TIKVAH-ETHIOPIA
1.63M subscribers
71.7K photos
1.96K videos
252 files
5.21K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

ማርኬቲንግ 📞 0979333111
@TikvahEthMarketingBot

መረጃና መልዕክት ፦ 0998999899

​@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🚚 የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በሰሜን ኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ የሚሆኑ ከ71 ሜትሪክ ቶን በላይ መድኃኒቶች እና የሕክምና ቁሳቁሶች ማሰራጨቱን አስታወቀ። ይህ የሕክምና እርዳታ በትግራይ ፣ በአፋር እና በአማራ ክልሎች በሚገኙ 49 የተለያዩ የሕክምና መስጫ ቦታዎች የሚደርስ ነው። ድጋፉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት በጋራ ባደራጁት የተሽከርካሪ…
🚚 በግጭት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ አክሱም እየተጓጓዘ ይገኛል።

'ማረት' እንዳሳወቀው ከሆነ የድጋፍ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች አክሱም ገብተው በአቅራቢያ በሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች እየተከፋፈለ ነው።

ይህንን ሰብዓዊ ድጋፍ በማስተባበርና በማቅረብ ረገድ ለሲአርኤስ ኢትዮጵያ እና ለአሜሪካ ሕዝብና መንግሥት ምስጋና ቀርቧል።

'ማረት' በትግራይ ህብረተሰቡን ለመደገፍ እና ጫናዎችን ለማቃለል የተቀናጀ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አመላክቷል።

ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤409👏61🕊26😁14🤔13😭12🙏10🥰4💔3
TIKVAH-ETHIOPIA
የሺርካ ውሎ ምን ይመስላል ? በሺርካ ትናንት ጥቃት ከደረሰ ወዲህ ስለላለው ሁኔታ ዛሬ ጠዋት ቃላቸውን የሰጡት የወረዳ ቤተክህነቱ አመራር፣ " የሞቱት ተቀብረዋል ፤ ሌሊቱን ሰላም ነው ያደርነው " ብለዋል። ከሰዓት 12 ሰዓት ገደማም፣ " እስካሁን ሰላም ነን ፤ አዲስ ጥቃት የለም " ሲሉ ተናግረዋል። " ዝም/ጸጥ ያለ ሁኔታ ነው ያለው። ግን አሁንም ስጋት አለብን። ሁሉም ባለበት ተደብቆ ነው ያለው…
#Update : በአርሲ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ 60 ምዕመናን መገደላቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳወቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአርሲ ዞን በቅርቡ በተፈጸሙ ጥቃቶች ምዕመናን መገደላቸውን፣ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውንና ከ20 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን ገልጾ፣ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቅና ጥቃቶቹን የፈጸሙትን ለሕግ እንዲያቀርብ አሳሰበ።

ቅዱስ ሲኖዶሱ ዛሬ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ባወጣው የሐዘን መግለጫ፣ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በመርቲና ሸርካ ወረዳዎች ጥቅምት 10 እና 14 ቀን በተፈጸሙ ጥቃቶች ምዕመናን መገደላቸውን ከአርሲ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት የቀረበውን ሪፖርት በሐዘን መቀበሉን አስታውቋል።

በመርቲ ወረዳ አንጋዳ ቀበሌ ጎራ ሲሊንጎ በተባለ አካባቢ 14 ምዕመናን፣ በሸርካ ወረዳ ጠሬታ ጮሌ ቢርቦ በተባለ አካባቢ ደግሞ 46 ምዕመናን መገደላቸውን መግለጫው ያመለክታል።

በተጨማሪም 20 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የተቃጠሉ ሲሆን፣ ከ20 በላይ ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል እንደሚገኙ ተገልጿል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ በአርሲ ሀገረ ስብከትና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ ግድያ፣ መፈናቀልና የአካልና የንብረት ጉዳት እየተደጋገመ መፈጸሙን ጠቅሶ፣ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን አሳስቧል።

ሲኖዶሱ ጥቃቶቹ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብቶችን፣ በሕይወት የመኖርና የሃይማኖት ነፃነትን የሚጥሱ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች እንደሆኑ በመግለጽ በጽኑ አውግዟል። እንዲህ ያሉ ድርጊቶች የሀገሪቱን የመከባበርና አብሮ የመኖር እሴቶች የሚጎዱ መሆናቸውንም አመልክቷል።

በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥትና የጸጥታ አካላት ጥቃቶቹን በይፋ እንዲያወግዙ፣ የዜጎችን በሕይወት የመኖርና የሃይማኖት ነፃነት መብት እንዲያስከብሩ እና በአካባቢው የሚኖሩ ምዕመናን ከተመሳሳይ ጥቃቶች እንዲጠበቁ አሳስቧል።

ጥቃቶቹን የፈጸሙ ግለሰቦች ለሕግ እንዲቀርቡና ተመሳሳይ ድርጊቶች ወደፊት እንዳይደገሙ የሚያስችሉ እርምጃዎች እንዲወሰዱም ጠይቋል።

ቤተክርስቲያኗ በጥቃቶቹ ለሞቱት ሰዎች ቤተሰቦችና ለተጎጂዎች መጽናናትን በመመኘት፣ ለሟቾች ዕረፍተ ነፍስንና ክብረ ሰማዕታትን እንዲያድል እግዚአብሔርን መለመኗን ገልጻለች።

በዚሁ መሠረት ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት የጸሎተ ፍትሐት ሥነ ሥርዓት እንዲፈጸም፣ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ/ም ደግሞ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማትና አድባራት የጸሎተ ፍትሐት ሥነ ሥርዓት እንዲካሄድ መወሰኑን አስታውቋል።

በተጨማሪም ቅዱስ ሲኖዶሱ ከሚመለከተው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ጋር በመወያየት በአካባቢው ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት እንዲሠራ መወሰኑን በመግለጫው አስታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
😭1.57K❤344😡186💔71😁33🕊27🙏22😢16🥰7🤔4
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Tigray

ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ወ/ጊዮርጊስ (ጆን መዲድ) በሀገር መከላከያ ሰራዊት በዛሬው ዕለት መያዛቸውን የትግራይ ሰላም ኃይል አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጡ።

ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ዛሬ መያዛቸውን የገለጹት አመራሩ እንዴት እና በምን ሁኔታ የሚሉ ዝርዝር ጉዳዮችን ለጊዜው ከማብራራት ተቆጥበዋል።

ሌላ የትግራይ ሰላም ኃይል ምንጭ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የትግራይ ታጣቂዎች ከፍተኛ አዛዥ ጆን መዲዲ " በሀገር መከላከያ ቁጥጥር ስር ውለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ዛሬ በትግራይ ማእከላዊ ዞን ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር በሀገር መከላከያ ሰራዊት ከበባ ውስጥ ገብተው ተማርከዋል " ሲሉ ነው ያስረዱት።

ጀነራሉ ቀደም ሲል በሀገር መከላከያ ሰራዊት አገልግለው በጡረታ ከተሰናበቱ በኃላ ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምረው ከህወሓት ጎን ተሰልፈው ውጊያ ሲመሩና ሲያዋጉ ነበር።

ከወራት በፊት  "አንድ ትውልድ ለሰዋዕትነት መዘጋጀት አለበት " በሚል ንግግራቸው ሰፊ መነጋገሪያ ሆነው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
2❤764👏252😁102😡44🕊41🙏32😢13🤔12💔6
አዲስ አባባ

የቦሌ አራብሳ - አይሲቲ ፓርክ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የኮንትራት ውል ተቋርጦ ፤ ቀሪውን የግንባታ ሥራ ለማጠናቀቅ በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን መስሪያ ቤት የራስ ኃይል እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ።

" የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ ቀደም ሲል አለማየሁ ከተማ በተባለ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ አማካኝነት ሲከናወን ቆይቷል " ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ " የግንባታ ሥራው በተፈለገው ፍጥነት ባለማከናወኑ ምክንያት የኮንትራት ውሉ እንዲቋረጥ ተደርጓል " ሲል አመልክቷል።

አሁን ላይ የግንባታ ሥራው በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የራስ ኃይል እየተከናወነ ነው።

የፕሮጀክቱ አካል የሆኑ 3 ድልድዮች ደግሞ በሌላ ስራ ተቋራጭ እንደሚገነቡ ተገልጿል።

የአራብሳ -አይሲቲ ፓርክ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት፤ በአጠቃላይ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመትና የእግረኛና አረንጓዴ ስፍራን አካቶ 60 ሜትር የጎን ስፋት አለው።

በአሁኑ ወቅት የሰብቤዝ ንጣፍ ስራ በስፋት በመከናወን ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሳውቋል።

ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በጎሮ በኩል ወደ ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤቶችና አካባቢው ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች አቋራጭ መንገድ በመሆን የጉዞ ጊዜን ይቀንሳል።

በተጨማሪም ከመሐል ከተማ ወደ ጎሮ እና አራብሳ በሚደረግ ጉዞ ላይ ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ በእጅጉ ያቃልላል።

ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
❤934🙏86👏61🥰18😁17🕊11😢8😭8💔6😱4😡4
በ ሊቅ furniture እና በbed solution የወደዳችሁት ጥራት እና አገልግሎት በሶፋ ምርቶችም “ ሶፋ ቤት “  በሚል ስያሜ ጥራት ያላቸውን ምርቶችን ይዘን  መተናል ::
 
ጥንቅቅ ብሎ የተሰራ  በተጨማሪም በፈልጋቹት መንገድ "customize " ማድረግ የሚችሉት::

ሁሉንም ምርቶቻችንን መገናኛ በሚገኘው ሾዉሩማችን በአንድ ቦታ ላይ ያገኗቸዋል::

 የሶፋዎን ነገር በሶፋ ቤት ላይ ይጣሉት!
 
📍 አድራሻችን መገናኛ ከቤልቪው ሆቴል አጠገብ ዲያስፖራ አፓርትመንት

☎️ +251950600000
       +251950700000

 ሶፋ ቤት የሊቅ ፈርኒቸር እህት ኩባንያ!
❤116😢2🥰1💔1
በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ከ2 መቶ ሄክታር መሬት በላይ የተዘራ ሰብልን ላይ ጉዳት አደረሰ።

ከትላንት በስቲያ በሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ወረዳ በሳቅባ ቀበሌ አቁራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በተዘሩ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል።
‎
‎ባለፈው የመኸር ወቅት የተከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ/ኢሊኖ ምክንያት በወረዳው ከ17 በላይ የሚሆኑ ቀበሌዎች ዝናብ ባለማግኘታቸው የእርሻ መሬቶች ጦም አድረዋል፣ እንሰሳቶች ጭምር መኖ ለማግኘት ተቸግረዋል።
‎
‎በሌላ በኩል አብዛኞቹ ቀበሌዎች ደግሞ ከሚጠበቀው ጊዜ ዘገይቶም ቢሆን ውስን ዝናብ ማግኘት ችለዋል። ‎ከነዚህም በወረዳው የተሻለ ምርት ከሚገኝባቸው ቀበሌዎች አንዱ በሆነው የሳቅባ ቀበሌ አቁራ ጎጥ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ከ2 መቶ ሄክታር መሬት በላይ የተዘራ ሰብልን ተጎድቷል።
‎
በተለይ ‎ ፦
- የገብስ፣
- የስንዴ፣
- የባቄላ፣
- የአተር እና ምስር ሰብሎች ላይ ከፍ ያለ ጉዳት ደርሷል።
‎
424 የሚሆኑ አርሶ አደሮች በጉዳቱ ቀጥተኛ ተጎጂዎች መሆናቸውን ከጃናሞራ ወረዳ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
😭505❤248💔59😢42🕊17🙏8🥰7😱4😡4😁2
TIKVAH-ETHIOPIA
በባንክ ሂሳባቸው የሚታየውን ያልተገለጸ ከፍተኛ ገንዘብ "የእቁብ ነው" በማለት ምክንያት ለሚያቀርቡ ግለሰብ ግብር ከፋዮች ጥብቅ ማስረጃ ማቅረብ አስገዳጅ የሚያደርግ የዴስክ ኦዲት ማስፈጸሚያ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ይፋ አድርጓል። • የተሟላ የሂሳብ መዝገብ ለማያቀርቡ የይዘት ፈጣሪዎች ከጠቅላላ ገቢያቸው ላይ 15 በመቶ ግብር ተቀናሽ ይደረጋል። • ለዲጂታል ይዘት አመንጪዎች ክፍያ የሚያመቻቹ መድረኮች…
በ2018 ዓ/ም የግብር ዓመት የንግድ ትርፍ እንደሌላቸው በመግለጽ ኪሳራ ለሚያሳውቁ ግብር ከፋዮች በገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጁ መሰረት ከጠቅላላ ዓመታዊ ገቢያቸው ላይ 2.5 በመቶ " አማራጭ አነስተኛ ግብር " ተሰልቶ እንዲከፍሉ እንደሚደረግ ተገለጸ።

• ግብር ከፋዮች ያሳወቁት ኪሳራ አሳማኝ ምክንያት ካልቀረበበት በአካባቢው ተመሳሳይ ስራ ላይ ከተሰማሩ ነጋዴዎች አማካይ የማትረፊያ ህዳግ ወይም የገበያ ዋጋ ጥናት ጋር ተነጻጽሮ ግብራቸው እንዲስተካከል የሚደረግ መሆኑን የገቢዎች ቢሮ የአሰራር ማስፈጸምያ ያሳያል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የግብርና ታክስ አሰባሰብ ሂደቱን ይበልጥ ውጤታማና ተዓማኒ ለማድረግ ባዘጋጀው "ለ2018 ዓ.ም የታክስ ሂሳብ መግለጫ በግብር ማሳወቂያ፤ የዴስክ ኦዲት ጋይድ-ላይን" ማስፈጸሚያ በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎችና የክፍያ ሥርዓቶች ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ የቁጥጥር አሰራሮች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት፣ በንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚፈጸሙ የጥሬ ገንዘብ ክፍያዎች እስከ 50 ሺህ ብር ብቻ የተገደበ ሲሆን ይህም በአንድ ሰው፣ በአንድ ቀን እና በአንድ ግብይት ላይ የተከፈለ ጠቅላላ ክፍያን ያጠቃልላል።

ግብር ከፋዮች ከተፈቀደው ጣሪያ በላይ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ ከፈጸሙ ወጪው በሂሳብ መዝገባቸው ውስጥ ተቀናሽ ተደርጎ እንደማያዝላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብዓት ተቀናሽ ጥያቄያቸው ውድቅ እንደሚደረግ ተመላክቷል።

በተጨማሪም ከ50 ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ የተቀበለ ማንኛውም ግብር ከፋይ ከተፈቀደው መጠን በላይ በተቀበለው ገንዘብ ልክ ተመጣጣኝ አስተዳደራዊ መቀጫ እንደሚጣልበት ሰነዱ ያመለክታል።

በሌላ በኩል፣ በ2018 የግብር ዓመት የንግድ ትርፍ እንደሌላቸው በመግለጽ ኪሳራ ለሚያሳውቁ ግብር ከፋዮች፣ በገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ድንጋጌ መሰረት ከጠቅላላ ዓመታዊ ገቢያቸው ላይ 2.5 በመቶ «አማራጭ አነስተኛ ግብር» (Minimum Alternative Tax) ተሰልቶ እንዲከፍሉ ይደረጋል።

ለቀረበው ኪሳራ አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ ካልተቻለ ግብሩ በአካባቢው ተመሳሳይ ስራ ላይ ከተሰማሩ ነጋዴዎች አማካይ የማትረፊያ ህዳግ ወይም የገበያ ዋጋ ጥናት ጋር ተነጻጽሮ እንዲስተካከል የሚደረግ ሲሆን፣ ከአንድ በላይ የንግድ ዘርፍ ያላቸው ነጋዴዎችም ለእያንዳንዱ ዘርፍ የተናጠል መዝገብ አቅርበው ኪሳራ በታየባቸው ዘርፎች ላይ ይኸው አማራጭ አነስተኛ ግብር ተግባራዊ ይደረግባቸዋል።

ይሁን እንጂ ድርጅቱ በኪሳራ ምክንያት በመፍረስ ላይ ስለመሆኑ ወይም የዕዳ ሽግሽግ እያደረገ ስለመሆኑ የፍርድ ቤት ውሳኔ ማቅረብ የቻለ ግብር ከፋይ ከዚህ ክፍያ ነፃ እንደሚሆን ተገልጿል።

ሰነዱ አክሎም በሪል እስቴት ዘርፍ የተሰማሩ አልሚዎች የገቢና የተጨማሪ እሴት ታክስ አያያዝን በተመለከተም ማስፈጸሚያ አሰራሮችን አስቀምጧል።

በዚህም ደንበኞችን አስቀድመው በማዋዋልና ቅድመ ክፍያ በመቀበል ግንባታ የሚያከናውኑ አልሚዎች ገቢያቸውን በግንባታው አፈጻጸም ምጣኔ የሚያሳውቁ ሲሆን፤ ያለደንበኛ ውልና ቅድመ ክፍያ በራሳቸው ወጪ ገንብተው የሚያጠናቅቁ ደግሞ ግንባታው ተጠናቆ ሽያጭ ሲጀመር "በተጠናቀቀ ውል ዘዴ" ገቢያቸውን እንዲያሳውቁ ተወስኗል።

የሪል እስቴት አልሚዎች የግብዓት ተጨማሪ እሴት ታክስ ማቀናነስ የሚችሉት ቤቶቹ ተገንብተው ሲጠናቀቁ እና ሽያጭ መከናወን ሲጀምር ብቻ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በመሸጥ የተሰማራ አካል ሽያጩ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆንለት ከአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ በፊት ያቀናነሰውን የግብዓት ታክስ ለባለስልጣኑ ተመላሽ የማድረግ ግዴታ የተጣለበት መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰነዱ ላይ ተመልክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
❤507😡193😭32😁20🥰10🤔8🙏7🕊7😱3