Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
538 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉በሁለት ዓመታት ውስጥ በ863 ሚሊዮን ዶላር (112 ቢሊዮን የኬንያ ሺሊንግ) ወጪ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የሪሮኒ-ናኩሩ-ማው ሰሚት መንገድ ምስላዊ ገጽታ።

@etconp
👏4
👉ሜክሲኮ አካባቢ እየተገነባ ያለው የዓባይ ባንክ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ እዚህ ደርሷል

💫በ4ሺህ 591 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውና እየተገነባ ያለው የዓባይ ባንክ ግዙፍ ህንጻ በጠቅላላ 33 ወለሎች አሉት፡፡

🚧የባንኩን የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ እያከናወነ ያለው የቻይና ዉ ዪ የህንጻ ግንባታ ተቋራጭ ነው።

⭐️ባንኩ ከዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ግንባታው በተጨማሪ በባህር ዳር እና ደሴ ከተሞች እንዲሁም በአዲስ አበባ ለም ሆቴል አካባቢ ተጨማሪ ህንፃዎች እየገነባ መሆኑ ይታወቃል።

@etconp
❤8
የአማካሪ_ማህበራት_አገልግሎት_የጨረታ_ማስታወቂያ.pdf
484.2 KB
የአማካሪ ማህበራት አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 004/2018

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዲዛንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት በክፍለ ከተማው ሊያስገነባቸው የፈለገውን ስራ ልዩ አማካሪ አወዳድሮ በመዋዋል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በሟሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
02_የአማካሪ_የማማከር_ስራ_አገልግሎት_የጨረታ_ማስታወቂያ.pdf
668.5 KB
አማካሪ የማማከር ስራ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2018

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት በክፍለ ከተማው በግንባታ ሂደት ላይ ያሉና ሊያስነባቸው የፈለገውን ግንባታዎች ለማስገንባት እና የምክር ስራ ሃገር በቀል አማካሪዎችን አወዳድሮ በማዋዋል ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በሟሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤12
👉የንጉስ ኃይለ ሥላሴ አደባባይ በናይሮቢ

💫በኬንያ ናይሮቢ በአዲስ መልክ የሚገነባው የግሪን ፓርክ የታችኛው መንገድ (Underpass) - በኡሁሩ ሀይዌይ እና በኃይሌ ሥላሴ አደባባይ ላይ ያለው ጥበባዊ ገጽታ ይህን ይመስላል።

⭐️ግንባታውን ለማካሄድ የሚያስፈልገው ወጪ ወደ 15.5 ሚሊዮን ዳላር እንደሚጠጋ ይገመታል።

🚧ለእግረኞች የተሠራው ይህ የታችኛው መንገድ ከኡሁሩ ፓርክ አጠገብ ከሚገኘው የግሪን ፓርክ አውቶቡስ ተርሚነስ ጋር ያገናኛል።


@etconp
❤9👍1
👉አል-ኮባር በአረቢያ ባህረ ሰላጤ ዳርቻ ላይ የምትገኝ የሳውዲ አረቢያ ከተማ ነች፤

🏷ይህ ሰፊ የውሃ ዳርቻ ስፍራ፦ ካፌዎችና መጫወቻ ስፍራዎችን የያዘውን ልዑል ፋይሰል ቢን ፋሀድ የባህር ፓርክን አካቷል፤

💫በአቅራቢያው የሚገኘው የከተማዋ ደሴት የውሃ ማማ (Water Tower) አስደናቂ እይታን ይሰጣል፤

⏺የሱልጣን ቢን አብዱልአዚዝ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል (SciTech) የዓሳ ማቆያ (aquarium) እና የአይማክስ (IMAX) ቴአትር አለው፤

⏺በምዕራብ በኩል ደግሞ የሳውዲ ዘይት ኢንዱስትሪን የሚዳስስ የአራምኮ ኤግዚቢት (Aramco Exhibit) ሙዚየምም ይገኛል።

@etconp
❤6👍1
👉የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት የአሜሪካውን ኬፒኤምጂ የተባለ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አማካሪ ድርጅትን ቀጠረ

በአቪዬሽን ሕግና በሕግ ማማከር አገልግሎት የሚታወቀውን ክላይድ ኤንድ ኮ የተሰኘ ኩባንያን ደግሞ የሕግ ጉዳዮች አማካሪ አድርጎ መቅጠሩን ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ አጠገብ በሚገኘው አቡሴራ በተባለ አካባቢ ለሚያስገነባው፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት የአሜሪካውን ኬፒኤምጂ የተባለ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አማካሪ ድርጅት፣ እንዲሁም በአቪዬሽን ሕግና በሕግ ማማከር አገልግሎት የሚታወቀውን ክላይድ ኤንድ ኮ የተሰኘ ኩባንያን ደግሞ የሕግ ጉዳዮች አማካሪ አድርጎ መቅጠሩን ይፋ አድርጓል።

በፕሮጀክቱ የሕግ ማማከር አገልግሎት ይሰጣል የተባለው ክላይድ ኤንድ ኮ የሕግ አማካሪ ኩባንያ፣ ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ. በ2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አውሮፕላን ቦይንግ ቢ787 ድሪምላይነር በለንደን ሄትሮው አየር ማረፊያ በቆመበት ቦታ ያጋጠመውን የእሳት አደጋ አስመልክቶ፣ በእንግሊዝ የንግድ ፍርድ ቤት በአምራቹ ላይ ላቀረበው ከ5ዐ ሚሊዮን ዶላር በላይ ክስ ግሩፑን ወክሎ ተሟግቷል።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ የቴክኒካዊ ጉዳዮት አማካሪ ኩባንያው በበኩሉ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በአካባቢና በማኅበረሰቡ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖ የተመለከተ ያደረገውን ጥናት አጠናቆ በጥቅምት ወር መጀመሪያ አስረክቧል።

@etconp
❤15👍2
10 የፌራዮ ባለሞያዎች ስለሚፈለግ
በዚህ ስልክ ይደውሉ

☎️+251919145936

@etconpwork
👉Load Distribution Two Way Slab To Beam

💫A two-way slab carries load in both directions (toward beams on all four sides) when the slab aspect ratio (longer side ÷ shorter side) is not large (rough rule: between about 0.5 and 2.0).

📌The slab load is transferred to beams as line loads (kN/m) — think of the slab as many narrow strips that hand their load down to the beams beneath them.

📌Common practical methods to determine the load carried by a particular beam:

🏷1. Tributary-area method (simple, conservative): each beam takes the load from the slab area that is closest to it.

🏷2. Equivalent strip / direct design method (used in code handbooks: ACI, BS, IS/BIS) — account for two-way action and give moment distribution coefficients.

🏷3. FE / plate analysis (most accurate) — used for complex geometry, openings, irregular supports.

@etconp
❤7
👉CONCRETE HAMMER TEST:

💫የኮንክሪት ሀመር ቴስት (Rebound Hammer Test) ወይም Schmidt Hammer Test በመጠቀም የሚደረገው የቴስት ዓይነት ነው።

1.ጥቅሙ ምንድነው?

የዚህ ቴስት ዋና አላማ የኮንክሪት ጥንካሬን (Compressive Strength) ማረጋገጥ ነው። ቴስቱ በፓንች/በማሽን ግፊት/ ብቻ የኮንክሪቱን ደካማ ከባቢ /Weak zone/ እና ጥንካሬን ይለያል።

2.ሀመር ቴስት መስራት አስገዳጅ የሚሆነው መቼ ነው?

2.1.በግንባታ ወቅት የኮንክሪት ስራው ላይ ጥርጣሬ ከነበረ።

የፎርምወርክ ግንባታ ሂደትን ጨምሮ ኮንክሪት በሚሞላበት ወቅት ወይም ተሞልቶ ካለቀ በኋላ ከሚታዩ የኮንክሪት ግድፈቶች በመነሳት ጥርጣሬና ጥያቄ ሲፈጠር ሀመር ቴስት መስራት የግድ ይሆናል።

2.2.የ28ኛው ቀን የላቦራቶሪ (Compressive Strength) ውጤት የሚጠበቀውን ውጤት ሳያስገኝ ሲቀር:

2.3.ሀመር ቴስት መስራት በውል አስገዳጅ ሆኖ ከተቀመጠ:

የውል ቃልን/Contract Provision/መፈፀምና ሪፖርት ማቅረብ ግዴታ ሆኖ በውል ከተቀመጠ ሀመር ቴስት መስራት የውል ቃልን እንደማክበር ሊሰራ ግድ ይሆናል።ይህን መስራት በአብዛኛው የ28ኛው ቀን (Compressive Strength) በላቦራቶሪ መፈተሽን አያስቀርም።

2.4.(Non-Destructive Testing) ሲያስፈልግ

ከዋጋም ይሆን Destructive ከመሆኑ አንጻር የኮር ቴስት (Core Test) ለማድረግ ሳያስፈልግ ሲቀር።

2.5.ከግንባታ በኋ ድንገተኛ ማጣሪያ ሲያስፈልግ።

ሕንፃ ከተጠናቀቀ በኋላ በጊዜ ሂደት የኮንክሪቱ ጠንካራነት ወይም የውስጥ ሁኔታ ተለዋዋጭነት ሲታይ ወይም ጥርጣሬ ሲፈጠር።

2.6.Function Room Change:

በህንፃ ላይ ከጊዜ በኋላ ከባድ ጭነት የሚፈጥር የአገልግሎት ክለሳ ማድረግ ሲያስፈልግ።ለምሳሌ ለሱቅ/ቢሮ የተሰራወን ወለል ወደ ጂምናዚየም ወይም መጋዘን መቀየር ሲያስፈልግ

2.7. Building Modification/የህንጻ ማሻሻያ/

በጊዜ ሂደት በባለቤት የፍላጎት ለውጥ ምክንያት ተጨማሪ ፎቅ እንዲጨመር በሚፈለግበት ጊዜ የቀድሞ ኮንክሪት ጠንካሬ ብቁነት ለማረጋገጥ።

2.8.አሁናዊ ሁኔታ ግምገማ (Structural Assessment) ሲፈለግ

ሕንፃ ከጎዳና እና ከአየር ሁኔታ ተፅዕኖ በኋላ የኮንክሪቱ ጠንካራነት ለመገምገም።

ከጊዜ ብዛት፣ የእርጥበት መጠን፣ እና የኬሚካል ተፅዕኖ ወዘተ ሁኔታዎች የህንጻው ጥራት ላይ ያመጡት ችግር ካለና ለቀጣይ ጥገና ስራ እንደጥናት እንዲያገለግል ሲፈለግ።

3.ሀመር ቴስት እንዴት ይሰራል?

3.1. የሀመሩ መሣሪያ (Schmidt Hammer) መሳሪያው በኮንክሪት ላይ ባለው ውስን ግፊት ኮንክሪቱን ይመታል።

3.2. ሀመሩ ከመታው በኋላ የሚመለስበት መጠን (Rebound Value) ይለካል።

3.3. ይህ ቁጥር በሀመሩ ላይ ያለው ሰንጠረዥ/ጌጅ/የልኬት መስመሮች/ላይ በመመርኮዝ ኮንክሪቱ  ያለው የመጨረሻ ጥንካሬ ግፊት (Compressive Strength) ይታወቃል።

4.ምን ሊያጋጥም ይችላል?

የኮንክሪቱ ከባቢያዊ/Selected test zone/Test Points/ ግፊት በተለያዩ አንድ ላይሆን ይችላል።

ውጤቱም ባብዛኛው ትክክለኛ ውጤት/Certain Result/ ላያሳይ ይችላል።

ጥያቄ:
እንበልና ሀመር ቴስት ማሰራት ያስፈለጋቹ አሁን በግንባታ ወቅት ለተፈጠረ ጥርጣሬ ቢሆን እና የሀመር ቴስት ውጤት ጥሩ/ትክክል ባይመጣ ምን ታደርጋላቹ?

@etconp
❤11👍2