Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉መሐንዲስ ተገቢውን ክፍያ ፤ ክብርና ቦታ ሲያጣ ሀገር ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በጥቂቱ እንመልከት

📌 ​መሐንዲሶች (የሀገሪቱ የልማት ምሰሶዎች) ተገቢውን ቦታና ክፍያ ሲያጡ፣ የሚያስከትሉት መዘዞች ከግለሰብ አልፈው የሀገርን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ያደናቅፋሉ።

​1. የጥራት እና ደኅንነት ውድቀት (The Quality Crisis)

📌 ​የፕሮጀክት ጥራት መውረድ:

🔨 ልምድ ያለው መሐንዲስ በቂ ክፍያና ክብር ሳያገኝ ሲቀር፣ ለሙያው ያለው ቁርጠኝነት ሊቀንስ ይችላል። ይህም የዲዛይን ስህተቶች፣ የደኅንነት ጉድለቶች እና የፕሮጀክቶች ቶሎ መበላሸት ያስከትላል (ለምሳሌ፡ የመንገድና ድልድዮች ቶሎ መፍረስ፣ ህንፆዎች መውደቅ፤ የመብራትና ቴለኮም ሲስተም ፤ መጠጥ ውኃ ...ወዘተ)

📌 ​የሕዝብ ደኅንነት አደጋ

🔨 መሐንዲስ የሕዝብን ደኅንነት (Public Safety) የሚያረጋግጥ የሙያ ሰው ነው።

🎤🎤 ሙያው ሲናቅ፣

🔨በሙያ ብቃት ሳይሆን በዝምድና የሚሰሩ ሰዎች ይበዛሉ። ይህ ደግሞ የሕንፃዎች መደርመስ፣ የድልድዮች መፍረስ ወይም የፋብሪካ አደጋዎች ዕድልን ይጨምራል።

​2. የአዕምሮ ፍልሰት እና የካፒታል ብክነት (Brain Drain)

📌 ​የሰለጠነ ኃይል ወደ ውጭ መፍለስ:

🔨 በከፍተኛ ወጪ የተማሩ እና የተለማመዱ ወጣት መሐንዲሶች በሀገራቸው ሥራ ሲያጡ ወይም ከሙያቸው ጋር የማይመጣጠን ደመወዝ ሲከፈላቸው፣ የተሻለ ዕድል ፍለጋ ወደ ውጭ ሀገራት (አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ) ይፈልሳሉ።

📌 ​የሀገር ሀብት ብክነት:

🔨 ሀገር በግልና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰአታት እና ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገንዘቦችን አውጥታ ያፈራቻቸው የሰለጠኑ ዜጎች ጥቅም ሳይሰጡ ሲቀሩ፣ ያ ሁሉ ኢንቨስትመንት ለሌሎች ሀገሮች ዕድገት እንዲውል ይደረጋል።

​3. የኢንዱስትሪ ልማት መደናቀፍ (Stunted Development)

📌 ​በውጭ ኤክስፐርቶች ጥገኝነት:

🔨 የሀገር ውስጥ መሐንዲሶች ተገቢውን ልምድ እና ዕድል ሲያጡ፣ ሀገር ለትላልቅ ፕሮጀክቶች (እንደ አውቶሞቢል ፋብሪካዎች፣ የባቡር ፕሮጀክቶች፣ ትላልቅ የኢነርጂ ማመንጫዎች) ሁልጊዜ በውጪ አማካሪዎችና በውጪ መሐንዲሶች ላይ መደገፍ ትጀምራለች።

📌 ​የቴክኖሎጂ ሽግግር አለመኖር:

የሀገር ውስጥ መሐንዲሶች በፕሮጀክቱ ውስጥ ዋና ተዋናይ ካልሆኑ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና የሥራ ዕውቀት በብቃት ወደ ሀገር ውስጥ አይተላለፍም።
ሀገሪቱ ሁልጊዜ ተጠቃሚ እንጂ ፈጣሪና አሻሽይ መሆን አትችልም።

📌 ​የፈጠራ እጦት

🔨 መሐንዲሶች በተገቢው መንገድ ሳይከበሩ ሲቀሩ፣ ለአካባቢው ችግር ተስማሚ የሆኑ ፈጠራዎችን (Local Innovations) ለማምጣት ማበረታቻና ፍላጎት ይጠፋል። ችግሮችን በራሳችን መፍትሄ የመስጠት አቅም ይዳከማል።

ስለዚህ፣ ሀገራችን የምህንድስና ሙያን ከፍ ስታደርግ፣ ለተመራቂዎች የሥራ ዕድል ስትፈጥር እና ተገቢውን ክፍያ ስትከፍል፣ የምታገኘው ዘላቂ ልማት፣ የሥራ ቅልጥፍና እና የሀገር ሀብት ይሆናል።

******

🎤መሐንዲስ የሀገር ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር ነው ፤ ያ ሞተር ተገቢውን ነዳጅ (ክብር፣ ክፍያ እና ሥራ)
ሊያገኝ ይገባል !!👷‍♂️

@etconp
👍32❤14👏4
👉ትኩረቱን በግንባታ ውል ላይ ያደረገ የዓቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

💫የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የኢንዱስትሪውን ዓቅም ለመገንባት የሚያስችለውና ተከታታይነት ያላቸው የክህሎት እና የእውቀት ማሳደጊያ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።

🚧በዘሬው ዕለትም ‹‹በመንግስት የግንባታ ግዥ/Public Procurment Agency (PPA) እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ የምንድህስና ውል አስተዳደር Fédération Internationale des Ingénieurs-Conseils (FIDIC) ›› ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ የዓቅም ግንባታ ስልጠና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ኢ/ር ተክለብርሐን ኪዳኔ ተሰጥቷል።

⏺ከማዕከልና ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ የኮንትራት አስተዳደር ባለሙያዎች የተሰጠው ይኸው ስልጠና ሕግን መስረት ያደረገ የግንባታ ውል ማስተዳደሪያ መርሆዎችን ለባለሙያው የማስጨበጥ ዓላማን አንግቦ እንደተሰጠ ከቢሮው የዓቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ተገልጿል።

Via ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

@etconp
❤6👏2
👉ለግንዛቤዎ!

▪️የዋስትና አይነቶች

 📓 ዋና ዋና የዋስትና አይነቶች ሶስት ናቸው፡፡

1. የጨረታ ማስከበሪያ፣

2. የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና

3. የውል ማስከበሪያ

1.  የጨረታ ማስከበሪያ

▶️ አሸናፊው ተጫራች ውሉን ካልፈረመ ወይም በውሉ ላይ የተገለፀውን ተጨማሪ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ካልቻለ በድጋሚ ለሚወጣው ጨረታ ከወጭ ለመዳን፣

▶️ አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ አቅርቦ ውል ከተፈረመ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያው ለአሸናፊው ተጫራችና ለሌሎችም ተጫራቾች ይመለሳል፡፡ 

2.  የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና

▶️ ለተቋራጩ የተከፈለውን ማንኛውንም የቅድሚያ ክፍያ አስተማማኝ ለማድረግ ይጠቅማል፣

▶️ ዋስትናው ከመቅረቡ በፊት ክፍያ አይፈፀምም

▶️  የሚቀርበው የዋስትና መጠን ለቅድሚያ ክፍያ ከሚከፈለው ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፣ 

3.   የውል ማስከበሪያ

▶️ ተጫራቹ የውል ግዴታውን ሳይወጣ ሲቀር ገዥውን ከጉዳት (ከኪሳራ) ለመጠበቅ ይጠቅማል፣

▶️  ብዙ ጊዜ ለውሉ ውጤታማ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

▶️ ተቋራጩ ስራውን ሳያከናውን ቢቀር የግዥ ፈፃሚው አካል በተያዘው የዋስትና ገንዘብ ስራውን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ወጭዎችን ይሸፍንበታል፡፡

@etconp
👍10❤6
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
👉መሐንዲስ ተገቢውን ክፍያ ፤ ክብርና ቦታ ሲያጣ ሀገር ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በጥቂቱ እንመልከት 📌 ​መሐንዲሶች (የሀገሪቱ የልማት ምሰሶዎች) ተገቢውን ቦታና ክፍያ ሲያጡ፣ የሚያስከትሉት መዘዞች ከግለሰብ አልፈው የሀገርን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ያደናቅፋሉ። ​1. የጥራት እና ደኅንነት ውድቀት (The Quality Crisis) 📌 ​የፕሮጀክት ጥራት መውረድ: 🔨 ልምድ ያለው መሐንዲስ በቂ…
👉የመሐንዲስ የማይተካው ጥቅም

🏗 ​መሐንዲሶች ዘመናዊውን ዓለም የገነቡ ችግር ፈቺና ፈጣሪዎች ናቸው። ጥቅሞቻቸውን በጥቂቱ ለትዝብት ብናይ

​1. 🏢 የመኖሪያ እና የሥራ ምቾት

🎤​ደህንነቱ የተጠበቀ ሕንፃዎች፤ መንገዶች፤ ድልድዮች፤ ግድቦች ቢገነቡ በመሐንዲስ ነው!!

🔨 ከትናንሽ ቤቶች እስከ ግዙፍ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ድረስ፣ ነዋሪዎችን ከአደጋ የሚከላከሉና የመሬት መንቀጥቀጥን የሚቋቋሙ መዋቅሮችን ዲዛይን በማድረግና በመገንባት፤ ዘመናዊ ከተሞች ለኑሮ ተስማሚ እንድሆኑ ከቅየሳ እስከ ግንባታ ፤ ።

🔨 ​የአየር ንብረት ቁጥጥር ቢደረግ በመሐንዲስ ነው!!

በክረምት ሙቀት፣ በበጋ ቅዝቃዜ (HVAC systems) በማቅረብ የኑሮና የሥራ ምቾት ደረጃን ከፍ በማድረግ።

​2. 💊 የጤና እና የሕክምና ግስጋሴ

🎤 ​የሕክምና መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂ ቢፈጠሩ በመሐንዲስ ነው!!

እንደ MRI ማሽኖች፣ የኤክስሬይ መሳሪያዎች፣ እና የሰውነት አካል ተከላ (prosthetics) በመንደፍና በማልማት የሰዎችን ሕይወት በማዳንና የጤና ጥራትን በማሻሻል።

🎤 ​ንጹህ የምግብ እና የመድሃኒት ምርት ቢረጋገጥ በመሐንዲስ ነው!!

የፋብሪካዎችን የማምረቻ ሂደት (Processing Plants) በመንደፍ፣ የምርቱን ደህንነትና ደረጃውን የጠበቀ ጥራት እንዲኖረው በማረጋገጥ ጉልህ ሚና አላቸው።

​3. 🚀 የቴክኖሎጂ እና የኢኮኖሚ ዕድገት

🎤 ​ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎች ቢቋቋሙ በመሐንዲስ ነው!!

የማኑፋክቸሪንግ ሂደቶችን በማቀላጠፍ፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የምርት ወጪን በመቀነስ የሀገርን ኢኮኖሚ በማሳደግ።

🎤 ​ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ቢኖሩ በመሐንዲስ ነው:

ኮምፒውተሮችን፣ ሶፍትዌሮችን፣ ኢንተርኔትን እና ሞባይል ስልኮችን በመንደፍና በማሻሻል መረጃንና እውቀትን ለዓለም በማዳረስ ትልቅ ባለ ብሩዕ አዕምሮ ባለቤቶች ናቸው።

​4. 🗑️ የአካባቢ ጥበቃ እና ዘላቂነት

🎤 ​ቆሻሻ በአግባቡ ቢወገድ በመሐንዲስ ነው!!

የቆሻሻ አያያዝ (Solid Waste Management) እና የውኃ ፍሳሽ (Sewage Treatment) ሥርዓቶችን በመንደፍ የከተሞችን ንጽህናና ጤና በመጠበቅ።

🎤​ታዳሽ ኃይል ቢመነጭ በመሐንዲስ ነው!!

እንደ ንፋስ (Wind) እና ፀሐይ (Solar) ኃይል ያሉ አካባቢን የማይበክሉ የኃይል ምንጮችን በመጠቀም ለወደፊት ትውልድ ንጹህ ዓለምን በማስጠበቅ።

​መሐንዲሶች ባይኖሩ ኖሮ፣ ከፍ ያለ የኑሮ ደረጃችን፣ ምቾታችን እና የጤና ደህንነታችን አይኖርም ነበር።

🏗 መሐንድሶች የሃሳብን ወደ ተጨባጭ እውነታ የሚቀይሩ የዘመናችን ግንበኞች ናቸው።

🎤 የሚንጠጣው ውኃ ፤ የሚንጠቀመው መብራትና ስልክ ፤ የሚንቀሳቀሰው ተሽከርካሪ ቢሰሩ ብቻ ምን አለፋችሁ ብዘረዘረ አያልቅም መሐንዲስ የሀገር ባለዉለታ ነው!!

🎤🎤ትኩረትና ክብር

🎤ለኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ለሀገር ዋልታና ማገር ሆነው ለተረሳው ምሕንድስና!!
🎤ክብር ፅንሰ-ሀሳቦችን ወደ መሠረተ ልማት፤ ምናብን ወደ ተጨባጭ እውነታ ለሚቀይሩ ጀግና መሐንድሶች!!

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ መልዕክታችን ነው👷‍♂️

@etconp
❤26🥰4
👉JOB VACANCY

💫Job Title: Draft Man

🚧Betwon Consulting PLC.

⭐️Bachelor's Degree in Civil Engineering or in a related field

📜Duties and Responsibilities:

- Basic skills on 2D and 3D drawings using Computer-Aided Design (CAD)
- Revise drawings based on feedback from engineers, architects, and clients during the design development phase.
- Gather and organize product information, material specifications, and standard details for inclusion in the drawing sets.

⏺Quanitity Required: 1

⏺Experience: 1 year and above in Draft Man

💵Salary: As per company scale

⚡️Deadline: November 7, 2025

📍Location: Around Bambis, Addis Ababa

📩How To Apply: Interested applicants fulfilling the above requirements can send your CV to on telegram👇

https://t.me/Betwon12

@etconp
❤7👏1
👉JOB VACANCY

🚧Scaffolding Forman

💫ቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 ወይም ዲፕሎማ ኦን ሳይት ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የተመረቀ/ች አግባብ ከሆነ የስራ ልምድ ጋር

🏷ዋና ሃላፊነቶች፡

- የስካፎልዲንግ ቡድንን በመመራት የስካፎልዲንግ መዋቅሮችን መገንባት፣ መቀየር
- የደህንነት ደንቦችን እና የኢንዱስትሪ መመሪያዎችን መከተል።
- የስካፎልዲንግ እቃዎችን እና መሳሪያዎችን ከመጠቀም በፊት መቆጣጠር።
- የስካፎልዲንግ ሰራተኞችን መምራት እና ማስተማር።
- የስካፎልዲንግ እቃዎችን መቆጣጠር ።
- ሪፖርቶችን ለአስተዳደር ማቅረብ።
- በስካፎልዲንግ ስራዎች ውስጥ የሚነሱ ችግሮችን መፍታት።
- በህንፃው ሂደት ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ደረጃዎች ሂደቶች መከታተል። የተለያዩ ቡድኖችን ማስተባበር, ስራዎችን መመደብ እና ችግሮችን መፍታት
- ተዛማጅ የደህንነት ደንቦችን ማክበር እና ማስከበር

⏺Quanitity Required: 10

⏺Minimum Years Of Experience: #6_years

⚡️Deadline: November 14, 2025

📩How To Apply: ከላይ ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች፣ የትምህርት ማስረጃችሁን እና የስራ ልምዳችሁን ፎቶ በማንሳት በቴሌግራም ይህን ሊንክ በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ👇

https://t.me/Heranye

@etconp
❤3👏1
👉በ1ኛ እና 2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስራዎች :-

🚧342 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ፣

🚧185 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ መንገድ ፣

🚧241 ኪ.ሜ የሳይክል መንገድ ፣

💫101 የህፃናት መጫወቻዎች ፣

💫155 የስፓርት ማዘዉተሪያዎች ፣

💫153 ዘመናዊ ፓርኪንግ እና ተርሚናሎች ፣

💫210 የሕዝብ መፀዳጃዎች፣እንዲሁም ዘመናዊ የመንገድ መብራቶች፣በርካታ የህዝብ መገልገያ እና መዝናኛ ቦታዎች፣ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች፣ተገንብተዉ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

@etconp
❤5👍2