Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
doc05979620240919055336.pdf
481.2 KB
የ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ቺፑድ፣ፕለይውድ፣አጠና

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
doc05979720240919055404.pdf
390.7 KB
👉ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ ገልባጭ መኪኞች ኪራይ ጨረታ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
🙏1
🔺NEW VACANCY

Oromia Construction Corporation


🚧0 years experience

🏷Civil Engineer

🏷COTM
& Hydraulics Related

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
🙏4
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ዘመን መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK
👍2
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ዘመን መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK
🙏3
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ዘመን መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK
🙏3
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ዘመን መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK
🙏3👍1
👉የቤት እድሳት ለማድረግ ለግንባታ ፈቃድ እስከ 100 ሺህ ብር ጉቦ እየተጠየቁ እንደሆነ የለሚ ኩራ ነዋሪዎች ተናገሩ

🚧በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታቸውን ወይም የንግድ ሱቆቻቸውን ለማደስ ፈልገው የግንባታ ፈቃድ ሲጠይቁ እስከ 100 ሺህ ብር ጉቦ አምጡ እየተባሉ እንደሆነ ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

❇️"እኔ ለምሳሌ ሰሚት ፍየል ቤት አካባቢ ነዋሪ ነኝ፣ የንግድ ቤቴን ትንሽ ለማደስ ፈቃድ ጠይቄ 80 ሺህ ብር ስጠን ተብያለሁ" ያሉ አንድ ጥቆማ ሰጪ ይህም ያለምንም ሀፍረት በግልፅ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

⏺የክፍለ ከተማው ወረዳ 10 ነዋሪ ደግሞ ከዚህም በተጨማሪ ይህ ብር ቢከፈል እንኳን ደንቦች ከ3 እስከ 4 ሆነው በቡድን በመምጣት ለአንድ ሰው እስከ 10 ሺህ ብር አምጡ እንደሚሉ በምሬት ተናግረዋል።

⏺"መስራትም፣ አለመስራትም አማራጭ እየሆነ እየሆነ አይደለም የህዝብ አገልጋይ ተብለው የተቀመጡ ሰዎች ይህን ያህል ገንዘብ ከጉቦ ተቀብለው ካለ ምንም ሀፍረት በቀጥታ ወደ ባንክ አካውንታቸው ሲያስገቡ ማየት ያሳዝናል" ብለው አስተያየታቸውን የሰጡን ደግሞ የሰሚት ኖክ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ነዋሪ ናቸው።

Via Meseret Media

@etconp
😭7👍2
👉የቻይናው First Highway Engineering Company (CFHEC) ለ102 ወጣት ኢትዮጵያውያን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

🚧የግዙፉ CCCC ኩባንያ እህት ተቋም የሆነው CFHEC፤ ስልጠናውን ለአንድ ወር የሚሰጥ ሲሆን፤ ሰልጣኞቹ ከCCCC የኢትዮጵያ ፕሮጀክት ሳይቶች የተመረጡ መሆናቸው ተገልጿል።

💫ግንባታ፣ ሰርቬዪንግ፣ የግንባታ ቁሳቁስ ፍተሻ እና የቻይንኛ ቋንቋ በስልጠናው የተካተቱ ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል።

🏷Seagull Talent Nurturing Project በሚል የሚሰጠው ስልጠና፤ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት፣ በሉባን ወርክሾፕ በኢትዮጵያ እና በ CFHEC በጋራ የተዘጋጀ ነው።

Via Xinhua

@etconp
👍3👏2
👉በ57 ሚሊየን ዶላር እየታደሰ የሚገኘው የአፍሪካ አዳራሽ ሕንፃ በጥቅምት ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተባለ

🚧በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው የአፍሪካ አዳራሽ ሕንፃ እድሳት ስራ ተጠናቆ በጥቅምት ወር አጋማሽ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ።

⭐️በኮሚሽኑ የአፍሪካ አዳራሽ አስተዳደር ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አንቶንዮ ሕንፃውን ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ባስጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት፥ የእድሳት ስራው ሕንጻው ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ዘመኑን የዋጀ ገጽታ እንዲላበስ አስችሏል።

⭐️የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽኑን በአዲስ አበባ የተመሰረተው በፈረንጆቹ 1961 ሲሆን፥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የድርጅቱ ሕንፃ 62 ዓመታትን አስቆጥሯል።

⭐️የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የቻርተር ፊርማን ጨምሮ በርካታ አፍሪካዊ ኩነቶች የተካሄዱበት ታሪካዊው ሕንፃ፥ ጥንታዊነቱን በጠበቀ መልኩ እድሳት ተደርጎለት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

🚧ተመድ በተለያዩ ምክንያቶች ሕንፃውን ለማደስ እንደተነሳ የተገለፀ ሲሆን፥ በዋናነት ሕንፃው ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ያሉት ሆኖ በቀጣይ ዓመታት አገልግሎት መስጠት እንዲችል ለማድረግ ያለመ ነው።

💫በሕንፃው ውስጥ የነበሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ወደ ተለዋጭ ቦታ የማዘዋወር ስራ ከተካሄደ በኋላ በሁለት ምዕራፎች የተከናወነው የሕንፃው የእድሳት ስራ በተለያዩ ካምፓኒዎች የተከናወነ ሲሆን፥ ዋናውን የእድሳት ስራ "አልክ" የተሰኘ የዱባይ ካምፓኒ ሰርቶታል።

💫57 ሚሊየን ዶላር የተመደበለት የሕንፃው እድሳት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት ሲሆን፥ ከድርጅቱ ጋር የተያያዙ ታሪካዊ ክዋኔዎችና ቅርሶች የሚጎበኙበት የኤግዚቢሽን ማዕከል እንደተሰራለትም ተገልጿል።

⭐️የሎሬት አፈወርቅ ተክሌ የስዕል ስራን ጨምሮ በርካታ ጥበባዊ ቅርሶች ያሉበት ሕንፃው በጥቅምት ወር አጋማሽ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ  ለአገልግሎት ክፍት ይሆናልም ተብሏል ።

Via FBC

@etconp
❤2👍2
👉የግንባታ ውል ሰነድ በግልጽ ማስቀመጥ ያለበት ነጥቦች:-

📜የፕሮጀክቱን ዲዛይን እና ዝርዝሮች:

▶️የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላትን ድርሻ፣ መብትና ግዴታ፣

▶️የሚጠበቀውን የግንባታ ጥራት የሚገልጹ ትንታኔዎች፣

▶️የፕሮጀክቱን ተጠባቂ የጊዜ ሰሌዳዎች፣

▶️የፕሮጀክቱን ዋጋ እና አከፋፈል ሁኔታዎች፣

▶️የደህንነት እና የጤና አጠባበቅ፣ መመሪያዎች፣

▶️ፕሮጀክቱን የሚመለከቱ የሕግ ማእቀፎች

▶️የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላትን ፊርማ እና ማኅተም

▶️ፕሮጀክቱ የሚፈልገውን የሰው ኃይል ብቃትና ብዛት

▶️ፕሮጀክቱ የሚፈልገው ማሺነሪ አይነትና ብዛት

▶️የእያንዳንዱን የሥራ አይነት ዝርዝርና የግንባታ ስነዘዴ

▶️የፕሮጀክቱን ባለድርሻ አካላት ዝርዝር መረጃ

❇️አንድ የግንባታ ውል ሰነድ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ጭብጥ ጉዳዮች በግልጽ እና በዝርዝር ማስቀመጥ ይኖርበታል።

💫የተወሳሰበ፣ ያልተብራራ እና እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሀሳብ ቢኖርበት ግን በሚኖረው የፍርድ ቤት ክርክር ባለድርሻ አካላትን በተናጠል አልያም በጋራ ኪሳራ ላይ ሊጥል ይችላል።

🚧ይህ ሁኔታ ደግሞ ፕሮጀክቱን በጤናማ ግንኝነት ለመፈጸም እክል ሊፈጥር ስለሚችል ለጥራት ችግር እና ለጊዜ ብክነት እንዲጋለጥ ያደርገዋል። 


@etconp
👍2🙏2❤1
በአዲስ አበባ ለብዙሃን ትራንስፖርት ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ መስመሮች ይፋ ሆኑ።

ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ከመጪው እሑድ ጀምሮ በተመረጡ መስመሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

መስመሮቹም ከቦሌ- ፒያሳ፣ ከቦሌ- ሜክሲኮ፣ ከቦሌ- አራት ኪሎ፣ ከቦሌ- አውቶቢስ ተራ፣ ከቦሌ- ሽሮሜዳ፣ ከጀሞ- ፒያሳ እና ከጀሞ- ሜክሲኮ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ  ከፒያሳ- ቦሌ፣ ከሜክሲኮ- ቦሌ፣ ከአራት ኪሎ- ቦሌ፣ ከአውቶቡስ ተራ- ቦሌ፣ ከሽሮ ሜዳ- ቦሌ፣ ከፒያሳ ጀሞ እና ከሜክሲኮ - ጀሞ  የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ መሰጠት እንደሚጀምር ተመላክቷል፡፡

ቢሮው " የአገልግሎቱ መጀመር የመንገድ መዘጋጋቱን ለመቀነስ እና ብዙ የሰው ቁጥር ያለው ተጓዥ በአንድ ጊዜ ማመላለስ ያስችላል " ብሏል።

በዚህም ተማሪና መምህራን ብሎም ሌሎች ተገልጋዮች በሰዓታቸው ወደ ሚፈልጉት ቦታ በመንቀሳቀስ አገልግሎት እንዲያገኙ ያግዛል ተብሏል፡፡

" በከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው የተነቃቃ እንዲሆን ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል " ሲልም አክሏል።

ዜጎች የሚያጋጥሟቸውንና የሚስተዋሉ ችግሮችን በአቅራቢያ ለሚገኙ የትራንስፖርት ቁጥጥር ሰራተኞች ወይም በ9417 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ተጠይቋል፡፡

@etconp
👍3
👉በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ለሦስት ዓመታት የተቋረጠው የአዋሽ- ወልድያ-ሃራ ገበያ የባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት ዙሪያ መንግሥት እና ተቋራጩ እንግሊዝ ውስጥ ድርድር እያካሄዱ መኾኑ ታውቋል።

🚧ተቋራጩ የቱርኩ ያፒ መርከዚ ኩባንያ፣ በጦርነቱ ወቅት ውሉን አቋርጦ መውጣቱና በንብረት ውድመት የደረሰበትን ኪሳራ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲከፍለው ሲጠይቅ ቆይቷል።

💫ድርድሩ የሚካሄደው፣ ከፕሮጀክቱ መጀመር በፊት ኹለቱ አካላት በተፈራረሙት ስምምነት መሠረት መኾኑንና ኩባንያው በካሳ ክፍያ ዙሪያ ከመንግሥት ጋር ከስምምነት ላይ መድረስ ከቻለ አኹንም ፕሮጀክቱን የማጠናቀቅ ፍላጎት እንዳለው ታውቋል።

⭐️ኩባንያው ምን ያህል የካሳ ክፍያ እንደጠየቀ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጠበቃ ከመናገር ተቆጥበዋል::

Via Wazema Radio

@etconp
❤5👍1
አዲስ አበባ መንገዶች ለወሰን ማስከበር ሥራ ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ካሳ ከፈለ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት ባከናወናቸው የመንገድ ግንባታ ሳቢያ ለተነሱ መሠረተ ልማቶች እና የመኖሪያ ቤቶች 1.8 ቢሊዮን ብር የካሳ ክፍያ መፈጸሙን ገለጸ።

መስሪያ ቤቱ በዘንድሮው በጀት ዓመት በሚገነባቸው መንገዶች እና ከሁለተኛው ዙር የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ 546 የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች እንደሚነሱ አስታውቋል።

መስሪያ ቤቱ በ2016 ዓ.ም 1,140 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አከናውኗል።

በመንገድ ግንባታ እና ጥገናው ሳቢያ 682 ቤቶች እንዲነሱ መደረጋቸውን የገለጸው መስሪያ ቤቱ፤ ከ1,200 በላይ በሆኑ የመብራት እና የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ላይም ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል።

ቤቶቹ እና መሰረተ ልማቶቹ እንዲነሱ የተደረጉት፤ መንገዶች በሚገነቡበት “ወሰን ውስጥ የሚገኙ” በመሆናቸው ምክንያት ነው።

ባለስልጣኑ በመንገድ ሥራው ተነሺ ለሆኑ ነዋሪዎች እና መሠረተ ልማቱን ለገነቡ ተቋማት ተገቢውን ካሳ መከፈሉ ታውቋል።

ባለፈው ዓመት ለካሳ የከፈለው የገንዘብ መጠን 1.1 ቢሊዮን ብር መሆኑ ተገልጿል።

ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ተግባራዊ ማድረግ በተጀመረው የኮሪደር ልማት ለተከናወኑ የመንገድ ግንባታዎች፤ መስሪያ ቤቱ በተጨማሪነት 795 ሚሊዮን ብር ካሳ መክፈሉ ተጠቅሷል።

ይህ የካሳ ክፍያ የተፈጸመው “ለንግድ እና ለመኖሪያ ቤቶች ብቻ” መሆኑ ታውቋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መስሪያ ቤቱ በዚህ ዓመት ሊገነባቸው ካቀዳቸው መንገዶች ጋር በተያያዘ፤ 546 የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ከ1,800 በላይ የመብራት እና የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች እንደሚያነሳ ታውቋል።

@etconp
👍3❤1