Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
538 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉ሼክ አላሙዲን አዳዲስ የቅንጦት ሆቴሎችን በአዲስ አበባ ሊገነቡ መሆናቸው ተሰማ

💫ታዋቂው ቢሊየነር ሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን በአዲስ አበባ ከተማ አዳዲስና ዘመናዊ የሆኑ የቅንጦት ሆቴሎችን ለመገንባት ማቀዳቸው ተሰምቷል።

የሼኩን ኢንቨስትመንቶች የሚያስተዳድረው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ (MIDROC) ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ፣ የሆቴል ግንባታዎቹ የአገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ለማጠናከር ያለመ ነው።

ምንም እንኳ ፕሮጀክቶቹ በግልጽ ባይገለጹም፣ ግንባታው በቅርቡ እንደሚጀመር እና የአዲስ አበባን የዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ከፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

የሸራተን አዲስ ሆቴል በታሪኩ ከፍተኛ ትርፍ ማስመዝገቡ ተነገረ
በተያያዘ ዜና ደግሞ፣ የአዲስ አበባው ታዋቂ ሆቴል ሸራተን አዲስ በቅርቡ በኢትዮጵያ በተደረገው የገንዘብ ምንዛሬ ለውጥ ምክንያት በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን ትርፍ ማስመዝገቡ ተገለጸ።

የገንዘብ ምንዛሬው መስተካከል እና የሆቴሉ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ሸራተን አዲስ ባለፈው የፋይናንስ ዓመት እጅግ የላቀ የትርፍ መጠን ማግኘቱ ተገልጿል።

የሆቴሉ የፋይናንስ ሪፖርት በይፋ ባይገለጽም፣ የዘርፉ ተንታኞች የኢትዮጵያ ብር ተመን መቀነስ ለውጭ ምንዛሬ የሚሰበስቡ የቅንጦት ተቋማትን ገቢ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድግ ሲገመቱ ቆይተዋል።

@etconp
❤18👍5
የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ፕሬዚዳንት

አቶ ሀብታሙ ጌታቸው የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበርን ለሁለተኛ ግዜ በፕሬዚዳንትነት ለማገልገል በማህበሩ በድጋሚ ተመርጠዋል።

እንኳን ደስ አለዎት!

@etconp
❤27
👉አገልግሎት ላይ ያልዋሉ ህንጻዎች ሙሉ ግብር ሊጣልባቸው ነው

💫Ethiopia is introducing a stricter property tax framework that directly targets underutilised buildings and vacant land, aiming to curb urban speculation and accelerate municipal development.

The Federal Property Tax Proclamation No. 1365/2025, accompanied by a Model Regional Property Tax Proclamation from the Ministry of Finance, directs city administrations to levy the highest permissible rates on idle properties.
Urban areas are classified into three tiers, Emerging Towns, Municipalities, and City Administrations. While the law provides for a four-year phased implementation of tax rates, top-tier city administrations are instructed to apply the maximum tax rate immediately on properties deemed "vacant" or "unused." For major cities, this could result in tax liabilities of 1.0 percent of the taxable value from the outset.
“Urban centers shall apply the highest tax rate to vacant land in accordance with the provisions of relevant laws,” the law reads.
The legislation defines "vacant land" as urban plots without any permanent improvements or lawful use as prescribed by land use regulations, contracts, or official notifications.

A new category, "Unused Building or Improvement," extends this to completed structures that remain unoccupied or are not put to lawful use during the tax year. This ensures that even abandoned or underutilised buildings contribute to municipal revenue.
The law also introduces an "In-Lieu-of Tax Contribution" for properties previously exempt, requiring them to pay a substitute fee reflecting the benefits they derive from municipal services, including roads, street lighting, and other infrastructure.
To support enforcement, the Ministry of Finance has mandated the creation of two digital public registers to track land administration and revenue collection, monitoring identification, valuation, and lawful use for every urban plot. "This is a historic step to correct fragmented and inconsistent practices," the Ministry said, noting that the revenue will be reinvested in public services to promote sustainable urban growth.

Property owners are being warned that holding land or buildings idle is no longer cost-free.

As regional authorities adopt the model laws, keeping property unused is expected to become a significant financial burden👇

https://birrmetrics.com/unused-buildings-now-subject-to-full-municipal-tax/

@etconp
❤8🤩1
👉በ6 ሰዓታት ውስጥ 2.4 ኪ.ሜ የአስፋልት ንጣፍ ያከናወኑት ቻይናውያን አድስ ሪከርድ አስመዝግቧል

🚧በቤጂንግ የሚገኙ ቻይናውያን የመንገድ ግንባታ ሠራተኞች፤ 2.4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን መንገድ በ6 ሰዓታት ውስጥ ብቻ አስፋልት በማንጠፍ አዲስ ሪከርድ አስመዝግበዋል።

💫በተለምዶ እንዲህ ዓይነቱን የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ለማከናወን በርካታ ቀናትን አልፎ ተርፎም ሳምንታትን የሚወስድ ሲሆን፣ ይህም ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅን ያስከትል ነበር።

🏷ሆኖም እነዚህ ቻይናውያን ባለሙያዎች መንገዱን ለቀናት ከመዝጋት ይልቅ፣ ሥራውን በ6 ሰዓታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አጠናቀዋል።

⏺በሌሎች የዓለም ሀገራት 2.4 ኪሎ ሜትር መንገድን በ24 ሰዓታት ውስጥ ማንጠፍ እንደ ስኬት ቢታይም፣ ይህንን ሥራ በ6 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ያጠናቀቀ ከቻይና ውጪ ሌላ ሀገር የለም።

@etconp
❤8👍5🔥5🤩1
👉የሀገር ውስጥ የሴራሚክ ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው

የሀገር ውስጥ የሴራሚክ ምርት ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን የሚያስችሉ ፋብሪካዎች በቅርቡ ስራ እንደሚጀምሩ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ገለፁ።

ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በቢሾፍቱ፣ በሞጆ እና በዱከም ከተሞች በሀገር ውስጥና በውጭ ባለሃብቶች በመገንባት ላይ ያሉና ስራ የጀመሩ የሴራሚክ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል።

ፋብሪካዎቹ ለምርት አገልግሎት ከሚጠቀሙት ግብዓት 90 በመቶውን ከሀገር ውስጥ ማግኘታቸው በዘርፉ ውጤታማ ስራ ለማከናወን የላቀ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

ፋብሪካዎቹ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚታዩ የግብዓት እጥረቶችን ለመፍታት ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ካለው የሴራሚክ ፍላጎት 60 በመቶው በሀገር ውስጥ ምርት እንደሚሸፈን ጠቁመው፤ ቀሪው 40 በመቶ ከውጭ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

በዚህ ረገድ የፋብሪካዎቹ ስራ መጀመር በጉባ ብስራቶች ለመገንባት ለታቀዱት መኖሪያ ቤቶች የግብዓት አቅርቦት ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

የሀገር ውስጥ የሴራሚክ ምርት ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን የሚያስችሉ ፋብሪካዎች በቅርቡ ስራ እንደሚጀምሩም ተናግረዋል።

አንዱ ፋብሪካ በቀን እስከ ሃያ ሺህ ሜትር ካሬ ሴራሚክ የማምረት አቅም እንዳለው ጠቁመው ምርቶቹ ጥራታቸውን የጠበቁ በመሆናቸው ያላቸው ተፈላጊነት ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

ለመኖሪያና ለንግድ ቤቶች ግንባታ መሰረታዊ የሆኑት የሴራማክ ውጤቶች በተለይም ለግድግዳና ለወለል የሚውሉ ሲሆን፤ ፋብሪካዎቹ ለዚህ የሚያስፈልገውን ምርት ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ የማምረት አቅም እንዳላቸው ነው ሚኒስትሩ የገለጹት።

የማዕድን ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸው፤ በተለይም ለግብርናው እድገት ወሳኝ የሆነውን ማዳበሪያ ለማቅረብ የላቀ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ግንባታቸው ተጠናቆ ወደ ምርት የሚገቡት ፋብሪካዎች የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ዓይነተኛ ሚና እንዳላቸው አስታውቀዋል።

ፋብሪካዎቹ ከሀገር ውስጥ ፍላጎት ባሻገር ለውጭ ገበያ የሚውል በቂ ምርት የማምረት አቅም እንዳላቸውም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

የግራንድየር ሴራሚክ ፋብሪካ ማርኬቲንግ ማኔጀር ኪሙንግ ፋንግ በበኩላቸው፤ ፋብሪካው በቻይና ባለሃብቶች መገንባቱንና ከአንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀም መሆኑ ለእውቀት ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

የካም ሴራሚክ ውጤቶች ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ተሻለ በልሁ ፋብሪካው በመንግስትና በግል ባለሃብት ትብብር መገንባቱን ጠቁመው የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን መጠቀሙ የውጭ ምንዛሪን ከማዳን ባሻገር ለኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል።

Via ኢዜአ

@etconp
❤9👍4
አልሲሲ በሕዳሴ ግድብ ዙርያ አስገዳጅ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ጠየቁ

ታህሳስ 12/2018 (ገበያ ሚዲያ) የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ምንም አይነት ጠብ እንደማትፈልግና ብቸኛው ፍላጎቷ የዓባይ ውሃ ድርሻዋ እንዳይነካ ሕጋዊ ስምምነት ላይ መድረስ መሆኑን ገልጸዋል። 

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በካይሮ እየተካሄደ በሚገኘው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም ላይ ለመሳተፍ የመጡ የአፍሪካ ሀገራት የልዑካን ቡድኖችን ትላንት ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

ፕሬዝደንቱ በንግግራቸው "ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ልዩነት ቢኖራትም እስካሁን ድረስ ማንንም አስፈራርታ አታውቅም" ያሉ ሲሆን፤ ወደፊትም ችግሮች በውይይትና በፖለቲካዊ መንገድ እንዲፈቱ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

አክለውም የግብፅ ብቸኛ ጥያቄ የዓባይ ውሃ መብቷ እንዲከበር እና በሕዳሴ ግድብ አሞላልና አሰራር ላይ "ሕጋዊና አስገዳጅ ስምምነት" ላይ መድረስ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም የግብፅ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ማስጠበቅ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ይህንን "ለስለስ" ያለ ንግግር ያደረጉት፤ ባለፉት ወራት በሁለቱ ሀገራት መካከል ከፍተኛ የቃላት ጦርነት ሲካሄድ ከቆየ በኋላ ነው። 

ከጥቂት ቀናት በፊት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግድቡን "የጥፋት ግድብ" በማለት ሲገልፁት፤ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በሕዳር ወር መጨረሻ ባወጣው መግለጫ "ግብፅ አሁንም በቅኝ ግዛት ዘመን አስተሳሰብ ውስጥ ናት" በማለት ንግግሩን ኮንኖ እንደነበር ይታወሳል።

Via ገበያ ሚዲያ

@etconp
❤7👍1🤩1
⭐️ቀላል ያለች BOQ

🔰መሠረት ግምታዊ (Approximate) Bill of Quantity – BOQ

1. የቤቱ መጠን (Basic Dataኸ)
ስፋት፡ 6 m × 8 m = 48 m²
ቁመት (Wall height)፡ 3.1 m
የግንባታ አይነት፡ Block work
1 ፎቅ (Single storey)
የጣሪያ አይነት፡ ቆርቆሮ (CGI sheet)
2. የብሎኬት መጠን (Block Quantity)
2.1 የውጪ ግድግዳ ርዝመት
Perimeter = 2(6 + 8) = 28 m
2.2 የግድግዳ አካባቢ
28 m × 3.1 m = 86.8 m²
2.3 የብሎኬት ቁጥር
1 m² ≈ 12.5 blocks (40×20 cm block)
86.8 × 12.5 ≈ 1,085 blocks
5% ተጨማሪ (wastage) ≈ 55 blocks
👉 ጠቅላላ ብሎኬት ≈ 1,140 ብሎኬቶች
3. የብረት (Reinforcement) መጠን (ግምታዊ)
3.1 ኮሎም (Columns)
ቁጥር፡ 9 (ኮርነር + መካከለኛ)
መጠን፡ 20×20 cm
Main bars: 4Ø12
Stirrups: Ø8 @ 20 cm
👉 ጠቅላላ ብረት (Columns) ≈ 280 kg
3.2 ቢም (Ring beam)
ርዝመት = 28 m
4Ø12 main bars
Ø8 stirrups @ 20 cm
👉 ጠቅላላ ብረት (Beam) ≈ 200 kg
3.3 ጠቅላላ የብረት መጠን
👉 ≈ 480 – 500 kg (0.5 ቶን)
4. የጣሪያ (ቆርቆሮ) መጠን
4.1 የጣሪያ አካባቢ
የቤት አካባቢ = 48 m²
15% slope + overlap
👉 48 × 1.15 ≈ 55 m²
4.2 ቆርቆሮ ብዛት
1 sheet ≈ 2.5 m²
👉 55 ÷ 2.5 ≈ 22 sheets
2 ተጨማሪ (wastage)
👉 ጠቅላላ ≈ 24 ቆርቆሮ
5. አጭር BOQ ማጠቃለያ
ንጥል
መጠን
ብሎኬት
≈ 1,140 pcs
ብረት
≈ 500 kg
ቆርቆሮ
≈ 24 sheets
የግድግዳ አካባቢ
86.8 m²
የጣሪያ አካባቢ
55 m²

@etconp
👍28❤17
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

♧ ሁሉን በአንድ ቦታ ለሁሉም ቅርብ

♧ ምስክራችን ስራችን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

♧ ይደውሉልን ያማክሩን

0904040477
0911016833
❤2
ማስታወቂያ

የቴክኒክ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ
❗️

የመጀመሪያውን ዙር ግምገማ ላለፋችሁ ተሳታፊዎች የቴክኒክ ሰነድ መግዣ እና ማስገቢያ ቀነ-ገደብ እስከ ታኅሳስ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መሆኑን መግለፃችን ይታወቃል።

*ሆኖም በመጨረሻው  የሰነድ ማስገቢያ ቀን ባጋጠመ የኔትወርክ መጨናነቅ ምክንያት በርካቶች ሰነዶቻቸውን አለማስገባታቸውን በመግለፅ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የሰነድ ማስገቢያ ቀነ-ገደብ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

በዚህም መሰረት የሰነድ ማስገቢያው ቀን ለተጨማሪ 3 ተከታታይ ቀናት ማለትም እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት 6:00 ሰዓት ድረስ መራዘሙን እያሳወቅን እስካሁን ሰነድ ገዝታችሁ ያላስገባችሁ ተሳታፊዎች፤ የመጨረሻ ቀን መጨናነቅ ሳይፈጠር ይህንን ዕድል ተጠቅማችሁ በፍጥነት ሰነዶቻችሁን እንድታስገቡ ጥሪ እናቀርባለን።

ማሳሰቢያ:- ከዚህ ቀነ-ገደብ በኋላ የሚመጣን ማንኛውንም ቅሬታ የማንቀበል መሆኑን በድጋሚ እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

@etconp
❤5👍1
👉በግንባታ ግዥ የስራ ልምድ ወይንም ዓመታዊ ተርን ኦቨር አላሟላም ብለው ከጨረታ ተሳትፎ ለመውጣት ከመወሰኖ በፊት ይህንን ይንብቡ?

🏷በፌደራል መንግስት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥ መመሪያዎች ላይ ከተቀመጡ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል በግንባታ ግዥ ጨረታ ውድድር ላይ የስራ ልምዱ እና  ዓመታዊ ተርን ኦቨር ላይ በዶላር ምንዛሬ ለውጥ መሰረት የሚደረግ ማስተካከያ መኖሩ ሲሆን ይህም እንደሚከተለው ይሰላል።

1) ለጨረታ ግምገማ ዓላማ የሥራ ተቋራጩ በስራ ልምድነት እንዲያዝለት በሚያቀርበው የግንባታ ውለታ ዋጋ ላይ ማስተካከያ የሚደረግለት ሲሆን ይህም የሚሰላው ጨረታ ከሚቀርብበት የመጨረሻ  ቀን 28 ቀናት በፊት የነበረው የምንዛሪ ምጣኔን ውሉ በተፈረመበት  ጊዜ በነበረው የምንዛሪ ምጣኔ በማካፈል ከተሰላ በኋላ በሚገኘው ውጤት በማባዛት ነው።

2) በተመሳሳይም በጨረታ ግምገማ ጊዜ ለሚደረግ ማስተካከያ አላማ ለተርን ኦቨር ስሌት የሚወስደው ሥራ ተቋራጩ ያቀረበው አመታዊ የግንባታ ሥራ ተርን ኦቨር መጠን' ጨረታ ከሚቀርብበት የመጨረሻ ቀን 28 ቀን በፊት የነበረውን የምንዛሪ መጠን በእያንዳንዱ በጀት አመት የመጨረሻ ቀን ላይ ባለው የምንዛሪ መጠን በማካፈል ነው።

3) ሁለቱም ማስተካከያዎች የሚሰሉት የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ የሚሰጠውን የውጭ አገር ገንዘብ መሸጫ ዋጋ መረጃ መሠረት በማድረግ ይሆናል።

📜ለምሳሌ: 1 ዶላር 20 ብር በሚመነዘርበት ወቅት የተፈረመ የአንድ መቶ ሚሊዮን ብር የስራ ልምድ ዛሬ አንድ ዶላር በ155 ብር ሲመነዘር ለሚከናወን ጨረታ የስራ ልምዱ : 100 ሚ × (155/20) = 775 ሚሊየን ብር ይሆናል።

@etconp
❤11
Forwarded from Kelemat Ads
📚 አጠቃላይ የፋይናንስ እና የግብር Online ስልጠና!

🖥 ለመመዝገብ:

1️⃣ ወደ ድህረ-ገፃችን ይግቡ
👉 https://www.apextaxschool.com

2️⃣ “Join Now” የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ

3️⃣ ሙሉ ስምዎን ኢሜልዎን እና Password ፈጥረው ያስገቡ

4️⃣ የሚፈልጉትን የስልጠና ክፍል ይምረጡ

5️⃣ “Enroll Now” በመጫን ከዝያም “Buy Now” በማለት ክፍያዎን ፈፅመው ምዝገባዎትን ያጠናቁ

በ0995958351 በመደወል መመዝገብም ይችላሉ።

📍 አድራሻ: ሃያ ሁለት፣ በየነ ጠበሉ ህንፃ፣ 1ኛ ፎቅ
📞 0995 958 351

#ApexFinancialSolution
#Onlinetraining
❤5
ዕለታዊ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ አጫጭር መረጃዎች

1. በ3D ፕሪንቲንግ የሚገነቡ ቤቶች፦


የ3D ኮንክሪት ፕሪንቲንግ ቴክኖሎጂ የግንባታ ጊዜን እስከ 70% መቀነስ መቻሉ ተረጋገጠ። ይህ ቴክኖሎጂ በአጭር ቀናት ውስጥ ጥራቱን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ሲሆን፣ በቅርቡ በኢትዮጵያም ለሚገነቡ መጠነ ሰፊ የቤት ፕሮጀክቶች እንደ ትልቅ አማራጭ እየታየ ነው።

2. ራስን የሚጠግን ኮንክሪት (Self-Healing Concrete)፦


ሳይንቲስቶች በኮንክሪት ውስጥ የሚገቡ ልዩ ባክቴሪያዎችን በመጠቀም፣ ኮንክሪቱ ሲሰነጠቅ ራሱን በራሱ እንዲጠግን የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ አድርገዋል። ይህ ፈጠራ የህንፃዎችን ዕድሜ ከማራዘሙ ባለፈ የጥገና ወጪን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።

3. ድሮኖች በግንባታ ሳይት ላይ፦


በአሁኑ ወቅት ድሮኖች የግንባታ ሂደትን ለመከታተል፣ የቦታ ቅየሳ (Surveying) ለማድረግ እና የደህንነት ቁጥጥርን ለማጠናከር በስፋት እየዋሉ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ በእጅ የሚሰሩ አድካሚ ስራዎችን በዲጂታል መንገድ ትክክለኛነታቸውን ለማረጋገጥ ይረዳል።

4. የግንባታ መረጃ ሞዴሊንግ (BIM) ፋይዳ፦


ህንፃን በአካል ከመገንባታችን በፊት በዲጂታል መልክ በ3D መስራት የሚያስችለው BIM ቴክኖሎጂ፣ በቁሳቁስ ብክነት ምክንያት የሚጠፋን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ማዳን እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ። ዲጂታል ግንባታ ለተሻለ የፕሮጀክት አመራር ወሳኝ ነው።

5. ከፕላስቲክ ቆሻሻ የሚሠሩ ጡቦች፦


አካባቢን ለመጠበቅና የግንባታ ወጪን ለመቀነስ ከፕላስቲክ ቆሻሻዎች የሚመረቱ ጡቦች (Plastic Bricks) በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እያገኙ ነው። እነዚህ ጡቦች ከባህላዊው ጡብ በበለጠ ቀላል፣ ጠንካራ እና ለሙቀት መከላከያነት ምቹ ናቸው።
▪️▫️▪️
❤12
👉 ለአየር መንገድ ሠራተኞች የቤት ግንባታ የሚውል የ27.8 ቢሊዮን ብር የብድር ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል የ27.8 ቢሊዮን ብር የብድር ስምምነት ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈራረመ።

ስምምነቱ የተፈጸመው በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል ሲሆን፤ ዓላማውም የአየር መንገዱን ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና የፋይናንስ አቅርቦቱን ለማመቻቸት ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ተወካይ ኤፍሬም መኩሪያ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ ባንኩ የብድር አቅርቦቱን ለሁሉም ዘርፎች ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ይገኛል።

በተለይም ባለፈው ዓመት ባንኩ ካቀረበው 458 ቢሊዮን ብር ብድር ውስጥ 88 በመቶው ለግል ዘርፉ የተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ባንኩ ለኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች የሚሰጠውን ትኩረት እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

አሁን የተደረገው ስምምነትም የሀገሪቱን ግዙፍ ልማቶች ለማሳለጥ የሚረዳ መሆኑን ኤፍሬም አክለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው፤ አየር መንገዱ የሠራተኞቹን የቤት ችግር ለመፍታት ቀደም ሲል 1 ሺህ 200 ቤቶችን አስገንብቶ ማስተላለፉን አስታውሰዋል።

በአሁኑ ወቅትም ለተጨማሪ 5 ሺህ ሠራተኞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ይህን ሰፊ የግንባታ ሂደት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ፋይናንስ የሚጠይቅ በመሆኑ፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የተደረገው የብድር ስምምነት ለግንባታው መሳካት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አቶ መስፍን ገልጸዋል።

Via Press Magazine

@etconp
❤8
የቤታቸውን አጥር ያላደሱ እና ግራጫ ቀለም ያልቀቡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የመብራት እና የውኃ አገልግሎት አታገኙም መባላቸውን ተናገሩ

በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የመኖሪያ የቤታቸውን አጥር ግራጫ ቀለም ያልቀቡ፣ አምፖል ያልሰቀሉ፣ እንዲሁም በአካባቢያቸው የደኀንነት ካሜራ ያልገጠሙ ነዋሪዎች “የመብራት እና የውኃ አገልግሎት አታገኙም” ተብለናል ሲሉ መናገራቸውን ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። ከሚኖሩበት ቀበሌ በመጡ የመንግሥት ኃላፊዎች፤ በሀገር ደረጃ እየተሠራ ካለው የኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን “ማስዋብ” አለባችሁ የሚል መመሪያ እንደተሰጣቸው ዘገባው አመላክቷል። በየአካባቢው “ዋና ዋና ቦታዎች ላይ” ይሰቀላል የተባለው የደኅንነት ካሜራው ያስፈለገው፤ በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ በተደጋጋሚ የሚነሳ የደኅንነት ጥያቄ በመኖሩ ነው ተብሏል።

ለነዋሪዎቹ ከተሰጣቸው መመሪያዎች ውስጥ፤ ሁሉም የመኖሪያ ቤቶች አጥር በተመሳሳይ መልኩ ግራጫ ቀለም መቀባት ያለባቸው ሲሆን ከዚህ የተለየ ቀለም መጠቀም እንደሌለባቸው ተግልጾላቸዋል። የከተማዋ ኃላፊዎች ይህን መመሪያ “በፍጥነት ያልተገበረ” ነዋሪ ለቅጣት እንደሚዳረግ መናገራቸው ተሰምቷል።

ቅጣቱ የሚፈፀመው ነዋሪውዎቹ መንደራቸውን “የማስዋብ” ሥራ ማከናወናቸውን በድጋሚ ከተፈተሸ በኋላ መሆኑ ተመልክቷል። ይህን ያላከናወነ ግለሰብ እንደ “መብራት” እና “ውኃ” ያሉ መሠረተ ልማቶች ይቋረጥበታል መባሉን ከዘገባው ላይ ተመልክተናል።

@etconp
❤4😢3
👉ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ

📆Deadline : December 26, 2025

@etconp
👍2