Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
549 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉በ1ኛ እና 2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስራዎች :-

🚧342 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ፣

🚧185 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ መንገድ ፣

🚧241 ኪ.ሜ የሳይክል መንገድ ፣

💫101 የህፃናት መጫወቻዎች ፣

💫155 የስፓርት ማዘዉተሪያዎች ፣

💫153 ዘመናዊ ፓርኪንግ እና ተርሚናሎች ፣

💫210 የሕዝብ መፀዳጃዎች፣እንዲሁም ዘመናዊ የመንገድ መብራቶች፣በርካታ የህዝብ መገልገያ እና መዝናኛ ቦታዎች፣ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች፣ተገንብተዉ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

@etconp
❤5👍2
👉የአዲስ አበባ አሁናዊ የምሽት ገፅታ❤️

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤13
👉5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነጻ ስልጠናን ይከታተሉ!

💫የስልጠና ኮርሶች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ

🚧ስልጠናው የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የዲጂታል ክህሎቶችን በኦንላይን በማስተማር ከሚታወቀው ዩዳሲቲ ተቋም ጋር በመተባበር ነው፡፡

🏷ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

📜ስልጠናውን በስምንት ሳምንት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።

@etconp
❤10
👉ኤድናሞል አደባባይ እየተነሳ ነው

🚧ከብራስ ወደ አትላስና አካባቢው፣ እንዲሁም ከቦሌ ወደ 22 እና አካባቢው ለመጓዝ ለረጅም ዓመታት መተላለፊያ ሆኖ የቆየው ኤድናሞል አደባባይ እየተነሳ ነው።

💫ከብራስ ወደ አትላስ የሚወስደው እና ከኤድናሞል ወደ ጎላጎል የሚወስደው መንገድ እየተሰራ ይገኛል።

Via አዲስአበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

@etconp
❤6👍5😢2
👉የቦሌ ኤድናሞል - 22 የመንገድ ግንባታ በራስ ኃይል እየተከናወነ ይገኛል

🚧የእንግሊዝ ኤምባሲ - ድንበሯ ሆሲፒታል  - ጎላጎል አደባባይ - ቦሌ ኤድናሞል የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ አካል የሆነው እና ከኤድናሞል ወደ 22 የሚወስደው  የመንገድ ግንባታ በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የራስ ኃይል እየተገነባ ይገኛል፡፡

💫ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ቀደም ሲል በቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዓለም ባንክ በተገኘ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ የግንባታ ስራው የተጀመረ ቢሆንም፤ በተለያዩ ምክንያቶች የግንባታው ሥራ በተፈለገው ፍጥነት ሳይፈፀም ቆይቷል።

⭐️ይሁን እንጂ መንገዱ ካለው ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት እና የከተማ ገፅታ ፋይዳ አንፃር፤ የግንባታ ሥራውን ለማፋጠን ከኤድናሞል ወደ 22 ጎላጎል የሚወስደው የመንገዱ ክፍል በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የራስ ኃይል መንገድ ግንባታ እየተሰራ ይገኛል፡፡

📍ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 2 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ25-30 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ፤ ከእንግሊዝ ኤምባሲ ወደ 22 የሚወስደው የመንገዱ ክፍል ደግሞ በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየተገነባ ይገኛል፡፡

⏺በአሁኑ ወቅት ከኤድናሞል እስከ ጎላጎል አደባባይ ድረስ በሚገነባው መንገድ የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ እና ተያያዥ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ በተያዘው በጀት ዓመት የአስፋልት ማንጠፍ ስራውን በማጠናቀቅ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በመሰራት ላይ ነው፡፡

@etconp
❤6👍3