Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍4❤1
👉ታሪካዊ ኪነህንጻ

💫እመኪና/መኪና መድሃኔ ዓለም

🚧የአቡነ ዮሴፍ ተራራ ከእጸዋቱ፣ ከእንሰሳቱና ከአእዋፉ በተጨማሪ አስደናቂ ቤተ ክርስቲያናትን በውስጡ ይዟል፡፡ እመኪና መድሃኔ ዓለም አንዱ ነው።

⭐️ምንም እንኳ የተለመደው የንብብር ኬክ ገጽታ ቢኖረውም ከእንጨትና ከድንጋይ ግንብ ይልቅ ቀይ ኖራና በግራጫ ሸክላ ስብርባሪ ተለዋዋጭ ንብብሮች የተሰራ ነው፡፡

⏺እመኪና መድሃኔ ዓለም ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው ትረካ መሠረት የተገነባው በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው፡፡

📜የእናትና ልጅም ታሪክ አለው፡፡

እመ→እናት
ኪና→ልጅ

🔰በርካታ የጥናት ውጤቶች እንደሚሉት ከሆነ ግን በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዐጼ ይኩኖ አምላክ ነው የተገነባው፡፡

በ ጀማል አብዱልአዚዝ በኩል

@etconp
❤7👍2
👉ዓለሙ ስሜ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ፈንድ የቦርድ አባል ሆኑ

የኢፌዲሪ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ፈንድ (UNRSF) የቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራዊ የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ በመቅረፅና የመንገድ ደህንነት ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት በማድረግ የወሰደችው እርምጃ የመንገድ ደህንነትን ለማስፈን ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን ለክቡር ሚኒስትሩ በተፃፈው የሹመት ደብዳቤ ተገልጿል፡፡

በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ሥራዎች የተገነቡ ምቹ የብስክሌትና የእግረኛ መንገዶች እንዲሁም የተሻሻሉ የመንገድ ትስስር ሥራዎች እንደ ሀገር የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ቅንጅትን የሚያሳድጉ መሆናቸውም በደብዳቤው ተጠቁሟል፡፡

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ኢትዮጵያ በመንገድ ደህንነት ላይ ያላትን ቁርጠኝነትና የምታደርገውን ጥረት በመገንዘብና እውቅና በመስጠት ክቡር ዶ/ር ዓለሙ ስሜን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ፈንድ (UNRSF) ስር የባለአደራዎች ቦርድ (Board of Trustees) የቦርድ አባል ሆነው መሾማቸውን አሳውቋል፡፡

የክቡር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ በቦርድ አባልነት መሾም ኢትዮጵያ ልምዷን ለሌሎች ሀገራት እንድታጋራና ከመላው ዓለም በመንገድ ደህንነት ላይ የተሻሉ ተሞክሮዎችን እንድታገኝ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ፈንድ (UNRSF) እ.ኤ.አ አፕሪል 2018 የተመሠረተ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጠቀሜታ ላላቸው ፕሮጀክቶች ተጨማሪ ገንዘብ የማሰባሰብ እና የመደገፍ ሥራን የሚሠራ ዓለማቀፍ ድርጅት ነው፡፡

Via MoTL

@etconp
👍13😁3
👉NEW VACANCY

💫Structural Engineer and Draftsperson

#yotor_building_design_and_consultancy

#Addis_Ababa


🚧Bachelor's Degree in Civil Engineering or in a related field of study with relevant work experience on structural design work

📜Duties & Responsibilites:

- Structural design work using all structural design software
- Drafting AUTOCAD
- Site supervision

⏺Quanitity Required: 1

▶️Minimum Years Of Experience: #2_years

⚡️Deadline: March 19, 2025

📩How To Apply: Submit your application and CV with supporting documents only via email: yotorbuildingdesign@gmail.com

@etconp
👍7❤3😢1
#ሊዝ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አውጥቷል።

ቢሮው በ5ኛው ዙርለጨረታ የቀረበው መሬት ፦
- በአራዳ
- በየካ
- በአቃቂ ቃሊቲ
- በአዲስ ከተማ
- በለሚ ኩራ
- በጉለሌ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎች እንደሆኑ ገልጿል።

በዚህ ዙር 427 የሚሆኑ ቦታዎች ለጨረታ መቅረባቸው ተጠቁሟል።

በተለይ አቃቂ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተሞች በርካታ ስፋት ያላቸው ቦታዎች መቅረባቸው ነው የተነገረው።

በ5ኛው ዙር የሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 2 ሺህ 300 ብር በቴሌብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ እስከ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ/ም ቀን 9 ሰዓት ድረስ ከ
2merkato.com / https://addisland.2merkato.com ወይም afrotender.com link-https: addisland.afrotender.com) ላይ መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ተጫራቾች ቦታዎቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባቸው ተብሏል።

አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት እንደማይችል ተገልጿል። ተጫርቶ ቢገኝ ግን ከጨረታው ውጭ እንደሚሆን ተመላክቷል።

ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ጠቅላላ ዋጋ 50 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ለየቦታ ኮዱ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ከ50 በመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል።

አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ እንደማይችልም ተገልጿል።

(ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች ከላይ ተያይዟል)

@etconp
👍6
👉የመከላከያ አፖርትመንቶች

መከላከያ በድሬዳዋ ከተማ በ3.2 ቢሊየን ብር ያስገነባቸው ከባለ አንድ እስከ ሦስት መኝታ ያላቸው የመኖሪያ አፓርትመንቶች 768 አባወራዎች እና እስከ አራት ሺህ የሚደርሱ ነዋሪዎችን የሚይዙ ናቸው።

ግንባታዎቹ በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ተቋራጭነት ፤ በመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ባለቤትነት ፣ በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ተቆጣጣሪነት የተገነቡ ሲሆን፣ የመከላከያ ግብአት ማምረቻ ድርጅት የግንባታ አቅርቦቶችን መሸፈኑ ታውቋል።

@etconp
🙏2🔥1
👉NEW VACANCY

💫Project Manager

▶️Addis Ababa, Ethiopia

⚡️ቀነ ገደብ: March 22, 2025
⏺ክፍት የስራ ቦታዎች: 4

📍Location: Various Construction Sites
❇️Project Types: Building Construction, Water Works, and Irrigation Projects

📜We are seeking a highly skilled and experienced Project Managers to oversee and manage multiple construction projects across the country. The ideal candidate will have a strong background in managing diverse construction projects, including buildings, water works, and irrigation projects.

🚧Key Responsibilities:

- Plan, execute, and finalize projects according to strict deadlines and budgets.
- Coordinate and manage construction teams, subcontractors, and suppliers.
- Ensure compliance with safety regulations, building codes, and quality standards.
- Monitor project progress, prepare reports, and communicate updates to stakeholders.
- Resolve any issues or delays that may arise during the construction process.
- Manage project documentation, including contracts, permits, and approvals.

🌟Qualifications:

- Bachelor’s degree in Civil Engineering, Construction Management, Hydraulics and/or Irrigation Engineering or a related field.
- Minimum of 7 years of experience in managing construction projects (buildings, water works, and irrigation projects preferred).
- Strong knowledge of construction processes, materials, and legal regulations.
- Excellent leadership, communication, and problem-solving skills.
- Proficiency in project management software and tools.
- Ability to travel and work at various project sites nationwide.

📩How to Apply:

⏺Interested candidates are invited to submit their CV, cover letter, and relevant certifications. Please indicate "Project Manager Application" in the subject line.
Join our team and contribute to the successful delivery of impactful construction projects across the country!
[KBEK CONSTRUCTION]
[HR AND ADMINSTRATIVE DIRECTOR]
[www.kbekconstruction.com]

@etconp
👍4👏2
👉ኢኮስኮ 3D ቴክኖሎጂን ወደ ኢትዮጵያ ሊያስገባ ነው

💫የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን 3D የኮንክሪት ሕትመት ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ ከCasa D'Argilla FZE ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

🚧የመግባቢያ ሰነዱ ዓላማ ጥራትን፣ ቅልጥፍናን እና ወጪ ቆጣቢነትን ለማሳደግ የላቀ 3D የኮንክሪት ሕትመት ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ማድረግ ነው።

⏺ሁለቱ ወገኖች የጀመሩት ተነሳሽነት በተመጣጣኝ ዋጋ እና ፈጣን የመኖሪያ ቤት መፍትሄዎችን በማስተዋወቅ የአገር ውስጥ የግንባታ ኢንዱስትሪን ለመለወጥ ያለመ ነው።

⏺የመግባቢያ ሰነዱን የኢኮስኮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እና የCasa D'Argilla FZE ኩባንያ መስራች ሚስተር ሮላንድ ጃንሰን ተፈራርመዋል።

Via ECC

@etconp
👍8❤3
ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍2❤1
ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2👏2
ጨረታ

አዲስ ዘመን መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤3
👉ቢሮው የቀረቡለትን የኮንስትራክሽን አማራጭ ቴክኖሎጂዎች ተቀብሎ ገምግሟል።

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት እንዲሁም የመዲናዋን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ከተለመደው አሰራር ለማውጣትና ዘመኑን የዋጀ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ዕውን ለማድረግ አልሞ የተለያዩ አማራጭ ቴክኖሎጂዎችና ዕሳቤዎች ያላቸውን አካላት በመጋበዝ ወደኢንዱስትሪው ለማስገባት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በአይ ኤች ኢትዮጽያ የቀረበለትን ፖሊሽድ ኮንክሪት የገመገመ ሲሆን ቴክኖሎጂ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውና ጠንካራ ግንባታዎችን ለማቅረብ የሚያስችሉ 5 አማራጮች እንዳለው በአቅራቢዎቹ ተገልጿል።

እነዚህ አማራጮችም ቤቶችን ቀስ በቀስ ማሳደግ / Increamental Housing /፤ በጋራ ቤቶችን መገንባት/ Coo Housing /፤ በመንግስትና በግለሰቦች ትብብር ግንባታዎችን ማካሂድ / Public and Private Partnership/ አና አሮጌ ቤቶችን ማደስ / Renew Old Housing / ናቸው ተብሏል።

ሌላኛው በቢሮው የታየው ቴክኖሎጂ ደግሞ በኤን ኤን ስቶን ፕሮዳክሽን የቀረበው /Basalt Continues Fiber/ ሲሆን ይህም ባዛልት ፋይበር ፤ ሜሽ እና ቾክ ፋይበርን በግብዓትነት እንደሚጠቀሙ ተገልፆ እነዚህ በሀገር ውስጥ ማምረት የሚቻሉ መሆናቸው ፤ ብረትን ተክተው ማገልገላቸውና የአሽዋና የሲሚንቶ ወጪን መቀነሳቸው ተመራጭ ያደርጋቸዋል ተብሏል።

በግምገማው ማጠቃለያ ላይ የቢሮው ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ኬርያ ሁሴን እንዳሉት የቀረቡት ቴክኖሎጂዎች ከተለያዩ መመዘኛዎች አንፃር ለዘርፉ የሚጨምሩት ዕሴት በቢሮው ታይቶ አዋጭነታቸው ሲታመንበት ወደኢንዱስትሪው የማስገባትና የማስረፅ ስራ ይሰራል ብለዋል።

የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

@etconp
❤3👍3