የኛ ግጥም
46 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
Forwarded from ༺Mâřķóñãľ༻
​​😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፈል 1


.
.
.
በጠዋት ከ ቅዱስ ጊወርጊስ ቤተክርስቲያን የሚወጣው ህይወትን የሚያለመልም የቅዳሴ ዜማ በጆሮዬ አቀጨለና ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ።ከብርድ ልብሱ ውስጥ ሳልወጣ አይኔን ሸፍኜ ይሔን ጥዑም ዜማ እየኮመኮምኩ ሳለሁ "ዮርዲ ቁርስ ደርሷል" የሚል ድምፅ ከተመሰጦዬ መለሰኝ ።ብርድ ልብሱን ከአይኔ ላይ ቀስ ብየ ስገልጠው መጋረጃውን አምልጣ ሰርጋ ከገባችው የጠዋት ፀሐይ ጋር ተጋጨን።ቢጫ ቀለም ከተቃባው ምኝታ ቤት ጋር ፀሐይ ተደምራ ክፍሉን በብርሀን አሽቆጥቁጣዋለች።"ዋው ደስ የሚል እሁድ "አልኩና ከአልጋየ ላይ ወረድኩ። ................ቁርስ እንደነገሩ ከቀማመስኩ በኋላ አንድ ሲኒ ቡና ፉት ብዬ ወደ ክፍሌ ገባሁና ከውስጥ ዘግቼ ቁጭ አልኩ ።ትንሽ በሀሳብ ስባክን ቆየሁና "ደሳለኝ ያለኝ ነገር እውነት ነው እሱን መስማት አለብኝ" አልኩና በውስጤ ከተቀመጥኩበት በወኔ ተነስቼ ከመሳቢያው ውስጥ እስክሪብቶ እና ወረቀት አወጣሁና በድፍረት ጫር ጫር እድርጌ ወደ ኪሴ አስገባሁት ። ወደ መስታወቱ ተገጠቼ ከምስሌ ጋር ተፋጠጥኩ ።"ድፈር ዮርዲ አንተ እኮ የኔ ወንድም ነህ አንተ እኮ ዮርዳኖስ ነህ ታደርገዋለህ" የደሳለኝ ድምጽ ደጋግሞ ጆሮዬ ላይ ደወለ።በረጅሙ ተነፈስኩ እና መስታወቱ ውስጥ ሆኖ የሚያየኝን የራሴው ምስል "ድፈር ዮርዳኖስ ድፈር ካለመናገር ደጅ አዝማችነት ይቀራል " አልኩት ከሌላ ሰው ጋር የማወራ ያሀል ጮህ ብዬ ።ዛሬ ከየት እንደመጣ የማላውቀው የወኔ ካባ በላዬ ላይ ተደፍቷል ።ግቢያችንን ለቅቄ ጉዞ ጀመርኩ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዳኖስ ተሾመ እባላለሁ ከእናቴ ከ ወ/ሮ አለም አወቀ እና ከአባቴ ከአቶ ተሾመ ታምሩ መስከረም 05,1992ዓ.ም ይችን ዓለም ተቀላቀልኩ ።ለቤተሰቡ ሁለተኛ ልጅ ነኝ አህቴ ቤዛዊት ተሾመ ።በጣም የምወዳት ታላቅ እህቴ ነች በሊትሌቸር ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በዚህ ክረምት ነው የተመረቀችው።አባቴ ነጋዴ ነው እናቴ የቤት እመቤት።ኑሯችን ከደብረ ማርቆስ 15 ኪ.ሜ እርቃ ከምትገኘው ትንሿ አምበር ከተማ ነው።ሀብታሞች አይደለንም ድሆችም አይደለንም የጎደለን የለም ።ቤተሰባችን ውስጥ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች አሉ።እድሜ ጠገቧ አያቴ እና የቤት ሰራተኛዋ እልፍነሽ።ቤተሰባችን ፍቅር ነው። ፍቅር ማለት የእኛ ቤተሰብ ነው ብል ማጋነን አይሆንም! 2007 ማትሪክ ተፈትኜ ውጤት እየጠበኩ ነው ።ብዙ ጓደኞች አሉኝ።ደሳለኝ ግን ከጓዳኛ በላይ ወንድሜ ነው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከግቢያችን በስተሰሜን በግምት 100 ሜትር ያክል ከተጓዝኩ በኋላ ከአንድ ትልቅ ግቢ ላይ ደረስኩ።ትንሽ ከአቅማማሁ በኋላ "አብርሃም አብርሃም " ብዬ እንደተጣራሁ ያ እንደ ጦር የምፈራው ምዕታተኛው የሔዋን ድምፅ ማነው አለኝ።መልስ አልመለስኩም ልቤ አታሞውን ይደልቅ ጀምሯል። በሩም ተከፈተ ወኔየን ሰብሰብ አድርጌ ቆምኩ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
Forwarded from ༺Mâřķóñãľ༻
​​😘ሰሜናዊት ሙሽራ🔥

😘ክፍል 2


.
.
.
"እንዴ ዮርዲ እንዴት ነህ"አለች ሔዋን።
"አብርሀምን ፈልጌ ነበር "አልኳት ሰላምታዋን አልሰማሁም አሉ።
ጉንጬን ዳበስ አደረገችና "ዮርዲዬ ዛሬ ደግሞ ሰላምታ የለም እንዴ ምን ሆንክብኝ የኔ አስቀያሚ ደህና አይደለህም?"አለችኝ እንደመጨነቅ ብላ።"ሒዊ ምንም አልሆንኩም አብርሃምን ማግኘት ብቻ ነው የምፈልገው" አልኳት አይኗን የመሸሽ ያህል ወደ መሬት አቀርቅሬ።ሔዋን ያለመፈለግ ስሜት ተሰማት መሰለኝ ተበሳጭታ መንቀር መንቀር እያለች አብርሀምን ለመጥራት ወደ ውስጥ ገባች። አብርሀም መጣ።ሳቂታው አብርሀም እሱ ማለት ለመሳቅ የተፈጠረ ፈገግ ለማለት ብቻ የሚኖር አይነት ልጅ ነው።
"ዮርዳኖስ እንዴት ነህ"አለ አብሪሽ ፈገግ ብሎ
"ደህና ነኝ ሁሉ ሰላም ነው አይደል"አልኩት
"ሰላም ነው ። በጠዋት ምን ጎርፍ ጣለህ?
"ውይ አብሪሽዬ ስራ ላይ ነበርክ እንዴ?"አልኩት እንደመሳቀቅ ብዬ
"አረ በጭራሽ ምንም ስራ የለኝም ከዚህ በፊት በዚህ ሰዐት መጥተህ አታውቅም ብዬ ነው" አለኝ
"በል እንግዲያስ ስራ ከሌለህ ከለመድነው ቦታ እንሒድ እማማክርህ ጉዳይ ነበረኝ።"አልኩት
"በደስታ ነዋ እሺ የምልህ"አለ አብሪሽ እየሳቀ።ተያይዘን ከለመድንው ቦታ ሔደን ተቀመጥን።ለብዙ ደቂቃዎች ያህል ስንጨዋወት ቆየን እና።"እሺ ወንድም ዮርዳኖስ ለምን ነበር የፈለግከኝ ?"አለኝ
ትንፋሼን ሰብሰብ አድርጌ ለመናገር ተዘጋጀው "ምን መሰለህ እኔ ሔዋንን አ...ፈ...ቅራ...ታለሁ ለብዙ ጊዜ ልነግራት እወስን እና ድፍረት እያጣሁ ወኔ ከእኔ ገሸሽ እያለ ስቸገር ቆየሁ።"አልኩና የማማጥ ያህል ተጨነቄ ተነፈስኩ።ቀና ብዬ አብርሀምን ስመለከት ደነገጥኩ።ምንም አይነት የስሜት መለወጥ አይታይበትም።አልደነገጠም አልተገረመም አይኔ ጋር የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ሁሉ አይኖቹን አይኔ ላይ ተክሏል።"እንዴ እንደዚህ ተጨንቄ በመከራ ነግሬው አልሰማኝም ማለት ነው"አልኩኝ በውስጤ።ግራ መጋባቴን የተመለከተው አብርሃም "ዮርዳኖስ ሔዋንን እንደምታፈቅራት አቃለሁ"ብሎኝ እርፍ
"አረ በቂርቆስ አትቀልድ "አልኩት
"እሚቀለድበትን ሰዐት እና ቦታ አውቃለሁ ትንሽ ልጅ አይደለሁም"አለኝ ኮስተር ብሎ
"እና ጠንቋይ ትቀልባለህ ልበል?እኔ እኮ ከ ጓደኛዬ ከደሳለኝ ውጭ ለማንም ትንፍሽ አላልኩም።እንዴት አንተ ልታውቅ ቻልክ?"አልከት
"እሱን በሰፊ ፕሮግራም እናወራለን ።አሁን ከእኔ ምን እንደሚጠበቅ ንገረኝ እና እንለያይ ዝናብ ሊዘንብ ይመስላል"አለኝ ሰማዩን ቀና ብሎ እየተመለከተ።
"አብርሀም ለአመታት ያህል እንደወንድም ከጎኔ ውስጥ ከእቅፌ ላይ የነበረችን ልጅ በድንገት ከፊቷ ቆሜ አፈቅርሻለሁ ለማለት ሞራል አጣሁ።አንተን ማስቸገር ካልሆነብኝ ይችን ወረቀት አድርስልኝ?" አልኩት
"እንዴ ዮርዲ እኔ ሌላ ሰው መሆኔ ነው ካላስቸገርኩህ የምትለኝ በል ስጠኝ እና ልሒድ"አለ አብሪሽ ለመሔድ እየተነሳ
"ወረቀቱን ሰጠሁት እና፤ስማ ደግሞ መልሱን ዛሬ ትፃፍልኝ እና መልስልኝ?"አልኩት
"እሺ መልካም እድል 10:00 እንገናኝ"አለና እየሮጠ ሔደ።ሰዓቴን ተመለከትኩ 6:03 ይላል።ቤት ለምሳ ይጠብቁኛል ብዬ ወደቤቴ አመራሁ።የጠዋቷ ፀሐይ ለውሸት ነበር የወጣችው።ቤት ከመግባቴ ትንሿን የአምበር ከተማ ዶፍ ዝናብ በአፍ እና በአፍንጫዋ ያዳፈት ጀመር።ቤተሰቦቼ በዛሬው ሁኔታዬ ሳይወዛጋቡ አልቀሩም ።ምሳ ቀመስኩ እንጂ አልበላሁም።ምሳ ተበልቶ የምሳ ሰዓቱ ቡና ሲጠጣ እኔ ግን እምቢ ብዬ ክፍሌን ዘግቼ አልጋየ ላይ ጋደም አልኩ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የማይታለፍ ነገር የለም እነዚህ አርባ አመት ያህል ረዝመው ያስጨነቁኝ አራት ሰዓታት በመከራ አለፉና ጉዴን ለመስማት
ከተለመደው ቦታ ቀደም ብዬ ሔድኩ።ከ30 ደቂቃ ጥበቃ በኋላ አብርሀም በ50 ሜትር ርቀት ላይ ሲመጣ አየሁት።የሞት መልዕክት ይዞልኝ የመጣ ይመስል ሳየው ልቤ በአፌ እስክትወጣ ያህል መምታት ጀመረች።

ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
Channel photo updated
​​😘ሰሜናዊት ሙሽራ🔥

💞ክፍል 3


.
.
.
ከሁለት አመታት በኋላ ..........................

ከሁለት አመት በፊት ያልታየችው ሔዋን ዛሬ ግን መነጋገሪያ ሆነች።ማንም ያላየውን ውበቷን ተመልክቶ በፍቅሯ የተነደፍው እሱ ብቻ ሳለ፤ዛሬ ግን ስር ስር ባዬች በዙ።ጉድ ተባለ ይችን የመሰለች ልዕልት ከዚህ ጋር ምን ትሰራለች አይመጥናትም አይገባትም ተባለ።እውነት ነው ዮርዳኖስ ቆንጆ የሚባል ባይሆንም ለወንድ ልጅ የሚገባውን ያህል ደስ የሚል ልጅ ነዉ።ፍቅራቸው ያስቀናል ።ማንም ምንም ቢያወራ ሔዋን እኔ የ ዮርዳኖስ ነኝ ከእሱ የሚለየኝ ሞት ብቻ ነው አለች።ዛሬ ሐምሌ 13 ነው ከሔዋን ገር ፍቅር ከጀመሩ ሁለተኛ አመታቸውን እያከበሩ ነው።ሁለቱም 12ኛ ክፍል ተፈትነው ውጤት እየጠበቁ ነው።ዮርዳኖስ ሶሻል ሳይንስ እርሷ ደግሞ ናቹራል ሳይንስ ነበር የገቡት ።
"ኩራተኛዋ ልዕልት"አለና ዮርዳኖስ ጉንጯን ሳም አደረገጋት።
"ማነው ባክህ ኩራተኛ ያደረገኝ፤እኔ እንደሆኩ ማንንም የማላስከፋ ሩህሩህ ልብ ነው ያለኝ"አለች የጉንዮሽ ስርቅ አድርጋ እየተመለከተችው።ዮርዳኖስን ለማስቀናት ሁሌ የምትናገራት ሽሙጥ መሆኗ ነው።
"እሱን ተይውና ኩራተኛማ ነሽ።ያኔ እስረኛ ክፍል እያለን ለአብርሃም የላኩልሽን ደብዳቤ ምን ብለሽ ነበር የመለስሽልኝ?"አላት
ከአፉ ቀለብ አደረገችና"እኔ ለአንተ መሆን አልችልም አቻህን ፈልግ ደፋር !"አለችና ሳቀች።መቼም ስትስቅ እንኳን የአፍቃሪዋን የጠላቷንም ልብ ያስደነግጣል ።
"ግን ምን አስበሽ ነበር?"አለ
"አንተ ደግሞ፣የሴት ወግ መሆኑ ነዋ በአንድ ጥያቄ እሻ ያለች ብቸኛዋ ሴት እንድባል ፈልገህ ነው እንዴ?"ቀጠለች እና "ደሳለኝ አይመጣም እንዴ?"አለች
"አረ የሱን ነገር ተይው" አለ እንደመሳቅ ብሎ ።
"ምነው ምን ብሎ አናደደህ ደግሞ"አለች ለመስማት እየጓጓች
"አንድ ቀን አነሱ ቤት ደርሰን ስንመለስ ፡አንዲት ቆንጆ ልጅ ከሆነ ሰው ጋር ቆማ ስትሳሳም ተመለከትን።"
"ከዚያስ?"አለች ሔዋን
"ከዚያማ ሞን ቢለኝ ጥሩ ነው "ይቺ ደግሞ ከዚህ ቦርኮ ጋር ምን ትሰራለች አለኝ።እኔም ምነው ዋናው ነገር መፋቀራቸው ነው አልኩት ።ቀለብ አደረገና ፍቅር እውር ያደርጋል የሚባለውን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ አረጋገጥኩ ።አለኝ"
"አንዴት? አልኩት።
"ምን እንዴት አለው እያየኸው ይቺ ቆንጆ ከዚህ ጉርድ በርሜል ጋር፤ሌላኛው የእኔው ጉድ" አለና በስርቆት አየኝ
"ምን ለማለት ፈልገህ ነው ?አልኩት
"ያው አንተ ከሔዋን ጋር ማለት ነዋ"አለና መናደዴን ሲመለከት "ያሉትን ነው"አላለኝም መሰለሸ።
ሔዋን ልቧ እስኪፈርስ ሳቀች እና "በቃ እሱ ግቢ ሔዶ ከመጣ በኋላ ስራው ሁሉ አንተን ማናደድ ሆነ አይደል"አለች ያልጨረሰችውን ሳቋን ለመጨረስ የምትስቅ በሚመስል መልኩ ደግማ እየሳቀች።
"አንቺማ ሳቂ የእኔ አስቀያሚ"አለና ሳም አደረጋት
"በቃ ማታ ከደሳለኝ ጋር ሆነህ ላግኝህ ልደታችንን እናከብራለን"አለች እና ፍዝዝ አለች
"እሺ የእኔ እመቤት ታዛዥ ነኝ የልደት ስጦታዬን እንዳትረሺ"አለ ዮርዳኖስ
"በደምብ ነው ያለህ የዛሬው ልዩ ነው"አለች ፍዝዝ እንዳለች።
ሁኔታዋ አላመረውም ።እንደዛሬው ሁና አይቷት አያውቅም።ከተገናኙ ጀምሮ በስስት ነበር የምትመለከተው።
"እሺ በቃ ግቢ፤ የማታ ሰው ይበለን"ብሎ ከንፈሯ ጋር ማህተም አስቀመጣና ምን ሆና ይሆን እያለ እያሰላሰለ ወደቤቱ ገባ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​‍ 😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

💞ክፍል 4

.
.
.
ዮርዳኖስ ቤት ሲገባ ደነገጠ አፉን ከፍቶ ቀረ።ቤቱ በዲም ላይት አሸብርቋል ።ከበሩ ፊት ለፊት የ ዮርዳኖስ እና የሔዋን ፎቶ በትልቅ መስታወት ተንጠልጥሏል።ከላይ እንኳን ለሁለተኛ አመት የፍቅር ጅማሪያችሁ አደረሳችሁ።የሚል ወረቀት ተለጥፏል።ልቡ ተሸበረ።"ዛሬ የሚፈጠር ነገር አለ እንጂ ካለነገር ልቤ አልፈራም፤ሔዋንም ልክ አልነበረችም"አለ በውስጡ ።እህቱ ቤዛ ወደ ሳሎን ገባች እና "ሰርፕራይዝ"ብላ ከሃሳቡ አባነነችው።
"በቃ ስራ አጥ መሆን እንደዚህ ነው የሚያደርገው? ለአንቺ ስራ ፈጠራ መሆኑ ነው አይደል?እስኪ ይሔን ሁሉ ለደከምሽበት ምንያህል ክፍያ ነው የምትጠይቂኝ?"አለ ዮርዲ ለመቀለድ
ቤዛ አኮረፈች እና ተመልሳ ወደ እናቷ ሔደች ።
"አንተ ምላሳም ሰምቼሃለሁ!አንተን ለማስደሰት ይሔንን ሁሉ ደክማ እንደዚህ ነው መልስህ?"አለች ወይዘሮ አለም እየሳቀች ።
እውነት ነው ቤዛዊት ከተመረቀች ድፍን ሁለት አመት ሞላት።ስራ የሚባል ነገር የለም።ከአባቷ ከአቶ ተሾመ ጋር ንግዱን እያጦጧፈችው ነው።አሁንማ ተስፋ ቆርጣ የስራ ማስታወቂያ ማየት ካቆመች ስድስት ወር ሞላት አረ አንዲያውም የተመረቀችበትን የትምህረት መስክ ሁሉ ሳትረሳው አልቀረችም ።
ዮርዲ ጓዳ ሲገባ እናቱ ምግብ በመስራት ተጠምዳለች።ቤዛ ደግሞ ለምቦጯን ጥላ ተቀምጣለች።
"አንቺ ደግሞ ሰው መቀለድ አይችልም እንዴ?"አለ ዮርዲ ፀጉሯን እንደ ህፃን ልጅ እዬደባበሰ
"አንደኛ ስራ አጥ አትበለኝ፤ሲቀጥል እኔ ስራ አጥ አይደለሁም ነጋዴ ነኝ አሺ።"አለች ኮስተር ብላ።
"እስኪ በእኔ ሞት በስነፅሁፍ ተመርቆ ነጋዴ አይከብድም " አለት ዮርዲ።
"አሱን ከጥቂት አመታት በኋላ በእኔ ቦታ ስትሆን ትነግረኛለህ ወሬኛ"አለች ቤዛ
"አንተ ስራ ፈት ሒድ ወደ ክፍልህ አባትህ እቃ አስቀምጦልሀል"አለች ወይዘሮ አለም
"እእእ ስራ ፈት ብለውማ የሰው ሞራል አይንኩ ወይዘሮ አለም"አለና ጓዳውን ለቆ እየወጣ ዞር ብሎ ቤዛን አየት ሲያደርጋት ነጠላ ጫማዋን አውልቃ ጀርባውን አቀመሰችው።ሳሎኑን አቋርጦ ወደ ክፍሉ እየሮጠ ገባ።
"ደግ አደረግሽ ትንሽ ምላሱን አርፈን እንቆያለን"አለች እና ወይዘሮ አለም ተሳሳቁ።
ዮርዳኖስ ክፍሉ ሲገባ አልጋው ላይ አዲስ ልብስ ተቀምጦለታል።ዋው አለና አንስቶ ተመለከተው።ሰማያዊ ጅንስ ሱሪ እና ብሉ ብላክ አጀ ጉርድ ሸሚዝ።የለበሰውን ሸሚዝ አወለቀ እና አዲሱን ሸሚዝ ለበሰው ።ወደ መስታወቱ ተጠገና ራሱን እየተመለከተ ቁልፎችን ቆለፋቸው።
"አንተ ያበደ ነው ሸበላ ነው የሆንከው
"አለች እልፍነሽ በመስኮት ታይ ኖሯል ልብስ እያጠበች ።
"አረ ተይ አልፊቱ አታሹፊብኝ" አለ ዮርዳኖስ
"አባቴ ይሙት ጋሼ ምርጫ ይችላሉ"አለች እልፍነሽ
"አንቺ ግን እስከ አሁን አጥበሽ አትጨርሽም እንዴ? የዛሬው ደግሞ ከአስራ ሁለት እስከ አስራሁለት ሰዐት ነው እንዴ አጠባው"አለ ዮርዲ
"ምን ባክህ ኬኩን ላዝዝ ሔጄ ነበር ለዛ ነው"አለችው
"የምን ኬክ ነው ቆይ እናንተ ሰዎች እንዴ ዛሬ ምን የተለየ ነገር አለ።እኔና እሷ እኮ የምናከብረው እዛው ከምንገናኝበት የሾላ ዋርካ ላይ ነው።"አለ ተገርሞ
"በል ስራ አስፈታኸኝ" ብላ ወደ ልብስ አጠባዋ ገባች።እሱም መዘነጡን ተያያዘው ።አባቱ የገዛለትን ሱሪ ለበሰው እና አጁን ወደ ኪሱ ሲከተው ኪሱ ውስጥ የሆነ ነገር አገኘ።በፍጥነት አወጣው እና ሲመለከተው ትንሽ ካርቶን ነች።ከፈተው።ውስጡ ሀብል ነበር ።ከካርቶኗ አወጣ እና ሲያይ ተንጠልጣዩ ጋር ኤች H ፊደል አለ።እንዴ "አባዬ ስሜ ጠፋበት እንዴ?" አለና አንገቱ ላይ አንጠልጥለው።ዝንጥ ብሎ ከክፍሉ ወጣ እና ወደ ጓዳ ተመለሰ።
"ትፍ ትፍ ከአይን ያውጣህ ልጄ! አንተ 18ኛ አመትህን እንኳን ስታከብር እንደዚህ አልዘነጥክም።"አለች እና እናቱ ግንባሩን ሳም አደረገችው
"ዛሬ ምሳ ሰዓት የለንም እንዴ 9ኝ ሰዐት አየሆነ እኮ ነው"
"ምነው ራበህ እንዴ" አለች ወይዘሮ አለም
"አይ እንደሱ እንኳን አይደለም ግን አባዬም የለም ብዬ ነው"አለ
"አባትህ እስኪመጣ እኔም እጨርሳለሁ ሒድ ለደሳለኝ ደውልለት የእሱም እቃ ተቀምጦለታል ቤዛ ክፍል አለልህ"አለች ወይዘሮ አለም ።
ዮርዳኖስ ግራ ተጋባ "ቆይ እነዚህ ሰወች ምን አስበው ነው?" ይሔ ሁሉ ሽር ጉድ ምንድን ነው።እናቱ ብዙ የድስት አይነት ደርድራለች ።ማህበር ያለ ነው ያስመሰለችው ።እንዲህ እንደተወዛገበ ወደ ሳሎን ሔደና ለደሳለኝ ደውሎ አሁን እንዲመጣ ነግሮት ወደ ቤዛ ክፍል ሔደና ለደሳለኝ የተቀመጠለትን እቃ አየው። ገረመው የእሱን አይነት ልብስ ነበር የቀመጠው ።ወደ ክፍሉ ይዞት ሔዶ ተቀመጠ።የ ዮርዳኖስ አባት የሁለቱን ጓደኛሞች ፍቅር ሲያወራ ውሎ ቢያድር አይጠግብም።በሁለቱ ልጆች ምክንያት ቤተሰቦቻቸው ተዛምደዋል። በእድሜ ደሳለኝ አመት ይበልጣል። ደሳለኝ ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ በሶፍትዌር አንድ አመት አስቆጥሮ ነው የመጣው።ዮርዲ ደግሞ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ውጤት እየጠበቀ ነው።
ቀና አለና ከግድግዳው ጋር የተሰቀለውን የሔዋንን ፎቶ ተመለከተ ።"የእኔ ልዕልት ሺ አመት ኑሪልኝ"አለ ፎቶዋ ላይ እንዳፈጠጠ።
ሔዋን ቀይ መልክ ያላት፣አፍንጫዋ ሰልከክ ብሎ የወረደ፣ጥርሶቿ በስርዓት የተቸመቸሙ እና ብርሀን የሚፈነጥቁት አይኖቿ ዛጎል የሚያካክሉ ሲሆኑ ፀጉሯ ከጀርባዋ ላይ ወርዶ ወርዶ እንደቄጠማ የተነሰነሰ ጡቶቿ የአራት መከራክር ተራራን መስለው የተቀሰሩ።አጠር ያለ ቁመና ያላት እና እና ቀጠን ያለች ሰትሆን ወገቧ ችቦ አይሞላም ወገቧ ተብሎ የተዘፈነላት አይነት ሴት።በአጠቃላይ ውብ የሆነች እንስት ነች።
"አንተ እስከ አሁን አበባውን አልገዛኸውም "አለና ደሳለኝ ዮርዳኖስን ከሀሳቡ አባነነው።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​‍ 😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

❤️ክፍል 5


.
.
.
"አፈር ብላ ጥላ ቢስ ሳታንኳኳ ትገባለህ እንዴ?"አለ ዮርዳኖስ
"ሙሽራው ዘንጠሀል ዮርዲ ሙት እንዴት እንዳመረብህ"አለ ደሳለኝ "ባክህ ይሔንን ልበስ እና ማን እንደዘነጠ ትነግረኛለህ።"አለና ዮርዳኖስ አባቱ የገዛላቸውን ሰጠው ።" አረ በለው ማች ማድረግ ግን ፋዘርየ ተቸገሩ" አለ የለበሰውን ልብስ አውልቆ አዲሱን እየለበሰ።
"አሱን ተወው እና በዚህ ተበልጠሀል" ብሎ ዮርዳኖስ ሀብሉን ከሸሚዙ አውጥቶ አሳየው ።
"አንተ ምን ነክቶህ ነው አሱን እኮ ለሔዋን እንድትሰጣት ነው ፋዘርየ የገዛው ፍጠነህ አውልቅ"አለ ደሴ እየሳቀ
"አንተ ደግሞ ይሄን የት አወቅክ? እኔ እኮ ኤች ፊደል ምንድን ነው እያልኩ ነበር ለካ ሔዋን! ነው ምን አይነት ቀሽም ነኝ በናትህ "አለ ዮርዲ ።
"ስማ ፋዘርየ በቃ ብቸኛ ወንድ ልጅ ስለሆንክ እንደዚህ ያቀብጥሀል የእኔ አባት ቢሆን እንኳን ፍቅር የጀመርኩበትን ሊያከብርልኝ እንዳፈቀርኩ ስነግረው ነው ገና ከቤተሰቡ ዜግነቴን የሚነጥቀኝ ።"አለ ደሳለኝ እየሳቀ።ደሳለኝ ለብሶ ጨረሰ እና ወደ መስታወቱ ተጠጋ "እ ዮርዲ እንዴት ነኝ ?"አለ
"ዘናጭ ቁጥር አንድ፤አንተ እኮ ቅጠል ብትለብስም ያምርብሀል"
ብሎ እንደተናገረ አቶ ተሾመ ገባ ።"በለው ውበት መንታ ልጆች መሰላችኋል" አለ
"እንዴ ምንድን ነው አባዬ ራስህን ተመልክተሃል?ቆይ ምንድን ነው ነገሩ ግራ አጋባችሁኝ"እኮ አለ ዮርዲ የአባቱን ሱፍ እያደነቀ
አቶ ተሾመ ሳቀና የያዘውን ሽቶ በላያቸው ላይ አርከፈከፈው ።
"በሉ ወደሳሎን ኑ ምግብ ቀርቧል።"ብሎ ትቷቸው ወደ ሳሎን ሔደ።
"ደሴ የምታውቀው ነገር ካለ ንገረኝ ሰው ሁሉ ምን ሆኗል?"አለ ዮርዲ
"በል ነገር አትፈልፍል ምሳ አልበላሁም መብላት እፈልጋለሁ"አለ ደሳለኝ
"የዛሬ ምሳ በመክሰስ ሰዐት ሆኗል"አለና ወደ ሳሎን ሲገቡ ወለሉ በቄጠማ አብዷል ።ቤዛ እና ወይዘሮ አለም ተመሳሳይ ጥልፍ ያለው ጥበብ ለብሰዋል ።እድሜ ጠገቧ አያቱ የሀበሻ ቀሚስ ለብሰው ሶፋ ጋር ተቀምጠዋል ።እልፍነሽ እንደነገሩ ዘንጣ ረከቦቱ ጋር ተቀምጣለች።ዮርዲ እና ደሴ የዮርዳኖስን አያት ጉልበታቸውን ስመው ተመርቀው ወደ ምግብ ጠረጴዛው ሔደው ከእነ ቤዛ ጋር ተቀላቀሉ ።ወይዘሮ አለም ወደ ደሴ ጆሮ ጠጋ ብላ "መልዕክቴን ለእናት አባትህ አድርሰሀል?"ብላ አንሾካሾከች ።
ደሳለኝ አዎንታውን በምልክት ለገሰ።
ዮርዳኖስ አሻግሮ ሲመለከት ሶስት ካሳ ቢራ ተደርድሮ አየ።"አንተ ደሴ ምንድን ነው ከእኔ የተደበቀው?"አለ ዮርዳኖስ ደሴን ተጠግቶ
"ሊያገባ ነው "አለ ደሴ
"ማነው የሚያገባው ?"አለ ዮርዲ ደንግጦ
"አቶ ተሾመ "አለና ደሴ ሳቀ። አነጋገሩ ስለገረመው ዮርዲ እየተናደደ ቢሆንም ሳቀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ምግብ አንደነገሩ ተቀማመሰ እና እልፍነሽ ቡና ልታፈላ ጉድ ጉድ ማለት ጀመረች ።በር ተንኳኳ ። እልፍነሽ ልትከፍት ሔደች
"ቤት ለእምቦሳ"ብለው የደሴ ቤተሰቦች ገቡ ።
"እምቦሳ እሰሩ "ብለው የዮርዳኖስ ቤተሰቦች ሰላምታ ተለዋውጠው ቦታ ስጥተው አስቀምጧቸው ።
"ሙሽራው ና እስኪ ይሔን አስቀምጥ"አለና የደሴ አባት አቶ ሀብቴ የተጠቀለለ ጠርሙስ ለዮርዲ ሰጠው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"አንተ ደሴ 11:30 ሆነ እኮ ሔዋንን እናግኛት"አለ ዮርዲ
"ተረጋጋ ሰዓት አለን ፥ደግሞ ደውላልኝ ነበር ስትጨርስ እንደምትደውል ነግራኛለች።"አለ ደሴ
"እሺ አንተ ግን እኛ ላይ ነው የምታድረው።ያንን ቢራ አመድ ስናደርገው ነው የምናድር።መቼም ምክንያቱ ባይገባኝም ድግስ ተደግሷል ድግሱን ትተህ አትሔድም "አለ ዮርዲ
"ትጠራጠራለህ እንዴ የትም አልሔድም። ሰማ ሳልረሳው ሔዋን የግጥም ደብተርህን አዘጋጅተህ አስቀምጥልኝ ብላለች" አለ ደሴ
"ምነው ለምን ፈልጋው ነው"
"ዘልዛላ ነው በስነ ስርዓት አያስቀምጥም "አለችኝ አለ ደሴ
"አትዋሻ !"አለ ዮርዲ
"ዮርዲ ሙት እንደዛ ነው ያለችኝ"አለ ደሴ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከደቂቃዎች በኋላ የግቢ በር ተንኳኳ ።እልፍነሽ ሔዳ ከፈተችው።
ቤት ውስጥ የነበሩ አይኖች በሙሉ ወደ በሩ ተወረወሩ ።
ዮርዳኖስ ግን አፉን ከፍቶ ቀረ።
"ደሴ ህልም ነው በለኝ ምንድነው የማየው"አለ እየተንተባተበ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​‍ 😋ሰሜናዊት ሙሽራ😋

💞ክፍል 6


.
.
.
"ደሴ ህልም ነው በለኝ።ምንድን ነው የማየው?"አለ ዮርዲ እየተንተባተበ ።
"ሙሽራው አታስፎግራ ቀብረር ብለህ ቁም።ቤተሰብ ትውውቅ መሆኑ ነው"አለ ደሴ ዮርዳኖስን ጠጋ ብሎ
"የምን ቤተሰብ ትውውቅ ?እኔ የሔዋንን ቤተሰቦች አላውቃቸውም?ወይስ የእኔ ቤተሰብ ሔዋንን ከእነ ቤተሰቧ የማያውቅ መሆኑ ነው?አንድ ሰፈር ውስጥ ለብዙ አመታት እኮ ኖረናል።ደሴ አባዬ ምን እያደረገ እንደሆን ምንም ሊገባኝ አልቻለም።"አለ ዮርዲ
"አንተ ፈገግ በል ሔዋን እያየችህ ነው አታስደብራት"አለ ደሴ
ዮርዳኖስ የግዱን ፈገግ ብሎ ለቤተሰቡ ሰላምታ ሰጠ።ሁሉም ቦታ ቦታውን ይዞ ተቀመጠ።የደሳለኝ እናት አና አባት አንድ ሶፋ ላይ፣የሔዋን ቤተሰቦች አብርሀምን ጨምሮ ሌላ ሶፋ ላይ ።ደሴ፣ዮርዲ እና አቶ ተሾመ አብረው ተቀምጠዋል።ቤዛና ወይዘሮ አለም መስተንግዶውን ተያይዘውታል ።እልፍነሽ ቡናውን እያደራረሰች ነው።
ዮርዳኖስ በሀፍረት ሽምቅቅ እንዳለ ቀና ብሎ ሔዋንን ተመለከታት ።በጥበብ አሸብርቃ ሙሽሪት መስላለች።"ሺ አመት ኑሪልኝ የእኔ ልዕልት።"አለ በውስጡ ።አይኑን ከእሷ ላይ መንቀል አልቻለም።የእሱ አልመስልህ አለችው ።ደሴ በጫማው እረገጠ እና "አረ ፍሬንድ ንቃል ምንሼ ነው "አለ ደሴ
"ወይ አፈጠጥኩ እንዴ "አለና በሀፍረት አንገቱን ደፋ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ቡናው ተጠጥቶ፣ምግቡ ተበልቶ አሁን ቢራ ተከፍቶ ጨዋታው ደርቷል ።አቶ ተሾመ ደሴን አጁን ይዞ ወደ ኮሪደሩ ወሰደው እና የሆነ ነገር አንሾኳሽከው ተመለሱ።አቶ ተሾመ ሔዶ ሲቀመጥ ደሴ ከምግብ ጠረጴዛው አጠገብ ቆመና አጨበጨበ።ጆሯችሁን አውሱኝ ለማለት ነበር።ሁሉም በፀጥታ ወደ ደሳለኝ ዞሩ።
"በመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለመጣችሁ በአቶ ተሾመ እና በወይዘሮ አለም ስም ምስጋናየን አቀርበዋለሁ ።"ጭብጨባ ተከተለ።
"በመቀጠል ወንድሜ ዮርዳኖስ እንዲሁም እህቴ ሔዋን እንኳን ለሁለተኛ አመት የፍቅር ጅማሪያችሁ አደረሳችሁ እያልኩ ኬኩን እንድትቆርሱ እጋብዛችኋለሁ ።"አለ ደሴ ።ሔዋን እና ዮርዲ በጭብጨባ ታጅበው ወደ ምግብ ጠረጴዛው አመሩ።ኬኩን እየቆረሱ ቤዛ ፎቶ አነሳቻቸው ።ደሳለኝ ምስጋና አበርክቶላቸው ወደ መቀመጫቸው ሸኛቸው ።
"በመቀጠል ወንድሜ ዮርዳኖስ ለሔዋን ስም እንዲያወጣላት እና አንዲዘፍንላት ።እጋብዛለሁ ።"አለ ደሴ ።ጭብጨባ ተከተለ ።
ዮርዲ ያላሰበውን ዱብዳ ነገር ደሴ ሲያወርድበት በድንጋጤ ድርቅ ብሎ ቀረ።ሁሉም መነሳቱን እየጠበቁ እንደሆነ ሲመለከት የግዱን ፈገግ ብሎ ተነሳ ።
"እሺ በቅድሚያ ለዚች ልዕልት ልጅ ስም እንድታወጣላት ዕድል ሰጠሁህ "አለ ደሴ እየሳቀ
ዮርዲ በድንጋጤ ብዛት አፍንጫው ላይ ችፍፍ ያለውን ላቡን በእጁ ሞዠቀ እና መናገር ጀመረ።
"በመጀመሪያ ያላሰብኩት ነገር ስለተፈጠረ መደንገጤን አልክድም ። እንደዚህ አይነት ፕሮግራምም ሰርፕራይዝም አጋጥሞኝ አያውቅም ።ሁላችሁንም ላመሰግን እወዳለሁ ።ሲቀጥል ለዚች እንደ ከዋክብት ለምታበራ ልጅ የሚመጥናት ስም ባይኖረኝም "ሳልዕሳዊት"ብየ አውጥቼላታሉሁ "አለ ዮርዲ
"ትርጉም "አለ ደሴ እየሳቀ
"ትርጉሙ ሶስተኛዋ ማለት ነው "አለ
"ሶስተኛዋ ምን?"አለ የሔዋን አባት አቶ አንድነት
ደሳለኝ ቀለብ አደረገና "እንግዲህ እኔ ሲመስለኝ በአስራ ስምንት አመት ውስጥ ያፈቀራት ሶስተኛዋ ሴት መሆኑ ነዉ።"አለና ሳቀ።የእሱን መሳቅ ተከትሎ ቤቱ በሳቅ ተናጋ።
ዮርዲ ሳቁ ጋብ እስኪል ጠበቀና"እንተ ብቻችንን ስንገናኝ ትነግረኛለህ"አለ ዮርዲ ደሴን በፍቅር ጎሸም አድርጎ ።ቀጠለና"ሔዋን ማለት ለእኔ ከእናቴ እና ከእህቴ ቀጥሎ ያገኘኋት ሶስተኛዋ ሴት ነች ።ስለዚህ ሳልዕሳዊት ።ተናግሮ ሳይጨርስ ጭብጨባ ቀደመው ።
"ዝፈንላት ላላችሁት ሁለት አመት ሙሉ ዘፍኜላት ክር ጨርሻለሁ ።እንደማፈቅራት ንገሩልኝ" አለና ሀብሉን ከደረት ኪሱ አውጥቶ ሔዶ አንገቷ ላይ አደረገላት እና ግንባሯን ሳም አድርጎ ወደ መቀመጫው ተመለሰ።ጭብጨባ ተከተለ።
"አሁን ደግሞ ለአቶ ተሾመ መድረኩን እለቃለሁ ።"አለና ደሴ እየሳቀ ወደ ቦታው ተመለሰ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አቶ ተሾመ ተነሳና መናገር ጀመረ ።"በመጀመሪያ ልጄ ዮርዲ ላመሰግንህ እወዳለሁ ።በአንተ ምክንያት ከሁለት ቤተሰብ ጋር ተዛምጃለሁ።ከሔዋን ቤተሰቦች እና ከደሴ ቤተሰቦች።እኔ እና የሔዋን አባት አቶ አንድነት ተመካክረን ስጦታ ገዝተናል ።እሱም ምንድን ነው እ....እንግዲህ ልቦቻችሁ በፍቅር ተሳስረዋል ።እኛ ደግሞ በቀለበት ልናስተሳስራችሁ ወደድን።"አለና የቀለበት ፓኬቱን ለዮርዳኖስ ሰጠው ።
ቀለበቱን አጠለቀላት እሷም እንደዚሁ ።ቤቱ በዕልልታ እና በጭብጨባ ድብልቅልቅ አለ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ፕሮግራሙ ተጠናቀቀ ።የደሳለኝ ቤተሰቦች እና የሔዋን ቤተሰቦች አመስግነው ወደ እየቤታቸው ተበተኑ ።
ሔዋን፣አብርሃም እና ቤዛ ስፕራይት ይዘው ደሳለኝ እና ዮርዳኖስ ደግሞ ቢራ እየጠጡ።የዮርዳኖስን ክፍል በአንድ እግሯ እስክትቆም ድረስ በሳቅ በጨዋታ አመሹ ።
ሔዋን ስልኳን ተመለከተች 3:08pm ይላል ።"እንግዲህ ሸኙን ሊነጋ እኮ ነው"አለች እየሳቀች
"ገና በሶስት ሰዐት "አለች ቤዛ
"አይ መሽቷል ይሒዱ" አለና ዮርዲ ተነሳ ።ከመሳቢያው ውስጥ ደብተሩን አወጣና "ይሔዉ አዘጋጅ የተባልኩት የግጥም ደብተር"አለና ለሔዋን ሰጣት ።
ተቀበለችው እና በተራዋ አብርሀምን ፖስታ ተቀብላ"ይሔው ስጦታየ "ብላ ለዮርዲ ሰጠችው ።
መሳቢያው ውስጥ አስቀመጠው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ደሳለኝ እና ዮርዳኖስ ሔዋንን እና አብርሀምን ይዘው እነ ሔዋን በር ደረሱ ።ሔዋን መጀመሪያ ደሴን አቅፋው ደህና አደር አለች እና ወደ ዮርዲ ተመለሰች ።
ዮርዲ ትክ ብሎ ተመለከታት ።እነኛ ውብ አይኖቿ እንባ ቋጥረዋል።
"ምነው እማ ምን ሆንሽብኝ"አለ እንባዋን እየጠረገላት
"ደስ ስላለኝ ነው "አለችው እና ከንፈሩን በከንፈሯ ከደነችው ።
አንገቱ ውስጥ ሆና "ጠብቀኝ"አለችው
"እማ ግን ደህና ነሽ ?"አለ ዮርዲ
"ፖሰታውን ነገ ክፈተው "አለች እና ጥብቅ አድርጋ አቅፋው" ደህና እደር "ብላ እያለቀሰች ከአብርሃም ጋር ተያይዘው ገቡ።

ይቀጥላል
​​‍ 😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 7


.
.
.
ከአስር አመት በፊት .....................................
ከኮረብታማው ጥንታዊ አምበር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ግርጌ ድሮ በጣሊያን ወረራ ጊዜ በጣሊያን ይዞታ ውሰጥ የነበረው እና ጣሊያን በአባት አርበኞች ድባቅ ተመታ ሴራዋ ተንኮላሽቶ አፍራ ስትመለሰ ስራ ያቆመው የድንጋይ ወፍጮ እና ሴራሚክስ አምራቹ ሰፊ ግቢ በ1999 ዓ.ም እደሳ ተደርጎለት ስራ ጀመረ ።ባላ ሀብቱ ከአዲስ አበባ መጥቶ የገዛው ሲሆን ስሙ ኢሳያስ ተ/አረጋይ ይባላል ።የደብሩ አስተዳዳሪ እና ጠባቂ የአባ ቶማስ ዘመድ ነው አሉ እየተባለ ጭምጭምታ ይሰማል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጥንታዊው አምበር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተው ሁለቱ ወንድማማቾች ማለትም አብርሀወአጵብሀ ወይም ኢዛና እና ሳኢዛና ኢትዮጵያን ይገዙበት በነበረበት ዘመን ክርስቶስ ከተወለደ 300 አመት ገደማ እንደተመሰረተ አባቶች ይናገራሉ።ቤተ ክርስቲያኗ በግራኝ አህመድ ወረራ ጊዜ የጥፋቱ ገፈት ቀማሽ እንደሆነች እና እንደተቃጠለች አንዳንድ የታሪክ መፅሐፍት አና አፈ ታሪኮች ያስረዳሉ።ከዚህ በተጨማሪ ግን ለአካባቢው ማህበረሰብ እንቆቅልሽ ሆኖበት እየኖረ ያለው ነገር ከደብሯ በሰተ ደቡብ በኩል ያለው ሰፊው ኮረብታማ ቦታ ነው።ቦታው አጅግ የሚያስገርም ከመሆኑ በተጨማሪ ሲቆሙበት የሚያሰማው ድምፅ ለእንግዳ ሰው በድንጋጤ ይገድላል።ቦታው ሲረግጡት የሚያወጣው ድምፅ ከከበሮ አይተናነስም ።ህብረተሰቡ ውስጡ ዋሻ ሰለሆነ ነው አንደዚህ የሚጮኸው ይላሉ ።እውነት አላቸው።አዎ ዋሻ ነው ማረጋገጫው ደግሞ ከኮረብታው ምስራቃዊ አቅጣጫ ወረድ ብሎ ለዋሻው መግቢያ ተብሎ የተሰራ በሚመስል መልኩ ቅርፅ አልባ መስኮት መሳይ ቀዳዳ አለ።በተለምዶ የዘንዶው ዋሻ በር ተብሎ ይጠራል። ጥንት አባቶች እና እናቶች ንብረታቸውን ከጠላት ለማሸሽ የቆፈሩት ዋሻ ነው ይባላል ።ወስጡ መንፈሳዊ የሆኑ እና መነሰፈሳዊ ያልሆኑ ሀብቶች እንደተደበቁ እና በዘንዶ እንደሚጠበቅ ሰፊው ማህበረሰብ ብትጠይቀው የሚሰጥህ መልስ ነው።ወደ ውስጥ ግን ማንም አልገባም ማንም ሊገባ አልሞከረም።ምክንያቱም የዘንዶ እራት መሆን የሚፈልግ የለም።እየተባለ ይወራል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከአምስት አመት በፊት ........................
የሔዋን ትልቅ ወንድም የአቶ አንድነት የግል ልጅ ምናሴ አንድነት ይህን የጥንታዊ ቅዱስ ቂርቆስ አስገራሚውን ኮረብታማ ቦታ ጎብኝቶ የተመለሰ ማግስት የውሀ ሽታ ሆነ።የአካባቢው ኗሪ የዮርዳኖስን ቤተሰቦች ጨምሮ ምናሴ የት ደረሰ ብለው ጠየቁ።የሔዋን ቤተሰቦችም ምናሴ ዲቪ ደርሶት አሜሪካ ሔደ ብለው ተናገሩ ።ኗሪው የአቶ አንድነት ልጅ አሜሪካ ሔደለት ብለው የአቶ አንድነትን ቤት በድግስ አስጨንቀውት ሰነበቱ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከአንድ አመት በፊት .....................................
"እሰኪ ስለ ስደት ምን ትያለሽ ?"ሲል ሔዋንን ዮርዳኖስ ጠየቃት
"ህዝባችን እኮ ኑሮን ለማሸነፍ ቤተሰብ ለመርዳት ራስን ለመለወጥ ብሎ ከእናት ሀገሩ እየወጣ በበረሃ የጊንጥ ሲሳይ በባህር ደግሞ የአሳ ነባሪ እራት እየሆነ ፣ገሚሱ ደግሞ አልሳካለት ብሎ ተጠርዞ ሲመለስ ተስፋ ቆርጣ ፤የዚች ምስኪን ሀገር እጣፈንታ እርሱ ትክሻ ላይ መሆኗን ዘንግቶ በሱስ እየዳከረ የሱን ህይወት አባላሽቶ እሱን እያዩ ለሚያድጉ ታናናሽ እህት እና ወንድሞቹ ነገን እንዳያዩ የአይን ቆብ ሆኖባቸው የተሸከመውን የሀላፊነት ቀንበር ከ ጫንቃው ላይ ጥሎ ለቤተሰብም ለሀገርም ሸክም ይሆናል።ተሳክቶለት የወጣውም በአፍ ብቻ እናት ሀገሬን እወዳታለሁ።ከማለት ውጭ ለዚች ሀገር ምን የፈየደላት ነገር አለ?እንዲያውም የዚች ምስኪን ሀገር ጥሪት ሊያጫርስ ከነጫጭባ ፈረንጅ ባላንጣ ጋር ሆኖ ለወጥመዱ ሽቦ ሲያቀብል ይውላል። እስኪ የእኔን ወንድም ምናሴን ተመልከት ።ለእናት ሀገሬ እሞታለሁ እኔ የምኖረው እሷ ስትኖር ነው ።ጥርኝ አፈሯን ልሼ እንዳደኩ ሁሉ የላስኩባትን ጥርኝ አፈር ወርቅ አድርጌ እመልስላታለሁ እያለ ኖሮ እድል ሲቀናው ይኸው ትቷት ሔደ።ምን አደረገላት?ምንም።ጭንቅላት ያላቸው ሰዎች በእስኮላር መልኩ ይወሰዳሉ ።ተምረው መጥተው ለዚች ሀገር የፈየዱት ነገር አለ?የለም።የእግሯን እሾህ በመርፌ ለመንቀስ የሞከረ ምሁር እስከ አሁን አላየሁም አልሰማሁም ።በሔዱበት ሀገር እስረኛ ሆነው ይቀራሉ ።እስኪ እሩቅ ሳንሔድ ከዚው ከመንደራችን እንነሳ ።እንዳወቀ ካሴ ምሁር ይባላል ።ሳይንቲስት ይባላል ።ግን ሳይንቲስት ሆኖ ለዚች ሀገር ምን ጠቀማት?ይልቅ በችግር ማቃ የሞተችውን እናቱን ለመቅበር በእልፍ አእላፍ የፈረንጅ ወታደር ታጅቦ።መጣ።አስቀበረ።እንባው እንኳን ሳይደርቅ ነበር አንጠልጥለው የወሰዱት ።ይሔ ዘመናዊ ባርነት አይደለም ?አየህ የአገርህን ሰርዶ በአገርህ በሬ ድሮ ቀረ። የአገርህን ጥሪት የአገርህ ልጆች
አሳልፈው ሰጡ ለፈረንጆች ።ብሎ አገሬው መተረት ከጀመረ ቆይቷል ።ይቺን ሀገረ እግዚአብሔር ይቺን የተስፋ ምድር የቺን የቃል ኪዳን ሀገር ኢትዮጵያን ፤ቀቢፀ ተስፋ በልባችን ያደረብን ወጣቶቿ ከተስፋ መንገድ እየራቅን በትንሳኤዋ ፋንታ ተስፋዋን እያጨለምን እኛ ሌላ ሀገር እንሽታለን ።የእኛን ቤት እያፈረስን ለባዕድ አገር ምሰሶ እንተክላለን ።"ብላ በምሬት ስትናገር ቆይታ "የግል አሰተያየቴ ነው"አለችው።

ይቀጥላል
በደህንነት ድብቅ ካሜራዎች የተቀረፁ ያልተጠበቁ ክስተቶች https://get.et/34503c242
Forwarded from ༺Mâřķóñãľ༻
Contact us for any kind of string art for your new house, gift, logo…. @babusem 0947187851
ነገ እንደሚሞት ሰው ዛሬን ተደሰት
ዘላለም እንደሚኖር ሰው ጠንክረህ ስራ
Hey