Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉ትላንት በይፋ የተመረቀው የአዲስ አለምአቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል:-

- 40 ሄክታር መሬት ላይ አርፏል
- እያንዳንዳቸው ከ3 ሺሕ እስከ 4 ሺሕ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው 2 ትላልቅ አዳራሾች፣ 8 አነስተኛ እና መካከለኛ የመሰብሰቢያ አዳራሾች በጠቅላላ እስከ 10 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ
- እስከ 1 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ አልጋዎችን የያዙ 2 ሆቴሎች
- ከቤት ውጪ እስከ 50 ሺሕ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የኤግዚቢሽን ስፍራ
- ሁለት አንፊ ቴአትር
- 2 ሄክታር የዉጪ ኤግዚቢሽ ቦታ
- ሁለት ሞሎች
- ሬስቶራንቶች፣ በርካታ የንግድ ሱቆች፣ ባንኮች እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት
- በሀገራችን ትልቁ የኮንፍራንስ ማዕከል
- አለምአቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁነቶችን የሚያስተናግድ
- በከተማችን ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው ግዙፍ አደባባይ ከሆነው የለሚ ፓርክ ጋር ተያይዞ የተሰራ በአጠቃላይ እስከ 2 ሺሕ መኪናዎችን የማቆም አቅም ያላው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው::

@etconp
👍7❤2
👉BS 8110 is a British Standard that provides guidelines for the structural use of concrete. Here's a simplified breakdown:

⭐️Purpose:

⏚It sets out rules and recommendations for designing and constructing reinforced concrete structures.

⏚Its goal is to ensure that concrete structures are safe, durable, and perform as intended.

💫Key Concepts:

▶️Limit State Design: BS 8110 uses the limit state design approach, which considers various potential failure modes (limit states) and ensures that the structure can withstand them.

📜This includes:

⏺Ultimate Limit State: Preventing collapse.

⏺Serviceability Limit State: Controlling things like deflection and cracking.

⏺Reinforcement: It provides detailed guidance on the use of steel reinforcement in concrete, including:

⏺Minimum and maximum reinforcement requirements.
     
⏺Rules for bar spacing and concrete cover.

⏺Design of reinforcement for different structural elements (beams, columns, slabs, etc.).

⏺Concrete Properties: It addresses the properties of concrete, such as its strength and durability.

@etconp
👍10
👉NEW VACANCY

💫ስትራክቸራል ፎርማን (የመንገድ ግንባታ)

🚧ማንበብና መጻፍ የሚችል አግባብ ባለው የሥራ ልምድ ከዚህ ውስጥ 6 ዓመት እንደ ፎርማን የሰራ

📜ችሎታዎች

- ድሮዊንግ በአግባቡ ማንበብ የሚችል
- ከስሩ ላሉ ሰራተኞች የስራ ክፍፍል መስጠት እንዲሁም መምራት የሚችል

⏺Quanitity Required: 2

📍Addis Ababa

⏺Minimum Years Of Experience: #9_years

⚡️Deadline: March 12, 2025

📩How To Apply: የትምህርት ማስረጃችሁን እና የስራ ልምዳችሁን ፎቶ በማንሳት ከታች ያለውን የ ቴሌግራም ሊንክ በመጠቀም ያመልክቱ👇

https://t.me/anduamlak4

@etconp
👍6🙏3❤1
ሲጠና በነበረው የግንባታ ዘረፍ የአማካሪዎች ክፍያ ተመን የአሰራር ሥርዓት ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ኢንስቲትዩቱ  የግንባታ ዘርፍ የአማካሪዎች የክፍያ ተመን  አሰራር ሥርዓትን ለመዘርጋት ከኢትዮጵያ አማካሪ ኢንጅነሮችና ከአርክተክቶች ማህበር ጋር በመተባበር ሲያስጠና በነበረው የጥናት ሰነድ ላይ አጥኝ አባላቱና የኢንስቲትዩቱ ሼል ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት አድርጓል፡፡

የዚህ ውይይት ዓላማም  ሲጠና የነበረውን የአሰራር ሥርዓት በተቀመጠው ስታዳርድ፣ መዳሰስ የነበረባቸውን መረጃዎች  እና የኮንስትራክሽን ዘርፉ ነባራዊ ሁኔታዎችን መሠረት ባደረገ መልኩ መጠናቱን በመገምገም የማዳቢያ ሀሳብ ለመስጠት ያለመ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

የጥናት ሰነዱም በአጥኝ ቡድኑ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን፣ ከቀረቡት ጉዳዮች ውስጥም አሁናዊ የአማካሪዎቹ ክፍያ ሁኔታ በተለይም ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ አርክተክቶች ማህበር የወጣውን የክፍያ ተመን አሰራር ጋር በማነጻጸር ሲታይ ከፕሮጀክት ፕሮጀክት የተለያዬና የሚዋዥቅ መሆኑ፣ ይህንኑ አሠራርም የተከተለ የአተማመን ሁኔታ አለመኖሩ ተመላክቷል፡፡  ለዚህም እንደምክንያት ከተጠቀሱት ውስጥ ወጥነት ያለው ስታንዳርድ አለመኖር፣ በዘርፉ ከፍተኛ የገበያ ውድድር መኖሩ፣  የገበያ መዛባት ዋነኞቹ እንደሆኑ  ተጠቅሰዋል፡፡

የአሁኑ ጥናት የዓለም አቀፉን እና ሀገር አቀፉን የኮንስትራክሽ ዘርፉን ነባራዊ ሁኔታ በመዳሰስ ወጥነት ያለው የክፍያ ተመን አሰራር ሥርዓት ለማዘጋጀት ጥረት እንደተደረገ  ተብራርቷል፡፡

ተሳታፊዎቹም በቀረበው የጥናት ሰነድ ላይ የተለያዩ አስተያዬቶችንና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን  እንደ ግብዓት የሚወሰዱትን በመውሰድ በቀሪዎቹ ላይ ማብራሪያና ምላሽ  ሰጥቷል፡፡

የዕለቱን መድረክ ሲመሩ የነበሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ታምራት ሙሉ በማጠቃለያው ላይ ባስተላለፉት መልዕክትም ኢንስቲትዩቱ የዘርፉን ተዋናይ ችግሮችን በማቃለል የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማጎልበት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው ከዚህም ውስጥ አንዱ ይህንን አሰራር ሥርዓት መዘርጋት እንደሆነ ጠቁሟል፡፡ የጥናት ሰነዱም የዘርፉን ችግር በሚፈታ መልኩ ፣ ግልጽና መረጃን መሠረት አድርጎ በጥልቀት መዘጋጀት ይኖርበታልም ብለዋል፡፡ ይህም መድረክ ይህኑ በመገምገም ክፍተት ያለባቸው ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ስለሆነም ከመድረኩ የቀረቡትን በግብዓትነት በመጠቀም እንድሁም አስፈላግ የሆኑ መረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በተጨማሪነት በማካተት የተሟላ የጥናት ሰነድ በቀጣይ እንዲቀርብ አቅጣጫ በማስቀመጥ የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።

ምንጭ~ Construction Management Institute
👍7👏2🕊1
👉አያት መንግሥት ባለበት አገር የገዙትን ሱቅ አላስረክብም ብሎ ለ18 ዓመታት እያሰቃያቸው መሆኑን ገዥዎች ተናገሩ

🏷የሚመለከተው የመንግሥት አካል መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል
‹‹ያሉትን ችግሮች በንግግር እንፍታ ብለናቸዋል››

አያት ሪል ስቴት
ከአያት አክሲዮን ማኅበር ከ18 ዓመታት በፊት የንግድ ሱቆችን ግዥ ሲፈጽሙ በገባው ውል መሠረት ሙሉ ለሙሉ ገንብቶ በ18 ወራት ሊያስረክባቸው ስምምነት የፈጸሙ ቢሆንም፣ የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠትና ምላሽ በመንፈግ ላለፉት 18 ዓመታት እያሰቃያቸው መሆኑንና ሊያስረክባቸው እንዳልቻለ ገልጸው፣ መንግሥት ባለበት አገር መበደል ስለሌለባቸው የሚመለከተው አካል መፍትሔ እንዲሰጣቸው ገዥዎች ጠየቁ፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ አሥር አያት ባቡር ጣቢያ አካባቢ ከ550 በላይ የንግድ ሱቆች...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/138841/

@etconp
👍9
👉ክፍት የስራ ቦታ

💫UNOPS

🚧ስትራክቸራል መሀንዲስ ማስተርስ ዲግሪ

🏷የሚከተለው ማስፈንጠርያ በመንካት ያመልክቱ👇

https://jobs.unops.org/pages/ViewVacancy/VADetails.aspx?id=29836

@etconp
👍2👏2
👉ለአዲስ አበባ ባለጓሮዎች

📜በ 2016 ዓ.ም በተሻሻለው የአዲስ አበባ የህንፃ መመሪያ መሰረት በከተማ አስተዳደሩ ክልል ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች በይዞታቸው ላይ ማልማት የሚችሉበትን ህጋዊ አሰራር ያሳያል፡፡

⏺በመመሪያው ከገጽ 34 እስከ 36 በተገለፀው መሰረት ከ1,000 ካሬ በታች ላሉ ይዞታቸው ስፋት 80 በመቶ ያልበለጠ፣ከ1,001 እስከ 2,000 ካሬ ሜትር ላሉ ይዞታዎች የይዞታው 70 በመቶ ያልበለጠ፣ከ2,001 እስከ 3,000 ካሬ ሜትር ላሉ ይዞታዎች የይዞታው 50 በመቶ ያልበለጠ፣ከ3,001 እስከ 4,000 ካሬ ሜትር ላሉ ይዞታዎች የይዞታው 25 በመቶ ያልበለጠ፣ከ4,001 እስከ 5,000 ካሬ ሜትር ላሉ ይዞታዎች የይዞታው 20 በመቶ ያልበለጠ እንዲሁም ከ5,001 ካሬ ሜትር በላይ ላሉ ይዞታዎች የይዞታው 20 በመቶ ያልበለጠ ነገር ግን አጠቃላይ ግንባታው ከ2,000 ካሬ ሜትር በላይ መብለጥ የለበትም ሲል ይደነግጋል፡፡

▶️ይህ ማለት ቀደም ብሎ አርሶ አደሩ ማልማት የሚችለው 5% በሚል ተቀምጦ የነበረው አሰራር ከላይ በተዘረዘሩት አገላለፆች ተቀይሯል ማለት ነው፡፡

⏺የአርሶ አደር ማቋቋምና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ አርሶ አደሩ ለረጂም ጊዜ ሲጠይቅ የነበረው ጥያቄ መልስ ያገኘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መከላከል ይገባል ብለዋል አያይዘውም በየደረጃው ያሉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መመሪያው ሳይሸራረፍ መተግበር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

⏺የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሣ ባይሳ በበኩላቸው መመሪያውን ለክፍለ ከተሞች እንዳወረዱ፤ በባለሙያም አተገባበሩ ላይ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

@etconp
👍7
👉NEW VACANCY

💫Junior QA/QC Engineer

⭐️Bachelor's Degree in Civil Engineering or in a related field of study with a CGPA of 3.00 and above

📜Duties & Responsibilities:

- Inspect construction works and sample materials parts or products for defects and any deviations from specifications and provide inspection reports
Required Skills:
- Excellent Communication Skills
- Excellent Reporting Skills
- Excellent Conduct/Ethics

📍Addis Ababa

⏺Quanitity Required: 5

⏺Minimum Years Of Experience: #0_years

⚡️Deadline: March 19, 2025

📩How To Apply: Submit your credentials via email: MarakiE@eeigconstruction.com

🎲Note: Please make sure you apply with a proper CV along with the scanned copy of your educational documents.

@etconp
🙏7👍6
👉በከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን መሠረት የመንገድ መሠረተ-ልማት ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ ነው

በ10ኛው የአዲስ አበባ መዋቅራዊ ፕላን መሠረት የከተማዋን 30 በመቶ ክፍል በመንገድ መሠረተ-ልማት ማስተሳሠርን ታላሚ በማድረግ እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

በዚሁ መሠረት የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግ ባለፉት ሥድስት ዓመታት የነባር መንገዶች ማሻሻያ እና የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ መከናወኑን የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢያሱ ሰሎሞን ገልጸዋል፡፡

ለአብነትም የቃሊቲ - ቱሉ ዲምቱ፣ የቂሊንጦ - ቃሊቲ፣ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ - አይ.ሲ.ቲ ፓርክ፣ የአይ.ሲ.ቲ ፓርክ - አራብሳ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በባለሥልጣኑ አቅም የተገነቡ አጫጭር እና አንደኛውን ጎዳና ከሌላኛው የሚያስተሳሥሩ አዳዲስ መንገዶች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የከተማዋ 10ኛው መዋቅራዊ ፕላን መሠረት 40 በመቶ የከተማዋ ክፍል ለግንባታ፤ 30 በመቶው ለመንገድ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ ለአረንጓዴ ልማት ማዋልን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከከተማዋ አጠቃላይ የመንገድ ሽፋን አንጻር እየተሠራ ያለው ሥራ ዋነኛ መነሻው የከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን መሆኑን ለፋና ዲጂታል አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የኮሪደር ልማቱ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች እንዲኖሩ ማስቻሉ፣ የፔዳል ሳይክል መተላለፊያ መሥመሮችን ማመቻቸቱ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር ማድረጉ ለከተማዋ ዕድገት አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ ተቋማት ተሣትፎ የመንገድ አካፋይና ዳርቻዎች በአረንጓዴ እፅዋት እንዲዋቡና ደማቅ ብርሃን ባላቸው የመንገድ ዳር መብራቶች መሸፈናቸው የከተማዋ ጎዳናዎች ዘመናዊና ማራኪ ገፅታ እንዲላበሱ ማስቻሉን አቶ ኢያሱ ጠቁመዋል ፡፡

ምንጭ፡ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን

@etconp
👍4❤3
👉ክፍት የስራ ቦታ

💫UNOPS

🚧ሀይድሮሊክ ኢንጅነሪንግ

🏷የሚከተለው ማስፈንጠርያ በመንካት ያመልክቱ👇

https://jobs.unops.org/Pages/ViewVacancy/VADetails.aspx?id=29697

@etconp
🙏5👍4
👉" የግንባታ ደረጃዎች "
"Building Construction Classification"


⭐️በሊዝ የተያዘ መሬት ላይ ግንባታ የመጀመሪያ እና የማጠናቀቂያ ቀነ ገደብ እንደ ግንባታዎቹ ደረጃ ተለያይቶ ተቀምጧል (በሚቀጥለው ክፍል ይዳሰሳል)።

📜ለዛሬው የግንባታ ደረጃዎ አከፋፈልን እንመልከት።

⏺የሀገራችን የኮንስትራክሽን ሕግ ግንባታዎችን በሦስት (3) ዋና ዋና መደብ ይከፍላቸዋል።

🎲እነሱም፦ አንሰተኛ ደረጃ ግንባታዎች፣ መካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች፣ እና ከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች ናቸው።

💫A. አነስተኛ ደረጃ ግንባታዎች (Small scale constructions)

አነስተኛ ደረጃ ግንባታዎች የሚባሉት እስከ ሦስት ወለል ያላቸው የተናጠል መኖሪያ ቤቶች (private residential building) ወይም እስከ ሦስት ወለል ያላቸው የሕዝብ መጠቀሚያ ያልሆኑ ሌሎች ግንባታዎች ወይም የይዞታ ስፋቱ እስከ 250 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚገነቡ ግንባታዎች ናቸው።

💫B. መካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች (Intermediate scale constructions)

መካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች የሚባሉት 5 ወለል እና ከዚያ በታች የሆኑ የሕዝብ መጠቀሚያ ሕንጻዎች፣ ወይም የይዞታ ስፋቱ ከ251 ካሬ ሜትር እስከ 5000 ካሬሜትር ይዞታ ላይ የሚገነቡ ግንባታዎች፣ ወይም የመኖሪያ ቤት ባለ 4 እና ባለ 5 ወለል የሆኑ ግንባታዎች፣ ወይም የመኖሪያ ቤት በአንድ ጊዜ እስከ 80 ነጠላ ቤቶች የያዙ ግንባታዎች፣ ወይም የሕዝብ መጠቀሚያ ያልሆኑ ሌሎች ወለላቸው ባለ 4 እና ባለ 5 የሆኑ ግንባታዎች፣ ወይም ለትምርት ተቋማት እስከ 2ኛ ከፍተኛ ደረጃ የሚያጠቃልሉ ግንባታዎች፣ ወይም ለቤተ መጻሕፍትና ለሁለገብ አዳራሾች እስከ 500 ሰው የሚይዙ ግንባታዎች፣ ለጤና ማዕከል እስከ ከፍተኛ ክሊኒክ የሚያጠቃልሉ ግንባታዎች፣ ለስፖርት ሜዳዎች እና ለስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት እስከ 500 ሰው የሚይዙ ግንባታዎች፣ ወይም በአጠቃላይ የወጪ ግምታቸው እስከ ብር አምስት ሚሊዮን (5,000,000) ብር የሆኑ መካከለኛና አነስተኛ የማምረቻ እና ማከማቻ ተቋማትን ያጠቃልላል።

💫C.  ከፍተኛ ግንባታዎች (High scale constructions)

ከፍተኛ ደረጃ ግንባታዎች የሚባሉት ባለ ስድስት (6) ወለል እና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ግንባታ፣ ወይም የይዞታ ስፋቱ ከ5000 ካሬሜትር ቦታ በላይ የሆነ ይዞታ ላይ ለሚገነቡ ወይም በዓለም በሀገር እንዲሁም በከተማ አቀፍ ደረጃ ለሚገነቡ የትራንስፖርት የመናኸሪያ ተቋማቶች፣ ወይም ትላልቅ የዲፕሎማቲክ ተቋማት የሚገነቧቸው ግንባታዎች፣ ወይም ከላይ በአነስተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ከተጠቀሱት ውጪ ያሉ ግንባታዎችን ያጠቃልላል።

@etconp
👏9👍7❤1