Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉NEW VACANCY

💫Structural Design Engineer

#ethiopian_engineering_corporation

#Addis_Ababa

🚧Bachelor's Degree in Architecture and Design or in a related field of study with relevant work experience

⏺Work will involve designing and analysis of RCC structures, reinforcement verification on site as per design drawings.

⭐️Duties & Responsiblites

- Project delivery from Concept Design to Issue for Contract documentation, the BIM/Revit modeler shall be able to develop Building Services design solution working in close collaboration with other design team stakeholders.
- Assist in establishing and setting up new projects with the relevant file structures and adhere to all agreed BIM standards, BIM Execution plans etc.
- Timmy reporting to the discipline Respective Team leader BIM modeler  
- Manage the implementation of the full BIM potential in terms of collaboration, clash detection and resolution of digitally constructed building elements. 
- Manage the implementation of discipline specific software for BIM/Revit design development.

🔰Quanitity Required: 3

🏷Minimum Years Of Experience: #3_years

⚡️Deadline: January 3, 2025

📩How To Apply: Apply using the provided link below👇

https://forms.office.com/Pages/ResponsePage.aspx?id=fbibbAsHyk2HrMuCOdJR7l_tOeSslK1NsGRsQb8bHJdURUg0Q1JGN1VVNUs0MlNZSUFDRzFGVFk1My4u

@etconp
👍6🙏2
አገራችንን በውድድር ያስጠሩ 3 ወጣት ህንጻ ነዳፊዎች

በፍልስጤም  ሀገር ለሚገነባ ተንቀሳቃሽ ትምህርት ቤት በተዘጋጀ አለም አቀፍ የአርክቴክቸራል ዲዛይን ውድድር ላይ ቢኒያም በውቀቱ፣ ዳንኤል ዋጁ እና ፍሬዘር አብርሃ የተባሉ ሶስት ወጣት ኢትዮጵያውያን ህንጻ ነዳፊዎች ከ 231 ተወዳዳሪ ነዳፊዎች መካከል "ጣልያንን" በመከተል የ 2ኛ ደረጃ በመያዝ ከአፍሪካ ብቸኛ የደረጃ ተወዳዳሪ ሆነው አጠናቀዋል። በውድድሩም ጣልያን 1ኛ፤ ኢትዮጵያ 2ኛ እንዲሁም ቻይና 3ኛ ሆነው ጨርሰዋል። ከዚህ በፊት እኚህ ወጣት ህንፃ ነዳፊዎች ለተከታታይ 5 ጊዜያት የተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮችን ለሶስት አመት ያክል የሞከሩ ሲሆን በነሱም የተለያዩ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችለው ነበር። ከሶስት አመት ሙከራ በኋላ ለዚህ ከፍተኛ ስኬት መብቃት ችለዋል። በውድድሩ ላይ  በኪነህንጻ  ሙያ  የታወቁ  እንደ አሌሃንድሮ አራቬና (ሎሬትና የ 2016 እኤአ ፕሪትዝከር ሽልማት አሸናፊ)፣ ሌስሊ ሎኮ ( የRIBA ወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ) እንዲሁም እጅግ ስመ ጥር አለም አቀፍ አርክቴክቶች(ህንፃ ነዳፊዎች እና ፕሮፌሰሮች)  በዳኝነት ተሳትፈዋል። በስተመጨረሻም ከዚህ አለማቀፍ ውድድር 2ኛ በመሆን የ2000 ዩሮ እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነው የሃገራችንን ስም ከፍ አድርገው አስጠርተዋል።  ይህም በሃገራችን ኢትዮጵያም ብሎም በአፍሪካ ብዙ እምቅ ችሎታ ያለቸው ወጣቶች አንዳሉ ማሳያ ነው።

የንድፋቸው መነሻ ሃሳብ በቦታው ከሚኖሩ የቤዶይን ጎሳ የአኗኗር ዘይቤ ፣ ባህላዊ እልፍኝ እና የተለያዩ ሃገር በቀል የግንባታ ቁሳቁስ የተነሳ ሲሆን፤ ጦርነት ባለበት አካባቢ በቀላሉ ተታጣፊ እና ተነቃቃይ እንዲሆን ታስቦ የተሰራ ነው::

ፎቶ ከግራ ወደ ቀኝ ( ቢኒያም በውቀቱ፣ ዳንኤል ዋጁ፣ ፍሬዘር አብርሃ)

@etconp
👏30❤5👍5
👉አልነጃሺ መስጅድ እድሳት

💫የ አልነጃሺ መስጅድ እድሳት 52 በመቶ እንደደረሰ ተዘግቧል።

Via TiKA Addis Ababa

@etconp
❤3👍1
ጨረታ

አዲሰ ዘመን  ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍4
ጨረታ

ኢትዮጵያን ሄራልድ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍4
ጨረታ

ኢትዮጵያን ሄራልድ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍3
ጨረታ

አዲሰ ዘመን ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1👍1
ጨረታ

አዲሰ ዘመን ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍3
ጨረታ

አዲስ ዘመን ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍5
_@etconp_ታህሳስ_ወር_የ_ኮንስትራክሽን_ማተርያሎች_ዋጋ.xlsx
19.4 KB
👉2017 ታህሳስ ወር የ ኮንስትራክሽን ማተርያሎች ኣሁናዊ ዋጋ

https://t.me/ETCONp

@etconp
👍7🙏7
👉በሀረር ከተማ በኢጣሊያ ወረራ ጊዜ ተገንብቶ በአፈር ደለል ተደፍኖ የነበረው 1.8 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የፍሳሽ ማስወገጃ ጽዳት ተደርጎለት ተከፈተ።

@etconp
👍8
👉የጨረታ ማስታወቂያ

🏷የጨረታ ቁጥር:
SSNT-T516

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሰመራ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ሕንፃ ማስፋፊያ እና ጥገና ስራ ዲዛይን ግምገማ፣ የግንባታ ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር የምክር አገልግሎት (Category l Local and International Consultant for the Design Review, Contact Administration and Construction Supervision of Semera Airport Terminal and Ancillary Facilities Renovation) የሚሰሩ ደረጃ አንድ የማማከር ፍቃድ ያላቸውን የሀገር ውስጥና እና አለም አቀፍ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

በአገልግሎቱ ዘርፍ ለ2015/2016 ዓ.ም ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ እና የTN ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ VAT ተመዝጋቢ የሆነ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2015/2016 ዓ.ም የታደሰ ደረጃ አንድ በሲቪል ምህንድስና የማማከር ፍቃድ እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E -99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T516 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) አየ በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት  ይችላሉ፡፡

በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ለሀገር ውስጥ ተጫራቾች ወይም እኩሌታ በአሜሪካን ዶላር ለአለም አቀፍ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና የሚቀርብ ቅድመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የቀድሞ የሰው ሀብት ሕንፃ በስትራቴጂክ ሶርሲንግ የጨረታ መክፈቻ ክፍል በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል አሊ አስፋው ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4552
ኢ-ሜይል: AliAs@ethiopianairlines.com 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ  የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@etconp
👍4❤2🙏2
👉We Need Urgent Excavator Rental

⭐️አስቾኳይ የ ኤክስካቫተር ኪራይ እንፈልጋለን

መቱ -300hrs
አጋሮ -300hrs
ሀዋሳ -300hrs
ባሌ -300hrs
ሚዛን ቴፒ - 1000hrs

📩Contact Me @Tsilch

@etconp
👍15
የቅጥር ማስታወቂያ- ኮንስትራክሽን

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍6❤4👎1
በመሬት መንቀጥቀጡ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደረሰባቸው‼️

በጋቢ ረሱ ዞን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸው ነዋሪዎች ሌላ አማራጭ እንዲፈልጉ አስገድዷል፡፡

በአዋሽ 7 ከተማ አሥተዳደር፣ በአዋሽ ፈንታሌ እና አሚባራ ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

በዚህም እስከ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ እና ዶኾ ቀበሌዎች ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

ጉዳት በደረሰባቸው እና ሌሎችም ሥጋት ባለባቸው መኖሪያ ቤቶች ያሉ ወገኖችን ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ቀለል ባለ ባህላዊ ቤት እንዲኖሩ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በሰው ላይ የተመዘገበ ጉዳት ባይኖርም÷ በሰብል የተሸፈኑ ማሳዎች እና የመኪና መንገዶች ላይ የከፋም ባይሆን የመሰነጣጠቅ አደጋ መድረሱን አንስተዋል፡፡

@etconp
👍8❤3💔1