሲጠናቀቅ፤ ደረጃቸውን የጠበቁ 18 የቀዶ ሕክምናና 40 የማገገሚያ ክፍሎች፣ እንዲሁም ከ700 በላይ አልጋዎች የሚኖሩት ሲሆን፤ ለአስተዳደርና ለልዩ ልዩ ሥራዎች ማከናወኛ የሚውሉ በርካታ ክፍሎችን እንደሚይዝም ተገልጿል፡፡

@etconp
👍6
👉ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት

በገበታ ለትውልድ እየተገነቡ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች በሶማሌ ክልል በመገንባት ላይ ያለው የሸቤለይ ሪዞርት ግንባታ ሂደት

@etconp
👍6
👉ዓለም ዐቀፍ የውል ሰነዶች (መደበኛ ውሎች)

🚧ከ 'FIDIC' በተጨማሪ በእኛ ሀገር ብዙም አይታወቁም እንጂ ሌሎች ተቋሞች ያዘጋጇቸው ስታንዳርድ ውሎችም አሉ።

💫ለምሳሌ፦ Joint Contract Tribunal (JCT) የሚባል ዘርፉ የሚመለከታቸው ቡድኖች ተሰባስበው ያዘጋጁት ከ1909 ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሰነድ አለ።

📜ሰነዱ በ2005 ተሻሽሎ የወጣ ሲሆን JCT Standard Building Contract የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

💫የአሜሪካ አርክቴክቶች ማኅበር (AIA) ያዘጋጀውም  General Conditions አለ።

💫Institute of Civil Engineers (ICE) ደግሞ በ2005 ያወጣው The New Engineering Contract (NEC 3) በጣም ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱንና በእንግሊዝ ሀገር በባሕር ሥር የሚያልፈውን የባቡር ሐዲድ ውል የተፈራረሙበት መሆኑን Murdoch and Huges የተባሉ ጸሐፊዎች የኮንስትራክሽን ውሎች በሚል ርእስ በጻፉት መጽሐፍ ጠቅሰዋል።

ይህ ተቋም ቀደም ብሎ በ1945 ለመጀመሪያ ጊዜ ስታንዳርድ ውል አዘጋጅቶ ነበር።

⭐️በየጊዜው እየተሻሻለ መጥቶ ሰባተኛው እትም በ1999 ICE 7 Condition of Contract – measurement Version በሚል ርእስ ታትሟል።

💫FIDIC ያዘጋጀው ስታንዳርድ ውል ከዚህ ICE ካዘጋጀው ስታንዳርድ ውል ከ4ኛ እትም የተወሰደ ወይም የተቀዳ እንደሆእነ መርዶክ የተባለ ጸሕፊ እና ዘውዱ ተፈራም ጠቅሰውታል።

🏷ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች (ለምሳሌ የዓለም ባንክ) Standard Biding Docuement for Procurement በሚል በ1995 ባዘጋጀው ሰነድ ውስጥም ጠቅላላ አናቅጽ ሰፍረው እናገኛለን።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ዋናው ቻናላችን ለመቀላቀል @ETCONp

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍4🙏2❤1
የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር አዋሽ አካባቢ መጠነኛ ጉዳት አጋጠመው

15 ሜትር ርዝመት ያለው የባቡር ሃዲዱ ብረት ወደ መሬት መስጠሙን እና አንዳንድ የሃዲዱ ማሰሪያዎች (ማያያዣዎች) መቆራረጣቸውም ተገልጿል፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) የጉዳት መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተፈጠረውን መጠነኛ ጉዳት በፍጥነት በማስተካከል መስመሩን ወደ ሙሉ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

@etconp
👍4❤1
👉አዲስ የ ስራ ቅጥር

🏷አዲስአበባ መንገዶች ባለስልጣን

@etconp
👍4
👉በሐዋሳ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል

በሐዋሳ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሼል በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ተናግረዋል፡፡ 

የኮሪደር ልማት ሥራው ሐዋሳ ከተማን አዲስ ገፅታ እያላበሳት እንደሚገኝም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ በከተማዋ እየተካሄደ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ሥራ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በኮሪደር ልማት ሥራው የተያዙ ዕቅዶችን በተሟላ መንገድ መተግበር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡

@etconp
👍4❤1
👉ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎችን የሚያከናውኑ ላይ ከእስራት እስከ ፈቃድ ዕገዳ ቅጣት የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

🚧ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎች በሚያከናወኑና ሌሎች የወንጀል ድንጋጌዎችን የሚጥሱ ባለሙያዎች፣ የሥራ ተቋራጮችና አማካሪዎች ላይ ከእስራት እስከ ፈቃድ ማገድ ቅጣት የሚጥል በሕንፃ ረቂቅ አዋጅ ተካቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡ 

⏺ረቂቁ የቀረበው ሐሙስ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄው ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ ስብሰባ ነው፡፡ በረቂቅ አዋጁ ክፍል ዘጠኝ የተቀመጠው አስተዳደራዊ የወንጀል ቅጣቶችን በተመለከተ፣ አዋጁን ለማስፈጸም የሚወጡ ድንጋጌዎችን በሚተላለፉ ሰዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ ይደነግጋል፡፡

በአሠሪ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ የአማካሪነት የሙያ ኃላፊነት መጣስና በረቂቅ አዋጁ የተቀመጡ ዝርዝር ድንጋጌዎችን ተላልፈው የተገኙ ግለሰቦች፣ የሥራ ተቋራጮችና የሚመለከታቸው አካላት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ በተባሉበትና አንቀጽ እስከ ተመለከተው ከፍተኛ እስራት ዘመን ቅጣት በተጨማሪ፣ የሙያ ወይም የሥራ ፈቃዳቸው እንደሚታገድ ተደንግጓል፡፡

በሕንፃ በረቂቅ አዋጅ ዘጠኝ የተቀመጠው አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶችን በተመለከተ፣ አዋጁን ለማስፈጸም የሚወጡ ድንጋጌዎችን በሚተላለፉ ሰዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ በረቂቁ ተመላክቷል፡፡

ያላግባብ በተሰጠ የግንባታ ፈቃድ፣ እንዲሁም የመቆጣጠር ግዴታን ባለመወጣት ሕገወጥ ግንባታ እንዲከናወን የረዳ ግለሰብ ከአምስት ዓመታት እስከ አሥር ዓመታት የሚደርስ ፅኑ እስራት፣ ከአሥር ሺሕ ብር ጀምሮ እስከ አምስት ሺሕ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡

ደረጃው የማይፈቅድለት ወይም ተገቢው ፈቃድ ሳይኖረው ግንባታ ያከናወነ ግለሰብ (ሥራ ተቋራጭ) እስከ አሥር ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራትና እስከ አሥር ሺሕ የሚደርስ የገንዘብ መቀጫ እንደሚቀጣ በረቂቁ ተዘርዝሯል፡፡

ማንኛውም የተመዘገበ የሥራ ተቋራጭ ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ሲያከናውንና ግንባታው አደጋ ያስከተለ ከሆነ፣ ከአምስት ዓመታት እስከ አሥር ዓመታት ፅኑ እስራትና ከ50,000 እስከ 100,000 ብር እንደሚቀጣ በረቂቁ ተቀምጧል፡፡

የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ የሕዝብ ጤንነትና ደኅንነት መጠበቅ፣ የሕንፃ ተደራሽነት ለአካል ጉዳተኞችና ለሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ለማረጋገጥ የሚያስችል፣ በአገሪቱ በአጠቃላይ ተፈጻሚ የሚሆን ዝቀተኛውን ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ነባሩ ሕግ በአፈጻጸም ወቅት የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ስላሉበት፣ የአካል ጉዳተኞችን ተደራሽነት የሚያረጋግጥ፣ የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ግልጽና ለአተገባር ምቹ የሆኑ አሠራር መዘርጋት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቁ አዋጅ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

ረቂቁ በአሥር ክፍሎችና በ54 አንቀጾች የተዋቀረ መሆኑን፣ የተፈጻሚነት ወሰኑ ስለሕንፃ ግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ክትትልና ቁጥጥር፣ አስፈጻሚ አካላት ተግባርና ኃላፊነት፣ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶችን የተመለከቱን ጨምሮ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ተካተውበታል፡፡

የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 2/2017 ሆኖ ለፓርላማው የከተማ መሠረተ ልማትና ትርንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

Via Reporter

@etconp
👍10❤3
👉የ ጨረታ ማስታወቂያ

🔰የገበያ ማዕከል ህንጻ የማሻሻያ ዲዛይን ሾል የጨረታ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‏ ማስታወቂያ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‏

▶️የብርሀን ጮራ ኮልፌ የገበያ አዳራሽ አክሲዮን ማህበር የገበያ ማዕከሉን ህንጻ የማሻሻያ ዲዛይን ስራ በዘርፉ ዕውቀትና ልምድ ባለው ድርጅት ወይም ባለሙያ ማሰራት ይፈልጋል።

🚧ስለሆነም ተጫራቾች፡-

⏺1.በሙያው በቂ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

⏺2.በስራ ዘርፉ የንግድ ምዝገባና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።

⏺3.የቲንና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው።

⏺ቢቻል በገበያ ማዕከል ህንፃ ማሻሻያ ዲዛይን ስራ ልምድ ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

💫ተጫራቾች ለዲዛይኑ ስራ መነሻ እንዲሆን የተዘጋጀውን የመግለጫ ፅሁፍ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከአ ማህበሩ ጽ/ቤት መውሰድ ይገባቸዋል።

⏺ተጫራቾች ለዲዛይን ስራው መነሻ የሆነው መግለጫ ላይ ግልፅ ያልሆነ ጉዳይ ቢኖር ከአክሲዮን ማህበሩ ስራ አመራር ቦርድ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።

⏺ተጫራቾች የተዘጋጀውን የዲዛይን ስራ የመነሻ ሀሳብ መሰረት በማድረግ ዲዛይኑን የሚሰሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም 10 ሰዓት‍‍‍‌‌‍‍‍‌‌‌‍‌‌‍ ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።

⏺አክሲዮን ማህበሩ ለጨረታ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‏ ውድድር ከቀረቡት ድርጅቶች ወይም ባለሙያዎች መካከል ጠቃሚና አሳማኝ የሆነ ማሻሻያ ያቀረበውን የመምረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው።

🏷የጨረታ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‏ው አሸናፊ የተሰራውን ዲዛይን ማፀደቅ አለበት።

📜ከላይ በተራ ቁጥር 1 ፣ 2 እና 3 የተጠቀሱ መረጃዎች ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አብሮ መቅረብ አለበት።

⭐️ጨረታ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‏ው ጥቅምት 13 ቀን 2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

⏺አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‏ው አይገደድም።

የብርሀን ጮራ ኮልፌ የገበያ አዳራሽ አክሲዮን ማህበር

@etconp
👍5
2017_E_C_1st_QUARTER_CONSTRUCTION_WORKS_ONLY_DIRECT_COST_01_02_171.pdf
26.8 MB
ቢሮው ጥቅምት 01/2017 ዓ/ም ባወጣው የ2017 አንደኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ (Direct Cost) ጥናት ሰነድ ላይ sanitary እና Road work ጥናቶችን የያዙ ገፆች በመዘለላቸው ይቅርታ እየጠየቅን የተሟላው ሰነድ እንሆ፡፡

ጥቅምት 04/2017 ዓ/ም የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
@etconp
👍7🙏2
ጥያቄ፦ በግንባታ ሥራ ሂደት የሚመጡ የሥራ መለዋወጦች ወይም በውል ከተያዘው ሥራ የሚጨምሩ ወይም የሚቀንሱ ልዩነቶች (Variation) ሲኖሩ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ በራሱ ውሳኔ ማጽደቅ የሚችለው በውል ከተያዘው የግንባታ ዋጋ ላይ ከስንት ፐርሰንት በላይ ካልጨመረ ወይም ካልቀነሰ ነው? @etconp

📩(ለመልስዎ ህጋዊ ድጋፍ ያለው ማብራሪያ በአስተያየት መስጫው ላይ /comment box/ ይስጡ)
Anonymous Quiz
33%
🔘 ሀ) 10%
44%
🔘 ለ) 15%
16%
🔘 ሐ) 20%
7%
🔘 መ) 30%
👍12👎9❤2👏2
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
👉ስለሥራ መለዋወጥ (ጭማሪ ወይም ቅናሽ - Variation)

💫በግንባታ ሂደት የሥራ መለዋወጥ (Variation) የሚከሰት አጋጣሚ ሲሆን ይህ መለዋወጥ የሥራ መቀነስ ወይም የሥራ መጨመር ሊሆን ይችላል።

🏷ይህ የሥራ መለዋወጥ በተቆጣጣሪ መሐንዲሱ (Engineer) ትዕዛዝ የሚከናወን ነው።

⏺ነገር ግን በ1988 እና በ1992 ሁለተኛ እና ሦስተኛ እትም በወጣበት FIDIC 1987 አንቀጽ (clause) 52.3 መሰረት የሥራ መለዋወጡን ተቆጣጣሪ መሐንዲሱ ለአሠሪው አካል ሳያሳውቅ የማጽደቅ መብታ ያለው  የውሉን ጠቅላላ ዋጋ ከ15% በላይ የማይጨምር ወይም የማይቀንስ እስከሆነ  ድረስ ብቻ ነው።

🌟የሥራ መለዋወጡ ከ15% በላይ የሚጨምር ወይም የሚቀንስ ከሆነ ግን ከአሠሪው ባለቤት (Employer) ጋር ተወያይቶ በጋራ ቃለጉባኤ ወስነው መሆን ይገባዋል።

📜በመሆኑም ከላይ ለተነሳው ጥያቄ መስሉ፦ ለ) 15% ነው።

❇️ለማንኛውም አስተያየትዎ  እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!

📜ለ ስራ እና ጨረታዎች ምንለቅበት ቻናል ለመቀላቀል👉 @ETCONpWORK

📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT

💫ቲክቶክ:👇

www.tiktok.com/@etconp7

@etconp
👍6
👉NEW VACANCY

የስራው መጠሪያ: Junior architect

የስራው አይነት: በተመደቡበት የሚሰራ - ቋሚ

የስራው ዘርፍ: #አርክቴክቸር_እና_የከተማ_ፕላን

የስራው ቦታ: አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

የትምህርት ደረጃ: የመጀመሪያ ዲግሪ

የልምድ ደረጃ: ጀማሪ

የተፈላጊ ሰው ብዛት: 1

ደሞዝ/ክፍያ: ወርሃዊ

የማመልከቻ ማብቂያ ቀን: November 15th, 2024

የስራው ዝርዝር:

We are looking for graduate Architect with the following skills and interest

* The applicant  should have a proficient Skill  in sketch up, Autodesk revit, lumion, Autocad

* creativity and innovation

* Interested in architectural design and landscape design

* creating photorealistic model and render

* working on a tight schedule and meeting dead line

*Willing to work for long hours

*must have his/her own workstation gaming pc and smart phone

*bsc in architecture

*send ur portfolio that shows ur work

*Experience: 0 - 1year

📩Send Your CV ON Telegram: @m_i_n_t_u

__

https://t.me/ETCONp
👍3🙏2❤1