Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
"የስኮላርሺፑን የሙሉ አመት የትምህርት ወጪ የሩሲያ መንግሥት ይሸፍናል " - ሩሲያን ሃውስ

የሩሲያ መንግስት በማንኛውም የትምህርት መስክ በሩሲያ ትምህርት የመከታተል ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ስኮላርሺፕ ማመቻቸቱን አሳውቋል።

ስኮላርሺፑ የሩሲያ መንግስት ለ155 የባችለር፣ ማስተርስ እና ፒ ኤች ዲ ተማሪዎች በማንኛውም ፊልድ እንዲማሩ የፈቀደው ነው።

ባለፈው አመት ለ100 ተማሪዎች ተፈቅዶ የነበር ስኮላርሺፕ በዘንድሮ አመት ቁጥሩ ወደ 155 ተማሪዎች ከፍ የተደረገ ሲሆን እንደ አመልካቾች ብዛት የሩሲያ መንግስት ቁጥሩን ከእዚህም ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል የሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የሩሲያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል ወይም በአዲሱ ስያሜው ሩሲያን ሃውስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ የስኮላርሺፑ ሙሉ የትምህርት ክፍያ በሩሲያ መንግሥት የሚሸፈን መሆኑን ገልጾ የጉዞ ትኬት እና የኢንሹራንስ ወጪዎችን ብቻ በአመልካቾች የሚሸፈን ይሆናል ብሏል።

የትምህርት ሂደቱ የቆይታው ጊዜ ለባችለር አራት አመት ለማስተርስ ሁለት አመት እንዲሁም ለ ፒ ኤች ዲ አመልካቾች እንደ ትምህርቱ አይነት የቆይታ ጊዜያቸው የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።

ስኮላርሺፑን አሸንፈው የሚሄዱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከመጀመራቸው በፊት ለአንድ አመት የቋንቋ ትምህርት የሚማሩ ሲሆን እንደ ሩሲያን ሃውስ መረጃ ስኮላርሺፑ የሙሉ የትምህርቱን እና የቋንቋን አንድ አመት ቆይታ ያካተተ ነው።

ተማሪዎች ካመለከቱ በኋላ ለስኮላርሺፑ ብቁ የሆኑትን የማጣራት ሂደት የመጀመሪያው ዙር በሳይንስ ማዕከሉ ከተከናወነ በኋላ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር የማጣራት ሂደቶች በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች እና በሚመለከታቸው አካላት የሚከናወን ይሆናል።

ለስኮላርሺፑ የማመልከት ሂደት ሴፕቴምበር 15 የተጀመረ ሲሆን እስከ ጃንዋሪ 15 የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።

በሩሲያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል የስኮላርሺፑ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ናድር መሃመድ " የራሺያን ስኮላርሺፕ እንዲሳካ እናደርጋለን እያሉ ብር የሚቀበሉ ኤጀንሲዎች እያየን ነው " ያሉ ሲሆን በስኮላርሺፑ ዙሪያ ህጋዊ ሰውነት ያለው እና የሚያስተባብረው የሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ብቻ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አተባባሪው አመልካቾች ለማማከር እና ለተጨማሪ መረጃ ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰአት ወደ ማዕከሉ በመደወል መረጃ በነጻ ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ለስኮላርሺፑ ለማመልከት መሟላት ያለባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው ?

ፓስፖርት አስፈላጊ ቢሆንም ስኮላርሺፑን ለማመልከት አስገዳጅ አይደለም።

በቀበሌ ወይም በፋይዳ መታወቂያ ማመልከት ይቻላል።

የአመልካቾች የ9 ፣ 10 ፣ 11 እና 12 የትምህርት ማስረጃቸው እንዲያስገቡ ይጠየቃል።

አሁን 12 ክፍል እየተማሩ ያሉ አመልካቾች እስካመለከቱበት ጊዜ ያለውን የትምህርት ማስረጃ አስገብተው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ደግሞ ሲደርስ መስገባት ይችላሉ።

ለማስተርስ አመልካቾች ዲግሪ እና ግሬድ ሪፖርት አስፈላጊ ነው (ዲግሪው ያልደረሰለት ቴምፖራሪውን ማስገባት ይችላል)።

ለፒ ኤች ዲ አመልካቾች የሪሰርች ፕላናቸው ምን እንደሆነ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን አስገዳጅ ባይሆንም ፕብሊሽ የተደረገ የጥናታዊ ጽሁፍ ቢኖራቸው ይመከራል።

ባለፈው አመት ስኮላርሺፑ የተሰጠው 50 በመቶ ለባችለር ዲግሪ ፣ 30 በመቶ ለማስተርስ ዲግሪ እና 20 በመቶ ለፒኤች ዲ ዲግሪ ቢሆንም ይህኛው ስኮላርሺፕ እንደ አመልካቹ ቁጥር ብዛት ፐርሰንቱን ሊሸጋሸግ ይችላል።

ጥሩ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች የመመረጥ እድላቸው ሰፊ ነው በመሆኑ ቢያመለክቱ ይመረጣል።

ጥሩ ውጤት የሌላቸው ተማሪዎች የስኮላርሺፑ የውድድር ሂደት የተማሪዎችን የትምህርት መረጃ በማስተያየት የሚከናወን በመሆኑ በአንዳንድ ትምህርቶች ጥሩ ውጤት ካላቸው ተማሪዎች የተሻሉ ሆነው ቢገኙ ባላንስ ስለሚያደርግ ማመልከት ይችላሉ።

ስኮላርሺፑን https://www.education-in-russia.com ሊንክ በመጠቀም ቋንቋውን ወደ እንግሊዝኛ በመቀየር ማመልከት ይቻላል።

ለተጨማሪ መረጃ ወደ ሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል በEmail - ethiopia@rs.gov.ru
ወይም n.mokhammed@eth.rs.gov.ru

እንዲሁም በስልክ ቁጥር 251 11 155 1343 ማግኘት ይቻላል።

@etconp
❤12
👉የመማክርት ጉባኤ ተመሰረተ

🚧የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት፣ ከሲቪክ ማህበራትና ከተገልጋይ ህብረተሰብ የተውጣጣ መማክርት ጉባኤ መስርቷል፡፡

የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ ፤ የመማክርት ጉባኤው መመስረቱ በተቋሙና በተገልጋይ መካከል ድልድይ በመሆን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በባለቤትነትና በጋራ አቅም መፍታት የሚቻልበትን ስርዓት ለመዘርጋት ትልቅ ሚና አለው ብለዋል፡፡

በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የአገልጋይነት መንፈስ በማጎልበት የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻልና እንዲዘምን የመማክርት ጉባኤው መመስረቱ እንደሚያግዝም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለፁት ፡፡

የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የመንገድ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መሐመድ አወል ሰይድ በበኩላቸው፤ የመማክርት ጉባኤው መመስረቱ ከተገልጋይ፣ ከሲቪክ ማህበራትና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመገናኘትና በመነጋገር የመንገድ ሀብቶችን ከጉዳት ለመጠበቅ እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡

የመማክርት ጉባኤ ማቋቋሚያ እና ትግበራ ሰነድ ያቀረቡት በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የተቋም ለውጥና ሲስተም ዲዛይን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ገብሬ እንደተናገሩት፤ መማክርት ጉባኤው በተቋማት የአገልግሎት አቅርቦትና በተገልጋይ ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችሉና የማስፈፀም አቅምን የሚያዳብሩ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማመንጨት ለመተግበር የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በምስረታው ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት፤ የመማክርት ጉባኤው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚሰራቸውን ስራዎች ይበልጥ ውጤታማና ተደራሻ ለማድረግ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳደግ እገዛ እንደሚኖረው ገልጸው፤ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም አረጋግጠዋል፡፡

በመጨረሻም ከባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ፣ ከባለድርሻ አካላት፣ ከሲቪክ ማህበራትና ከተገልጋዩ ህብረተሰብ የተወጣጡ ሰባት አባላት ያሉት የመማክርት ጉባኤ ተመስርቷል፡፡

@etconp
❤6
👉በግንባታ ሥራ ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችን በፍጥነት ሪፖርት ለማድረግ የሚያስችል የሞባይል መተግበሪያ ሥራ ሊጀምር ነው ተባለ

💫የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በግንባታ ቦታዎች ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን በፍጥነት ለመመዝገብና ለመቆጣጠር የሚያስችል የሞባይል አደጋ ጥሪ መተግበሪያ ማበልጸጉን አስታውቋል።

አዲሱ መተግበሪያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሱ አደጋዎችን ቁጥርና መንስኤያቸውን በተመለከተ የተደራጀና የጸዳ መረጃ ለመያዝ ያለመ ነው ተብሏል።

የባለስልጣኑ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ግንባታ ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈፃሚ በረከት ተዘራ (ኢ/ር) ከአሐዱ ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ መተግበሪያው በቀጣይ ሳምንት ይፋ ይደረጋል።

መተግበሪያው በግንባታ ቦታዎች ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን፣ የጉዳቱን መጠንና መንስኤውን በትክክል መመዝገብ የሚችል ሲሆን፤ ይህም በዘርፉ ያሉ የአደጋዎችን ምንነት በማረጋገጥ፣ መረጃን በዳታ ቤዝ ለማደራጀት ያስችላል ብለዋል።

መተግበሪያው ከብሔራዊ መረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመቀናጀት የበለጸገ ሲሆን፤ ይህ ትብብርም በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማሻሻል የሚያስችል የጋራ ሥራ መስራትን የበለጠ እንደሚያቀለው ኢንጂነር በረከት ገልጸዋል።

መሪ ሥራ አስፈፃሚው ለመተግበሪያው የተሰጠው የሙከራ ጊዜ ሁለት ዓመት እንደሆነ ገልጸው፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ መተግበሪያውን ተደራሽ የማድረግ ሥራ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

አክለውም፤ የትኛውም አስገንቢ አካል የሚገነባውን ሕንፃ አስቀድሞ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በማሳወቅ፣ በዘርፉ የሚስተዋሉ አደጋዎችንና የሚነሱ የጥራት ችግሮችን አስቀድሞ ማስቀረት እንደሚቻል ተናግረዋል። አስገንቢ አካላትም በባለቤትነት ስሜት ወደ ተቋሙ በመምጣት እንዲያመለክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via አሐዱ ሬዲዮ

@etconp
❤4
ጨረታ

ኢትዮጵያን ሄራልድ ጥቅምት 6 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤3👍1
ጨረታ

ኢትዮጵያን ሄራልድ ጥቅምት 6 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1
ጨረታ

ኢትዮጵያን ሄራልድ ጥቅምት 6 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1🔥1
ጨረታ

ኢትዮጵያን ሄራልድ ጥቅምት 6 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👏1
ጨረታ

ኢትዮጵያን ሄራልድ ጥቅምት 7 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍1
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥቅምት 7  ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥቅምት 7 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤6
ጨረታ

አዲስ ዘመን ጥቅምት 6 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤7👏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉የአስፓልት ጠርዝ ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ የማድረግ ሥራ

Asphalt Edge Protection


@etconp
❤10👏8👍4🙏1
👉Beam Design — Ultimate Strength Design (ACI 318) (Metric)

💫Design Inputs (Example):

⏺Span L = 4.00 m,Beam width b = 0.300 m, Overall depth D = 0.500 m, Effective depth d = 0.452 m,Slab thickness = 0.125 m, Tributary width = 2.00 m

⏺Unit weight RCC = 25 kN/m³,

⏺Live load on slab = 3.00 kN/m²,

⏺Finishes = 0.5 kN/m
⏺Concrete f'c = 30.0 MPa,
⏺Steel fy = 500.0 MPa

⏺Load factors: w_u = 1.2D + 1.6L (ACI)

⏺Strength reduction factors: φ_flexure = 0.9,

⏺φ_shear = 0.75

Step 1: Calculate Loads (per meter length of beam)

Self weight of beam = b × D × γ = 0.300 × 0.500 × 25 = 3.750 kN/m

Slab load on beam = slab_thickness × γ × Ls = 0.125 × 25 × 2.00 = 6.250 kN/m
Live load on beam = LL_slab × Ls = 3.00 × 2.00 = 6.000 kN/m

Dead load (DL) = Self weight + Slab load +

Finishes = 3.750 + 6.250 + 0.50 = 10.500 kN/m

Factored UDL w_u = 1.2×DL + 1.6×LL = 1.2×10.500 + 1.6×6.000 = 22.200 kN/m

Step 2: Compute Factored Moment and Shear (Simply Supported Beam, UDL)

Maximum factored moment Mu = w_u L² / 8 = 22.200 × 4.00² / 8 = 44.400 kN·m

Maximum factored shear Vu = w_u L / 2 = 22.200 × 4.00 / 2 = 44.400 kN

Step 3: Required Nominal Moment Capacity

Design moment Mu = 44.400 kN·m

Required nominal moment Mn = Mu / φ = 44.400 / 0.9 = 49.333 kN·m

Step 4: Compute Required Steel Area As (Singly Reinforced Rectangular Section)

Solved for As (closed form quadratic) → Required As = 221.8 mm² (≈ 0.000222 m²)
Recommended using 20 mm bars (area per bar ≈ 314.16 mm²) → Number of 20 mm bars = 1 nos

Step 5: Shear Check (Simplified ACI Approximation)

Approximate concrete shear capacity Vc = 126.261 kN

φ·Vc = 94.696 kN

Maximum factored shear Vu = 44.400 kN
Check: Vu <= φ·Vc → OK

Step 6: Reinforcement & Detailing Notes

1. Use selected tensile reinforcement As distributed in available bars, ensure clear cover andspacing.

2. Provide shear stirrups if Vu > φ·Vc; otherwise minimum shear reinforcement per ACI.

3. Check development length, anchorage, and serviceability (deflection, crack width).

4. Always run full ACI checks (interaction, torsion if present) and use appropriate safety factors.

📜Note: This worked example is illustrative and simplified. Use full ACI 318 procedures and software for finaldesign.

#BeamLoadCalculation
#USDMethod
#ACI318Design
#StructuralEngineering
#CivilEngineeringWorld
#EngineeringDesign
#StructuralDesignTips
#ConcreteBeamDesign
#UltimateStrengthDesign
#LoadCalculationStepByStep
#BeamAnalysis
#SiteEngineerGuide
#ConstructionEngineering

@etconp
❤28
👉በ14 ቢሊየን ብር የሚገነባው የዓለምገና - ቡታጅራ መንገድ ግንባታ እየተካሄደ ነው

💫ተቋራጩ የንኮማድ፣ የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን ኤ አይ ሲ ፕሮጀቲስፓ ከስትራይድ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ያከናውናሉ

🚧የኦሮሚያ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን የሚያስተሳስረው የዓለምገና - ቡታጅራ መንገድ ፕሮጀክት እየተካሄደ ነው።

የመንገድ ፕሮጀክቱ ወደ አዳዲ ማርያም ገዳም የሚወስደውን የ12.7 ኪሎሜትር መንገድ ጨምሮ በጥቅሉ 132.7 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲኾን፥ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል።


ከጥቂት ወራት በፊት የተጀመረው የመንገድ ግንባታው አሁን ላይ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ ቀበራ እንዲሁም የፉካ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው።

የመንገድ ፕሮጀክቱ በከተማ ክልል የብስክሌት እና የእግረኛ መንገድ፣ የአነስተኛ እና ከፍተኛ ከልቨርቶች  እንዲሁም የ16 ድልድዮች ግንባታ አካትቷል።

የመንገድ ግንባታውን የሚያከናውናው ሀገር - በቀሉ የንኮማድ ኮንስትራክሽን በርካታ ማሽነሪዎችን ወደ ሥፍራው በማንቀሳቀስ ፕሮጀክቱን ለማፋጠን እየሠራ ይገኛል።

የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን ኤ አይ ሲ ፕሮጀቲስፓ ከስትራይድ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ጋር በጥምረት ያከናውናሉ። ለመንገድ ግንባታው የተመደበው 14 ቢሊዮን ብር በፌደራል መንግስት በጀት የሚሸፈን መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታውቋል።


@etconp
❤13👍4
👉ዋጋ ማስተካከያ (Price Adjustment)

💫አዲሱ የፌደራል ግዥ መመሪያ ምን ይላል?

🚧ለግንባታ ግዥ 12 ወራት እና ከዚህ በላይ ለሚቆዩ የግንባታ ስራዎች ውሉ ተፈጻሚ መሆን ከጀመረበት ከስድስት ወራት በኋላ የዋጋ ማስተካከያ ይደረግላቸዋል።

⏺ከ12 ወራት በታች የሆኑ የግንባታ ስራ ውሎች የዋጋ ማስተካከያ አይደረግላቸውም።

🚧ስራ ተቋራጩ በውል ስምምነቱ መሰረት መስራት ላልቻላቸው እና ዘግይተው ለተሰሩ የግንባታ ሥራዎች የዋጋ ማስተካከያ ማድረግ የሚቻለው የግንባታ ሥራዎቹ መሰራት በነበረባቸው ወቅት በነበረው ዋጋ መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡

🚧ለምክር አገልግሎት ግዥ የሚደረግ የዋጋ ማስተካከያ ደግሞ 24 ወራት እና ከዚህ በላይ ለሚቆዩ ግዥዎች፣ ከ12ኛው ወር ጀምሮ የዋጋ ማስተካከያ ይደረጋል።

🚧በምክር አገልግሎት (Consultancy Services) ግዥ የውል አፈጻጸም ወቅት የአማካሪው ስህተት ባልሆነ ምክንያት የውል መፈጸሚያ ጊዜው በመራዘሙ ለአማካሪው የዋጋ ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን መ/ቤት ሲያምንበት የዋጋ ማስተካከያ ሊያደርግ ይችላል።

🚧6 ወራት እና ከዚያ በላይ ለሚቆይ በማዕቀፍ ስምምነት ለሚፈጸም ግዥ ደግሞ ውሉ ተፈፃሚ መሆን ከጀመረበት ከሶስት ወራት በኋላ ለሚኖረው የዋጋ ለውጥ ማስተካከያ ይደረጋል።

📍YouTube ቻናላችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ ገብተው Subscribe ያድርጉ👇🙏

https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO

@etconp
❤13👏1