Paradise
662 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_11

#ዳግም እማልነቃ እስኪሆን ድረስ ከማልነሳበት ዘላለማዊ እንቅልፍ ከሚመስል ቦታ ቀስ በቀስ አይኔን ገለጥኩ ሁሉም ነገር በብዥታ ይታየኝ ጀመረ እኔ ያለሁበት ክፍል ውስጥ የተቀመጠ ሰው ይታየኛል ትኩረቴን ወደሱ አደረኩ ማንነቱን በደምብ መለየት ባልችልም ፊት ለፊት ካለው ሶፋ መሰል ወንበር ላይ ተቀምጦ አቀርቅሮ የሆነ ነገር እየፃፈ ነው። አይኔ የእይታው አድማስ ቀስበቀስ እየተስተካከለ እየጠራ እየጠራ ሄደ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ የሚፅፈው ሰው ታድኤል ነበር ከዚ ቀደም የማውቀውን ታድኤል አልመስልሽ አለኝ ፊቱ ጠቋቁሯል ፂማም ሆኗል በመጠኑም ቢሆን የከሳ ይመስላል አላየኝም አሁንም አቀርቅሮ ወረቀቱን ጉልበቱ ላይ አስደግፎ እየፃፈ ነበር። ወደራሴ መመለስ ስጀምር የተፈጠረውን ነገር ማስታወስ ጀመርኩ የመጨረሻ ትውስታዬ ነጭ የቤት መኪና ሲገጨኝና ታድኤል ተንበርክኮ እያለቀ ሲያየኝ ነበር! ልቤ መደንገጥ ጀመረ አእምሮዬ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች መምጣት ጀመሩ... ምኔን ነው የተጎዳሁት? አካል ጉዳተኛ ነኝ? ምን ያህል ግዜ ነው ሆስፒታል የተኛሁት ወዲያው ታድኤልን ለመጨረሻ ግዜ የነበረውን መልክ እና አሁን ያለውን አስታውሼ ረጅም ግዜ ሳልነቃ እንደተኛው ገባኝ። ልቤ ከቅድሙ የበለጠ ይመታ ጀመር። ከተኛሁበት አልጋ ለመነሳ ስጣጣር ታዲ ድምፅ ሰምቶ ካቀረቀረበት ቀና አለ ሲያየኝ ነቅቻለው ድብልቅልቅ ያለ ስሜት አየሁበት እየሮጠ መጥቶ አልጋው ስር ተንበርክኮ እጄን ጭብጥ አድርጎ ያዘኝ። ፂ... ፂ... ነቃሽ ....ነቃሽ ፂ... በእውንህ ነው በይኝ በህልሜ እንዳይሆን እእእ ነቃሽ ፂ አለኝ አይኖቹ መንታ መንታ እንባ እያፈሰሱ። እንባዎቹን ሳይ እኔም እያለቀስኩ አው ታዲ ነቃው አልኩት ቀልቤ ለብዙ ግዜ ተኝቼ እንደነበር ይነግረኛል። የታዲ እንባዎች ችምችም ብለው ለብዙ ግዜ እንዳልተቆረጠቅ ከሚያስታውቅበት ፂሙ ውስጥ እየገቡ ይሰወራሉ ፊቱ በጣም ገርጥቷል። ታዲ በደስታ ብዛት እጄን እየሳመ እንባውን አዘራው ወዲው እንባውን እየጠራረገ ዶክተሮቹን ጠርቻቸው መጣው ብሎ እየሮጠ ሄደ...።

ብዙም ሳይቆይ ታዲ ከሁለት ዶክተሮች ጋር ወደ ክፍሉ ገባ ሁለቱም ዶክተሮች በመገረም ነበር ነበር የሚያዩኝ። አንደኛው ዶክተር ወደኔ ቀረብ ብሎ ቀለል ያሉ ምርመራዎችን ካደረገልኝ በኃላ ምን እየተሰማኝ እንደሆነ ጠየቀኝ ነገርኩት እግሬን እንዳንቀሳቅሰው ጠየቀኝ ሁለቲንም እግሮቼን አወዛወዝኳቸው እጆቼንም እንደዛው። ዶክተሮቹ በጣም ተገረሙ ቀላ ያለው ዶክተር በደስታ ስሜት እያየኝ ፅናት! በእውነት እስከዛሬ ድረስ እንዳቺ ከባድ የመኪና አደጋ ደርሶበት በአምላክ ተአምር የዳነ ሰው አይቼ አላውቅም እኛ ብዙ ግዜ በጣም ተስፋ ቆርጠን ነበር አንቺ ግን ምንም ፓራላይዝ ሳትሆኚ ነቃሽ ትልቁ ስጋታችን እሱ ነበር እውነትም እንደስምሽ ፅናት ያለሽ ሴት ነሽ በርቺ አምላክ ከጎንሽ አለ! አለኝ ሌላኛው ዶክተር ደግሞ አልጋው ጎን ላይ ያለውን ዶሴ ወረቀቶቹን አገላብጦ ካየ በኃላ ብዙ ምርመራ እናደርግልሻለን አሁን ያለሽበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ነው.... ብሎ የሚያወራውን ሳይጨርስ እህቴ... ምን ሆነች የሚል ጩኀት ከበሩ ተሰማ የሊና ድምፅ እንደነበር መለየት አልከበደኝም ዶክተሮቹን እየገፈታተረች ወደኔ ስትመጣ እማላውቃት ሴት ሆነችብኝ ሊናን አይቼ በጣም ደነገጥኩ በኔ ምክንያት ብዙ መከራ እንዳየች ብዙ እንደተሰቃየች ህይወቷን እንደጣለች ገባኝ በጣም በጣም ከስታለች እሷም እንደ ታዲ ፊቷ ጠቋቁሮ አጥንታ ጎልቶ ይታያል የዚህ ምክንያት እኔ እንደሆንኩ ሲገባኝ ደም እንባ ማልቀስ ጀመርኩ። ሊና በድንጋጤ ምን እንደተፈጠረ ሳይገባት በእጇ የያዘችውን ፌስታል እያውለበለበች ክፍሉን በአንድ እግሩ አቆመችው ዶክተሮቹ እና ታዲ ሊያረጋጓት ሞከሩ ታዲ አቅፏት ተረጋጊ ሊና መጥፎ ነገር አይደለም ፅኑ ነቅታለች አላት። ሊና ሁሉም ነገር ከአቅሟና ከአእምሮዋ በላይ ሆኖ እኔ መንቃቴን እንኳን ማስተዋል እንደተሳናት እና ያበደች መስሎ ተሰማኝ ሃዘኔ ይበልጥ በረታ። ታዲ እንደነቃው ሲነግራት እየሮጠች መጥታ አቀፈችኝ እኔም አቅፊያት ለረጅም ግዜ ተላቀስን ዶክተሮቹ የተወሰነ ግዜ ለብቻችን እንድናገኝ ብለው ትተውን ሄዱ። ሁለታችንም ተላቅሰን ስናበቃ ሊኑ አስር ግዜ ግንባሬን ትስመኛለች የእህትነትና እናታዊ ፍቅሯ ይበልጥ ሲጨምር ተሰማኝ። ታዲ እሚሆነውን ሁሉ አይኑ እንባ እንዳቀረረ እያየን ነበር ሁለታችንም እንደተቃቀፍን መጥቶ ሁለታችንንም አቀፈን።
ሊናና ታዲ እንዳቀፉኝ ምን ያህል ግዜ ሆነኝ ሆስፒታል ከገባው አልኳቸው ሁለቱም ደንገጥ አሉና ለቀውኝ እርስ በእርስ ተያዩ ፊታቸው ላይ እንንገራት አንንገራት የሚል የማንገራገር ስሜት ይነበብ ነበር። ሊኑ እንባዋን እየጠራረገች እእእ ፂዬ እሱ ችግር የለውም ዋናው አንቺ አሁን በሰላም መመለስሽ ነው አለችኝ እኮ ስንት ግዜ አልኳት ሊኑ እንደማመንታት እያለች ወደ ሰባት ወር ሊሞላሽ ነው መሰለኝ አለችኝ በጣም ደነገጥኩ ሰ..ባ..ት ወ..ርርር! ሰባት ወር 7 ሙሉ ሳልነቃ!
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_12_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:
http://t.me/USA2A
4 u by @USA2A
#ገምሃልያ_ክፍል_12

#ሊኑ ልታረጋጋኝ ሞከረች.. አይዞሽ ፅኑዬ ዋናው አንቺ መንቃትሽ ነው እንጂ የፈጀውን ግዜ ይፍጅ ደሞ ምንም ነገር አላመጠጠሽም ትንሽ ግዜ ናት አይዞ..ሽ አይዞሽ እያለች ታባብለኝ ጀመር ራሴን ለማረጋጋጥ ጣርኩ ግን አልሆነልኝም ላለፉት ሰባት ወራት ምን እንደተፈጠረ ባላውቅም ለሊና እና ታድኤል ቀላል ግዜ እንዳልነበር አልጠፋኝም ሁለመናቸው ለኔ ለኔ ሲሉ በጣም ብዙ እንደተሰቃዩ እና እንደተሸገሩ ገብቶኛል ፀፀተኝ ከታድኤል ጋር የተገናኘንባትን ቀን ረገምኳት ግና ምን ያደርጋል የነሱ ስቃይ ሲያቆም የኔ የስቃይ እና የመከራ ህይወት ሊጀምር ነበር። በደምብ ከተረጋጉ በኃላ ታድኤል ቅድም ሲፅፍባቸው የነበሩትን ወረቀቶች ከመሬት ላይ ሰብስቦ እያስተካከለ ወንበሩ ላይ ተቀመጠ ለምን እንደሆነ ባላውቅም እዚች ወንበር ላይ በጣም ብዙ ግዜ እኔን እየጠበቀ ያሳልፍ እንደነበር ተሰማኝ። እግሩን አጣምሮ ተቀምጦ ወረቀቶቹን አስተካከለና መፃፍ ጀመረ የለበሰው ጥቁር ሰማያዊ ሹራብ አንገቱ ድረስ ሸፍኖታል ከታች የለበሰው ብኒ ሱሪ ጎልቶ ይታያል የሆነ የድሮ ደራሲዎች አለባበ መሰለኝ ወረቀቱን ይዞ ሳየው። ሁሉንም ወረቀቶች ካስተካከላቸው በኃላ ከኪሱ ውስጥ ፖስታ አውጥቶ አጣጥፎ ከተትታቸውና ፖስታው ላይ የሆነ ነገር ፅፎ ከወንበሩ ስር ያለ ካርቶን ውስጥ ከተተው ካርቶኑ ውስጥ ብዙ እንዳሁኑ አይነት ያሉ ደብዳቤዎች እንዳሉ አየው ብዙ ናቸው እሚያደርገውን በጥሞና እየተከታተልኩት ነበር ለማን ነው ይሄንን ሁሉ ደብዳቤ የሚፅፈው አልኩ ለራሴ።
ሊና ድንገት የሆነ ነገር ትዝ ያላት ይመስል ውይ... ብላ ተነሳች ታዲ ደንገጥ ብሎ ምነው አላት ቅድም ዶክተሮቹ እዚ ተሰብስበው ሳያቸው ደንግጬ ላንተ ያመጣሁልህን ምግብ ውጪ ላይ ደፍቼው ነበር አለችውና ወደበሩ አመራች ነገር ግን ውጪው ላይ ምንም ነገር አልነበረም አይ... ፅዳቶቹ ወይም ነርሶቹ አንስተውት ይሆናል አለችና ወደ ታዲ እያየች እራት በልተሃል ይዤልህ ልምጣ አለችው አይ እበላለው ትንሽ ቆይቼ አረፍ በይ አንቺ እኔ ሄጄ አመጣለው ዛሬ የኔ ተራ አይደል አላት። እውነት ታዲ አይሆንም ዛሬ እኔ ላምጣ ደሞ ከነጋ ጀምሮ አልበላህም ብላ መልሱን እንኳን ሳትጠብቅ ሄደች። እኔ እህቷ ከነቃው ጥቂት ሰአታት ሆኖኝ እንዴት አስችላት እንደሄደች አስቤ ገረመኝ ግን ብዙም ሃሳብ አልሰጠሁትም ሃሳቤ ዳግም ወደምወደው ሰው ሆነ ታዲ! አልኩት አይኑን ከበሩ እየመለሰ ወዬ ፂ አለኝ። ለማነው ግን ያንን ሁሉ ደብዳቤ የምትፅፈው እእእ በጣም ብዙ ነው ቅድም ካርቶኑ ውስጥ ስትከት እያየሁህ ነበር አልኩት። ትንሽ አሰብ ካረገ በኃላ እእእ... ላንቺ ነበር የምፅፍልሽ የዛኔ የመኪና አደጋ የደረሰብሽ ቀን ከኔጋ ልንገናኝ የነበረበት ቀን ነበር እና ከዛን ግዜ ጀምሮ እስካሁን እኔና ሊና ሆነን ከዛሬ ነገ ትነቂያለሽ ትድኛለሽ እያልን ስናስብ እና ስንጨነቅ ነበር እህትሽ ሙሉ የህክምናሽን ወጪ መሸፈን ስላልቻለች እኔ በቻልኩት ሁሉ አግዛት ነበር በብርም በሁሉም ነገር አግዛታለው ላንቺ እንዲ መሆን እኔ ምክንያት እንደሆንኩ ይሰማኛል ዘውትር እዚች ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ከአሁን አሁን ትነቂያለሽ እያልኩ እጠብቅሽ ነበር አምላኬን ከገባሽበት ረጅም እንቅልፍ ይቀሰቅስሽ ዘንድ እለምነው ነበር እና ሁሌም እጆችሽን ይዤ አንቺ ባትሰሚኝም ውሎዬን ስለኔ እነግርሽ ነበር እናም አንድ ቀን ምናልባት ወደፊት ስትነቂ እምታነቢው ደብዳቤ ብዬ መፃፍ ጀመርኩልሽ በዛው ቀጠለ አንቺም አልነሳ አልሽ እኔም የዚች ክፍል ብቸኛ ፀሃፊ ሆንኩልሽ አለኝ ፈገግ እያለ። ታዲ ይህንን ሲነግረኝ ምን ያህል የጭንቀት ግዜ እንዳሳለፈ አስቤ ሳላውቀው ከአይኖቼ እንባ ፈሰሰ ታዲ በእጆቹ ዳብሶ ጠረገልኝ እጆቹን በእጄ ይዤ በተማፅኖ እያየሁት ታዲ! አልኩት ወዬ አለኝ አንዱን ደብዳቤ አንብብልኝ ደስ የሚልህን አልኩት። ፈገግ እያለ እውነት? እሺ አለና ወደ ካርቶኑ ሄዶ ካሉት ደብዳቤዎች ውስጥ ፍፕለግ ፈለግ አድርጎ አንዱን አወጣውና ወደኔ ተመለሰ እኔም ለማዳመጥ ዝግጁ ሆንኩ።
ደብዳቤውን ከፈተውና ውስጡ ያለውን ወረቀት አወጣው ለማንበብ ዝግጁ ሆኖ ጉሮሮውን ጠራረገ....
የታድኤል ደብዳቤ ቁጥር አንድ መቶ ሃያ
ጨለማ ውስጥ ያለ ሰው ስለ ብርሃን መስማት አይፈልግም ብርሃንን ማየት እንጂ፣ የከፋው ሰው ስለደስታ መስማት አያስፈልግም ደስታን ማግኘት እንጂ አውቃለው የሄድሽበት የህልም አለም እሩቅ ቢሆንም አንድ ቀን እንደምትነቂ አውቃለው። ታውቂያለሽ ብዙ ሰዎች ብቻቸውን ነው የሚኖሩት ለምን ይመስልሻል? እነሱም በደጉ ዘመን የኔ የሚሉት ሰው ነበራቸው ነገር ግን በአንድ የቀን ጎዶሎ ያንን ሰው ይነጠቃሉ የዛኔ ዳግም ሰው መቅረብ ዳግም ማፍቀር ይፈራሉ። ይገርምሻል አሁን እየዘነበ ነው ሰሞኑን ሸገር ሆዷን ባር ባር እያላት ነው መሰለኝ ለቅሶዎን ቀንን ከለሊት ታሽጎደጉድብናለች ምናልባት ያንቺን ሁኔታ ሰምታ ይሆን። ፂዬ ቅድም ስትናፍቂኝ የተገናኘንበት እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ደርሼ መጣው አምላኬን ያነቃሽ ዘንድ እያለቀስኩ ለመንኩት ፂዬ ባሁን ሰአት ብዙ ስዎች ሆስፒታል ናቸው እነሱም ግን ድነው ተሽሏቸው ዳግም እንደሚራመዱ ተስፋ አላቸው ሲነሱ ማስተካከል የሚፈልጒቸው ብዙ ነገሮች አሏቸው... እያለ ታዲ ሲያነብኝ የሚያነብልኝን ነገር በአእምሮዬ እየሳልኩ ተመስጬ አዳምጠዋለው። ድንገት ሊኑ ስትገባ ማንበቡን አቆመ እእእ ደራሲው እያነበብክላት ነው የፃፍከውን አለችው እየሳቀ አው አላት በል እራት አምጥቼልሃለው እንብላ እኔም አልበላሁም ነበር አለችው እሱም ቆይ አንዴ ፂ እእእ እርቦኛል አለኝና ወደ ምግቡ ሄደ። ታዲና ሊና ሲበሉ ታዲ ያነበበልኝን ደብዳቤ አስቤ ተደሰትኩ ይሄ ሁሉ ደብዳቤ ለኔ ነው! ታዲ እኔን ወዶኛል! እንኳንም መኪና ገጨኝ አልኩና ለራሴው ፈገግ አልኩ እኔና ታዲ በፍቅር ማእበል ስንዋኝ ስንደሰት ስንጋባ... ሁሉም በአእምሮዬ ተሳሉ ደስታዬ ለከት አጣ!። በልተው ከጨረሱ በኃላ ላለፉት ወራት ያመለጡኝን አዳዲስ ነገሮች እየነገሩኝ አመሹ ናፍቆታችንን ተወጥተን እንቅልፍ ሲይዘኝ ተኛው ታዲ ወንበሯ ላይ ኩርምትምት ብሎ ተኛ ሊኒም እኔ የተኛሁበትን አልጋ ተደግፋ ተኛች።
ጠዋት ላይ ኮሽታ እና ሹክሹክታ ሰምቼ ከእንቅልፌ ነቃው። ሊናና ታዲ እየተንሾካሸኩ ነበር እኔ እንዳልነቃ ድምፃቸውን ቀንሰው ያወራሉ። በቃ እኔ ወደስራ ልሂድ አንተ ጠብቃት ከሰአት እመለሳለው ምሳ ምን ላምጣልህ አለችው እሱም እያንሾካሾከ ድምፅሽን ቀነስ አድርጊ እንዳትነሳ ቆይ እንደውም ልሸኝሽ እታች ድረስ አላትና ተያይዘው ወጡ እኔም ከአልጋዬ ቀና ብዬ ወደ በሩ አየው የሉም የኮቴያቸው የዳና ድምፅ ይሰማል ደረጃውን ሲወርዱ ተሰማኝ። ትንሽ ቆይተው እታች የሆስፒታሉ በር ጋር ቆመው ያወራሉ መስኮቱ ክፍት ስለነበር ሁለቱንም በቀላሉ እያየኃቸው ነበር። ትንሽ ካወሩ በኃላ ሊና ታዲን አቀፈችው አስተቃቀፏ ከወትሮው ለየት ያለ መበር ግራ ገባኝ ታዲም አቀፋትና እጁን አንገቷ ስር አድርጎ ከንፈሯን ሲስማት አየው እንደ በኃ ድንጋይ ደርቄ ቀረው እኔ ይህንን ማመን አልችልም አልልችልም አልችልልልልልልም! አይሆንም ታዲ የኔ ነው የኔ ብቻ! ጮህኩ።
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍
ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_13_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:
@USA2A የቀረበ