Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉በሰሜን ምዕራብ ቻይና በመገንባት ላይ የነበረ ድልድይ ገመድ በመበጠሱ ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ዘጠኝ ደግሞ ጠፍተዋል ሲል የቻይና መንግስት ሚዲያ ዛሬ ዘግቧል።


🚧'ዘ ፒፕልስ ዴይሊ' እንደዘገበው ከሆነ በኪንግሃይ ግዛት በቢጫው ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ በነበረው ድልድይ ላይ 15 ሰራተኞች እና አንድ የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አርብ ጠዋት 3 ሰዓት ገደማ ገመዱ ሲበጠስ በስራ ላይ ነበሩ። የጠፉትን ለማግኘት የነፍስ አድን ስራ እየተከናወነ ነው።

በዘገባው መሰረት፣ የሲቹዋን-ኪንግሃይ የባቡር ድልድይ በአለም ላይ ትልቁ ድርብ መስመር ያለው የባቡር ተከታታይ የብረት ድርድር ቅስት ድልድይ ነው።

በቢጫው ወንዝ ላይ የተሰራ የቻይና የመጀመሪያው የባቡር የብረት ድርድር ቅስት ድልድይ ሲሆን በሀገሪቱ ሁለተኛው ረጅሙ በመባል ይታወቃል።

በድረ-ገጹ ላይ የወጡ ፎቶዎች እንደሚያሳዩት ከፊሉ የተገነባው ድልድይ መካከለኛው ክፍል አሁንም አልተጠናቀቀም።

በሁለቱም በኩል ሁለት ግዙፍ የቁመታዊ ማቆሚያዎች (scaffolding towers) እና በርካታ ክሬኖች ይታያሉ።

ባለፈው አመት ታህሳስ ወር ላይ ደቡባዊቷ የቻይና ከተማ ሼንዘን ውስጥ ትልቅ የባቡር ግንባታ ቦታ ፈርሶ 13 ሰዎች ጠፍተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከዚህ አደጋ ተርፎ የወጣ ሰው አልነበረም።

@etconp
❤8
👉ቱሪዝምና መሠረተ ልማት

💫ከድሮ ጀምሮ (ለበርካታ አመታት) በኢትዮጵያ ከቱሪዝም ኢንዱስትሪ ተጠቃሚ ላንሆን የቻልነው ከመሠረተ ልማት ጋር መስፋፋት አለመኖር ጋር የተያያዘ ምክንያቶች ሲቀርቡ መስማት የተመደ ነበር። የመንገዶች አለመኖር፣ የማረፊያ ቦታዎች እጥረት፣ እንዲሁም የቴሌኮም እና የመብራት አለመኖር እንደ ችግርም ሲነሳ ይደመጥ ነበር። ለቱሪዝም ዕድገት የመሠረተ ልማት ስርጭት ወሳኝነቱ ላቅ ያለ ነው። 

አሁን አሁን ግን ቀስ በቀስ ከዚህ በፊት ሲጠቀሱ የነበሩት የመሠረተ ልማት እጥረት ችግሮች ከሞላ ጎደል እየተቀረፉ መጥተዋል። አሁን ከፀጥታ ጋር የተያያዙ ችግሮች እንደ እንቅፋት ሲነሱ ይደመጣል እንጂ፣ በኢትዮጵያ የቱሪስት መዳረሻዎች እየተስፋፉ በመሄድ ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ቱሪዝም ደረጃ በደረጃ አቅሙን እያሳደገ ስለመምጣቱ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል።


ይህ በአፋር ክልል አፋምቦ የሚገኝ ውብ ቦታ ቀልብን ሰብሰብ የሚያደርግ ልዩ ስፍራ ነው።

የአዋሽ ወንዝ በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ትልቅ ሃይቅ ሆኖ ለጥ ብሎ ያረፈበት። ሌላው በዚህ አካባቢ የሚታወቀው የቴምር  ምርት በስፋት የሚገኝበት መሆኑ ነው።


በዚህ አካባቢ የእንስሳት መኖን ጨምሮ በርካታ የግብርና ሥራዎች ከግለሰብ እስከ ኢንቨስተር ይሠሩበታል።

በአፋምቦ ሃይቅ ላይ ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው ዓሣ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆነዋል።
በአፋምቦ ሃይቅ ላይ ሰዎችን አይነኩም (ለማዳ) ናቸው የሚባልላቸው አዞዎችም ይገኛሉ። እነዚህን አዞዎች ጨምሮ የአካባቢውን ውብ ፀጋ ለማየት በርካታ ቱሪስቶች ወደ አካባቢው ይጓዛሉ።


የአሳይታ-አፋምቦ-ጅቡቲ መንገድ በመሠራቱ ለአካባቢው ትልቅ ውበት ከመስጠት በተጨማሪ ለመሠረተ ልማት ዕድገት አቅም ፈጥሯል።

@etconp
❤9🥰1
👉በሕንድ ቦፓል በተባለ ከተማ ውስጥ ሰባት ኢንጂነሮች ከሥራ ኢንዲታገዱ ተደርጓል።

🚧የታገዱበት ምክንያትም በከተማዋ የገነቡት ድልድይ የ 90 ዲግሪ አንግል እንዲኖረው አድርገው እንዲገነባ በማድረጋቸው ነው።

💫ይህ አሠራር ለአደጋ የሚጋብዝ እና መኪኖች ለመዞርም የማያመቻቸው መሆኑ ተገልፆል።


የድልድዩ ያልተለመደ ዲዛይን ለተሽከርካሪዎች ከሞላ ጎደል ጥቅም ላይ እንዳይውል አድርጎታል፣ ይህም ይፋዊ ጥያቄን ሊያስነሳ ችሏል።


🏷ድልድዩ ለአገልግሎት ብቁ ነው በሚል የማጽደቁ ሂደት አሁን በቅርበት እየተፈተሸ ሲሆን፣ እገዳዎቹ በመሠረተ ልማት ደረጃዎች እና ተጠያቂነት ላይ ውይይቶችን አስነስተዋል።

⏺ባለስልጣናት ማስተካከያዎችን በመተግበር ላይ ሲሆኑ፣ አወዛጋቢው ድልድይ ግን የደህንነት መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ ተዘግቶ ይቆያል።

ይህ ክስተት በሕዝብ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ ጥብቅ ቁጥጥር እና የተሻሻለ ዕቅድ አስፈላጊነትን አጉልቶ የሳየ መሆኑ ታውቋል።
▪️▫️▪️


@etconp
❤9
👉ፈንድቃ አዲስ የሚያስገነባውን ህንፃ ይፋ አደረገ

💫በካርሎ ራትቲ አሶሺያቲ የሚመራው  በዓለም ታዋቂ የሆነ የኢጣሊያ የስነ ሕንፃ ተቋም ለአዲሱ የፈንድቃ ህንፃ ንድፍ ይፋ አድርጓል።

🚧ፈንድቃ የባህል ማዕከል በጥቅምት 2017 ከፈረሰ በኋላ በቦታው የራሱን ህንጻ እንዲሰራ ቦታው ለፈንድቃ መሰጠቱ ይታወሳል።

🏷ከታህሳስ 2017 ጀምሮ ፈንድቃ ከሀያት ሬጀንሲ ጋር በመተባበር ኮንሰርቶችንና እና አዝማሪ ፕሮግራሞችን እያቀረበ ይገኛል።

@etconp
❤6🔥1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ለሚያስገነባው አየር ማረፊያ ለሚያስነሳቸው ነዋሪዎችና ገበሬዎች ካሳ ከ350 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስወጣዋል ተባለ

ዘ ሪፖርተር እንደዘገበው ገንዘቡ ከ2,000 በላይ ለሚሆኑ የአርሶ አደር ቤተሰቦች መልሶ ማቋቋሚያ ፓኬጅ የሚያውል ሲሆን፣ የመኖሪያ ቤቶች፣ የንግድና የመኖሪያ አገልግሎት መስጫ ህንፃዎች፣ የእርሻ ምርት ማቀነባበሪያ እና የመስኖ እቅዶችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

@etconp
❤12👍1
👉የገደብ ወንዝ ድልድይ ከዛሬ ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል

🚧ነሐሴ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት ጮቄ ተራራ ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት በተገጣጣሚ ብረት የመገንባቱ ሥራ ሲከናወንለት የቆየው የገደብ ወንዝ ድልድይ በዛሬው ዕለት ሥራው ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል፡፡

በጎርፍ ምክንያት ድልድዩ ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ግንባታው እስኪጠናቀቅ በትዕግስት ሲጠባበቁ ለቆዩ መንገደኞችና አሽከርካሪዎች የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምስጋና እያቀረበ ድልድዩ ሁለት መኪና በአንዴ ማስተላለፍ ስለማይችል በመጠባበቅ እንዲተላለፉ፣ ድልድዩ የሚገኝበት ቦታ ኩርባ ላይ ስለሆነ ፍጥነት በመቀነስ እና ቅድሚያ በመስጠት በትዕግስት እንዲተላልፉ ያሳስባል፡፡

@etconp
👍3❤1😢1
👉አስደሳች ዜና ለዚህ ቻናል ቤተሰቦች

💫ሁለተኛ ዙር የ "Quantity Surveying" Full Course ኦንላይን ላይ በ አማርኛ ቋንቋ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች እና የ ኮንስትራክሽን ባለሞያዎች ሁለተኛ ዙር በተመጣጣኝ ዋጋ ለጥቂት ተማሪዎች ምዝገባ ጀምረናል
               
🔥 ይህ ስልጠና ምን ምን ትምህርቶችን ያካትታል?
💫Takeoff sheet
💫Bill of Quantity(BOQ)
💫Payment Certificate

🏷በዘርፉ ብዙ አመታትን ባስቆጠሩ መምህራን ስልጠናውን ለመስጠት ዝግጅቶቻችንን ጨርሰን እርሶን በመጠባበቅ ላይ እንገኛልን ስለዚህ ዛሬ ነገ ሳይሉ ፈጥንው በመመዝገብ እራሶዎትን በትምህርት አዳብረው በቀላሉ ወደ ስራው እንዲቀላቀሉ አንርዳዎት እንላለን።

📍ታዲያ ምን ይጠብቃሉ ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ቀድመው ቦታ በመያዝ ይመዝገቡ                       

📩መመዝገብ የምትፈልጉ @Philemona7 ወይም ለበለጠ መረጃ በ 0925446661 ደውለው ያግኙን🙏

@etconp
❤6👏2
You are managing a road project. The client’s payment is delayed by two months, but you must pay workers and suppliers. What is the BEST action?
Anonymous Quiz
6%
A) Stop all work until the client pays
81%
B) Request an advance from suppliers and negotiate delayed payment terms
10%
C) Increase daily work pace to cover the delay
4%
D) Ignore the issue and wait for client
❤13🔥1
Your company is running 4 projects simultaneously. Head office overhead costs 40 million ETB annually. If your project value is 200 million ETB out of a total 800 million ETB company turnover, how much overhead should be allocated to your project?
Anonymous Quiz
12%
A) 5 million ETB
21%
B) 8 million ETB
42%
C) 10 million ETB
25%
D) 20 million ETB
👏10❤6🤩1
Your company borrowed 100 million ETB at 12% annual interest to finance a PPP housing project. Due to delays, repayment will extend from 3 years to 5 years. What is the financial consequence?
Anonymous Quiz
5%
A) No effect since principal is unchanged
72%
B) Total interest increases significantly, reducing profitability
18%
C) Repayment period extension reduces interest cost
5%
D) Loan becomes cost-free after 3 years
❤9🙏3👍1
Your project budget = 120 million ETB.

Actual Cost (AC) so far = 70M ETB Earned Value (EV) so far = 60M ETB Cost Performance Index (CPI) = EV ÷ AC = 0.86 What is the Estimate at Completion (EAC)?
Anonymous Quiz
15%
A) 120M ETB
36%
B) 130M ETB
38%
C) 140M ETB
11%
D) 150M ETB
❤6👍4👏1🏆1
A crane costs 30M ETB to buy.
Depreciation life = 10 years, resale value = 5M.
Leasing cost = 500K/month. Project duration = 36 months. Which is cheaper for the project?
Anonymous Quiz
42%
A) Buy crane
42%
B) Lease crane
11%
C) Both equal cost
6%
D) Cannot be determined
❤3🙏2👍1🥰1
In your monthly financial report, actual site expenses are under-reported by 15% due to delayed invoices. What is the risk?
Anonymous Quiz
24%
A) Client will reject invoices later
43%
B) Project appears healthier than reality, leading to poor decisions
20%
C) Profit margins increase automatically
13%
D) No risk if invoices are paid later
❤9👍1🫡1
👉በመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ መባከኑን የኦዲት ሪፖርት አጋለጠ!

የፌዴራል ዋና ኦዲተር በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ በመንግሥት ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ የገንዘብ ብክነትና የሥርዓት ክፍተት መኖሩን አጋልጧል።

ሪፖርቱ እንደሚያሳየው በመንገድ ግንባታና በዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክቶች ላይ ብቻ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ መባከኑን አረጋግጧል።

ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ ከ180 በላይ የመንገድ ፕሮጀክቶች ከመጀመሪያ በጀታቸው በተጨማሪ ከ13.26 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ አስከትለዋል። ይህም ከ75% በላይ የሚሆኑት ፕሮጀክቶች ከፍተኛ የሆነ ተጨማሪ ወጪ እንደደረሰባቸው ያሳያል።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ለዚህ ችግር እንደምክንያት የካሳ ክፍያና የመሬት ወሰን ችግሮችን፣ የጸጥታ ሁኔታዎችን፣ የፋይናንስ ፍሰት መጓተትን፣ የዋጋ ግሽበትን እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ጠቅሰዋል።

Via Capital

@etconp
❤9
Tender Fairness | የ ጨረታ ፍትሃዊነት


💫በጨረታ ሂደት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ጨረታውን የሚያወጣው ተቋም የሚከተሉትን አራት ነገሮች ማድረግ ይኖርበታል:-

🚧1) በጨረታ ጥሪ ሁሉም ዕጩ ተወዳዳሪዎች በቂ መረጃ ማግኘታቸውን ማረጋገጥ፣ የሚዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በጨረታው ለመሳተፍ እና ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችል የመጫረቻ ሰነድ ለማዘጋጀት የሚያስችል የተሟላ እና ግልጽ መረጃ መያዙን ማረጋገጥ፤

🚧2) በጨረታ ሰነዱ የተገለፀው ማንኛውም የመወዳደሪያ መስፈርትም ሆነ የፍላጎት መግለጫ ዝርዝር የተወሰነ ዕጩ ተወዳዳሪን ሊጠቅም በሚችል መልኩ አለመዘጋጀቱን ማረጋገጥ፣

🚧3) የጨረታው ውጤት ለሁሉም ተሳታፊዎች በእኩል ጊዜ መገለጹን ማረጋገጥ፣

🚧4) በውል ሰነድ ላይ ለአቅራቢዎች የሚሰጠው ኃላፊነት ግዴታቸውን ሆን ብሎ ለማቅለል ወይም ለማክበድ ያላለመ እና እስከተቻለ ድረስ ተመሳሳይ ውል ለሚፈርሙ አቅራቢዎች ተመሳሳይ ይዘት ያለው ውል ሆኖ መዘጋጀቱን ማረጋገጥ ይገባል።

@etconp
❤13
👉ወጋገን ባንክ በመቐለ ከተማ ባለ 25 ፎቅ ሕንፃ ሊገነባ ነው

🏷ከአሸናፊው ተቋራጭ የግንባታ ቦታ ርክክብ አድርጓል

💫ወጋገን ባንክ በመቐለ ከተማ ለሚያስገነባው ለሁለገብ አገልግሎት የሚውል ባለ 25 ወለል ህንፃ ለአሸናፊው የግንባታ ተቋራጭ የዛምራ ኮንስትራክሽን የግንባታ ቦታ ርክክብ ፈጸመ፡፡

በግንባታ ቦታ ርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባንኩ ቺፍ ሰፖርት ሰርቪስስ ኦፊሰር አቶ መንገሻ ፍሰሃ የህንፃው ግንባታ ጅማሮ በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየ መሆኑን ጠቅሰው የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ማኔጅመንት በሰጡት ከፍተኛ ትኩረት ግንባታውን ለማከናወን ለተቋራጭ ድርጅቱ የግንባታ ቦታ ርክክብ መፈፀሙን ተናግረዋል፡፡

አቶ መንገሻ ፍሰሃ ዛምራ ኮንስትራክሽን ሥራውን በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት በጥራት ሰርቶ በማጠናቀቅ እንደሚያስረክብ ያላቸውን ከፍተኛ እምነት ገልፀው አማካሪው ድርጅት ኢኢኤስ ኮንሰልቲንግ አርክቴክቶች እና ኢንጂነሮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ለግንባታው በስኬት መጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


🚧በግንባታ ቦታ ርክክቡ ወቅት የወጋገን ባንክ የዋና መስሪያ ቤት፣ የሰሜን ሪጅናል ኦፊስ፣ የመቐለ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ፣ የዛምራ ኮንስትራክሽን እና የኢኢኤስ ኮንሰልቲንግ አርክቴክቶች እና ኢንጂነሪንግ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

@etconp
❤8