Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉ሥራ ፈላጊ ነዎት❓

💫መልካም ዕድል‼️

https://t.me/ETCONp
👍6🙏5
እንኳን ለደብረ ታቦር(ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!🤚


መጣና ባመቱ፤
ኧረ እንደምን ሰነበቱ

ክረምቱ አልፎ ወደ ብርሃን መሻገራችንን በሚያበስረው፤ በህጻናት ውብ ዜማ እና የጅራፍ ድምጽ ለሚደምቀው ቡሄ እንኳን በሠላም አደረሳችሁ ብለናል🤚🤚

እንዲሁ እንዳለን አይለየን!
ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን!

መልካም ቡሄ😇

@etconp
🙏7
በኮንስትራክሽን ስራ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ ኢንጅነሮች ሊያውቃቸው የሚገቡ:-


1) የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING MATERIALS) አንድ ጥሩ ኢንጅነር በሳይት ላይ የሚሰሩ
የግንባታ እቃዎችን ለመፈተሽ የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ ይጠበቅበታል።

ከታች የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች ተጠቅሰዋል የኮንክሪት ፍተሻ

(Concrete Test):

•Slump test,
•compression test (cubic or cylindrical test),
•split tensile test, soundness etc.

የአፈር ፍተሻ (Soil Test):

•Core cutter test,
•compactiontest,sand replacement test, triaxial test,
consolidation test etc.

Bitumen Test:

•Ductility test, softening point
test, gravity test, penetration test etc.

(በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ አንማር ይሆናል ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የግድ መማር ማወቅ አለብን ዩ ቲዩብ ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉቁም ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማችን ነው ::

2) የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL)

የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም አቅም እና ርጉእነት (settlement and stability) የምንገነባው አካል ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን።

እንደ ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ በሳይት ላይ የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው።

3)የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ(USES OF SURVEYING INSTRUMENTS)

በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ መሳሪያዎች ለምሳሌ ቶታል ስቴሽን እና ቴዎዶላይት አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅነር የግድ ማወቅ አለበት። የግድ !

4). የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD CODES USED IN CONSTRUCTION)

ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካምድራቸው የአየር፣ የንፋስ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ   ፀባያቸው አንፃር የሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ (Construction codes) አላቸው።

አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን ስታንዳርድ ኮድ የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው ቁስሃገሪቱ ባላት ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና እንዳይወድም።

እነዚህን ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል የሚገነባ የትኛውም ግንባታ የመፍረስአቅሙ በእጥፍ የጨመረ ነው።

5) BAR BENDING SCHEDULE

ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት (በተለይ ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)።

ይህ ቻርት ሬንፎርስድ የሆነው የግንባታ አካል ማለትም ቢም፣ኮለን፣ስላብ፣ዋል...የሚጠቀማቸውን ቤረቶች የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና ምን ያክል ተመሳሳይ እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል ውስጥ እንደሚኖሩ በግልፅ ይነግረናል።

ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም እና የስትራክቸሩን ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ ይጠቅመናል

6) የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND DESIGN)

አንድ ሳይት ኢንጅነር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ የማንበብ በጣም ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል።

ዲዛይን እና ንድፎችን በትክክል ማንበብ እናመተርጎም ከቻለ ለሳይት ኢንጂንየርነት የሚያበቃውን 60% እውቀት አካብቷል ማለት ነው።

ስለዚህ በተለይ ተማሪዎች ለቴክኒካል ድራዊንግ እና አውቶካድ እውቀቶች የምትሰጡትን ክሬዲት ከፍ አርጉ የፔጃችን መልእክት ነው::

7) ግምት እና ክፍያ ( ESTIMATION AND BILLS)

ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ ግምቱን የሚያስቀምጠው የሳይት ኢንጅንየሩ ነው።

8 )የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL)

ከኢንጅነሪንግ መርሆች ውስጥ አንዱ ጥራት ነው።

ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ ለተጠቃሚው አካል ገንብቶ ማቅረብ ግዴታችን ነው።

አንዳንዴ ለሆዳቸው ያደሩ ኢንጂነሮች ጥራቱን ባልጠበቀ የግንባታ መሳሪያ ገንብተው ያስረከቡት ህንፃ ምን አይነት ጉዳቶች እንዳደረሰ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው።

አንድ ሳይት ኢንጅነር የሚጠቀመውን የግንባታ ቁስ ጥራት የማወቅ ግዴታ አለበት ኋላ በሃገርም በግለሰብም ላይ የሚደርስን አደጋ ለመከላከል።

9) የሳይት ላይ አመራሮች (ON FIELD MANAGEMENT)
እንዴት ፎርም ወርክ መታሰር እንዳለበት፣ የኮንክሪት አሰራር፣ ለጥንቃቄ የምንሰራቸው ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች ማወቅ ግዴታችን ነው

10) ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ያለን መናበብ መቀራረብ (COORDINATION)

የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የተማሩ እና ያልተማሩ ሰራተኞችን እንዴትማስተዳደር እንዳለብን እውቀቱ ሊኖረን ይገባል።

ትእዛዝ ማስተላለፍ ብቻሳይሆን ወርዶ መስራትም ይጠበቅብናል።

ለስራችን መቀላጠፍ ከሁሉምጋ ተናቦና በፍቅር መስራት ወሳኝ እና ወሳኝ ነገር ነው።

@etconp
👍27❤2🙏2👏1
👉የኢትዮጵያ የህንጻ ኮዶችን የሚያሻሽልና አዲሶችን የሚያካትት ፕሮጀክት ስምምነት ተካሄደ

🚧የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን  ነባር የህንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶችን የሚያሻሽልና አዳዲዲስ ኮዶችና ስታንዳርዶችን የሚያካትት ፕሮጀክት ስምምነት ከአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር ተፈራርሟል።

🏷ነሀሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የስምምነት ፊርማ ስነስርአት ላይ እንደተመለከተው 20 ነባርና በስራ ላይ የሚገኙ የህንጻ ኮዶችና ስታንዳርዶችን የማሻሻልና የማዘመን እንዲሁም 10 አዳዲስና አስገዳጅ ኮድና ስታንዳርዶችን የማዘጋጀት ፕሮጀክት ነው።

⏺ለፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በኩል 57 ሚሊዮን ብር የተበጀተ ሲሆን የአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ11 ወር አገባዶ ያስረክባል።

▶️ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ  እና የኢንስቲትዩቱ ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ልብሰወርቅ ነጋሽ ተፈራርመዋል።

▶️በስነስርአቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች በሰነዶቹ ዝግጅት ላይ መካተት ያሉባቸውና ትኩረት በሚሰጣቸው ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

🚧የ ኢትዮጵያ ህንጻ ኮዶች  ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ሶስት ጊዜ ክለሳና ማሻሻያ የተካሄደባቸው ሲሆን የኮንስትራክሽን ዘርፉ ፍላጎት ውስብስብ መሆን፣ እንደሀገርም በዘርፉ ከፍተኛ ለውጥ  በመኖሩ እና አዳዲስ ግብአቶችና አሰራሮች  እያደጉ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህን ነባራዊ ሁኔታዎች ያገናዘበ የኮድና ስታንዳርድ ማሻሻያና አዳዲስ ሰነዶች ዝግጅት እንደሚደረግ ተሰምሮበታል።

💫በቀጣይም የዘርፉን ውጤታማነት ከፍ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን  ለማከናወን ሁለቱ ተቋማት ግንኙነታቸው እንደሚጠናከር በስምምነት ስነስርአቱ ላይ ተመልክቷል።

@etconp
👍4👏2❤1
@etconp EBCS 1-8.rar
122.5 MB
📚ETHIOPIAN BUILDING CODE STANDARD
.
it is compressed by zip file you should use wrinrar to extract the file.

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
@ETCONp ASTM MNL 41 .PDF
9 MB
Fracture and Fatigue Control in Structures - Applications of Fracture Mechanics


Author(s): Barsom, John M.; Rolfe, Stanley T.

Series: MNL 41

Publisher: ASTM International,

Year: 1999

https://t.me/ETCONpWORK
👍10🙏1
🖐ቴሌግራም ላይ የ Star Gift በ Reaction መልክ መስጠት ተጀምሮዋል!

🏷ምንቀርብላቹ ኮንተንቶች ከተመቻቹ Star Gift በመስጠት ይበልጥ እንድንሰራ አበርቱን🙏
👍11❤4👏1😭1