Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
549 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉በኮንስትራክሽን ውል አሰሪው የተቋራጩን ክፍያ አዘግይቶ መክፈል ጉዳይ/Delay payment/

✍️ የኮንስትራክሽ ውል መሰረታዊ ባህሪው ሲታይ በዋናነት አሰሪና ተቋራጭን በተዋዋይነት የሚይዝ ሲሆን ጉልህ የሆነው ግዴታቸው ሲታይ ደግሞ ተቋራጩ በውሉና ዲዛይኑ/ስፔስፊኬሽኑ መሰረት ግንባታውን የማከናወን ሀላፊነት የሚኖርበት ሲሆን ክፍያ የመክፈል ጉዳይ ደግሞ ለአሰሪው ዋናውና ትልቁ ግዴታው ነው፡፡የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610፣3019እና 3020 እንዲሁም 3244 ተገናዝቦ ሲታይ ይሄን ሁኔታ ያስገነዝባል፡፡
✍️ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3020(1) ላይ "ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ስለሚፈጽሙት ስራዎችና ስለዋጋው ካልተስማሙ በቀር የተቋራጭነት ውል አለ አይባልም" በሚል የተደነገገው በኮንስትራክሽን ውል ለተቋራጩ የሚከፈለው ክፍያ ጉዳይ የውሉ መሰረታዊ ነጥብ መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ ስለክፍያ አይነቶች የህጉን ጉዳይ ወደፊት በሌላ ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡
✍️አሰሪው ለተቋራጩ ክፍያ የመክፈሉን ሁኔታ ያለበቂ ምክንያት ማዘግየት አይችልም፡፡
# አማካሪ መሀንዲሱ በተለይ ከተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ በቀረበለት ጊዜ የማረጋገጥና የማጽደቁን ስራ በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማጠናቀቅ ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(d)
✍️አሰሪው መስሪያ ቤት ደግሞ በአማካሪ መሀንዲሱ የጸደቀ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡(የመመሪያው አንቀጽ 28.5(e)
✍️ አማካሪ መሀንዲሱ በተቋራጩ የቀረበውን የክፍያ ጥያቄ በሰባት ቀናት ውስጥ የማረጋገጥና የማጽደቅ ስራ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
*በዚህ ረገድ የመመሪያው አንቀጽ አንቀጽ 28.5(f) ግልጽ ምላሽ አስቀምጧል፡፡
✍️ይሄውም ተቋራጩ በዚህ ምክንያት ከአሰሪው ላይ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ የጠየቀ እንደሆነ አማካሪ መሀንዲሱ ይህን ተጨማሪ ክፍያ የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል፡፡
*ሆኖም ግን አማካሪ መሀንዲሱ ለሚሰጠው አገልግሎት ከሚከፈለው ክፍያ በላይ የሆነ ክፍያ ለመክፈል ሀላፊነት አይኖርበትም፡፡
✍️በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636 የአማካሪ መሀንዲሱን የእውቀት ስራ ውል ግዴታ ይደነግጋል፡፡ይሄውም አማካሪው "የኪነ ጥበብን ደንቦች በማፍረስ ጥፋት ጥፋት ካላደረገ በቀር በአሰሪው በኩል ስራ ተቋራጩን ሀላፊነት አይነካውም" በሚል ተቀምጧል፡፡(2636(2)) እንደዚሁም አማካሪው ሳይሰራ ከመቅረቱ የተነሳ ወይም በአሰሪው ላይ ጉዳትን የሚያመጣ ስራ ያደረገ እንደሆነ አጥፊ ነው ለመባል እንደሚችል የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2636(3) ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ አማካሪው ክፍያ የማረጋገጥ እና የማጽደቅ ስራውን በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ባለማከናወኑ አሰሪው ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍል በተቋራጩ የተጠየቀ እንደሆነ አማካሪው አጥፊ ነው ሊባል ያስችለዋል ማለት ነው፡፡
#አሰሪው በአማካሪው የጸደቀው የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14 ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያ ባይፈጽም ምን ውጤት ይኖረዋል?
✍️አሰሪው ያለበቂ ምክንያት ክፍያ ያዘገየ እንደሆነ ለተቋራጩ ተጨማሪ ክፍያ/additional payment/ ለመክፈል ሀላፊነት እንደሚኖርበት የፌዴራል የግዥ መመሪያ/Federal public procurement directive/ አንቀጽ 28.5(g) ይደነግጋል፡፡
✍️ተጨማሪ ክፍያ ሲባልስ ምንን ያጠቃልላል? የሚለው ሲታይ በዋናነት ወለድ የመክፈል ሀላፊነትን የሚመለከት ይሆናል፡፡በዚህ ረገድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3268 ተቋራጩ መክፈልን በማዘግየት የሚታሰበውን ወለድ እንዲያገኝ መብትመብት ይሰጠዋል፡፡የወለዱ መጠንም በውል ያልተወሰነ የሆነ እንደሆነ በአንቀጽ 1751 መሰረት ህጋዊ ወለድ በአመት 9(ዘጠኝ) በመቶ ሆኖ የሚሰላ ይሆናል፡፡
✍️ሌላው እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነጥብ ተዋዋዮች በውላቸው ላይ ክፍያን ማዘግየት የሚኖረውን ውጤት አስመልክቶ የቅጣት ስምምነት/penality clause/ ያካተቱ ከሆነ የፍትሀብሄር ህጉ አንቀጽ 1889 እና ተከታዮቹ ድንጋጌ እውቅና ስለሚሰጠው እና በአንቀጽ 1731 መሰረት ውል በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ስለሚቆጠር ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡
✍️አንዳንድ ክልሎችም በዚህ ረገድ በግዥ መመሪያቸው ላይ ዝርዝር ውጤቱን ያስቀምጣሉ፡፡
✍️አሰሪው ክፍያ በወቅቱ ባለመፈጸሙ ምክንያት ከወለድ ባለፈ ሌላም ጉዳት የደረሰበት ተቋራጭስ ከጉዳቱ ጋር እኩል የሆነ ኪሳራ ሊከፈለው አይገባም ወይ? የሚል ጥያቄም ሊነሳ ይችላል፡፡ምክንያቱም የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2091 እና 1790(2) ለደረሰው ጉዳት ሀላፊ መሆኑ በህግ የታወቀ ሰው የሚከፍለው የጉዳት ካሳ ሀላፊነቱን ያመጣው ጉዳይ በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን አለበት በሚል በግልጽ ይደነግጋል፡፡
#በአጠቃላይ አሰሪው በማናቸውም ምክንያት የተቋራጩን ክፍያ በሚያዘገይበት ጊዜ ተቋራጩን ለውድቀት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው፡፡ምክንያቱም በሀገራችን አብዛኛው ተቋራጭ ድርጅት የፋይናንሽያል ማኔጅመንት ስርአት የለውም፡፡ተቋራጮቻችን የገንዘብ አቅማቸውም ደካማ ነው፡፡አብዛኛው ተቋራጭ ለአንዱ ፕሮጀክት የሚወስደውን የቅድሚያ ክፍያ ሌላ ፕሮጀክት ላይ ይጠቀምበታል፡፡በዚህ ምክንያት አንድ ተቋራጭ ሲከስር ብዙ ሰራተኛ እንደሚበተን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ስለዚህ በአሰሪዎች በኩል ተቋራጮች የሰሩበትን ክፍያ በወቅቱ እና በተሰራው ስራ ልክ አንዲከፈላቸው ለማድረግ እና በህጉ የተቀመጠው የክፍያ የጊዜ ገደብ እንዲከበር ጠንከር ያለ አቋም ወስዶ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

@etconp
1❤15
👉The Basic Design Concepts of Highway Road Construction

🏷1. Design Speed

⏺This is the speed used by engineers to design curves, gradients, visibility, and safety features.
⏺Higher design speed = smoother curves and gentler slopes.

🏷2. Traffic Volume & Capacity

⏺Engineers study:How many vehicles use the road per day
Future increase in traffic
This helps decide number of lanes, lane width, and pavement thickness.

🏷3. Road Alignment

⏺Road alignment means the position of the road on the ground.

🚧It has two parts:

❇️a) Horizontal Alignment
Curves and straight sections seen from above.
❇️b) Vertical Alignment
Slopes and hills seen from the side.

📍Good alignment gives:Safety,Comfort and Proper drainage

🏷4. Cross-Section Elements
These are the physical parts of the road:

⏺Carriageway (driving lanes)
⏺Shoulders
⏺Median
⏺Side slopes
⏺Drains
⏺Proper cross-section ensures stability and safety.

🏷5. Pavement Design

⏺Pavement must carry traffic loads without failure.

🔰Two main pavement types:

⏺Flexible (Asphalt)
⏺Rigid (Concrete)

⭐️Design considers:

⏺Traffic load
⏺Soil strength
⏺Climate

🏷6. Subgrade and Soil Strength

⏺The soil below the pavement must be strong and well-compacted.
⏺Weak soil → thick pavement or soil improvement needed.
Tests include CBR and compaction tests.

🏷7. Drainage Design

⏺Water is the enemy of roads.
⏺Good drainage prevents:Potholes,Cracking,Weak subgrade,Drainage includes side drains, culverts, camber (slope), and ditches.

🏷8. Geometric Design

⏺Geometric design ensures vehicles move safely and comfortably.

📍Includes:
⏺Lane width
⏺Shoulder width
⏺Sight distance
⏺Superelevation (banking of curves)
⏺Gradient (slope of road)

🏷9. Materials Selection

⏺Good materials give long road life.

📍Engineers choose:
⏺Strong aggregates
⏺Proper asphalt mix
⏺Concrete grade
⏺Quality soil
⏺Testing is done before use.

🏷10. Safety Design Features

📍Includes:
⏺Guardrails
⏺Road signs
⏺Markings
⏺Crash barriers
⏺Lighting Designed to reduce accidents and protect road users.

🏷11. Environmental & Social Considerations

⏺Road design must consider:
⏺Noise
⏺Dust
⏺Land use
⏺Impact on communities
Protected areas

🏷12. Cost & Maintenance Planning

❇️Engineers plan:
⏺Construction cost
⏺Future maintenance
⏺Life-cycle cost
⏺Good design reduces
⏺long-term repair expenses.

@etconp
❤15
👉JOB VACANCY

🚧Engineering Corporation of Oromia

@etconp
❤4👍1
👉JOB VACANCY

🚧 applicants can apply inperson to the below address within 3 consequative days from the date of this announcement upto Nov 26, 2025 Any application after the deadline is not acceptable!!!

📍Address: AGY Construction PLC, Arround Urael Beside Bambis Supermarket, Afework Building, 8th Floor

@etconp
👍7❤3
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 13  ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 13  ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 14  ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 14  ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 14  ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
😢1
ጨረታ

አዲስ ዘመን  ህዳር 15 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2🔥1
👉አልሚዎች ወደግንባታ ለመግባት በእያንዳንዱ የመንገድ አይነት ላይ ሊያሟሉ የሚገባቸው ጉዳዮች እነሆ!

💫በከተማዋ ውስጥ ያሉ የመንገድ አይነቶች (Type/Hierarchy) ፣ ስፋት (Street Width) ፣ ግንባታ ከመንገድ የሚኖረው ርቀት (setback) እንዲሁም በተሻሻለው የመሬት አጠቃቀም ፕላን መሰረት በግል ይዞታቸው ላይ በራሳቸው የማልማት ፍላጎት ያላቸው ባለይዞታዎች ወደግንባታ ለመግባት በእያንዳንዱ የመንገድ አይነት ላይ ሊያሟሉ የሚገባቸውን ከሴትባክ በኃላ ቀሪ ዝቅተኛ የቦታ ስፋት(Plat Area) እና የፊት ገፅታ (Plot Frontage) በተመለከተ የሚከተለውን ተወስኗል፤

🏷መልዕክቶች፡- ለከተማችን ከፍታ የፕላን ህግን የተከተለ ህንፃ ግንባታ ወሳኝ ሚና አለው!

⏺ደረጃቸውን የጠበቁ ግንባታዎች ለውብ የከተማ ገፅታ!
⏺ህግ አክባሪነት የስልጡን ከተሜነት ምልክት ነው!
⏺የሴት ባክ ህግ ለዘላቂና የተረጋጋ የከተማ ዕድገት መሰረት ነው!

ከተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታዎች ከመንገድ የሚኖራቸውን ርቀት እና ተያያዝ የግንባታ ፈቃድ መመሪያዎች ከተላላፈ ውሳኔ የተወሰደ።

Via ፕላንና ልማት ቢሮ

@etconp
❤3🔥1
👉ለስራ ተቋራጮችና አማካሪ ድርጅቶች የዓቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡

💫ለዘርፉ ተዋንያን ከወቅቱ ጋር ተናባቢ የሆነ እውቀትና ክህሎት በማላበስ ተግባራቸውን በመልካም አፈፃፀም እና በላቀ ክህሎት እንዲከውኑ የሚያስችላቸው የዓቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በተከታታይ እየሰጠ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ዛሬም ለስራ ተቋራጮች እና አማካሪ ድርጅቶች ያሰናዳውን ስልጠና ሰጥቷል።

🚧ቢሮው ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ባዘጋጀውና Leadership and Construction Company በሚል ርዕስ ዙሪያ ባተኮረው በዚህ ስልጠና 222 ስራ ተቋራጮች እና አማካሪ ድርጅቶች ተሳትፈውበታል፡፡

Via የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

@etconp
❤5
👉ማስታወቂያ

🚧በድጋሚ ስራ ተቌራጮችን ለመመልመል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የወጣው ማስታወቂያ

@etconp
❤11