Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
549 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ዋና ጽሕፈት ቤቱን ወደ ቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሕንፃ አዘዋወረ‼️

💫ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አዲሱን ዋና መስሪያ ቤት ጎብኝተው የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል፦

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ዋና ጽሕፈት ቤቱን ቀድሞ ከነበረበት በመለወጥ መሃል ከተማ ወደ ቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሕንፃ አዛውሯል።

በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ አስደናቂ የግንባታ ለውጥ እና ዘመናዊ የመሥሪያ ሥፍራ ጥበብን በማሳየት ለሠራተኞቹ እጅግ ምቹ የሆነ ስፍራንም መፍጠር ችሏል።

ተቋሙ በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሕይወታችንን በፍጥነት በመቅረጽ ውስጥ ያለውን ስፍራ በሚያንፀባርቅ እና ሀገራችንም በዚህ አለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር በንቁነት መሳተፏን በሚያረጋግጥ መንገድ ከፍታ ላይ ደርሷል።

ኢንስቲቲዩቱ በጤና፣ በግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ እያደረገ ያለው የመሪነት አስተዋፅኦውን እየተወጣ ሲሆን በክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ትላልቅ የመረጃ ቋቶች፣ የመረጃ ፍለጋ፣ ሮቦቲክስ እና ኢመርሲቭ ቴክኖሎጂዎች አቅሙን በማጎልበት ላይ ይገኛል።

በቅርቡ የተጀመረው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስታርት አፕ መዐከል ደግሞ ይኽንን ከባቢ የበለጠ ያጠናክረዋል።

ዜጎች ሀሳብ ብቻ ይዘው በመምጣት ፕሮቶታይፕ ለመፍጠር፣ ለማባዛት ብሎም ከግሉ ዘርፍ ኢንቬስተሮች ጋር እንዲገናኙ እድል ያመቻቻል። እስከ አሁን 200 ሀሳብ ፈጣሪዎች በዚህ እድል ተጠቅመዋል።


@etconp
❤6🤩2👍1
👉በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አውቶብስ ፈጣን መስመር ግንባታ በሚቀጥለው ወር እንደሚጀመር ተገለፀ

🚧በመዲናዋ የመጀመሪያ የሆነውና ከፒያሳ እስከ ጀሞ-3 ኮንዶሚኒየም የሚዘረጋው የኤሌክትሪክ አውቶቡስ ፈጣን መንገድ ኮሪደር ግንባታ በታህሳስ ወር ይጀመራል።

🏷ፕርጀክቱ 15.64 ኪሎ ሜትር ሽፋን፣ 20 ዘመናዊ ጣቢያዎችን እና 12 ተጨማሪ አገልግሎቶችን ያካትታል።

⏺ግንባታው በሁለት ዓመት ግዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@etconp
❤10
👉ለ70/30 ማህበር ቤት ተጠባባቂ ተመዝጋቢዎች

❇️የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ከጥቅምት 4 እስከ 8/ 2018 ዓ፣ም ድረስ በ70/30 ማህበር ቤት ተደራጅተው ለመስራት ፍላጎት ያላቸውን የ2005 ተመዝጋቢዎችን በተጠባባቂነት በኦንላይን መመዝገቡ ይታወሳል፡፡

💫በመሆኑም ከዚህ በታች ስም ዝርዝራችሁ የተገለፀው ተመዝጋቢዎች ባምቢስ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 6ኛ ፎቅ የጋራ መኖሪያ እና ቤት ማህበራት ክትትል ዳይሬክቶሬት ከህዳር 8/2018 ጀምሮ እስከ ህዳር 12/2018 ዓ.ም ድረስ ዘውትር በስራ ሰአት በመገኘት ቅጽ 01 እንድትወሰዱ እና መረጃ አሟልታችሁ እንድታስገቡ እናሳውቃለን፡፡

⚡️ማሳሰቢያ ሌሎች ተመዝጋቢዎች በኦንላይን ምዝገባ ወረፋችሁ መሰረት በቀጣይ የምንጠራ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

@etconp
❤6👍2
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

♧ ሁሉን በአንድ ቦታ ለሁሉም ቅርብ

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

♧ ይደውሉልን ያማክሩን

0904040477
0911016833
❤2👏1
👉How to Measure Sand & Aggregate in a Dumper

🚧Accurately measuring the quantity of sand or aggregate delivered to the site is a key responsibility for any site engineer or quantity surveyor. This image illustrates a practical method to calculate the volume of a dumper using basic geometry.

⏺Formula: Volume = Length x Width x Height

📜In this case, two different lengths of the dumper are measured:

- Front (L1) = 6 m

- Rear (L2) = 5.5 m

So, the average length = (6+5.5)/2 = 5.75 m

- Width (B) = 1.7 m

- Height (H) = 2 m

📍Calculated Volume: 5.75 x 1.7 x 2 = 19.55 cubic meters

💫This technique is extremely useful to verify material quantities on-site and prevent shortages or overbilling.

@etconp
❤6👏4😢1
👉JOB VACANCY

💫Junior Civil Engineering Officer

🚧Bunna Insurance S.C

⚡️November 16, 2025 - November 22, 2025

📜Job Requirement

⭐️Educational Qualification: BSc Degree In Civil Engineering or related field of study.

⏺Directly Related Experience: 1 year of relevant experience
⏺Salary & Benefits: As per the salary scale of the Company with Other benefit packages.

📍Place of work: A.A Head office

📩How to Apply

⏺Interested and qualified applicants fulfilling the above requirements can submit non-returnable application letter, CV and copies of supporting credentials along with the original document in person to Human Capital Management Department located at Sarbet behind Africa Union Bunna Insurance S.C Head Quarter 1st floor within 5 working days of this announcement.

Human Capital Management Department

Bunna Insurance S.C
Tel. 011 4 70 63 02

@etconp
❤8
👉JOB VACANCY

🏷Company: Ovid Respan Consult

⏺Position: Resident Engineer/Site Engineer

⭐️Job Qualifications and Skills:

● BSc degree in Civil Engineering

● 8 years or above relevant site experience 

● AutoCAD and Microsoft Office knowledge 

● A strong understanding of engineering principles, construction methods, and regulations

⏺Salary: Negotiation 

📩Please send your complete CV to the email ovidrespan@gmail.com

⏺Only selected candidates will be contacted via phone call for an interview

@etconp
❤13👍2
👉ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው ከአትላስ- ቦሌ መድኃኒዓለም - ብራስ የኮሪደር ልማት

🚧የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከአትላስ- ቦሌ መድኃኒዓለም - ብራስ የሚዘልቀውኮሪደር በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በቀንና በለሊት ክፍለ ጊዜ በትጋት እየሰራ ይገኛል።

💫የኮሪደሩ አጠቃላይ ርዝመት 2 ነጥብ 34 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን በአማካኝ ከ42 እስከ 50 ሜትር የጎን ስፋት አንዲኖረው ሆኖ በራስ ሀይልና በስራ ማህበራት እየተገነባ ይገኛል፡፡

⏺በእስከ አሁኑ የግንባታ ሂደት ከቦሌ መደኃኒዓለም- ብራስ በሁለቱም አቅጣጫ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመር ትቦ ቀበራ፣ የማንሆል ክዳን ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ከቦሌ መድኃኒዓለም - አትላስ በግራና በቀኝ በኩል 960 ሜትር የትቦ ቀበራ በራስ ኃይል ደቡብ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ፅ/ቤት መከናወን ተችሏል፡፡

⏺በቀሪው የመንገዱ ክፍል የመንገድ አካፋይ ከርቭስቶን ስራ፣ የገረጋኒቲ ሙሌት፣ የሰቤዝ ስራና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

⏺በሌላ በኩል በስራ ማህበራት እየተከናወኑ ከሚገኙ ስራዎች መካከል የአፈር ቆረጣ፣የውሃ፣የቴሌና የመብራት መስመሮች ዝርጋትና የእግረኛ መንገድ ዝግጅት ስራዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

⏺ኮሪደሩ የሳይክል መንገድ ጨምሮ ምቹ የእግረኛ መንገድ፣ የህፃናት መጫዎቻ ሥፍራ፣የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች፣ የመኪና ማቆሚያና ተርሚናል፣አረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎችን አካቶ እየተገነባ ይገኛል፡፡

Via የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

@etconp
❤2
#ማስታወቂያ

Vivo interior design

በዘመናት መኻከል በማይሰለች፣ ሁልጊዜ ኑሩብኝ በሚያሰኝ ቤት መኖር ይፈልጋሉ እንግዲያውስ በተመጣጣኝ ዋጋ በጥንቃቄ እና ጥራቱን በጠበቀ ለሚመለከት ሳቢ አድርገን፤ ቤትዎን አስውበን እናስረክባለን።

ቪቮዎች ነን የቤት ውስጥ ዲዛይን እና ግንባታ  ማሰራት ከፈለጉ ይደውሉልን

Vivo design

0921332907
0923607995
❤2👌2
👉የሪል እስቴት ማስታወቂያዎች የመቶኛ ቁጥሮች

በሪል እስቴት ግብይት ማስታወቂያዎች ይዘት ወስጥ ብዙውን ጊዜ ስሰማ እንደ መሃንዲስ የሚያሸማቅቀን በግብይት ባለሙያዎች በመቶኛ የሚነገሩ የግንባታ እርከን መግለጫዎች ይገኙበታል ( Percentage Progress) ።

ገና ከመሬት ብቅ ያለን ህንጻ 50% የተጠናቀቀ ሲሉ፣ የመዋቅር ( ስትራክቸር) ስራው ተጠናቆ ብሎኬት እየተደረደረለት ያለን ህንጻ 85% የተገባደደ፣ ገና ልስን እየተለሰነ ያለውን 90% የተጠናቀቀ .....ለመጠናቀቅ ሁለት ዓመት የሚጠብቀውን በሁለት ወር የሚረከቡት.... ምናምን እያሉ ሰውን ማሳሳት የተለመደ ተግባር ሆኗል ፣ ይህንን ስህተት ለማስተካከልየግንባታ እርከኖች ግምት ገላጭ የሆኑትን እንመልከት ....

፩) 30% ደረሰ የሚባል ፕሮጀክት የመሰረትና ከመሬት በታች ያሉ ምድር ቤቶች (Basment) ስራ ተጠናቅቆ ከሬት በላይ የተወሰኑ ወለሎች የመዋቅር ስራ የተከናወነለት ሆኖ የህንጻውን ይዘት ( ግዝፈት ) በሚያሳይ ቁመና ላይ የደረሰ ነው።

፪) 60% አካባቢ ደረሰ ለመባል የመዋቅር ስራው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ቢያንስ የብሎኬት ስራ የተጠናቀቀለት ሊሆን ይገባል።

፫) ከ70-85% ደረሰ ለማባል የውስጥና የውጭ ልስን ተጠናቆ፣ የቤቶች የውስጥ የኤሌክትሪክና የውሃ መስመር ዝርጋታዎች ተገባደው ፣ የጋራ መጠቀሚያ ቦታዎች ደረጃና ኮሪደሮች የማጠናቀቂያ ስራዎች ተጠናቀው ፣ የአሳንሰር ገጠማ ተጀምሮ፣ የውጭ ገጽታ ላይ የአሉሚኒየም መስኮቶችና በሮች ተጥመው ፣ የውጭና የውስጥ የቀለም ስራ ቢያንስ ተጀምሮ ልንመለከት ይገባል።

፬) 90-95% ተጠናቀቀ ለመባል ብዙ የማጠናቀቂያ ስራዎች ( Finishing Works) ተገባደው የመገልገያ ቁሶች ( Fixtures ) ገጠማ ማለትም የመብራት፣ ሶኬት፣ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ፣ የመታጠቢያ ገንዳ፣ ኪችን ካቢኔት፣ የውስጥ በሮች፣ የውስጥ ቀለም ..... መጠናቀቅ አለባቸው ።

፭) 95-100% ተጠናቋል ለመባል ዋና ዋና የሚባሉ ስራዎች ተጠናቀው በጠቅላላ በህንጻውና በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ያሉ ጉድለቶችን የማስተካከል የእርማት ስራዎች ውጪ ሁሉም ስራ የተጠናቀቀ ሊሆን ይገባዋል። እየተለዩ ከሚደረግ እርማትና ማስተካከያ ውጪ ሙሉ ስራው ሊጠናቀቀና የህንጻ የመጠቀሚያ ፈቃድ ሊያገኝ ይገባዋል።

ስለዚህ የሪል እስቴት አገበያይ ተቋማትና የሽያጭ ሰራተኞች ሆይ ፕሮጀክቶቻችሁ የደረሰበትን ደረጃ በትክክል የሚገልጽ መረጃ በመስጠት እኛንም ከመሳቀቅ ዘርፉንም ከውሸት ታደጉት።

Via በደሳለኝ ከበደ፣ መሀንዲስ፣ ገንቢ እና ሪል ስቴት አማካሪ

@etconp
👍12❤10