Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉በአደይ አበባ ፋብሪካ የቀን ሰራተኛ ላይ ግድግዳ ተንዶበት ህይወቱ አለፈ

🏷ዛሬ ዓርብ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋድ 4ሰአት ከ25 ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አደይ አበባ ግቢ ዉስጥ በደረሰ የስራ ላይ አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ህይወቱ ያለፈዉ ግለሰብ ዕድሜዉ 32 ዓመት የተገመተ የቀን ሰራተኛ ሲሆን በፋብሪካዉ ምድር ቤት ዉስጥ የነበረ የቀድሞ የዉሀ ገንዳን ግድግዳ በማፍረስ ላይ እያለ ግድግዳዉ ተንዶበት በደሰበት ከፍተኛ ጉዳት ህይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የፖሊስ አባላት እንዲሁም የፋብሪካዉ ሰራተኞች የግለሰቡን አስከሬን ማዉጣት ችለዋል።

💫በትላንትናዉ ዕለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፊጋ መብራት ሀይል እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በህንጻ ግንባታ ስራ ላይ የነበረ የ27 ዓመት ወጣት ህይወቱ ማለፉ ብስራት መዘገቡ ይታወሳል።

በማናቸዉም የህንጻና መሰል ግንባታዎች መሰል አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊዉን የደህንነት መርሆዎችን መከተል የሚገባ ሲሆን ለዚሁም ከባለሞያዎች ባሻገር አሰሪዎች ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸዉም ተብሏል።

Via ዳጉ ጆርናል

@etconp
👍9😭4❤1
👉የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

🚧ሚክሰር ሹፌር

📍ቦታ:-አዲስአበባ

💫10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ እና ልዩ መንጃ ፈቃድ ያለው አግባብ ከሆነ የስር ልምድ ጋር

📜ዋና ሃላፊነቶች፡

- የኮንክሪት ማደባለቅ መኪና በአስተማማኝ እና በተቀላጠፈ መንገድ ማንቀሳቀስ
- በመጓጓዣ ጊዜ ትክክለኛውን የኮንክሪት ቅልቅል ማረጋገጥ
- ዕለታዊ የቅድመ-ጉዞ እና የድህረ-ጉዞ የተሽከርካሪ ምርመራዎችን ማድረግ

⏺Quanitity Required: 1

⏺Minimum Years Of Experience: #4_years

⚡️Deadline: February 14, 2025

📩How To Apply: የትምህርት ማስረጃችሁን እና የስራ ልምዳችሁን ፎቶ በማንሳት ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ያመልክቱ👇

https://t.me/MarakiEyassu

@etconp
👍8🙏1
👉በአዲስ አበባ ሁለተኛው ምዕራፍ የ ኮሪደር ልማት ምን እየተሰራ ነው?

https://t.me/ETCONp

@ETCONpWORK
❤3👍1🖕1
👉በኮሪደር ልማት የተሳተፉ ከ400 በላይ ኮንትራክተሮች መንግስት ክፍያ ሊፈፅምላቸው እንዳልቻለ ተናገሩ

በኮሪደር ልማት ምክንያት እንደ ካዛንችስ ካሉ ቦታዎች ለተነሱ ሰዎች በፍጥነት የተዘጋጁ የጋራ መኖርያ ቤቶችን ያዘጋጁ ከ400 በላይ ኮንትራክተሮች ክፍያቸውን መንግስት እንደያዘባቸው ገልፀው ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳሉ ተናገሩ።

ኮንትራክተሮቹ ለመሠረት ሚድያ በሰጡት መረጃ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ኮንትራክተሮቹ በግዴታ ከ3 ሺህ በላይ ቤቶችን ለኮሪደር ተነሺዎች እንዲገነቡ ካደረገ በኋላ ክፍያ መፈፀም አልቻለም።

"በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጀን እኛ ኮንትራክተሮች ከ3 ሺህ በላይ የ40/60 የጋራ መኖርያዎች ውስጥ ያሉ ለንግድ ተብለው የተሰሩ ክፍሎችን ወደ መኖርያነት ቀይረን ገንብተን ብንጨርስም መንግስት ክፍያችንን ከልክሎናል" የሚሉት ኮንትራክተሮቹ አብዛኞቹ በብድር ወስደው ስራውን ቢሰሩም አሁን ትርፉ ቀርቶ ብድራቸውን ለመክፈል ተቸግረው እንዳሉ አብራርተዋል፣ አንዳንዶቹ ብድሩን ለመክፈል የግል ንብረታቸውን ለመሸጥ እየተገደዱ እንደሆነ ተናግረዋል። 

እነዚህ ለተነሺዎች በኮንትራክተሮቹ የተዘጋጁ  ቤቶች በአያት፣ አራብሳ፣ ቡልቡላ እና አስኮ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

"ቤቶች ልማት እና ፋይናንስ ቢሮዎችን ስንጠይቃቸው ምላሻቸው ገንዘብ የለንም ነው፣ ታድያ ገንዘብ ከሌላቸው ለምን እኛን አሰሩን?" የሚል ጥያቄ የሚያነሱት እነዚህ አነስተኛ እና ጥቃቅን ኮንትራክተሮች አንዳንዶቹ ቤተሰባቸው ጭምር ችግር ላይ እንደወደቀ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከኮንትራክተሮቹ ጋር መረጃ ይለዋወጥበት የነበረ የቴሌግራም ግሩፕን ስራው ካለቀ በኋላ ሰው መረጃ እንዳይቀያየርበት መቆለፉን ለማየት ችለናል።

የቤቶች ልማት ኮንትራክተሮቹን ወደ ስራ ሲያስገባ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ እንዳይጠይቁ አስፈርሞ እንደነበር መሠረት ሚድያ የተመለከተው አንድ ሰነድ ያሳያል።

"ወደን ሳይሆን በግዴታ ነው ካለ ቅድመ ክፍያ ተስማምተን የገባነው፣ እንደዛ ካልተስማማን ወደፊት ምንም ስራ ከተማ ውስጥ መስራት አትችሉም ተብለን ማስፈራርያ ተሰጥቶን ነበር" ያሉት ግለሰቦቹ አሁን ላይ ለሁሉም ስራ ሳይከፈል የተከማቸው ገንዘብ 4.4 ቢልዮን ብር ገደማ እንደሆነ ጠቁመዋል።

መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ባደረገው ተጨማሪ ከ3 ሚልዮን ብር እስከ 42 ሚልዮን ብር የተያዘባቸው ኮንትራክተሮች እንዳሉ የተረዳ ሲሆን ከነዚህ ኮንትራክተሮች ውጪም በኮሪደር ልማት ዙርያ የመንገድ ግንባታ የተሳተፉ አቅማቸው ከፍ ያለ ኮንትራክተሮችም ክፍያ ተነፍጓቸው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችላል።

Via Meseret Media

@etconp
👍9❤1
👉የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በኮሪዶር ልማቱ እያከናወናቸው ከሚገኙ በርካታ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የሜክሲኮ ፓርኪንግና ታክሲ ተርሚናል በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

💫ሜክሲኮ ኬኬር ሕንፃ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በ9,200 ካ.ሜ. ቦታ ላይ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ዘመናዊ ፓርኪንግ እና ታክሲ ተርሚናል በውስጡ ካፊቴሪያ፣ ሱቆች፣ የህዝብ መፀዳጃዎች፣ የአስተዳደር ሕንፃ እና ምቹ የተሳፋሪ መጠበቂያ ስፍራ ይኖረዋል።

@etconp
👍5❤2
👉ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ኣዲስ የ ETABS በ ኣማርኛ ቲቶርያል ከ introduction ጀምሮ Analysis እና Design ኣካተን ምርጥ ቪድዮ እየለቀቅን እንደምንገኝ ይታወቃል።

🫵እንሆ ቀጣዩ ክፍል 4 👇

https://youtu.be/gKJ1EOwLP-k?si=ILh-MEkFRI0Yiamt
❤3
👉ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን እየገነባው የሚገኘውን 160 ቤቶች የያዛ አፓርታማ አስጎበኘ

💫በመድረኩ ለቤት ባለቤቶች የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓትም ተከናውኗል


🚧ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግል/ማህበር ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም እና ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም ለተለዩ እድለኞች ቅዳሜ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከቃሊቲ ወደ ጋርመንት በሚወስደው መንገድ ያለው ሳይት ያስጎበኘ ሲሆን ግን ለጎንም የፎሎር እጣ የማውጣት ስነስርዓት አከናውኗል።

አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በአነስተኛ ቅድመ ክፍያ እና በዝቅተኛ ወርሃዊ ቁጠባ የቤት ባለቤት ለማድረግ እየሰራው እገኛለው ያለው ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን፤ በአሁኑ ሰዓት እየተገነባ የሚገኘው የቃሊቲ ሳይት በአንድ ወለል ላይ 10 ቤቶች ያሉት ነው ያለው ድርጅቱ ህንፃው በአጠቃላይ ባለ አንድ፣ ሁለትና ሶስት መኝታ የሆኑ 160 ቤቶች የያዘ እንደሆነ ተገልጿል። ድርጅቱ አክሎም ህንፃውን ገንብቶ ሚያዝያ 30/2017 ዓ/ም ለማስረከብ እየተሰራ እንደሆነ ገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ እስካሁን ያጋጠሙ ችግሮች እና በምን መንገድ እንደተቀረፉ እንዲሁም ወደፊት ለመስራት የታሰቡ እቅዶች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

Via ዳጉ ጆርናል

@etconp
👍3
👉"Oresund Bridge" ይባላል በሲዊዲን እና ዴንማርክ መካከል ነው የሚገኘው።

🚧ይህ ድልድይ በአውሮፖ አህጉር በባህር ውስጥ የተገነባ ረጅሙ ነው።

💫ድልድዩ መነሻውን ከሲዊዲን ያደርግና በባህር ውስጥ የውስጥ ለውስጥ ዋሻ አድርጎ ዴንማርክ ውስጥ ብቅ ይላል።

⏺ሁለቱም አገሮች ለዚህ ድንቅ ኢንጂነሪንግ አበርክቶአቸው ላቅ ያለ ነው።

⏺በጠቅላላው የድልድዩ ርዝመት 16 ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ ሁለቱን አገሮችን በኦሬሱንድ ሰርጥ በኩል እንዲገናኙ ያደረገ ነው።

⏺ድልድዩ የተገነባው እ.ኤ.አ በ2000 ዓ.ም ነው።

⏺በመርከብ ብቻ ይገናኙ የነበሩት ሁለቱ አገሮች ከዚያ በኃላ መንገደኞችን በሚያጎጉዙ ባቡሮችና መኪናዎች አገልግሎት እያገኙ ነዉ።

@etconp
👍8🥰1
👉NEW VACANCY

💫Site forman

📍Addis Ababa, Ethiopia

⚡️Deadline: February 13, 2025

⏺Gender Needed: Male

⏺Vacancies: 1

⏺Education Qualification: Bachelors Degree

-በሲቪል ኢንጂነሪንግ የተመረቀ
-የስራ ሞራል ያለው፣ታማኝ እና ታዛዥ
-የስራ ሰአት ጠዋት ከ 2:00-11:00
-የስራ ቦታ ጀሞ 3
ደሞዝ: 8000 ብር የተጣራ

📩ለስራው ማመልከት ምትፈልጉ ስራ ፈላጊዎች ከታች ባለው የቴሌግራም አድራሻ የትምህርት ማስረጃዎችሁን በመላክ መወዳደር ትችላላችሁ
@endris988

@etconp
👍9❤2🥱1
👉በነገራችን ላይ የ Youtube ቻናላችን ቤተሰብ ካልሆነ ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይቀላቀሉን

🏷የ ኮንስትራክሽን ሶፍትዌሮች በ ኣማርኛ ቋንቋ ይማሩ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO

@etconp
❤3👍1