Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
_@etconp_ታህሳስ_ወር_የ_ኮንስትራክሽን_ማተርያሎች_ዋጋ.xlsx
19.4 KB
👉2017 ታህሳስ ወር የ ኮንስትራክሽን ማተርያሎች ኣሁናዊ ዋጋ

https://t.me/ETCONp

@etconp
👍7🙏7
👉በሀረር ከተማ በኢጣሊያ ወረራ ጊዜ ተገንብቶ በአፈር ደለል ተደፍኖ የነበረው 1.8 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የፍሳሽ ማስወገጃ ጽዳት ተደርጎለት ተከፈተ።

@etconp
👍8
👉የጨረታ ማስታወቂያ

🏷የጨረታ ቁጥር:
SSNT-T516

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሰመራ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ሕንፃ ማስፋፊያ እና ጥገና ስራ ዲዛይን ግምገማ፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር የምክር አገልግሎት (Category l Local and International Consultant for the Design Review, Contact Administration and Construction Supervision of Semera Airport Terminal and Ancillary Facilities Renovation) የሚሰሩ ደረጃ አንድ የማማከር ፍቃድ ያላቸውን የሀገር ውስጥና እና አለም አቀፍ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

በአገልግሎቱ ዘርፍ ለ2015/2016 ዓ.ም ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ እና የTN ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ VAT ተመዝጋቢ የሆነ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2015/2016 ዓ.ም የታደሰ ደረጃ አንድ በሲቪል ምህንድስና የማማከር ፍቃድ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E -99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T516 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) አየ በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት  ይችላሉ፡፡

በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ለሀገር ውስጥ ተጫራቾች ወይም እኩሌታ በአሜሪካን ዶላር ለአለም አቀፍ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና የሚቀርብ ቅድመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የቀድሞ የሰው ሀብት ሕንፃ በስትራቴጂክ ሶርሲንግ የጨረታ መክፈቻ ክፍል በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል አሊ አስፋው ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4552
ኢ-ሜይል: AliAs@ethiopianairlines.com 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ  የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@etconp
👍4❤2🙏2
👉We Need Urgent Excavator Rental

⭐️አስቾኳይ የ ኤክስካቫተር ኪራይ እንፈልጋለን

መቱ -300hrs
አጋሮ -300hrs
ሀዋሳ -300hrs
ባሌ -300hrs
ሚዛን ቴፒ - 1000hrs

📩Contact Me @Tsilch

@etconp
👍15
የቅጥር ማስታወቂያ- ኮንስትራክሽን

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍6❤4👎1
በመሬት መንቀጥቀጡ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደረሰባቸው‼️

በጋቢ ረሱ ዞን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸው ነዋሪዎች ሌላ አማራጭ እንዲፈልጉ አስገድዷል፡፡

በአዋሽ 7 ከተማ አሥተዳደር፣ በአዋሽ ፈንታሌ እና አሚባራ ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

በዚህም እስከ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ እና ዶኾ ቀበሌዎች ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

ጉዳት በደረሰባቸው እና ሌሎችም ሥጋት ባለባቸው መኖሪያ ቤቶች ያሉ ወገኖችን ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ቀለል ባለ ባህላዊ ቤት እንዲኖሩ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በሰው ላይ የተመዘገበ ጉዳት ባይኖርም÷ በሰብል የተሸፈኑ ማሳዎች እና የመኪና መንገዶች ላይ የከፋም ባይሆን የመሰነጣጠቅ አደጋ መድረሱን አንስተዋል፡፡

@etconp
👍8❤3💔1
👉የዲዛይን ለውጥ ሥራ የማን ኃላፊነት ነው??

በመጀመሪያ ስለዲዛይን ሥራ፦  በተለያዩ አካላት እና በተለያዩ መንገዶች ሊከናወን የሚችል ሲሆን የሚከተሉት መንገዶች ዋናዎቹ ናቸው።

[1]. አንድ የፕሮጀክት ባለቤት (client/owner/employer) በግለሰብ ባለሙያ ቢሆን ወይም በድርጅዉ ውስጥ  ድርጅቱ የዲዛይን ባለሙያዎች ያሉት ቢሆን እና ተያያዥ የዲዛይን አማካሪነት ንግድ ፍቃድ ያለው ከሆነ በራሱ ዲዛይን ሊሠራ ይችላል። በዚህ አግባብ የንባታ ባለቤቱም የዲዛይን አማካሪ ድርጅቱም ራሱ ይሆናል ማለት ነው። ተቋራጩ ግንባታ እያከናወነ ያለው ከዚህ አይነት ድርጅት ጋር ተዋውሎ ከሆነ ዲዛይኑን የማሻሻል ኃላፊነቱ ዲዛይኑን የሠራው /የግንባታ ባለቤቱ/ ነው። 

[2] አንድ የግንባታ ባለቤት በዘርፉ ዕውቀት ባይኖረው ወይም ተያያዥ የዲዛይን ሥራን ለመሥራት ሕጋዊ ፍቃድ ያለው ድርጅት ባይኖረው የዲዛይን ሥራውን ሕጋዊ ፍቃድ ላላቸው አማካሪ ድርጅት ሰጥቶ ያሠራል። ይህ በሆነ ጊዜ ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር ሁለት አይነት ውል ሊኖራቸው ይችላል። ዲዛይኑን ሰርቶ እስከሚጸድቅ ድረስ በሚሰጡ ሙያዊ አስተያየቶች መሰረት እስከ ማስተካከል ወይም የግንባታ ሂደቱን እስከመቆጣጠር የሚደርስ ውል ሊይዙ ይችላሉ። ነገር ግን ዲዛይኑን የሠራው አማካሪ የተዋዋለው ውል ዲዛይኑ እስከሚጸድቅ ድረስ ብቻ ላለው ግድፈት የሌለበትና የተሟላ ሥራ እስከማስረከብ ከሆነ ግንባታው ከተጀመረ በኋላ በባለቤቱ ወይም ሕጋዊ ወኪሉ መሐንዲስ በኩል የሚነሱ የዲዛይን ቅያሬ (ማሻሻያዎችን) የማስተካከል ግዴታ የለበትም። ተጨማሪ ውል ካልያዘ በቀር በሀሳብ ለውጥ መሰረት መጀመሪያ በተሰራበት ውል እና ዋጋ እንዲቀይር አይገደድም። ይህ በሚሆንበት ሰዓት ዲዛይን ለውጥ (ማሻሻያ) ማድረግ አዲስ ውል ተይዞ ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር ወይም በኮንትራክተሩ በኩል ሊሆን ይችላል። በ'FIDIC MDB-Harmonized Edition sub clause 4.1 እና 13.2  መሰረት "የኮንትራት ውል ስምምነት ሰነዱ የዲዛይን ለውጥ ማሻሻያን ኮንትራክተሩ እንዲሠራ የሚገልጽ ከሆነ  ተቋራጩ አስፈላጊውን የማሻሻያ ንድፈ ሀሳብ (proposal) አቅርቦ በሁለቱም ወገን (both contractor & employer) ስምምነት ላይ ተደርሶ ከተፈረመበት ራሱ ተቋራጩ ሊሠራ ይችላል" ብሎ አስቀምጧል።

[3] አንድ የሥራ ተቋራጭ ጎን ለጎን የዲዛይን ፍቃድ ያለው ድርጅት ያለው ከሆነ ዲዛይኑንም ግንባታውንም የሚሠራበት የውል ስምምነት (Contract agreement) መፈራረም የሚችልበት መንገድ ያለ ሲሆን ፕሮጀችት የማስተላለፍ ሂደቱ Design-Build (DB) project delivery method ተብሎ ይጠራል። (ዲዛይኑን የሠራው ይገነባዋል እንደማለት ነው)። በዚህ ሁኔታ ተቋራጩ ራሱ የሠራውን ዲዛይን እየገነባ ከሆነና የዲዛይን ለውጥ ከተፈለገ በአዲስ ውል ታስሮ የተቋራጩ ዲዛይን ቢሮ ተለዋጩን ዲዛይን ሊሠራ ይችላል።

[4]... ይቀጥላል


⭐️Youtube ገፃችን ላይም ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO

@etconp
👍10👏2
👉ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ኣዲስ የ ETABS በ ኣማርኛ ቲቶርያል ከ introduction ጀምሮ Analysis እና Design ኣካተን ምርጥ ቪድዮ ኣዘጋጅተንላቹዋል።

🙏ለ YOUTUBE ቻናላችን አዲስ ከሆኑ SUBSCRIBE በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ እንዲሁም ለወዳጅዎ ያጋሩ❤️

🫵እንሆ ዛሬ ክፍል 1 👇

https://youtu.be/KpdDcI0QPnY?si=43m3fudgDUOZtPxd

@etconp
👏9👍4🥰2🙏2
👉NEW VACANCY

⭐️Contract Administrator Engineer - Road Project

#ethiopian_engineering_corporation

#Adama


🚧Bachelor's Degree in Civil Engineering, or in a related field with relevant work experience in construction specializing in Road and Bridge construction.

❇️Duties & Responsibilities:

- Drafting, reviewing, and negotiating contracts, ensuring that they align with the organization's objectives and legal requirements
- Resolving disputes or issues that may arise during the course of the contract relationship.
- Establishing and maintaining relationships with vendors, suppliers, and other external parties involved in contract agreements.
- Identifying and assessing risks associated with contract agreements, including financial, legal, operational, and reputational risks.

⏺Quanitity Required: 2

⏺Minimum Years Of Experience: #3_years

⚡️Deadline: January 10, 2025

📩How To Apply: Apply using the provided link below👇

https://forms.office.com/Pages/ResponsePage.aspx?id=fbibbAsHyk2HrMuCOdJR7l_tOeSslK1NsGRsQb8bHJdURUg0Q1JGN1VVNUs0MlNZSUFDRzFGVFk1My4u

@etconp
👍8❤1
⭐️Junior Civil Engineer

#alemayehu_ketema_general_contractor

#Addis_Ababa


💫BSc Degree in Mechanical Engineer, Civil Engineer or in a related field of study

⏺Location: Different Projects

⏺Quanitity Required: 5

⏺Minimum Years Of Experience: #0_years

⚡️Deadline: January 10, 2025

📩How To Apply: Submit your application letter in person to Alemayehu Ketema General Contractor Human Resource Development & Administration Department, located at Yerer Ber LEKA Building 4th floor.

☎️For more information contact Tel. +251116477793\+251116477793

@etconp
👍13
👉«አንድ ተቋራጭ በመጀመሪያው ዉል (ጨረታ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ) Rebate ቢኖረው እና በዋጋ ንረት ምክንያት የዋጋ ማሻሸያ ቢሰራለት፤ አዲሱ ውል/ የተሻሻለው ውል REBATE  ይደረጋል ወይስ አይደረግም?»

🏷አንድ የሥራ ተቋራጭ በመጀመሪያው ውል መጀመሪያ ላይ የዋጋ ቅናሽ አቅርቦ ጨረታውን ቢያሸንፍ እና በኋላ ላይ የዋጋ ማስተካከያ (price adjustment) ከተደረገ በዋጋ ንረት ምክንያት የተሻሻለው ውል ባህሪ በአብዛኛው የሚመሰረተው በውሉ ላይ በተመለከተው «የዋጋ ማስተካከያን በሚመለከት በተቀመጡ ስምምነቶች (terms of price adjustment» ላይ ነው።

ለምሳሌ የግንባታ ሥራው የሕንጻ ግንባታ ከሆነ በሀገሪቱ Public Procurement Agency (PPA) General Condition  of Contract, Clause 62 ሥር ባለው ዝርዝር መሰረት የሚዳኝ ይሆናል።

ይህንን በሚመለከት ተዋዋዮች በልዩ ድንጋጌ (Special Conditions) ያስቀመጡት ስምምነት ካለ ገዢ ሆኖ ይቆጠራል።

💫ነገር ግን የተለመዱ አሠራሮችን እንደመነሻ ለማንየት ከፈለጉ፦

1ኛ) በዋጋ ማስተካከያው (adjustment) የተጠየቀበት ምክንያት የዋጋ ንረትን ወይም የግንባታ ቁሳቁስ (Material Cost) ወይም የሰራተኛ ወጭ (Manpower cost) ወይም የማሺነሪና እቃዎች (Machineries anr tools cost) ለውጦችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ሆኖ የተሰላ ከሆነ ይህ በአጠቃላይ የውል ዋጋ እንደጨመረ ይቆጠራል እንጂ የዋጋ ቅናሽ አይደለም።

ተቋራጩ በዋጋ ንረት ምክንያት የጨመረውን ወጪ እንዲያስተላልፍ ሊፈቀድለት ይችላል፣ ይህም በመጀመሪያ ከተስማማበት ዋጋ በላይ ይሆናል።

2ኛ) የዋጋ ቅናሽ የሚለው ጽንሰሀሳብ በውል ትርጉም መሰረት ተጫራቹ በውድድር ሰዓት ያስገባው ዋጋ አሸናፊ እንዲያደርገው የሚያስገባው በጊዜው የሚተገበር የጠቅላላ ዋጋን (--%) የቅናሽ እድል እንጂ በየጊዜው ተግባራዊ እንዲደረግ የፈቀደው አይደለም።

በኋላ ላይ የመጣው የዋጋ ማስተካከያ ተቀናሽን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ሆኖ ሊሰላ ይችላል።

ይህም ማለት አዲስ የተሰራው ዋጋ የመጀመሪያውን የዋጋ ተቀናሽ (Rebate) ከግምት ውስጥ ሳያስገባ የተተከለ ዋጋ ሊሆን ይችላል።

3) አንድ ጊዜ አሸናፊ ሆኖ የተዋዋለ ተጫራች በኋላ ለሚመጣው የዋጋ ማሻሻያ ላይ ለሚገባው ውል “ቅናሽ የተደረገ” ተብሎ ሊቆጠር የሚችለበት አግባብ የለም።

ምክንያቱም ቅናሹ በመጀመሪያ ስምምነት ላይ በተደረገው ዋጋ ላይ ነው አዲሱ ዋጋ (ከዋጋ ግሽበት በኋላ) ከመጀመሪያው ጨረታ የበለጠ ወጪን የሚያንፀባርቅ ሊሆን ይችላል እንጂ  ተቀናሽን ታሳቢ ማድረጉ ምንም አይነት ጥቅም የለውም።

ስለሆነም ቀድሞ የነበረው (ዋናው) ተቀናሽ በዋጋ ግሽበት ምክንያት ተስተካክሎ ይቀራል ማለት ነው።

⭐️Youtube ገፃችን ላይም ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO

@etconp
👍8❤7
👉ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ኣዲስ የ ETABS በ ኣማርኛ ቲቶርያል ከ introduction ጀምሮ Analysis እና Design ኣካተን ምርጥ ቪድዮ ማዘጋጀታችን ይታወሳል።

🫵እንሆ ዛሬ ክፍል 2 ጭነንላቹዋል👇

https://youtu.be/x6Q0_TKO6d8
👍13
👉በግንባታ ግዥ ዘርፍ ስራ ልምድ ወይንም ዓመታዊ ተርን ኦቨር አላሟላም ብለው ከጨረታ ተሳትፎ ለመውጣት ከመወሰኖ በፊት ይህንን ይንብቡ?

በፌደራል መንግስት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥ መመሪያዎች ላይ ከተቀመጡ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል በግንባታ ግዥ ጨረታ ውድድር ላይ የስራ ልምዱ እና  ዓመታዊ ተርን ኦቨር ላይ በዶላር ምንዛሬ ለውጥ መሰረት የሚደረግ ማስተካከያ መኖሩ ሲሆን ይህም እንደሚከተለው ይሰላል።

1) ለጨረታ ግምገማ ዓላማ የሥራ ተቋራጩ በስራ ልምድነት እንዲያዝለት በሚያቀርበው የግንባታ ውለታ ዋጋ ላይ ማስተካከያ የሚደረግለት ሲሆን ይህም የሚሰላው ጨረታ ከሚቀርብበት የመጨረሻ  ቀን 28 ቀናት በፊት የነበረው የምንዛሪ ምጣኔን ውሉ በተፈረመበት  ጊዜ በነበረው የምንዛሪ ምጣኔ በማካፈል ከተሰላ በኋላ በሚገኘው ውጤት በማባዛት ነው።

2)በተመሳሳይም በጨረታ ግምገማ ጊዜ ለሚደረግ ማስተካከያ አላማ ለተርን ኦቨር ስሌት የሚወስደው ሥራ ተቋራጩ ያቀረበው አመታዊ የግንባታ ሥራ ተርን ኦቨር መጠን' ጨረታ ከሚቀርብበት የመጨረሻ ቀን 28 ቀን በፊት የነበረውን የምንዛሪ መጠን በእያንዳንዱ በጀት አመት የመጨረሻ ቀን ላይ ባለው የምንዛሪ መጠን በማካፈል ነው።

3) ሁለቱም ማስተካከያዎች የሚሰሉት የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ የሚሰጠውን የውጭ አገር ገንዘብ መሸጫ ዋጋ መረጃ መሠረት በማድረግ ይሆናል

⭐️Youtube ገፃችን ላይም ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO

@etconp
👍5👏2
👉አዲሱ የሥራ አመራር ቦርድ

💫የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤14👍10
👉NEW VACANCY

⭐️Site Engineer

#minaye_plc

#Addis_Ababa


💫Bachelor’s Degree in COTM, Civil Engineering or in a related field of study with relevant work experience in civil engineering, with a focus on construction site management.
Experience in finishing work is a plus

📜Duties & Responsibilities:

- Supervise all civil engineering activities on-site, ensuring that work is carried out safely, efficiently, and in compliance with all project requirements and local regulations.
- Ensure that the work meets the required quality standards. Conduct regular inspections and audits to confirm that materials and workmanship adhere to project specifications.
- Coordinate with project managers, contractors, and subcontractors to ensure seamless execution of tasks, resolving any site issues as they arise.
- Maintain accurate site records, including daily logs, progress reports, safety inspections, and any deviations from the original plan.

📍Submit regular reports to the project manager or senior engineer.

⏺Quanitity Required: 3

▶️Minimum Years Of Experience: #2_years
▶️Maximum Years Of Experience: #4_years

⚡️Deadline: January 8, 2025

📩How To Apply: Submit your application and CV with supporting documents via email: hcminaye@gmail.com

@etconp
👍7🙏1