Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
538 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉CONCRETE HAMMER TEST:

💫የኮንክሪት ሀመር ቴስት (Rebound Hammer Test) ወይም Schmidt Hammer Test በመጠቀም የሚደረገው የቴስት ዓይነት ነው።

1.ጥቅሙ ምንድነው?

የዚህ ቴስት ዋና አላማ የኮንክሪት ጥንካሬን (Compressive Strength) ማረጋገጥ ነው። ቴስቱ በፓንች/በማሽን ግፊት/ ብቻ የኮንክሪቱን ደካማ ከባቢ /Weak zone/ እና ጥንካሬን ይለያል።

2.ሀመር ቴስት መስራት አስገዳጅ የሚሆነው መቼ ነው?

2.1.በግንባታ ወቅት የኮንክሪት ስራው ላይ ጥርጣሬ ከነበረ።

የፎርምወርክ ግንባታ ሂደትን ጨምሮ ኮንክሪት በሚሞላበት ወቅት ወይም ተሞልቶ ካለቀ በኋላ ከሚታዩ የኮንክሪት ግድፈቶች በመነሳት ጥርጣሬና ጥያቄ ሲፈጠር ሀመር ቴስት መስራት የግድ ይሆናል።

2.2.የ28ኛው ቀን የላቦራቶሪ (Compressive Strength) ውጤት የሚጠበቀውን ውጤት ሳያስገኝ ሲቀር:

2.3.ሀመር ቴስት መስራት በውል አስገዳጅ ሆኖ ከተቀመጠ:

የውል ቃልን/Contract Provision/መፈፀምና ሪፖርት ማቅረብ ግዴታ ሆኖ በውል ከተቀመጠ ሀመር ቴስት መስራት የውል ቃልን እንደማክበር ሊሰራ ግድ ይሆናል።ይህን መስራት በአብዛኛው የ28ኛው ቀን (Compressive Strength) በላቦራቶሪ መፈተሽን አያስቀርም።

2.4.(Non-Destructive Testing) ሲያስፈልግ

ከዋጋም ይሆን Destructive ከመሆኑ አንጻር የኮር ቴስት (Core Test) ለማድረግ ሳያስፈልግ ሲቀር።

2.5.ከግንባታ በኋ ድንገተኛ ማጣሪያ ሲያስፈልግ።

ሕንፃ ከተጠናቀቀ በኋላ በጊዜ ሂደት የኮንክሪቱ ጠንካራነት ወይም የውስጥ ሁኔታ ተለዋዋጭነት ሲታይ ወይም ጥርጣሬ ሲፈጠር።

2.6.Function Room Change:

በህንፃ ላይ ከጊዜ በኋላ ከባድ ጭነት የሚፈጥር የአገልግሎት ክለሳ ማድረግ ሲያስፈልግ።ለምሳሌ ለሱቅ/ቢሮ የተሰራወን ወለል ወደ ጂምናዚየም ወይም መጋዘን መቀየር ሲያስፈልግ

2.7. Building Modification/የህንጻ ማሻሻያ/

በጊዜ ሂደት በባለቤት የፍላጎት ለውጥ ምክንያት ተጨማሪ ፎቅ እንዲጨመር በሚፈለግበት ጊዜ የቀድሞ ኮንክሪት ጠንካሬ ብቁነት ለማረጋገጥ።

2.8.አሁናዊ ሁኔታ ግምገማ (Structural Assessment) ሲፈለግ

ሕንፃ ከጎዳና እና ከአየር ሁኔታ ተፅዕኖ በኋላ የኮንክሪቱ ጠንካራነት ለመገምገም።

ከጊዜ ብዛት፣ የእርጥበት መጠን፣ እና የኬሚካል ተፅዕኖ ወዘተ ሁኔታዎች የህንጻው ጥራት ላይ ያመጡት ችግር ካለና ለቀጣይ ጥገና ስራ እንደጥናት እንዲያገለግል ሲፈለግ።

3.ሀመር ቴስት እንዴት ይሰራል?

3.1. የሀመሩ መሣሪያ (Schmidt Hammer) መሳሪያው በኮንክሪት ላይ ባለው ውስን ግፊት ኮንክሪቱን ይመታል።

3.2. ሀመሩ ከመታው በኋላ የሚመለስበት መጠን (Rebound Value) ይለካል።

3.3. ይህ ቁጥር በሀመሩ ላይ ያለው ሰንጠረዥ/ጌጅ/የልኬት መስመሮች/ላይ በመመርኮዝ ኮንክሪቱ  ያለው የመጨረሻ ጥንካሬ ግፊት (Compressive Strength) ይታወቃል።

4.ምን ሊያጋጥም ይችላል?

የኮንክሪቱ ከባቢያዊ/Selected test zone/Test Points/ ግፊት በተለያዩ አንድ ላይሆን ይችላል።

ውጤቱም ባብዛኛው ትክክለኛ ውጤት/Certain Result/ ላያሳይ ይችላል።

ጥያቄ:
እንበልና ሀመር ቴስት ማሰራት ያስፈለጋቹ አሁን በግንባታ ወቅት ለተፈጠረ ጥርጣሬ ቢሆን እና የሀመር ቴስት ውጤት ጥሩ/ትክክል ባይመጣ ምን ታደርጋላቹ?

@etconp
❤11👍2
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

♧ ሁሉን በአንድ ቦታ ለሁሉም ቅርብ

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

♧ ይደውሉልን ያማክሩን

0904040477
0911016833
❤2
👉ለዚህ መሰንጠቅ ዋናው ምክንያት ምንድን ነው?

@etconp 👇
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
👉ለዚህ መሰንጠቅ ዋናው ምክንያት ምንድን ነው? @etconp 👇
👉ለዚህ መሰንጠቅ ዋናው ምክንያት ምንድን ነው?

📌​ይህ  በአጥሩ ብሎከትና masonry ግድግዳ ላይ የሚታየው ዋናው ቀጥ ያለ ስንጥቅ (major vertical crack)፣ በድንጋይ መሰረቱ እና በላይኛው የሲሚንቶ ብሎክ ክፍል ውስጥ የሚያልፍ ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው በመሰረት ችግሮች ምክንያት በሚመጣ መዋቅራዊ ውድቀት ምልክት ነው።

🚧​ለዚህ ዓይነቱ ውድቀት /መሰንጠቅ/ ምክንያቶች ሊሆኑ የሚችሉ እነሆ፦

🔨 ​ የመሰረት መንቀጥቀጥ ወይም መውረድ (Foundation Movement or Settlement)

📌​ዋናው መንስኤ በግድግዳው መሰረት ላይ ያለው ልዩነት ያለው መውረድ (differential settlement) ነው። ይህ የሚሆነው የመሰረቱ አንድ ክፍል ከአጠገቡ ካለው ክፍል በላይ ሲሰምጥ ወይም ሲንሸራተት ነው።

🔨 ​ያልተስተካከለ የአፈር ጥንካሬ

📌ከመሰረቱ በታች ያለው አፈር በግድግዳው ርዝመት ላይ የተለያየ የመሸከም አቅም ሊኖረው ይችላል። ለምሳሌ፣ አንዱ ክፍል ጠንካራ መሬት ላይ ሲያርፍ፣ የተሰነጠቀው ክፍል ደግሞ በላላ፣ በትክክል ባልተጨመቀ አፈር ላይ ወይም በጊዜ ሂደት በበሰበሰ አፈር ላይ ሊያርፍ ይችላል።

🔨​አፈር መታጠብ ወይም መሸርሸር

📌የውሃ መግባት (ለምሳሌ ደካማ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የፈሰሰ ቧንቧ ወይም ከባድ የዝናብ ፍሰት) መሰረቱን የሚደግፈውን አፈር ሊያበላሽና ሊያጥበው ይችላል።
📌ይህ ክፍተቶችን በመፍጠር ያ ክፍል እንዲሰምጥ ያደርጋል። በምስሉ ላይ የሚታየው የተንጣለለው መሬት የገፀ ምድር ውሃ ፍሰት ለችግሩ አስተዋፅዖ ሊኖረው እንደሚችል ይጠቁማል።

​🏗️ የግንባታ እና የንድፍ ጉድለቶች (Construction and Design Deficiencies)

📌​ግድግዳው የተገነባበት መንገድ ለመሰረት ችግሮች እንዲጋለጥ አድርጎት ሊሆን ይችላል።

🔨​በቂ ያልሆነ መሰረት

📌መሰረቱ ራሱ ለአፈሩ ሁኔታ በጣም ጥልቀት የሌለው ወይም በቂ ማጠናከሪያ (ሪባር/ብረት) የሌለው ሊሆን ይችላል። በመሰረቱ ወይም በግድግዳው የኮንክሪት ምሰሶዎች ውስጥ በቂ የብረት ማጠናከሪያ አለመኖር፣ መሰረቱ በሰመጠበት አካባቢ ላይ ያለውን ጫና ለመሸከም አቅም ያሳጣዋል።

🔨 ​የመቆጣጠሪያ መጋጠሚያዎች እጥረት (Lack of Control Joints)

📌ግድግዳው በጣም ረጅም ነው፣ እና ሁሉም የብሎከት እና የሲሚንቶ ቁሳቁሶች በሙቀት ለውጦች ይለጠጣሉ እንዲሁም ይኮማተራሉ። የቋሚ የመቆጣጠሪያ መጋጠሚያዎች (vertical control joints) አለመኖር ጭንቀትን ይፈጥራል፣ ይህም በተዳከመ ቦታ ላይ (በተለይ ከመሰረት መውረድ ጋር ሲደመር) ትኩረት አድርጎ ወደ ስንጥቅ ሊለወጥ ይችላል።

✍️ ​የስንጥቁ ቀጥ ያለ እና ያልተስተካከለ (በተለምዶ shear failure ተብሎ የሚጠራ) ባህሪው ከመሬት በታች ባለው እንቅስቃሴ ምክንያት ግድግዳው በአቀባዊ እየተገነጠለ መሆኑን ያሳያል።

@etconp
❤8👍1
👉 ለ7ኛው ዙር የ40/60 እና ለ1ኛው ዙር የካፒታል በጀት ንግድ ቤቶች ጨረታ አሸናፊዎች የወጣ የውል ጥሪ ማስታወቂያ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 21 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 21 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👏1
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍3
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 20 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤3
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 20 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 20 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
🔥4
👉የኦሮሚያ ባንክ የሽግግር ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ከተማ ልብ ውስጥ በጎማ ቁጠባ አካባቢ እየተገነባ የሚገኝ ማራኪ የምህንድስና እና የቴክኖሎጂ ውጤት ነው።

💫በ 2,373 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ይህ ህንፃ፣ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ የሥራ ቦታን ለመፍጠር የላቁ ቴክኖሎጂዎችን አጣምሮ የሚይዝ ነው ተብሏል።

የኦሮሚያ ባንክ የሽግግር ዋና መስሪያ ቤት ምድር ቤትን (Basement)፣ የመሬት ወለልን እና 28 ፎቆችን ያካተተ ባለ ብዙ ደረጃ ህንፃ ነው። የላይኞቹ ሁለት ፎቆች ሙሉ በሙሉ ለህንፃው የሜካኒካል ክፍሎች የተመደቡ ሲሆን፣ ይህም በህንፃው ውስጥ ያሉ የተለያዩ ስርዓቶች (Systems) ያለችግር መስራታቸውን የሚያረጋግጥ እንደሆነ ተጠቁሟል።


⏺ይህ ዘመናዊ ህንፃ ምድር ቤት፣ የመሬት ወለል እና 28 ፎቆች አሉት፦ ከእነዚህም ውስጥ የመሬት ወለሉን ጨምሮ የታችኞቹ አራት ወለሎች 'ፖዲየም' (የታችኛው ሰፊ መሠረት) ሲሆኑ፣ ከ5ኛ እስከ 28ኛው ፎቅ ያሉት ደግሞ የህንፃው 'ታወር' (የላይኛው ህንፃ) ክፍሎች ናቸው።

ህንፃው በ122 ሜትር የሚረዝም ሲሆን፣ የሰዎችን ትኩረት የሚስብ የአርክቴክቸር መግለጫ ነው በሚል ለመግለጽ ይቻላል፤


@etconp
❤10🙏5