🙏5👍3
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Itoophiyaa❤️)
" በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች #የብቃት_ምዘና ይጀመራል " - ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር)
በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ ላሉ ባለሙያዎች #የብቃት_ምዘና እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡
በዘርፉ ብቃት ሳይኖራቸው፣ አቅማቸው ሳይረጋገጥና ማረጋገጫ ሳያገኙ ራሳቸውን #መሐንዲስ እያሉ የሚጠሩበትን አሠራር ያስቀራል የተባለለት እንዲሁም የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት የሚረዳ የማሠልጠኛ ማንዋልና የሚመዘኑበት መመርያ መዘጋጀቱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ሚኒስትር ደኤታ ወንድሙ ሴታ (ኢንጂነር) ምን አሉ ?
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ተመርቆ ወደ ሥራ የሚገባ አንድ ባለሙያ በሚሠራበት ተቋም ውስጥ በቆየ ቁጥር የሙያ ደረጃዎች ከመስጠት ባለፈ መመዘኛ ሥርዓት ባለመኖሩ፣ ባለሙያው ለሚጠበቅበት ዕውቀትና ክህሎት ብቁ ነውወይ ሚለው አይታወቅም።
- ከኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየተዘጋጀ ያለው መመርያ በቅርቡ ለፍትሕ ሚኒስቴር ተልኮ ይፀድቅና ወደ ሥራ ይገባል።
- የሚወጣው መመርያ ባለሙያዎች የሚሠለጥኑበት ፣ የሚገመገሙበትና ዕውቅና የሚያገኙበት ከመሆኑም በላይ የሙያ ግድፈት ሲገኝባቸውም የሚቀጡበትን አሠራር አካቷል።
- አገሪቱ አሁን ባለችበት የኮንስትራክሽን ቁመና የግንባታ ጥራት አደጋ ውስጥ ነው። ሥራ ከተጀመረ በኋላም ሆነ ከመጀመሩ በፊት የሚታየው የጥራት መጓደል አሁን ካልተፈታ በቢሊዮን ዶላሮች የሚፈስበት ዘርፍ ተመልሶ የማይወጣበት ችግር ውስጥ ይገባል።
- በኮንስትራክሽን ዘርፉ የባለሙያ አቅምና የሙያ ሥነ ምግባር እየተሻሻለ ከመሄድ ይልቅ እየባሰበት ነው የሄደው ፤ ባለሙያው ከአዳዲስ ዕውቀትና ቴክኖሎጂ ጋር የሚተዋወቅበትና ራሱን የሚያበቃበት ሳይሆን እያጠፋ የሚማርበት ሆኖ ቀጥሏል።
- በዘርፉ በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች የሉም። ባለሙያዎቹ ወደ ሥራ ከገቡ በኋላ ብቃታቸው ሊያድግ የሚችለው በራሳቸው ጥረት እንጂ፣ ከዘርፉ በሚያገኙት ትምህርትና ተቋማዊ ዕውቀት አይደለም።
- በአገር ውስጥ የበቁ የሚባሉት እና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ወደ ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ናቸው። በተለይም በምሥራቅና በደቡብ አፍሪካ አገሮች ተፈላጊ ናቸው። በአገር ውስጥ ያሉ ባለሙያዎችም ባሉበት ተቋም ለረዥም ጊዜ ረግተው አይቆዩም። በበገበያ ውስጥም የዋጋ ጭማሪን በየጊዜው መተንበይ በማይቻልበት ሁኔታ የግንባታ መሣሪያዎች ዋጋ አልቀመስ ብሏል።
- ግዙፍ ፕሮጀክቶች አብዛኞቹ የውጭ ኮንትራክተሮች ብቻ የሚይዟቸው፣ የአገር ውስጥ ባለሙያዎች የውጭ ኮንትራክተሮች በሚይዟቸው ፕሮጀክት ውስጥ ገብተው ዕውቀት እንዲቀስሙ የሚያደርግ አሠራር አልተዘረጋም ይህ የዘርፉ ሌላው ተግዳሮት ነው።
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ የግዥ ሥርዓትን ጠንቅቆ የሚያውቅ ባለሙያ አለመኖሩ ፤ ሁሉም ባወቀውና በገባው ልክ እንጂ በትክክል ሥራውን ተገንዝቦ የሚሠራ የለም።
- በኮንትራት አስተዳደር የተሰማሩ ባለሙያዎች በአንድ ጉዳይ ባለመግባባታቸው ምክንያት ክስ ሲመጣ ተመልሶ ውልን ከመቃኘት ውጪ፣ ከጅምሩ የኮንትራት ውል አስተዳደርን ዝርዝር ጉዳይ ተረድቶ የሚያስረዳ ባለሙያ የለም።
- ለኮንስትራክሽን ጥራት መጓደል ፦ በግዥ ሥርዓቱ ላይ ያለው አሠራር፣ የፕሮጀክቶች ዲዛይን የተሟላና የተደራጀ አለመሆን የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው። ወደ አፈጻጸም ሲገባ ባሉት ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች የአቅም ውስንነት የተነሳ የሚታሰበውን ጥራት ለማረጋገጥ አዳጋች ሆኗል።
- በኢትዮጵያ የግንባታ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከመሬት ልየታ ጀምሮ ሕንፃው ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ መሟላት ያለባቸው ዓለም አቀፍ መሥፈርቶች፣ አጠቃላይ ይዘትና ቁመናው ምን መምሰል እንዳለበት የተቀመጡ ስታንዳርዶች የሉም። በዚህም በኢትዮጵያ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የመኖሪያ ቤቶች ሲገመገሙ፣ የመኖሪያ ቤት ለመባል የተሟላ ቁመና ያላቸው ከ25 በመቶ የማይበልጡ ናቸው። 75 በመቶ ያህሉ ከደረጃ በታች ናቸው።
- ለቤቶቹ ጥራት መጓደል ምክንያት ከመጀመሪያው የግንባታ ዕቅድ ጀምሮ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፣ መሟላት ባለባቸው ዓለም አቀፍ መሥፈርቶች የተቃኙ አለመሆናቸው ነው።
- ከዚህ በኋላ በሀገሪቱ ሚገነቡ ቤቶች ለሰው መኖሪያ ለመባል የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ መሥፈርቶችን ባሟላ መንገድ እንዲሆን፣ የሕግ ማዕቀፍና ስታንዳርድ ይዘጋጃል። በአሁኑ አሠራር ግን ማንኛውም የሥራ ተቋራጭ ውል ገብቶ ግንባታ ከጀመረ በኋላ ፣ በጥራትና በጊዜው ያጠናቅ ወይም አያጠናቅ መቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት የለም ብለዋል፡፡
ይህ መረጃ ከሪፖርተር ጋዜጣ የተወሰደ ነው።
@etconp

👍13❤4🥰1🙏1
🙏6👍3
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢ/ብ/ብ/ሕ/ከ/መንግሥት የጌዴኦ ዞን የራጴ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት የራሴ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ ቤት በቁጥር ራ/ወ/አ/ጽ/ቤት 2659/16 ዓ.ም በ26/2/2016 ዓ.ም በጻፈልን ደብዳቤ መሠረት የአስተዳደር ቢሮ G+1 ቀሪ የግንባታ ሥራዎችን ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በዚሁም መሠረት ተጫራቾች፡-
BC/GC level 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና በ2016 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፣
ከመንግሥት የሚፈለግበትን የዘመኑን የግብር እና ታክስ ዕዳ አለመኖሩን የሚገልጽ በበጀት ዘመኑ ብቻ የሚያገለግል የስምምነት ደብዳቤ ከክልሉ ታክስ አስተዳደር ቢሮ ማቅረብ የሚችል፣
ወርሃዊ የታክስ ማስታወቂያ በማቅረብ የሰበሰቡትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ማድረጋቸውን የሚገልጽ ከሚመለከታቸው ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱት እንደተጠበቀ ሆኖ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮችን እየጋበዘ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናልና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ በመያዝ በፕሮጀክቱ ስም በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመቅረብና በመመዝገብ ኮፒውን በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
ተቋራጮች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተሙንና ፊርማውን በማሳረፍ
አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ሰነድ /በፎቶ ኮፒ ማሽን ኮፒ የተደረገ/ እያንዳንዱን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ሃያ አንድ ቀናት/ ቆይቶ በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ በጌዴኦ ዞን ራኤ ወረዳ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
በኦርጅናል ሰነድ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ስርዝ ድልዝ በሚነበብ መልክ በድጋሚ መጻፍ ይኖርበታል። * እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ብቻ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና (unconditional) ማቅረብ ይኖርበታል፤ በጥሬ ገንዘብ /በኢንሹራንስ/በሌላ ማቅረብ አይቻልም።
በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያስደርጋል።
ጨረታው በውክልና የሚመጡትን አይመለከትም።
ጨረታው የሚዘጋው በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰአት ሲሆን የሚከፈተው ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ከፍሎች በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰአት በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 ይሆናል። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
· የቦታ ጉብኝት (Site Visit) ከአሰሪ መ/ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟሉ የሚቀርቡ የሥራ ተቋራጮች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናሉ።
ተጫራቾች በዞኑ ውስጥ ጨረታውን አሸንፈው ሥራውን ያቋረጡና ሥራውን ያጉላሉ በጨረታው አይሳተፉም፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 0948911976/ 0916378090
የጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
@ETCONpWORK

👍4👏2
የስራው መጠሪያ: Architect/ Interior designer
የስራው አይነት: በተመደቡበት የሚሰራ - ቋሚ
የስራው ዘርፍ: #አርክቴክቸር_እና_የከተማ_ፕላን
የስራው ቦታ: አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ
የልምድ ደረጃ: መካከለኛ
የተፈላጊ ሰው ብዛት: 1
ደሞዝ/ክፍያ: ወርሃዊ
የማመልከቻ ማብቂያ ቀን: 29/11/2023
የስራው ዝርዝር:
We are looking for an Architect/interior designer who is willing to adopt the work environment and ethics our company has.
work skills required
- communicative skill
- software skill ( Lumion, revit, Autocad, Illustrator, photoshop, Microsoft excel)
- Able to work under work pressure.
-Has minimum of ONE YEAR experience
please send ONLY you PORTFOLIO on @monalisa_amber

👍2🙏1