Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉የጨረታ ማስከበሪያ/bid bond/

💫የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና አይነት ነው፡፡

🏷አንድ ለግንባታ ጉዳይ ጨረታ ተሳታፊ የሚሆን ተጫራች ተቋራጭ የሚያቀርበውና ተጫራቹ እንደፈለገ ጨረታውን አቋርጦ እንዳይቀር ለማድረግ እና ምናልባት ተቋራጩ በጨረታው ቢያሸንፍ ውል እንዲገባ ማስገደጃና ዋስትና እንዲሆን ጨረታውን ባወጣው አካል የሚያዝ ዋስትና ነው፡፡

ይህንኑ በሚደግፍ ሁኔታ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጓል፡፡

የዚህ ድንጋጌ ይዘትም ተጫራቹ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ ውሉን ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም እንዲያቀርብ የተጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ካላቀረበ ወይም የጨረታ ማስከበሪያው ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ያገለለ እንደሆነ የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታውን ባወጣው የመንግስት መስሪያ ቤት የሚወረስ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው፡፡

ጨረታ የሚያወጡ መስሪያ ቤቶችም በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ላይ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ አብረው ማቅረብ እንዳለባቸው ሊገለጽ ይገባል፡፡

የጨረታ ማስከበሪያው መጠንም ጤነኛ ባልሆነ እና ቅንነት በጎደለው ሁኔታ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስቡትን ተጫራቾች ወደጨረታው እንዳይገቡ ከወዲሁ ለማስቀረት የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፡፡

ለአሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በምን ሁኔታ መገለጽ አለበት?በህጉ አግባብ ያለመገለጽ ውጤትስ?(Announcing the successful bidder)

ለአሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ መገለጽ ያለበት እና ሊደርሰው የሚገባ በጽሁፍ በደብዳቤ መልክ ነው፡፡

የደብዳቤውም ይዘት የመንግስት መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የተቀበለው ስለመሆኑ፣የአሸነፈበትን ዋጋ፣አሸናፊው ተጫራች ማቅረብ ያበትን የውል ማስከበሪያ መጠን (Amount of performance security) የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡

(Federal public procurement directive:አንቀጽ 16.24 እና አዋጅ ቁጥር 649/2001ዓ.ም አንቀጽ 46) ስለዚህ በህጉ አግባብ አሸናፊነቱ ያልተገለጸለትን አሸናፊ ተጫራች ውል አልተዋዋለም በማለት የውል ማስከበሪያ መውረስ የሚቻል አይሆንም ማለት ነው፡

@etconp
👍17❤1
👉ሀገር በቀል ህንጻ ተቋራጮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድሆኑ በትኩረት እየተሰራ ነው- የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት

ሀገር በቀል ህንጻ ተቋራጮች ከሀገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታምራት ሙሉ(ኢ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቴክኖሎጂ የዘመነና ተወዳዳሪ እንዲሆን ኢንስቲትዩቱ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው።

በዘርፉ ላይ ተወዳዳሪና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት ለዘርፉ ባለሙያዎች፣ ተቋማትና ህንጻ ተቋራጮች የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በተለይ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የህንጻ ተቋራጮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የክህሎት፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ክፍተትን ለመሙላት እየተሰራ ያለውን ስራ ለአብነት አንስተዋል።

ይህንን ተከትሎ የሀገር ውስጥ ህንጻ ተቋራጮች በሀገር ውስጥ ህንጻዎችን ጨምሮ እየተገነቡ በሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ለኢንዱስትሪው ሽግግርና የቴክኖሎጂ እድገት ከፍተኛ ሚና ባለው የቢውልዲንግ ኢንፎርሜሽን ሞዴል ወይም(BIM) ላይ የህንጻ ተቋራጮች፣ የዘርፉ ምሁራንና ኢንዱስትሪዎች በቴክኖሎጂው ዙርያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የማድረግና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል
የፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል ትሬኒንግ የተሰኘው ስልጠናም ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውና የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ለውጥ የሚያመጡ እንደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችን የሚመሩ ባለሙያዎችም ስልጠናውን እንዲወስዱ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት 89 ባለሙያዎች ስልጠናውን አጠናቀው አለም አቀፍ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ማረጋገጫ ወረቀት መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።

የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቴክኖሎጂ የዘመነና ተወዳዳሪ እንዲሆን ኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

Via Construction Management Institute

@etconp
👍10
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉የተጠናቀቀው የመገናኛ አካባቢ ድልድይ እና መንገድ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2👍2
👉NEW VACANCY

💫Civil Projects Engineer

📍Addis Ababa, Ethiopia

⚡️Deadline: January 15, 2025

⏺Vacancies: 1

🚧Education Qualification: Bachelors Degree

🔰Job Description

On behalf of our clients, Repi-Wilmar, we are looking for a Civil Projects Engineer for immediate engagement for a 1-year contract period with the possibility of extension for longer term at Alemgena Area Addis Ababa.

⏺Job Summary

The company is completing its new expansion plant project around Alemgena and has an ongoing other project.
The Civil Projects Engineer will be responsible for supervising the civil engineering works including buildings warehouse and other civil works.

⏺Qualifications

BSc. Degree in Civil Engineering with at least 8 years of experience in civil projects including manufacturing complexes and other civil buildings projects.

Experience in project management in a client side 
Experience in the use of design software and computer aided design and drafting
 
⏺Employment Term –Contract for 1 months with a possible extension
📍Work Location – Addis Ababa, Alemgena

📩How to apply:

⏹If you're interested in this role, email your PDF/Word CV and a brief cover letter to info@ethiocv.com until January 16th, 2025

📜Please write the Job Title (Civil Projects Engineer |Repi-Wilmar)) in your email subject line.

No calls or walk-ins.
Only qualified candidates will be contacted

@etcomp
👍10❤2
👉NEW VACANCY

🚧Century Addis Construction PLC

🏷Contract Bole on Atlas Road Above 2000 Habesha Restaurant or Near Aya  or Mado Hotel at Century   Executive Tower 17th Floor office Human Resources Development and Management Department , Addis Ababa

⚡️January 13, 2025 - January 25, 2025

⭐️1. Civil Engineer

Job Requirement
Qualification: MSc/B.Sc. in Civil Engineering or Related Field
Experience:  4/6 years relevant experience
Qty: 2
Work Place:  Addis Ababa


⭐️2. Site Engineer

Job Requirement
Qualification: MSc/B.Sc. in Civil Engineering or Related Field
Experience:  5/7 years relevant experience
Work Place: Debre brhan

📩How to Apply

❇️Interested and qualified applicants who meet the above requirements are invited to summit their copies of testimonials with update CV and work Experience within 10 working days in persons.

📍Address: – Bole on Atlas Road Above 2000 Habesha Restaurant or Near Aya  or Mado Hotel at Century   Executive Tower 17th Floor office Human Resources Development and Management Department

📞For More information: –  Any question please contact us at 09-60-99-99-97

@etconp
👍7
Procurement_Directive_Amharic(1).pdf
2.1 MB
👉የፌደራል መንግስት የግዥ አፈፃፀም ረቂቅ መመሪያ ከላይ ተያይዟል።

💫የፌደራል ግዥና ንብረት ባለስልጣን ባለድርሻ አካላትን በማወያየት ግብአት እያሰባሰበበት ይገኛል።

📜ከረቂቅ መመሪያው መረዳት እንደሚቻለው የውለታ ጊዜያቸው 18 ወራትና ከዚያ በላይ ለሆኑ የግንባታ ሥራዎች ብቻ የዋጋ ማስተካከያ እንደሚደረግ የሚገልፀውና ማስተካከያው ተፈጻሚ የሚሆነው ከአስራ ሁለት ወራት በኋላ መሆኑን የሚያስቀምጠው የዋጋ ማስተካከያ አንቀፅ ማሻሻያ አልተደረገበትም።

https://t.me/ETCONp

@ETCONpWORK
👍4
👉የ ካዛንቺዝ ኮሪዶር አካል የሆነው የሕዝብ ተሸከርካሪ ማቆሚያና ፕላዛ ዲዛይን ግምገማ ተደረገ፡፡

🚧በካዛንቺዝ ቶታል አካባቢ በ4000 ካ.ሜ ቦታ ላይ በመንግስት እና በግል አጋርነት የሚገነባው የሕዝብ ተሸከርካሪ ማቆሚያና ፕላዛ ዲዛይን ከከንቲባ ፅ/ቤት ፣ ከዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ፣ ከመንግስትና የግል አጋርነት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ፣ ከአልሚው ድርጅት እንዲሁም ከአማካሪው የተውጣጡ አካላት በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

🏷ከምድር በታች 2 ወለሎች እንዲኖሩት ተደርጎ እንደሚገነባ ተገልጿል።

Via የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ጥር 05/2017 ዓ/ም

@etconp
👍5❤3
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤3
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍3
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤3
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍4
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ጥር 2 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤4
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ጥር 2 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
🙏3
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ጥር 2 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👏2👍1
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ጥር 2 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2👍1