Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
549 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥቅምት 14  ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👏2
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥቅምት 14  ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤3👍3
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ያወጣው 7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለተጨማሪ 10 ሥራ ቀናት (እስከ ጥቅምት 28/2018) መራዘሙን የመሬት ሊዝ ጨረታ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታውቋል።

📜የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት👇
https://landleasedocument.aalb.gov.et/

@etconp
❤5👍3
"የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ በሊዝ የሚተዳደሩ 2,969 ቦታዎች የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል" - የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ በሊዝ የሚተዳደሩ 2,969 ቦታዎች ወደሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

በእስካሁኑ ተፈቅዶላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ ባለይዞታዎች 2,969 ሲሆኑ 2,581 (86%) የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ክፍያ ከፍለው በማጠናቀቅ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ ወይም የንግድ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል ነው ያለው።

በበጀት ዓመቱ ከዚህ የአገልግሎት ለውጥ 2.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ይሰባሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።

ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉና ለውጥ የተፈቀደላቸው የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን የሊዝ ቅድመ-ክፍያ እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ከፍለው ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸውም ቢሮው አሳስቧል።

@etconp
❤6👍1
👉JOB VACANCY

⭐️Lab technician or cordinating (concrete batching)

📌የሥራ ዓይነት: On-site - Permanent (Full-time)

🕹Addis Ababa

⚡️ቀነ ገደብ: November 3, 2025

⏺ክፍት የስራ ቦታዎች: 1

⏺የትምህርት ደረጃ: Diploma

📜የሥራ መግለጫ

💫We need Lab technician or coordinator in our concrete batching ( ready mix )
Educational level: level 3and above in construction or any related fields

⏺Experiance level : junior Who are ready to learn and to participate effectively

📩Send your cv on @motivated77

@etconp
❤7
👉ፍልውሃ የሚገኘዉ የተውፊቅ መስጂድ ግንባታ ሊጀመር ነው።

🚧መስጂዱን በተሻለ መልኩ ለመገንባት የአዲሰ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ባደረገዉ ጥረት አዲስ፣ ደረጃውን የጠበቀና የተለያዩ አገልግሎቶች የተሟሉለት ታላቅ መስጂድ በሚድሮክ ኢንቬስትመንት ግሩፕ ሙሉ ወጪ እንደሚገነባ ታውቋል።

⭐️Archi Design & Consultancy P.L.C የንድፍ እና የፍቃድ ሂደቱን አጠናቆ የግንባታ ማስጀመርያ እና የክትትል ቴክኒካዊ ሂደቶችን በኀላፊነት በመያዝ የተሻለ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመኑን የዋጀ መስጂድ ለመገንባት ፣ ከሚድሮክ ኮንስትራክሽን ጋር በመሳለጥ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የተለዋጭ መስገጃ ሰፍራ ግንባታ ይጀመራል።

⏺በቀጣይም ዋናዉ ግንባታ ስራ ተግባራዊ ይሆናል።

💫የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝደንት ክቡር ዶክተር ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ ኢትዮጵያዊው ባለሀብት ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አላሙዲን በኢትዮጵያ ለሚያከናውኗቸው ሁለንተናዊና የላቁ የልማትና የማሕበራዊ መልካም ስራዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

⏺የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ባለፈው አመት ከ15 በላይ ደረጃቸውን የጠበቁ መስጂዶች እንዲገነቡ ከተለያዩ ባለሀብቶችና ተቋማት ጋር መነጋገሩ ይታወሳል።

Via ያሚን አሚን ሰማን

@etcconp
❤20
👉ግንባታው የተጠናቀቀውን የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ምን ምን አካቷል

🚧589 ሄክታር በላይ የሚሸፍነው ከባቢ ከካዛንቺስ ቀጥሎ ሰፊው የልማት ስፍራ መሆኑ፤

💫16.5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ የ3 ኪሎ ሜትር ተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ብሎም 33 ኪሎ ሜትር የተዘረጋ የእግረኛ መንገድ፤

⏺ፕላዛዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች፤

⏺5.2 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን፤የመኪና ማቆሚያዎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ስፍራዎች፣ በግል እና የመንግሥት ተቋማት የተገቡ 1107 ሱቆች፤

🏷50.5 ሄክታር አረንጓዴ ሥፍራ፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ 13.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መጋለቢያ መንገድ፣ 38 የአውቶቡስ እና ታክሲ መጫኛ-ማውረጃዎችን አካትቷል።

@etconp
❤13🔥1
👉ሲጠናቀቅ አንድ ኪሎ ሜትር ወይም አንድ ሺህ ሜትር ርዝመት የሚኖረው ጂዳ ታወር እዚህ ደርሷል።

💫አሁን የአለማችንን ረጅሙ ሕንፃ በመባል የሚታወቀውን ቡርጅ ከሊፋን ሕንፃ በ180 ሜትር የሚበልጠው Jidda Tower በ2028 ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ጠቅላላ የግንባታ ወጪው ከ1.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል።

@etconp
❤6👏3
👉ሰሜን ኢትዮጵያን ከጅቡቲና ኤርትራ ወደቦች ጋር የሚያገናኝ ሐዲድ ለመዘርጋት ታቅዷል

🚧ፕሮጀክቱ 1.58 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሏል።

💫የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ሰሜን ኢትዮጵያን ከጅቡቲዋ ታጁራ እና ከኤርትራዎቹ አሰብና ምጽዋ ወደቦች የሚያገናኝ ሐዲድ በ1 ነጥብ 58 ቢሊዮን ዶላር ለመስራት ማቀዱን ሪፖርተርን ጠቅሳ ዋዜማ ዘግባለች።

⏺ፕሮጀክቱ ከመቀሌና ወልዲያ ወደ ሁለቱ አገራት ወደቦች የሚዘረጋ መኾኑን ዘገባው ጠቅሷል።

⏺ኮርፖሬሽኑ ይህንኑ እቅዱን ያቀረበው፣ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ በተካሄደ የባቡር ሐዲድ ኢንቨስትመንት ስብሰባ ላይ መኾኑን ዘገባው ጠቅሷል።

⏺አዲሱ ፕሮጀክት በዓለማቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት ከተያዘው የቱርኩ ኩባንያ ከጀመረው የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሃራ ገበያ የሐዲድ ፕሮጀክት ጋር ግንኙነት የለውም ተብሏል።

@etconp
❤17
👉ናይል ሶርስ ህንጻ

🚧አፍሪካ ጎዳና (ቦሌ መንገድ):በዘለቀ በላይ

💫ይህ ህንጻ እንደጣፋጭ ወግ፣ እንደአስደሳች ክሊፕ ደግማችሁ ደጋግማችሁ እዩኝ ይላል።

⏺ምክንያት አለው!

🏷ዘለቀ እንደወትሮው ህንጻው ላይ ሚዛን መለኪያ ነገር ያጠፋና ተመልካችን ግራመጋባት የቀላቀለበት ግርምት ይለቅበታል።

⏺እንደማንኛውም መደበኛ ህንጻዎች ከተግባራዊ አገልግሎታቸው ባሻገር ለሚዛን የሚጠቅሙ መደበኛ መስኮት እና በር ዘለቀ በጭራሽ አይጠቀምም።

⏺ከዚያም አልፎ ኪነህንጻን በስነቅርጽ ጨዋታ መግለጽ የሚፈልገው አነጋጋሪው ህንጻ ነዳፊ አርማታውን እንደክር ንድፍ አወዛውዞ ተስፈንጣሪ የእይታ ውጥረትን ያመጣበታል።

⏺የተወሰኑ ቦታዎች የሚያበጃቸው ክፍተቶችም የ "ምን ይሆኑ?" ጥያቄ ማስነሳቱም አይዘነጋም።

⏺ይህ ህንጻ በቀድሞው ግዜ በሽክላ ንጣፍ ሊሸፈን የነበረ ቢሆንም በጥሬ ህንጻ ዘይቤ የአርማታው ገጽታ እንዲታይ መደረጉም ሌላ አስደማሚ ደረጃ አጎናጽፎታል።

⏺ዘለቀ በመዲናዋ ውስጥ ከ "ስቴርስ" ህንጻ ባሻገር ሌላ አግራሞት ጫሪ ህንጻ መንደፉ ይበል የሚያሰኝ ሲሆን የጨዋታ ሜዳውን ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ወደአዲስ አበባ የቀየረው ይመስላል።

ጽሁፍና ምስል: ዳዊት በንቲ

Via ethiopian architecture and urbanism

@etconp
❤12👍2🥰1👏1