Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
549 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉Request for Expressions of Interest, Selection of Consulting Services for Procurement assistance, Construction Supervision and Contract Administration Cool Port Addis –Phase 1 Project.

💫(Cold Storage Warehouse Construction and operationalization at Modjo Dry Port Cool Port.

🚧Ethiopian Maritime Authority (EMA)

@etconp
❤1
👉በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር በጀርመን አደባባይ አካባቢ በ9 ወራት ውስጥ 832 ቤቶች የተገነቡ መሆኑ ተገልፆል።

💫ቤቶቹ የተገነቡት 1.7 ሄክታር በሆነ ቦታ ላይ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የሕንፃዎቹ ብዛት 16 ይደርሳል።

🚧በጠቅላላው በነዚህ ሕንፃ ውስጥ የሚገኙት 832 ቤቶች ናቸው፣ ከእነዚህ 800 የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ፦ ባለ አንድ መኝታ ቤት 403፣ ባለ ሁለት መኝታ ቤት 197 እና ባለ ሶስት መኝታ ቤቶቹ ደግሞ 200 ብዛት ሲኖራቸው የተቀሩት 32ቱ ደግሞ የንግድ ቤት መሆናቸው ተጠቁሟል።

@etconp
❤5👍1
👉ቻይናዎችን Sunrise Kempinski ሆቴል ብለው ይጠሩታል፤ ባለአምስት ኮከብ ቅንጡ ሆቴል ሲሆን፣ መገኛውም በዋና ከተማዋ ቤጂንግ ውስጥ ነው❤

ከሁሉም በላይ የሆቴሉ ኪነ ሕንፃ አስደማሚ ነገሮችን ያካተተ ነው። ሕንፃው የፀሐይ መውጣትን ለማሳየት የሚያስችል የኪነ ሕንፃ ቅንብርን የተላበሰ ከመሆኑም በላይ፣ ሕንፃው የተገነባበት ቦታ ተፈጥሯአዊ፣ በተራሮች የተከበበ እና Yanqi Lake ተብሎ በሚጠራው የባህር ዳርቻ መገኘቱ ውበቱን እና ተፈላጊነቱን ጨምሮለታል።


💫ሆቴል የጎልፍ፣ የቴኒስ ሜዳዎችን እና የአካል ብቃት ማዕከላት ያሉትም በመሆኑ ብዙዎች አካባቢውን ለቢዝነስ ሥራዎች እና ለመዝናናት ይመርጡታል።

🚧በአቅራቢያውም ታሪካዊውና በቱሪስቶች የሚወደደውና የሚጎበኘው ጥንታዊው የቻይና ግንብ ስለሚገኝ ይህን ሆቴል የበለጠ ተወዳጅ እንዲሆን አድርጓታል።

@etconp
❤7👍2
👉በሪል ስቴት ልማት እና ግብይት ላይ የሚሰጡ የተለያዩ አሳቦች።

💫የሪል እስቴት ኢንቨስትመንትና ወቅታዊ የገበያ ሁኔታን አስመልክቶ የሚሰጡ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ  ይሆንና የገበያ፣የኢኮኖሚ፣ ቴክኖሎጂ፣የህግና መመሪያ፣ እጥረት ፣ ኢንቨስትመንት፣የግንባታ ይዘትን፣ የዋጋ ዕድገና ሌሎች ከንብረት ግመታ  (ቫሉዌሽን) ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ፣ተተግባሪነቱን፣ የግንባታ ጥራትን፣ የቤት መሰረታዊ ፍላጎትነትን....ያላገናዘበ ይሆንና ያሳስታል።

ሌላ ምሳሌ:- መሃንዲሶችና አርኪቴክቶች አስተያየት ሲሰጡ በቶሎ መገንባትን የግንባታው ጥራትን፣ የግንባታ ቴክኖሎጂን  ጠቅሰው ግዙና አትግዙ ሊሉ ይችላሉ ። ነገር ግን የገበያና የፋይናንስ ሁኔታ ፣ የህግና ኢኮኖሚ፣ የኢንቨትመንት ፣ የወለድ ምጣኔን ...ያላገናዘበ ይሆንና አሳሳች ውሳኔ ሊያሰጥ ይችላልን

ደግሞ ሌላ ምሳሌ:- የሽያጭ ሰራተኞች የሚሰጡት አስተያየት በብዛት መሸጥ ይሆንና ገዢም ሆነ ሻጭ ትክክለኛ እውነታን ሳይመለከቱ በተስፋ ተሞልተው አየር ሊያስጨብጡ ይችላሉ። በተቃራኒው የህግ አማካሪን ብቻ አማክሮ ለመግዛት መሞከር በውል ይዘት ላይ ያተኮረ ከፍተኛ  መጠራጠርን ያበዛና ስምምነት ሊርቀው ይችላል።

እና ምን ይሻላል?

መልሱ አጭርና ግልጽ ነው። በሪል እስቴት ጉዳይ ውስጥ አማካሪ የሚሆን የትኛውም ባለሙያ በዘርፉ ውስጥ ሙያዬ ስለሚለው ስለ አንዱ ጉዳይ ጥልቅ እውቀት ሊኖረው ሲገባ ከሙያዊ ጥልቅ እውቀቱ ባሻገር በሌሎቹ ዘርፎች መጠነኛ እውቀት ሊኖረው ይገባል።

ለምሳሌ የፋይናንስ ባለሙያ ከሆነ በዘርፉ የሚጠቅመውን የህግና መመሪያዎች፣ የግንባታ ሂደት፣የገበያ ሁኔታ፣ የግብይት ውል ይዘት ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ዲዛይን..መጠናኛ እውቀት ሊኖረው ይገባል። ሌሎቹም እንደዛው....

በአንድ እውቀት ምክር ሃሳብ በማቅረብ ገበያውን ባለመረበሽ እንተባበር።

Via ደሳለኝ ከበደ:-መሀንዲስ እና ሪል ስቴት ልማት አማካሪ እና አሰልጣኝ

@etconp
👍4❤2
👉የተዳከመው የሙያ ምሰሶ

⭐️የምህንድስና ተስፋ እና የገበያ ተግዳሮቶች

🏗​የኢትዮጵያ ኢንጂነር ታሪክ የትልቅ ህልም እና የከባድ እውነታ ውህደት ነው። ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ማንም የማይፈልገው ስራ ማግኘቱ በራሱ እጅግ አድካምና ተስፋ አስቆራጭ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል።

📌 በልዩ ትጋት ዩኒቨርሲቲ ገብተው፣ ከባድ የትምህርት ዘመንን ጨርሰው፣ ቤተሰብ "የአገር ምሰሶ" ይሆናል ብሎ የጠበቀው ምህንድስና፣ ዛሬ በሙያው ገበያ ውስጥ ተገቢውን ቦታና ዋጋ በማጣት ተስፋ የመቁረጥ አደጋ ተጋርጦበታል።

​➀. የቤተሰብና የአገር ተስፋ መናድ

📌​የአምስት ዓመታት ዋጋ:

✍️ኢንጂነሪንግ ቀላል ሙያ አይደለም። ተማሪዎች ለሚሰጡት አምስት ዓመታት ጥልቅ ትኩረት፣ ለሚያወጡት ጊዜና ለሚያሳልፉት ትጋት፣ ቤተሰብ የሚጠብቀው የኢኮኖሚ ነፃነት እና ማኅበራዊ ክብር ነው።
📌ይህ ተስፋ በሥራ ዕድል እጦት ወይም በዝቅተኛ ደመወዝ ሲመክን፣ በቤተሰብና በምሩቁ ላይ የሚደርሰው የሥነ-ልቦና ጫና ከፍተኛ ነው።

➁ ​የአገር ሀብት ብክነት:

🔨በሺዎች የሚቆጠሩ ምሩቃን ሥራ ሲያጡ፣ አገር በነሱ ትምህርት ላይ ያፈሰሰችው ከፍተኛ የመንግሥት ገንዘብና ጊዜ ከንቱ ይሆናል።
ምሁር ኃይል ወደ ውጤት ሳይለወጥ መቅረቱ የአገርን የዕድገት ፍጥነት ይገታል።

​➂. "ያለ ቦታው መኖር" እና የሱስ አደጋ

📌 ​የሙያ መፈናቀል:

🔨ብዙ ኢንጂነሮች ተገቢውን የሥራ መስክ ሲያጡ፣ ቤተሰብን ለመርዳት ወይም ኪራይ ለመክፈል ሲሉ በዝቅተኛ ደመወዝ ወይም ከሙያቸው ጋር ባልተገናኘ ሥራ ለመቀጠር ይገደዳሉ። በተማረበት ሙያ ቀጥተኛ ግንኙነት ባለው ቦታ የሚሰራው ስንቱ ነው በሀገራችን
የሚያገኘውስ እራሱን ለማስተዳደር ፈተና የሆነበት የጓዳችን ችግር የሚታወቅ ነው።

📌 ​የሥነ-ልቦና ቀውስና ሱስ:

🔨የትጋትና የልፋት ውጤት በገበያ ውስጥ ዋጋ ሲያጣ፣ ምሩቃኑ ተስፋ የመቁረጥ፣ የመንፈስ ጭንቀት እና በከፋ ሁኔታ ደግሞ ወደ ሱስ የመሸሽ አደጋ ይገጥማቸዋል። ይህ በሙያው ብቃት ላይ ብቻ ሳይሆን በግለሰቦች ሕይወት ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል።

ለችግሩ መፍትሔዎች

📌​ይህንን ምህንድስና ችግር ለመፍታት ባለ ብዙ አቅጣጫ ያለው ጥረት ያስፈልጋል።

➀ ​የገበያ እና የትምህርት ትስስር:

📌ዩኒቨርሲቲዎች ከትልልቅ የግንባታ እና የኢንዱስትሪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሥልጠና (Internship) ፕሮግራሞችን ማስፋት እና የትምህርት ይዘታቸውን ከገበያው ፍላጎት ጋር በማጣጣም ተመራቅዎች የስራ ዕድል የማያገኙበት መንገድ መፍጠር አለባቸው።

➁ ​ምህንድስና ሙያ የሚመጥን ተገቢ ዋጋ ማሻሻያ :

📌 የመንግሥትና የሙያ ማህበራት ተባብረው የምህንድስና አገልግሎትን ዝቅተኛ የደመወዝ ስኬል በሕግ እንዲያስከብሩ ያስፈልጋል። ይህም የባለሙያውን ክብር እና የኑሮ ደረጃ ያሻሽላል። ልሰመርበት ይገባል!!

➂ ​የራስ ሥራ ፈጠራ (Entrepreneurship):

📌 ምሩቃን ከትልልቅ ድርጅቶች ሥራ ከመጠበቅ ይልቅ፣ በትንንሽ አማካሪነት (Consultancy) ወይም construction (በኮንስትራክሽን) ድርጅቶች እንዲደራጁ የብድር የሥልጠናና የስራ ዕድሎችን በማመቻቸት እራሳቸውን እስኪችሉ መደገፍ ።

⓸ ​በቴክኖሎጂ ላይ ማተኮር:

📌 መንግሥት እንደ ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣ ጂኦማቲክስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ባሉ የላቁ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ፣ ኢንጂነሮች ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ዋጋ ወደሚያገኙበት ዘርፍ እንዲገቡ መደገፍ አለበት።

🏷​በመጨረሻም

⏺ለኢንጂነሩና ለቤተሰቡ ተስፋው መመለስ የሚችለው በሙያው ጥራት ላይ መደራደር ሲቀር እና ለትጋት ተገቢው ዋጋ ሲሰጥና የስራ ዕድል ስመቻች ብቻ ነው የሙያው ህልውናን ከአደጋ መከላከል የሚቻለው።

⏺የኢትዮጵያ ልማት ያለ ኢንጂነሮቿ አይሳካም፤ ስለዚህ የኢንጂነሮቿን ተስፋ መታደግ የሁሉም ሰው ግዴታ ነው።

@etconp
❤29👍4
ADVERTISMENT

ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤1
👉የግዥ እና የኮንትራት አሰጣጥ ስርዓት ዓይነቶች

➀ Force Account

📌 የግንባታ ፕሮጄክት አቅርቦት ዘዴ ሲሆን ባለቤቱ ወይም ባለጉዳይ የግንባታውን ሂደት ከግለሰብ ነጋዴዎችና አቅራቢዎች ጋር በመዋዋል በቀጥታ የሚመራበት ነው።

📌 ይህ አካሄድ ደንበኛው በፕሮጀክቱ ላይ የበለጠ ቁጥጥር እንዲኖረው ያስችለዋል ምክንያቱም የሥራ ተቋራጮችን መምረጥ እና የሥራውን አፈፃፀም መቆጣጠር ይችላሉ::

📌 የግዳጅ መለያ ፕሮጄክቶች በተለምዶ ለአነስተኛ ፕሮጀክቶች ወይም ፈጣን ጥገና ወይም የጥገና ሥራ በሚፈልጉበት ጊዜ ያገለግላሉ።

➁. Design Bid Build (DBB)

📌ዲዛይኑ በአማካሪ ተጠናቆ፣ የግንባታው ኮንትራት በጨረታ ለአንድ ተቋራጭ የሚሰጥበት አሰጣጥ ስልት ነው ።

DBB ባህላዊ የፕሮጀክት ማስረከቢያ ዘዴ ሲሆን ፕሮጀክቱ በሦስት የተለያዩ ክፍሎች ማለትም ዲዛይን፣ ጨረታ እና ግንባታ ይከፈላል።

📌በዚህ አቀራረብ ባለቤቱ የፕሮጀክት እቅዶችን ለማዘጋጀት አርክቴክት ወይም የንድፍ ቡድን ይቀጥራል, ከዚያም የግንባታ ተቋራጮች ሀሳቦችን እንዲያቀርቡ ጨረታ ይወጣል::

📌ዝቅተኛው ተጫራች አብዛኛውን ጊዜ ኮንትራቱን ይሰጣል, እና ዲዛይኑ እንደተጠናቀቀ ግንባታው ይጀምራል::

📌ይህ ዘዴ በተለምዶ ለሕዝብ ፕሮጀክቶች ወይም ባለቤቱ በንድፍ እና በግንባታ ሂደት ላይ የበለጠ ቁጥጥር እንዲኖረው ሲፈልግ ጥቅም ላይ ይውላል.

➂ .Design Build

📌ዲዛይኑን እና ግንባታውን በአንድ ኮንትራት ለአንድ ተቋራጭ የሚሰጥበት ዘዴ ነው።
📌የዲዛይን ግንባታ (ዲቢ) ወይም ተርንኪ፡ ዲዛይን ግንባታ የፕሮጀክቱን ዲዛይንም ሆነ ግንባታ ለማስተናገድ ባለቤቱ ከአንድ አካል ጋር በቀጥታ የሚዋዋልበት የፕሮጀክት አቅርቦት ዘዴ ነው።
📌ይህ አካሄድ የንድፍ-ግንባታ ቡድን ለሁሉም የፕሮጀክቱ ገፅታዎች ኃላፊነት ያለው እና ወጪ ቆጣቢ መፍትሄዎችን ለማግኘት በትብብር መስራት ስለሚችል ሂደቱን ያመቻቻል::

📌ተርንኪ የዲዛይን-ግንባታ ቡድን የተጠናቀቀውን ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ እና የማስኬድ ሃላፊነት ያለበት ተመሳሳይ አካሄድ ነው።

📌የዲዛይን ግንባታ እና የማዞሪያ ዘዴዎች ብዙውን ጊዜ ፈጣን ግንባታ ለሚፈልጉ ፕሮጀክቶች ወይም ባለቤቱ ለጠቅላላው ፕሮጀክት አንድ ነጠላ የመገናኛ ነጥብ ሲፈልጉ ያገለግላሉ።

⓸.Finance / Build Operate Transfer (BOT)

📌 በዘመናዊ የኮንትራት አሰጣጥ እና በተለይም በትላልቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ውስጥ ወሳኝ የሆነ ዘዴ ነው።
📌Build-Operate-Transfer (BOT) በዋነኛነት በመንግሥትና በግል ባለሀብት ሽርክና (Public-Private Partnership - PPP) ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል የኮንትራት ዓይነት ነው።

📌Build (B)- ድርጅቱ የፕሮጀክቱን ዲዛይን ያወጣል፣ የገንዘብ ምንጭ ያሰባስባል እንዲሁም ግንባታውን ሙሉ በሙሉ ያጠናቅቃል።

📌operate (O) - ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ የግል ድርጅቱ ለተወሰነ ጊዜ (ለምሳሌ ከ15 እስከ 30 ዓመት) ፕሮጀክቱን ያስተዳድራል፣ ያስኬዳል (ይሠራል) እንዲሁም ጥገና ያደርጋል።

📌Transfer (T)- በፈቃዱ ‎የተወሰነው ‎ሲጠናቀቅ፣ ‎የግል ‎ድርጅቱ ‎ፕሮጀክቱን ‎(ለምሳሌ ‎መንገዱን፣ ‎የኃይል ‎ማመንጫውን) ‎ሙሉ ‎በሙሉ ‎በመልካም ‎ሁኔታ ‎ለመንግሥት ‎(ለህዝብ) ‎ክፍያ ‎ያስተላልፋል።

👉 የግል ባለሀብቱ በግንባታ ላይ ያፈሰሰውን ከፍተኛ ካፒታል እና የአሠራር ወጪውን የሚመልሰው እንዲሁም ትርፍ የሚያገኘው በአሠራር (Operate) ምዕራፍ ውስጥ ነው።
👉👉የተጠቃሚ ክፍያ (Tolls/Fees): ፕሮጀክቱ ገቢ የሚሰበሰብበት ከሆነ (ለምሳሌ አድስ አበባ አዳማ ፈጣን የክፍያ መንገድ/Toll Road፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ) የግል ድርጅቱ በዚያ ጊዜ ገቢውን በመሰብሰብ ኢንቨስትመንቱን ይሸፍናል።
👉ፕሮጀክቱ በቀጥታ ለህዝብ አገልግሎት የሚውል ከሆነ (ለምሳሌ የውሃ ተቋም) መንግሥት ፕሮጀክቱ ለአገልግሎት ዝግጁ እስከሆነ ድረስ ለግል ድርጅቱ ቋሚ ክፍያ ይፈጽማል።

5.Construction / Facility management Consultancy
📌ደንበኛው የፕሮጀክቱን አመራር ለባለሙያ በመስጠት፣ የግንባታ ሥራውን ግን ለተለያዩ ንዑስ ተቋራጮች (Sub-contractors) የሚሰጥበት ዘዴ።

📌 የኮንስትራክሽን/ፋሲሊቲ አስተዳደር አማካሪ፡ የግንባታ እና የፋሲሊቲ አስተዳደር አማካሪ አገልግሎቶች በግንባታው ሂደት ውስጥ ሙያዊ እና ድጋፍ ለመስጠት የሶስተኛ ወገን አማካሪ መቅጠርን ያካትታል።

📌ይህ እንደ የፕሮጀክት አስተዳደር፣ የወጪ ግምት፣ የጊዜ ሰሌዳ አወጣጥ፣ የጥራት ቁጥጥር እና ከግንባታ በኋላ ያሉ አገልግሎቶችን ሊያካትት ይችላል።

📌የግንባታ እና የፋሲሊቲ አስተዳደር አማካሪዎች ባለቤቶቹ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውን ውስብስብነት እንዲዳስሱ እና ፕሮጀክቶች በጊዜ እና በበጀት እንዲጠናቀቁ ያግዛሉ::

6.Alliances and Outsourcing

📌Alliance and Outsourcing በተለያዩ ኩባንያዎች ወይም ድርጅቶች መካከል በፕሮጀክት ላይ ተባብሮ ለመስራት ወይም የተወሰኑ የስራውን ገፅታዎች ለማስተላለፍ የሚደረጉ ሽርክናዎችን ያመለክታሉ።

📌ትላልቅ እና ውስብስብ ፕሮጀክቶችን ለመውሰድ ተጓዳኝ ችሎታዎች ወይም ሀብቶች ባላቸው ኩባንያዎች መካከል ጥምረት ይፈጠራል።

📌የውጪ አቅርቦት ከሶስተኛ ወገን ሻጭ ጋር የተወሰኑ ተግባራትን ወይም አገልግሎቶችን እንደ ዲዛይን፣ ግንባታ ወይም የፋሲሊቲ አስተዳደርን ማስተናገድን ያካትታል።

📌ጥምረት እና የውጭ አቅርቦት ኩባንያዎች ወጪዎችን እንዲቀንሱ፣ ቅልጥፍናን እንዲያሻሽሉ እና ልዩ ባለሙያተኞችን እንዲያገኙ ሊረዳቸው ይችላል።

@etconp
❤12👍1
👉JOB VACANCY

⭐️Head of Contract Administration (MEP)

#atta_trading_plc

#Addis_Ababa


🚧BSc Degree in Construction Management, Civil Engineering or in a related field of study with relevant work experience, out of which 2 years must have been in a senior/head of contract administration role.

📜Duties and Responsibilities:

- Lead the contract administration function for building‐construction projects (particularly G+15 and above), ensuring all contracts, subcontracts, variations and amendments are properly prepared, executed, monitored and closed out.
- Review, draft and negotiate contract documents (main contracts, subcontracts, procurement contracts) in line with project scope, timelines, budgets and building construction standards.
- Maintain and enforce contract change‑control procedures: evaluate change orders, variations, extensions of time, claims and ensure all are documented, approved and tracked.

⏺Quanitity Required: 1

⏺Minimum Years Of Experience: #5_years

⚡️Deadline: November 15, 2025

📩How To Apply: Submit your application and CV along with supporting documents Via email:attatradingplc@gmail.com

❇️Please ensure the subject line of your email clearly states the position you are applying for: “Head of Contract Administration”.

⏺Note: Experience in road construction will not be considered for this role.

@etconp
❤7
👉Variation and Supplementary work

📌ማንኛውም variation እና supplementary work ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 70/2017 አንቀጽ 31 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ንዑስ አንቀጽ 2 ድንጋጌዎችን ተከትሎ መፈፀም እንደሚገባ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።

🚧 መመሪያ ቁጥር 70/2017

⏺አንቀጽ 31(1)፡-በቀጥታ የሚፈፀም ግዥ ቅድመ ሁኔታዎች

⏺አንቀጽ 31(2)፡-ቀጥታ የሚፈፀም ግዥ አፈፃፀም ሥርዓቶች

🔨ቅድመ ሁኔታዎች መካከል የተወሰኑትን ለመግለጽ እንሞክራለን።

✍️አስቸኳይ ከመሆኑ የተነሳ በሰውና በንብረት ላይ ችግር የሚያስከትል ስለመሆኑ በማስረጃ መረጋገጥ ይኖርበታል።

✍️ስራው ተነጥሎ ሊያሰራ የማይችል ስለመሆኑ አሳማኝ ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል።

✍️ቀደም ሲል በግልጽ ጨረታ የተፈፀመ መሆን ይኖርበታል።

✍️ቀደም ሲል በአከባቢ ጨረታ ማስታወቂያ የተፈፀመ መሆን የለበትም።

✍️በዚህ መንገድ ካልተፈፀመ የመ/ቤቱን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚጎዳ መሆኑ በማስረጃ መረጋገጥ አለበት።

✍️ግዥውን በዚህ የግዥ ዘዴ መፈፀም ያስፈለገበት አሳማኝ ምክንያት መቅረብ ይኖርበታል።

✍️ግንባታ ሥራ በሚሆንበት ጊዜ የዋናው ውል ከ30% በላይ መሆን የለበትም።

✍️ከግንባታ ሥራ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ የዋናው ውል ከ25% በላይ መሆን የለበትም።

✍️አቅራቢው/ሥራ ተቋራጩ/ ብቸኛ መሆኑ መረጋገጥ አለበት።

✍️የግዥ ፈፃሚውን መ/ቤት ስምና አድራሻ፣ ዋና ዋና የውል ቃላትና ሁኔታዎች አጭር መግለጫ፣ የሚፈፀመውን ግዥ ዓይነት፣ ብዛት፣ የአቅርቦት ቦታ እና ግዥ እንዲጠናቀቅ የሚፈለገበትን ጊዜ የሚገልጽ ማስታወቂያ አገራዊ የስርጭት ባለው ጋዜጣ ቢያንስ አንድ ጊዜ ታትሞ መውጣት አለበት።

✍️የአደራዳሪ ኮሚቴ እና የአፅዳቂ ኮሚቴ ቃለ ጉባኤ መኖር አለበት።

✍️ሙሉ ሪፖርትን የያዘ መግለጫ ለግዥ ኤጀንሲ መቅረብ አለበት....ወዘተ።

@etconp
❤6👍3
👉JOB VACANCY

⭐️architect

📍አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ
⏺የሥራ ዓይነት: On-site - Permanent (Full-time)
⚡️ቀነ ገደብ: November 16, 2025
⏺ክፍት የስራ ቦታዎች: 2
⏺የትምህርት ደረጃ: Bachelors Degree

📜የሥራ መግለጫ

⏺Junior/ senior architect
We are seeking a highly motivated Junior Architect and skilled Architect with approximately 1 years of professional experience to join our growing landscape design team.

⏺The senior architect ideal candidate will be a design-oriented professional with a strong technical background of projects and a proven ability to manage project components.

🎲Key Responsibilities

⏺Modeling and rendering is a basic for both junior and senior architect.
⏺Also time management is a key
⏺Utilize strong problem-solving skills to address design and technical challenges.
⏺Contribute to a collaborative and positive office culture.

🏷Qualifications & Experience

❇️Required:Minimum BSc. in Architecture. For both Junior and senior architect.

⏺1+ years of  experience in an architectural practice for senior one.
⏺Proficiency in Revit and Lumion is mandatory; experience with AutoCAD, SketchUp, and Adobe Creative Suite is strongly preferred.
⏺Strong portfolio mainly focused on landscape projects or projects which have landscape integrations.
⏺Proven ability to work both independently and collaboratively in a team environment.

📩How to Apply
⏺Interested candidates should submit with the subject line "Landscape Architect Application - [Your Name]":
we appreciate if your location is around Ayat or near to Ayat 
📩send your portfolio to@kalopia

📍የሥራ አድራሻ:-Ayat around kibr demena

@etconp
❤1🙏1
👉ኮንትራክተር ለመሆን የሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነገሮች!

🚧1. ህጋዊ መዝገቦች እና ፈቃዶች

ሀ. የንግድ ምዝገባ (Business Registration)

➣ከፌዴራል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ወይም ከክልል ንግድ ቢሮ የንግድ ስም ማረጋገጫ ማግኘት።
➣ የዕውቅና ማረጋገጫ ማግኘት (ለማኅበር፣ ለኩባንያ፣ ወዘተ)።
➣ ታክስ መለያ ቁጥር (TIN) ማግኘት።

ለ. የግንባታ በቂነት ፈቃድ (Contractor's License)
➣ይህ በኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊ ነው። ከሚገባው አካል ማግኘት አለቦት።
➣በአሁኑ ጊዜ የግንባታ ፈቃድ ከ የኢትዮጵያ ግንባታ ኮንትራክተሮች ማኅበር (ECCA) ይሰጣል።
➣ፈቃዱ በደረጃ (Grade) ይሰጣል (ለምሳሌ GC/BC 1-9)፣ ይህም የሚሠራባቸውን ፕሮጀክቶች መጠን እና ዓይነት ይወስናል።

🚧2. የሙያ ብቃት እና ተሞክሮ

ሀ. ትምህርት እና ሙያዊ ማረጋገጫ
➣ቢያንስ ዲፕሎማ ወይም ባችለር ዲግሪ በግንባታ፣ ሲቪል ምህንድስና፣ አርክቴክቸር ወይም በተዛማጅ ዘርፍ ማግኘት።
➣ የሙያ ልምድ (ተሞክሮ) ማስረጃ።

ለ. የሙያ ማኅበር አባልነት
➣በ የኢትዮጵያ ግንባታ ኮንትራክተሮች ማኅበር (ECCA) አባል መሆን በጣም ጠቃሚ ነው።
➣ ይህ የንግድ ዕድሎችን፣ የስልጠና እድሎችን እና የፕሮጀክት መረጃዎችን ለማግኘት ይረዳል።

🚧3. ፋይናንስ እና ካፒታል

ሀ. የፋይናንስ ብቃት
➣የመጀመሪያ ካፒታል (መዋጮ)።
➣የባንክ ማረጋገጫ።
➣ የፋይናንስ መግለጫ (በፕሮጀክት ላይ የሚውል ገንዘብ እንዳለ ለማሳየት)።

ለ. የኢንሹራንስ (Insurance)
➣ የሶሻል ኢንሹራንስ።
➣የሥራ አጥነት ኢንሹራንስ (Third Party Insurance)።

🚧4. የሥራ አመራር እና ቡድን

ሀ. የሙያ እውቀት ያላቸው ሠራተኞች

➣ (Forman)
➣ (Skilled Workers)
➣(Supervisors)

ለ. የሥራ መሳሪያዎች

➣ መሠረታዊ የግንባታ መሳሪያዎች መኖር (ወይም ማቅረብ የሚችል መሆን)።

🚧5. ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች

ሀ. የግንባታ ሥራ ልምድ (Portfolio)
➣ቀደም ሲል የሠራቸውን ፕሮጀክቶች ማስረጃ (ፎቶ፣ ማመሳከሪያ፣ ወዘተ)።

ለ. የግብር አበል (VAT Registration)

➣ለትላልቅ ፕሮጀክቶች የግብር አበል ማድረግ ያስፈልጋል።
ሐ. የአካባቢ አስተዳደር ፈቃዶች
➣ከከተማ አስተዳደር ወይም ከቀበሌ ፈቃድ ማግኘት።

@etconp
❤16👏1
👉በግንባታ obsession ክፉኛ የተያዘችው ቻይና 45 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው አዲስ ማሳለጫ ገንብታ አጠናቃለች

ማሳለጫው በማዕከላዊ ቻይና የምትገኘውን ሁቤይን ከሄናን ከተማ ጋር የሚያገናኝ ነው፤


💫43 ድልድዮች እና አንድ የዋሻ ውስጥ መንገድ ያለው አዲሱ ማሳለጫ፦ በሁለት በኩል አራት አራት መኪናዎችን ሊያስተላፍ የሚችል ከመሆኑም በላይ ከዚህ በፊት ሁለት ሰአት የሚወስደውን ጊዜ ወደ 50 ደቂቃ የሚያሳጥር እንደሆነ ታውቋል።

@etconp
❤8
👉Vacancy Announcement

🕹Job Summary:

⏺We are seeking a qualified Site Engineer with solid experience in landscape construction and supervision to join our project team. The candidate will be responsible for overseeing day-to-day site operations, ensuring quality workmanship, proper material usage, and timely execution of landscape works in accordance with approved drawings and specifications.

📜Key Responsibilities:

-Supervise and coordinate landscape construction activities on site.
-Review drawings and ensure accurate implementation.
-Monitor work progress, quality, and compliance with safety standards.
-Prepare daily and weekly site reports.
-Coordinate between the consultant, client, and subcontractors.
-Verify materials and workmanship according to project standards.
-Support testing, inspection, and handover documentation.

⭐️Qualification & Experience:

-Bachelor’s Degree in Civil Engineering, or related field.
-Minimum 3 years of proven experience in landscape or infrastructure works.
-Strong technical knowledge in irrigation, paving, softscape, and site finishing
-Good communication and report writing skills.
-Ability to work under pressure and manage multiple activities on site.

📌Application Deadline: Nov 15,2025

📩How to Apply: Interested applicants are invited to send their CV and cover letter to @natanabiy with the subject line “Site Engineer – Landscape Project.”

@etconp
❤5🙏1
ጨረታ

አዲስ ዘመን ህዳር 1 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2