Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
549 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉JOB VACANCY

🏷Company: Ovid Respan Consult

⏺Position: Resident Engineer/Site Engineer

⭐️Job Qualifications and Skills:

● BSc degree in Civil Engineering

● 8 years or above relevant site experience 

● AutoCAD and Microsoft Office knowledge 

● A strong understanding of engineering principles, construction methods, and regulations

⏺Salary: Negotiation 

📩Please send your complete CV to the email ovidrespan@gmail.com

⏺Only selected candidates will be contacted via phone call for an interview

@etconp
❤13👍2
👉ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው ከአትላስ- ቦሌ መድኃኒዓለም - ብራስ የኮሪደር ልማት

🚧የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከአትላስ- ቦሌ መድኃኒዓለም - ብራስ የሚዘልቀውኮሪደር በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በቀንና በለሊት ክፍለ ጊዜ በትጋት እየሰራ ይገኛል።

💫የኮሪደሩ አጠቃላይ ርዝመት 2 ነጥብ 34 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን በአማካኝ ከ42 እስከ 50 ሜትር የጎን ስፋት አንዲኖረው ሆኖ በራስ ሀይልና በስራ ማህበራት እየተገነባ ይገኛል፡፡

⏺በእስከ አሁኑ የግንባታ ሂደት ከቦሌ መደኃኒዓለም- ብራስ በሁለቱም አቅጣጫ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመር ትቦ ቀበራ፣ የማንሆል ክዳን ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ከቦሌ መድኃኒዓለም - አትላስ በግራና በቀኝ በኩል 960 ሜትር የትቦ ቀበራ በራስ ኃይል ደቡብ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ፅ/ቤት መከናወን ተችሏል፡፡

⏺በቀሪው የመንገዱ ክፍል የመንገድ አካፋይ ከርቭስቶን ስራ፣ የገረጋኒቲ ሙሌት፣ የሰቤዝ ስራና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

⏺በሌላ በኩል በስራ ማህበራት እየተከናወኑ ከሚገኙ ስራዎች መካከል የአፈር ቆረጣ፣የውሃ፣የቴሌና የመብራት መስመሮች ዝርጋትና የእግረኛ መንገድ ዝግጅት ስራዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

⏺ኮሪደሩ የሳይክል መንገድ ጨምሮ ምቹ የእግረኛ መንገድ፣ የህፃናት መጫዎቻ ሥፍራ፣የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች፣ የመኪና ማቆሚያና ተርሚናል፣አረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎችን አካቶ እየተገነባ ይገኛል፡፡

Via የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

@etconp
❤2
#ማስታወቂያ

Vivo interior design

በዘመናት መኻከል በማይሰለች፣ ሁልጊዜ ኑሩብኝ በሚያሰኝ ቤት መኖር ይፈልጋሉ እንግዲያውስ በተመጣጣኝ ዋጋ በጥንቃቄ እና ጥራቱን በጠበቀ ለሚመለከት ሳቢ አድርገን፤ ቤትዎን አስውበን እናስረክባለን።

ቪቮዎች ነን የቤት ውስጥ ዲዛይን እና ግንባታ  ማሰራት ከፈለጉ ይደውሉልን

Vivo design

0921332907
0923607995
❤2👌2
👉የሪል እስቴት ማስታወቂያዎች የመቶኛ ቁጥሮች

በሪል እስቴት ግብይት ማስታወቂያዎች ይዘት ወስጥ ብዙውን ጊዜ ስሰማ እንደ መሃንዲስ የሚያሸማቅቀን በግብይት ባለሙያዎች በመቶኛ የሚነገሩ የግንባታ እርከን መግለጫዎች ይገኙበታል ( Percentage Progress) ።

ገና ከመሬት ብቅ ያለን ህንጻ 50% የተጠናቀቀ ሲሉ፣ የመዋቅር ( ስትራክቸር) ስራው ተጠናቆ ብሎኬት እየተደረደረለት ያለን ህንጻ 85% የተገባደደ፣ ገና ልስን እየተለሰነ ያለውን 90% የተጠናቀቀ .....ለመጠናቀቅ ሁለት ዓመት የሚጠብቀውን በሁለት ወር የሚረከቡት.... ምናምን እያሉ ሰውን ማሳሳት የተለመደ ተግባር ሆኗል ፣ ይህንን ስህተት ለማስተካከልየግንባታ እርከኖች ግምት ገላጭ የሆኑትን እንመልከት ....

፩) 30% ደረሰ የሚባል ፕሮጀክት የመሰረትና ከመሬት በታች ያሉ ምድር ቤቶች (Basment) ስራ ተጠናቅቆ ከሬት በላይ የተወሰኑ ወለሎች የመዋቅር ስራ የተከናወነለት ሆኖ የህንጻውን ይዘት ( ግዝፈት ) በሚያሳይ ቁመና ላይ የደረሰ ነው።

፪) 60% አካባቢ ደረሰ ለመባል የመዋቅር ስራው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ቢያንስ የብሎኬት ስራ የተጠናቀቀለት ሊሆን ይገባል።

፫) ከ70-85% ደረሰ ለማባል የውስጥና የውጭ ልስን ተጠናቆ፣ የቤቶች የውስጥ የኤሌክትሪክና የውሃ መስመር ዝርጋታዎች ተገባደው ፣ የጋራ መጠቀሚያ ቦታዎች ደረጃና ኮሪደሮች የማጠናቀቂያ ስራዎች ተጠናቀው ፣ የአሳንሰር ገጠማ ተጀምሮ፣ የውጭ ገጽታ ላይ የአሉሚኒየም መስኮቶችና በሮች ተጥመው ፣ የውጭና የውስጥ የቀለም ስራ ቢያንስ ተጀምሮ ልንመለከት ይገባል።

፬) 90-95% ተጠናቀቀ ለመባል ብዙ የማጠናቀቂያ ስራዎች ( Finishing Works) ተገባደው የመገልገያ ቁሶች ( Fixtures ) ገጠማ ማለትም የመብራት፣ ሶኬት፣ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ፣ የመታጠቢያ ገንዳ፣ ኪችን ካቢኔት፣ የውስጥ በሮች፣ የውስጥ ቀለም ..... መጠናቀቅ አለባቸው ።

፭) 95-100% ተጠናቋል ለመባል ዋና ዋና የሚባሉ ስራዎች ተጠናቀው በጠቅላላ በህንጻውና በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ያሉ ጉድለቶችን የማስተካከል የእርማት ስራዎች ውጪ ሁሉም ስራ የተጠናቀቀ ሊሆን ይገባዋል። እየተለዩ ከሚደረግ እርማትና ማስተካከያ ውጪ ሙሉ ስራው ሊጠናቀቀና የህንጻ የመጠቀሚያ ፈቃድ ሊያገኝ ይገባዋል።

ስለዚህ የሪል እስቴት አገበያይ ተቋማትና የሽያጭ ሰራተኞች ሆይ ፕሮጀክቶቻችሁ የደረሰበትን ደረጃ በትክክል የሚገልጽ መረጃ በመስጠት እኛንም ከመሳቀቅ ዘርፉንም ከውሸት ታደጉት።

Via በደሳለኝ ከበደ፣ መሀንዲስ፣ ገንቢ እና ሪል ስቴት አማካሪ

@etconp
👍12❤10
👉የዕለቱ የውጭ ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@etconp
❤5👍1
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

♧ ሁሉን በአንድ ቦታ ለሁሉም ቅርብ

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

♧ ይደውሉልን ያማክሩን

0904040477
0911016833
❤3
⭐️የ"Site Diary" ጥቅምና ይዘት በግንባታ ፕሮጀክት

✍️የሳይት ማስታወሻ (ወይም የግንባታ መዝግብ) በግንባታ ፕሮጀክት ላይ ባሉ ሱፐርቫይዘሮች ወይም መሐንዲሶች በየቀኑ የሚመዘገብ መዝገብ ነው። የሚከተሉት ምክንያቶች እጅግ በጣም አስፈላጊ ያደርጉታል፡ ​ሂደትንና ችግሮችን መከታተል: በየቀኑ የተሰራውን ስራ፣ የአየር ሁኔታን፣ መዘግየቶችን፣ አደጋዎችን ወይም የቁሳቁስ አቅርቦቶችን ይመዘግባል—ይህም ችግሮችን ቀድሞ ለመለየትና ስራን በጊዜ ሰሌዳው ለማስኬድ ይረዳል።

🔨 በግንባታ ሂደት ውስጥ የምናገኛቸው የተለያየ ዓላማና ይዘት ያላቸው ሰነዶች አሉ። ለምሳሌ ያህል፦ የውል ሰነድ (contract document)፣ የሥራ ፍቃድ (Work Permit/order)፣ የግንባታ ፍቃድ (Building Permit)፣ የሥራ ምዘና መዝገብ (Checklists)፣ የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary)፣ ንድፎች (Drawings) ... የመሳሰሉት ይገኙበታል።

🔨 በሀገራችን የውል ፈጻሚዎች (አሠሪ፣ ተቋራጭ እና አማካሪ) ግጭት ውስጥ ለመግባታቸው አንዱና ዋነኛው ምክንያት እነዚህ ሰነዶች በግንባታ ሥራ አለመሟላታቸው መሆኑን የተጠኑ ጥናቶችም ጠቁመዋል።

🔨 ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነውን የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary) እንመለከታለን። ብዙ ጊዜ ስለዚህ ሰነድ ያለን ትኩረት ለዘብ ያለ ሆኖ የሚስተዋል ቢሆንም ብዙ የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና አሠሪዎች ከስረውበታል።

📜ዋና ጥቅሙ በአጭሩ፦

🔨1ኛ). የዕለት ተግባራትን መመዝገቢያ

👉 ይህ የማስታወሻ ጥራዝ ወይም ሰነድ በየቀኑ በግንባታ ቦታው ላይ የተከናወኑ ሥራዎችን እንመዘግብበታለን። የተሰሩ ሥራዎችን፣ ግንባታው ያለበትን ደረጃ፣ በዕለቱ ያለውን የአየር ሁኔታ፣ ለግንባታ ሥራው የተሳተፉ ባለሙያዎችንና የጉልበት ሰራተኞችን ብዛት፣ የገጠሙ ችግሮችን፣ የተወሰዱ መፍትሔዎችን፣ በባለድርሻ አካላት የታዘዙ ልዩ ትእዛዞች (ካሉ) እነዚህ መረጃዎች የምንመዘግብበት የሁሉም የግንባታ ስራዎች አጠቃላይ ዕለታዊ መዝገብ ሆኖ ያገለግላል።
👉ይህ ሰነድ የፕሮጀክቱን እድገት ለመከታተል ወሳኝ ሲሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ውስጥ ግልፅነትን ያረጋግጣል፣ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ስለቦታው ሁኔታ እንዲያውቁ ያግዛል።

🔨2ኛ). ቅሬታ ወይም የክርክር የሚፈታበት ነው፦

👉በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መጓተትን፣ የአቅም ለውጥን ወይም የሥራ ጥራትን በተመለከተ አለመግባባቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ።
👉 በመሆኑም የዕለት ክስተት ማስታወሻው ሰነድ በቦታው ላይ ስለ ሁነቶች እና ሁኔታዎች ማስረጃ የሚያቀርብ ህጋዊ የግንባታ ሰነድ ሆኖ የሚቆጠር ስለሆነ በየትኛውም የፍትህ መንገድ ቅቡልነት አለው።
👉መዘግየቶች ወይም የጥራት ጉዳዮች) ባሉ የይገባኛል ጥያቄዎች ጊዜ እንደ ማስረጃ ያገለግላል፤ ይህም ከውሎችና ከደህንነት ደንቦች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጣል።
👉ለምሳሌ ፦ የጊዜ መጓተት የሚፈጥሩ ክስተቶች ካሉ (ለአብነት) ቀኑን ሙሉ ዝናብ ቢውል ወይም አካባቢው ረብሻ ቢሆን እነዚህ ክስተቶች የወሰዱትን ጊዜ (ሰዓት፣ ቀን፣ ወር) በቁጥር የምናሰላው ከ'Site Diary ላይ ለቅመን ስለሆነ ክስተቶቹ ባስተጓጎሉት የጊዜ መጠን ልክ በውሉ ላይ የነበረውን ግንባታ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ለማራዘም ያግዛል።
👉በሌላም በኩል (ለምሳሌ) የግንባታ ግብአት ማቅረብ የአሠሪው (Client/employer) ድርሻ ቢሆን እና የግንባታ ጊዜ በዚህ የተነሳ ቢጓተትበት ሥራ ተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ እና የሠራተኞች ያለሥራ የቆዩበትን ክፍያ አሠሪው እንዲከፍል ሊጠይቅበት የሚችለው በ'Site Diary ላይ በአግባቡ የተቀመጠ መዝገብ ካለ ነው።

🔨3ኛ) ጥራትን ለመቆጣጠር ማረጋገጫ ይሆናል፦

👉 site diary መያዝ የጥራት ቁጥጥር እርምጃዎችን እና ፍተሻዎችን ለመመዝገብ ያስችላል።
👉የጥራት ቁጥጥር: ፍተሻዎችን፣ ለውጦችን ወይም ማጽደቆችን በመመዝገብ ደረጃዎችን ይጠብቃል እንዲሁም ስራን ደግሞ መስራትን ያስቀራል።
✍️​በመሰረቱ፣ የፕሮጀክትዎ "ዕለታዊ ማስታወሻ ደብተር" ሲሆን ጊዜን፣ ገንዘብንና ጭንቀትን ይቆጥብልዎታል
👉ለምሳሌ፦ በዕለቱ የተሠራው ሥራ የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት ነው ብለን ብናስብ ለእያንዳንዱ ስትራክቸር የተጠቀምንው የፌሮ ብረት አይነትና ብዛት፣ የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠር ብዛት፣ የተከናወኑ የቤተሙከራ ሥራዎችና ውጤቶቻቸው እና የተስተዋሉ ያልተሟሉ ጉዳዮችን የምንመዘግብበት ስለሆነ የግንባታ ሥራ በዲዛይኑ መሰረት ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልቶ እየተከናወነ ስለመሆኑና ስላለመሆኑ ጥራቱን እንድንቆጣጠር፣ የሚፈለገውን ደረጃና መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና አጠቃላይ የፕሮጀክት ጥራትን ለማሻሻል ያግዛል።

​📋 የሳይት ማስታወሻ ቅፅ

🔨​ቀላል እና ወጥነት ያለው ያድርጉት—ማስታወሻ ደብተር፣ መተግበሪያ (እንደ Procore ወይም Excel ያሉ)፣ ወይም አስቀድሞ የታተሙ ቅጾችን ይጠቀሙ።

🏗 የሳይት ማስታወሻ የሚከተሉትን ያካትታል፡

🔨​ርዕስ (Header): ቀን፣ የፕሮጀክት ስም/መለያ፣ የሳይት ቦታ፣ አየር ሁኔታ (ለምሳሌ፡ ፀሐያማ፣ 25°C፣ ዝናብ ሥራውን አዘገየው)።
🔨​ሰራተኞች:
👉የተገኙ ሰራተኞች፣ ጎብኝዎች ወይም ንዑስ ተቋራጮች ስሞች/ኃላፊነቶች።
​የተሰራ ስራ: ስለ ተግባራት አጭር ማስታወሻዎች (ለምሳሌ፡ "የመሠረት ሰሌዳ ፈሰሰ—80% ተጠናቋል፤ ለግድግዳዎች ሬባር ተገጠመ")።

🔨​ቁሳቁሶች/መሳሪያዎች:
👉የደረሰው/የተጠቀመው (ለምሳሌ፡ "200 ከረጢት ሲሚንቶ ደርሷል፤ ማሽን ለ 8 ሰዓታት ሰርቷል")።

🔨​ችግሮች/መዘግየቶች:
👉ማንኛውም ችግሮች (ለምሳሌ፡ "የኤሌክትሪክ መቆራረጥ የኤሌክትሪክ ሥራን ለ 2 ሰዓታት አቆመ") እና የተወሰዱ እርምጃዎች።

🔨​ደህንነት/ፍተሻዎች:
👉አደጋዎች፣ ፍተሻዎች ወይም ማጽደቆች (ለምሳሌ፡ "ምንም አደጋ የለም፤ ሰሌዳው ፍተሻውን አልፏል")።
​ፎቶዎች/ንድፎች: ለእይታ ምስሎችን ወይም ፈጣን ስዕሎችን ያያይዙ።

🔨​ፊርማ:
👉በስምዎ፣ በኃላፊነትዎ እና በሰዓትዎ (የቀኑ መጀመሪያ/መጨረሻ) ይጨርሱ።
​ከሳይት ከመውጣትዎ በፊት በየቀኑ መመዝገብን ዓላማ ያድርጉ—እውነታን የያዘ፣ አጭር (ከ1-2 ገጾች) እና በቅደም ተከተል የተመዘገበ ይሁን።

@etconp
❤10👏1🙏1
👉የግንባታ ኮንትራቶች አይነቶች

1▪️ጠቅላላ ድምር ውል

በዚህ ውል ውስጥ ኮንትራክተሩ ፕሮጀክቱን በተወሰነ ጠቅላላ ዋጋ ለማጠናቀቅ ተስማምቷል። በግልጽ የተገለጸ ወሰን ላላቸው ፕሮጀክቶች ተስማሚ።

2▪️ የእቃ ዋጋ ውል

ክፍያ የሚከናወነው አስቀድሞ በተስማሙበት የክፍል ዋጋ በተሰራው ትክክለኛ የሥራ ብዛት ላይ በመመስረት ነው። ለተለዋዋጭ መጠኖች ላላቸው ፕሮጀክቶች ጠቃሚ ነው።

3▪️ ወጪ ፕላስ ውል

ኮንትራክተሩ ለተፈጠረው ትክክለኛ ወጪ እና የተወሰነ መቶኛ ወይም ክፍያ ይከፈላል። ወሰን በማይታወቅበት ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።

4▪️ ጊዜ እና ቁሳቁስ ውል

ክፍያው የሚወሰነው በጠፋው ጊዜ እና ጥቅም ላይ በዋሉ ቁሳቁሶች ላይ ነው። ለጥገና ወይም ለጥገና ሥራ የተለመደ።

5▪️የመቶኛ መጠን ውል

ኮንትራክተሩ ከተገመተው ወጪ በላይ ወይም በታች የሆነ መቶኛ ይጠቅሳል። በመንግስት ፕሮጀክቶች ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።

6 ▪️የተራ ውል

ኮንትራክተሩ ዲዛይን፣ ግንባታ እና ኮሚሽን ያስተናግዳል። ደንበኛው ሙሉ በሙሉ ዝግጁ የሆነ ፕሮጀክት ይቀበላል።

7 ▪️የEPC ኮንትራት (ኢንጂነሪንግ፣ ግዥ፣ ግንባታ)

ኮንትራክተሩ የምህንድስና ዲዛይን፣ የቁሳቁስ ግዥ እና ግንባታ በአንድ ጥቅል ስር ያስተዳድራል።

8 ▪️የዲዛይን-ግንባታ ውል

አንድ አካል የዲዛይን እና የግንባታ ስራዎችን ያከናውናል፣ ይህም የፕሮጀክት አቅርቦትን ፈጣን ያደርገዋል።

@etconp
❤11🥰1
👉ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

ቀኑ የሚያበቃበት 14/03/2018 ዓ.ም

@etconp
👍3
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
የወጣበት ቀን ኅዳር 7/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በተጋለጸው ክፍት የሥራ መደቦች ላይ የውጭ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

@etconp
1❤9
ሀረር ጀጎል ÷ አየር ምስል

Via አቤል ጋሻው

@etconp
❤4