Paradise
663 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_9

#ሰአቱ መሽቶ ነበር ምናልባት ተኝቶ ከሆነ እንዳልረብሸው ብዬ የፅሁፍ መልእክታ ላኩለት። ሰላም አመሸህ ታድኤል እንዴት ነህ ቅድም ቤተሰቦችህ ቤት ምሳ ግብዣ እንደነበረብህ ነግረኀኝ ነበር እንዴት አለፈ አሪፍ ነው? ይል ነበር። ሃኒ በነገረችኝ መሰረት ሁሉንም ስነስርአት ባለው መልኩ ነበር ላወራው ያሰብኩት ስሙን ማቆላመጥ የለ ምን የለ ይተኛል ብዬ ስላሰብኩ ምላሽ አልጠበቅኩም ነበር ልብሴን ቀያይሬ ገላዬን ታጥቤ ስመለስ ስልኬ ላይ መልእክት ገብቷል የታዲ ነበር ተሯሩጬ ከፈትኩት። አው አሪፍ ነበር ይመስገን አምላክ ደስ እሚል ግዜ አሳልፌ መጣው ቤተሰቦቼ ጋር አለኝ ላወራው ፈልጌ ነበር ግን ሃኒ ያለችኝ ትዝ ስላለኝ አሪፍ ነው ደስ ይላል በቃ አልረብሽህ ሰላም እደር ብዬ ፅፌ ላኩለት። እሱም ሰላም እደሪ አለኝ ተኛው።

ከታድኤል ጋር በየቀኑ ማታ ላይ ከስራ እንደገባው ትንሽ ትንሽ በፅሁፍ ማውራት ጀመርን ብዙም ሳላወራው ቻው እለውና እተኛለው እሱም አንዳንዴ ቻው ስለው አውሪ እንጁ ዛሬ ሁሌ በጊዜ መተኛት ይለኛል። ቀስ በቀስ ትውውቃችንና ቅርርባችን እየቀረበ መጣ ማውራት ከጀመርን 15 ቀን ቢያልፈንም ስለግል ታሪኩ ምንም ጠይቄው አላውቅም በጣም ልቀርበውና ላውቀው እፈልጋለው ግን ችኩልነቴ እሱን ከኔ እንዳያሸሸው እፈራና ሌላ ሌላ ነገር አወራዋለው ሰሞኑን ግን ሳልጠይቀው እራሱ ስለራሱ አንዳንድ ነገሮችን ይነግረኛል ትንሽም ብትሆን ውስጤን ደስ ይለዋል የተወሰነ ለውጥ እንዳለው ይሰማኛል አልፎ አልፎ ብዙም የግል ጥያቆዎች ባይሆኑም እጠይቀዋለው እሱም ቅር ሳይለው ይመልስልኛል። ትውውቃችን እና እምናወራው ነገር ከቀን ወደቀን እየጨመረ መጣ ደስ ስላለኝ ለሃናን ደውዬ ነገርኳት እሷም ደስ እያላት አላልኩሽም እንደሱ አይነት ሰዎች ግዜ እንጂ አንቺ አትፈቻቸውም አይዞሽ እሺ ፂ ያንቺ ይሆናል ግዜ ብቻ ስጪው ራሱ ይበልጥ ይቀርብሻል አለችኝ።
ማታ ማታ ብዙ ግዜ ቤት ስሆን ከታላቅ እህቴ ጋር ቁጭ ብለን ፊልም እናያለን ብዙ ግዜ ሊና የመኝታ ቤቱን ቡኒ ብርድ ልብስ ሳሎን አምጥታ ሶፋ ላይ ተቀምጣ ፊልም ማየት ታዘወትራለች እሷም ወጣት ብትሆንም ግን እንዲ ስልክ መጎርጎር ምናምን አትወድም እኔም በሷ ወጥቼ ብዙም ስልክ ላይ መጣድ አልወድም ነበር ሰሞኑን ግን ስልክ ላይ አፍጥጬ በደስታ ታጅቤ ሳመሽ ሊና ገርሟት ምን ተገኘ ሰሞኑን ጥርስ በጥርስ እየሆንሽ ስልክ ላይ ማፍጠጥ አብዝተሻል አለችኝ እኔም እየሳቅኩ አይ ምንም አልሆንኩም ሊኑ እንዲው ፌስቡክ እየተጠቀምኩ ነው አልኳት በእናታዊ ፍቅሯ እያየችኝ አትነግሪኝም! ወንድ ነው አይደል አለችኝ እኔም እንደማፈር እያልኩ አዎ አልኳት እሷም ይበልጥ ፈገግ እያለች ወደሷ እንደመጣ ትልቁን ብርድልብስ እየከፈተችልኝ እስኪ ንገሪኝ ስለልጁ አለችኝ። ደስ እያለኝ እንደለመደብኝ ሬጬ እቅፏ ውስጥ ጥቅልል ብዬ ገባው። ሊና በፍቅር አይኖቿ እያየችኝ እሺ ንገሪኛ አለችኝ እኔም ይበልጥ እያፈርኩ ጥሩ ሰው ነው በጣም ከ15 ቀን በፊት ነው የተዋወቅኩት እነሃናን ቤት ሄጄ ስመለስ ሜክሲኮ እያልኩ ስለ ታዲ ሁሉንም ነገር ዘርዝሬ ነገርኳት ነገር ግን ስሙን አልነገርኳትም ለምን እንዳልነገርኳት ለኔም ግልፅ አልነበረም። ታውቃለህ ረምሃይ እስከዛሬ ድረስ ከሰራኃቸው ስህተቶች ለኔ ይሄ ትልቁ ስህተት ነበር እስከዛሬ ድረስ በጣም ይፀፅተኛል ለምን የዛኔ የታድኤልን ስም አልነገርኳትም ብዬ እቆጫለው በጣም ምናልባትም የዛኔ ለታላቅ እህቴ የታዲን ስም ነግሪያት ቢሆን ኖሮ አሁን ላይ ሁሉም ነገር በሌላ የህይወት መስመር ይሆን ነበር። ፅናት ያለችው ነገር ግልፅ ስላልነበር አልገባኝም አልኳት ልነግርህ ነው አለችኝ እሺ ብዬ ፅናት እምታወራውን መጠበቅ ጀመርኩ ሳታወቀኝ እንዲው እንደቀልድ በተጀመረ ታሪክ ብዙ ሰአት ፓርኩ ውስጥ እንደቆየው ገባኝ ሰአቱ እየሄደ 10፡30 ሆኗል የፅናት ታሪክ እያስገረመኝ ነበር በአንድ ቀን ውስጥ ሰውን እንዲ መውደድ ይቻላል?
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_10_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:
http://t.me/usa2a
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_10

#ፅናት ታሪኳን ካቆመችበት ቀጠለችልኝ...
እና በቃ ያቺ ቀን በጣም ትፀፅተኛለች ዛሬም ድረስ ምናለ ለእህቴ ስሙን በነገርኳት እላለው። ከዛማ ከታዲ ጋር ያለን ቅርርብ ቀን ወደቀን በጣም እየጨመረ መጣ እሱም እንደመጀመሪያው ጭምት እና ኮስታራ ሳይሆን ያዋራኝ ጀመር አንድ ቀን በግድ አምጬ የፍቅር ጓደኛ እንዳለው ጠየቅኩት። እሱም ቅር ሳይለው በአሁን ሰአት እንደሌለው ግን ከዚ በፊት በጣም ይወዳት የነበረች ፍቅረኛ እንደነበረችው ቀለበት አድርገው ሊጋቡ ቃልኩዳን ተገባብተው እንደነበር ግን በአጋጣሚዎች ምክንያት እሷ ሌላ ባል አግብታ ወደ ውጪ ሃገር እንደሄደች እናም ከዛ በኃላ ልቡን ለማንም ሴት ክፍት አድርጎ እንደማያውቅ ነገረኝ በጣም ልቤ ተነካ እንደዛ ያደረገችውን ሴት በጣም ጠላኃት ታድኤል እንደዚ ለሰው ጭምት የሆነበት ምክንያት ገባኝ አሳዘነኝ በጣም ጥሩ ሰው ነው ማንም ሴት እሱን ብታገኝ እድለኛ ናት ይህንን አምናለው። በአሁን ሰአት ምን አይነት ሴት ለፍቅር እንደሚመርጥ ጠየቅኩት የተረጋጋች አስተዋይ እና የዋህ ሴት በጣም እንደሚወድ ነገረኝ እኔም እሱ ያላትን አይነት ሴት ለመሆን በአቅሜ በጣም እጥራለው አሁን አሁን ላይ የፍቅር ወሬዎች ስናወራ አይደብረውም የሚሰማውን ያወራኛል እኔም እሱ ፍቅርን የጠላበት ምክንያት ስለገባኝ እንደድሮው በጭፍን አልፈርድበትም ከተዋወቅን ወር አለፈን በየቀኑ በፅሁፍ ብናወራም በአካል አግኝቼው አላውቅም የዛኔ ከተገናኘን ውጪ ተገናኝተን አናውቅም። እሱ ራሱ እንገናኝ እስከሚለኝ ድረስ እየጠበቅኩት ነው አይኑን እስካየው በጣም ቸኩያለው በጣም ናፍቆኛል። በየቀኑ ማታ ማታ በቴክስት እያወራን እናመሻለን እኔ ሳልልክ ካመሸው እንኳን እሱ ቀድሞ ይልክልኛል ቢሆንም ግን አሁንም ድረስ ይውደደኝ አይውደደኝ ምንም እማውቀው ነገር የለም ምናልባት እንደ ጥሩ ጓደኛው አድርጎ እያየኝ ይሆናል ብዬ እከፋለው ለሱ ያ በቂ ሊሆን ይችላል ለኔ ግን በቂ አይደለም! እንደሚወደኝና። እንደማይወደኝ ለማረጋገጥ ሃኒ የነገረችኝን አንድ ፈተና ቢጤ ልፈትነው አሰብኩ ፈተናውን ካለፈ ይወደኛል ካላለፈው ግን እንደ ጓደኛው ነው የሚያየኝ ማለት ነው። ማታ ላይ በቴክስት አውርተን ከጨረስን በኃላ ቻው በቃ ሰላም እደር ስለው ዛሬ እንድታዋሪኝ እፈልጋለው አለኝ ታዲ ወሩን ሙሉ እንደዚ ብሎኝ ስለማያውቅ ልቤ ደነገጠ እንደሚወደኝ ሊነግረኝ ይሆን ብዬ አሰብኩ። ምነው ምትነግረኝ ነገር አለ አልኩት እየጓጓው። አይ የለም እንዲው ነገ እሁድ ስለሆነ ስራ ስለማትገቢ ላውራሽ ብዬ ነው ቢያስ እስከ እኩለለሊት ከደከመሽ ግን ተኚ አለኝ። አረ ችግር የለውም እናውራ ምን ይወራ አልኩት ዛሬ ገና እናውራ ስላለኝ ደስ ቢለኝ ም የጠበቅኩት መልስ ስላልነበር ደብሮኛል። ምሽቱን የባጥ የቆጡን ስንፃጫፍ አመሸን እና እኩለሌሊት ሲሆን happy birth day to u dear friend ማንም ሳይቀድመኝ ይህንን ልልሽ ስለፈለኩ ነበር ቅድም እናውራ ያልኩሽ መልካም ልደት ፂዬ ነገ በአሪፉ እንደምታከብሪው ተስፋ አለኝ ብሎ ፅፌ ላከልኝ። ልደቴ ነገ እንደነበር ፈፅሞ ረስቼዋለው ማንም ሳይቀድመው መጀመሪያ እሱ ስላለኝ ደስ አለኝ የተገናኘን ግዜ ልደቴ ከወር በኃላ እንደሆነ ነግሬው እሱን አስታውሶ መልካም ልደት ስላለኝ በጣም ደስ አለኝ በጣምም ገረመኝ ማስታወሱ ግን.... ግን ግን ምን ያደርጋል እሱ እኔን dear friend አለኝ እንደ ተራ ጓደኛው እንጂ እኔ በምፈልገው መንገድ እንደማያስበኝ ተረዳው ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነበር የሚሰማኝ ለይስሙላህ ደስ እንዳለኝ ነገርኩት።
ነገ ከሌላ ሰው ጋር ፕራግራም ከሌለኝ ልደቴን ከእሱ ጋር እንዳከብር ጠየቀኝ በጣም ደስ አለኝ ሁሌ ልደቴን ከእህቴ ጋር ነበር እማከብረው ግን ያሁኑን ከእሱ ጋር ላከብር ወሰንኩ ማን ያውቃል ምናልባት በልደቴ ቀን እሱም እንደሚወደኝ ሊነግረኝ ይሆናል በጣም ደስ አለኝ ምንም ሳላቅማማ እሺ አልኩት። ወር ሙሉ እሱን እየናፈቅኩት መገናኘት እየፈለግኩ ዋጥ አድርጌው እንገናኝ የሚለው ቃል ከእሱ እንዲመጣ ጠበቅኩ ታዲም አላሳፈረኝም በልደቴ ቀን እንገናኝ አለኝ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ሆነ የት እንደምንገናኝ ስጠይቀው ይሄንን ፓርክ ነገረኝ አሁን የተቀመጥንበትን ማለት ነው እኔም ከዚ በፊት ልደት ፕሮግራም.ለአንድ ጓደኛዬ ስናከብርላት አውቀው ስለነበር እሺ አልኩት ይሄ ፓርክ ለኔና ለታዲ ልዩ ትውስታ ያለው ቦታ ነው። ታዲን እስካገኘው ቸኮልኩ የመሸው ለሊት አልነጋልሽ አለኝ ግዜ ሲጠብቁት ይጎተታል።
በጥዋት ተነስቼ ፀጉሬን ልሰራ ፀጉር ቤት ሄድኩ አረፋፍጄ ስመለስ ቤት ውስጥ ሊና ልደቴን ልታከብር ተዘጋጅታ እየጠበቀችኝ ነበር ሊና ልደቴን አንድም ቀን ረስታው አታውቅም ግን ይህንን አመት ስራ እየበዛባት ስለነበር የረሳችው መስሎኝ ነበር ቤት ስገባ መልካም ልደደደ...ት ብላ ሰርፕራይዝ አደረገኝ ደስ አለኝ በስጦታ መጠቅለያ ወረቀት የተጠቀለለ ነገር ሰጠችኝ እየጓጓው ስከፍተው እሚያምር ቀሚስ ነው አሁኑኑ ለብሰሽ አሳዪኝ አለችኝ በደስታ እየሮጥኩ መኝታ ቤት ሄጄ የእራት ልብሱን ቀየርኩት ጥቁር ነው በጣም ያምራል በቁምሳጥኑ መስታወት እየተሽከረከርኩ አየሁት በጣም አምሮብኛል አቤቤቤትትት... አሁን ታዲ በዚ ቀሚስ ሲያየኝ ምን ይላል አልኩ እየሳቅኩ እህቴ በስጦታ ላይ ስጦታ የደረበችልኝ መሰለኝ ዛሬማ ታዲን እማገኘው ይህንን ቀሚስ ለብሼ ነው አልኩ ለራሴ። ሊና ከሳሎን እእእ... ቆየሽ እኮ ምንድነው ምታጓጊኝ ቶሎ በይ እንጂ አለችኝ እየተፍለቀለቅኩ ወደ ሳሎን ሄድኩ የቀሚሱን ጫፍ ወደላይ ከፍ አድርጌ እየተሽከረከርኩ እንዴት ነኝ ሊናዬ አልኳት ያምራል በጣም ይሄድብሻል ልእልት መስለሻል አለችኝ በደስታ። አመሰግናለው ሊናዬ ልእልት የመሆኔ ምስጢር አንቺ የኔ ንግስት ስለሆንሽ ነው አልኳትና ሄጄ ጥምጥም ብዬ አቀፍኳት። እሷም ጥብቅ አድርጋ እያቀፈችኝ በዚ አለም ላይ ማንንም ከምወደው በላይ አንቺን እወድሻለው ብቸኛ እህቴ ነህ አለችኝ እኔም.እወድሻለው ሊኑ አንቺ ለኔ ብዙ ነገር ከፍለሻል እናቴም እህቴም ነሽ ያላንቼ ህይወቴን ሳስበው ይጨልምብኛል እኔም እወድሻለው ስላት እሳም እየሳቀች ውድድድ ነው ማረግሽ አለችኝና እንደህፃን ልጅ ትኮረኩረኝ ጀመር ሰፋ ላይ ወድቀን ብዙ ተላፋን። ሱደክማት ተነሳችና ከአይኖቻ ላይ የደስታ እንባ እየጠረገች ኬክ ከፈለግሽ ፍርጅ ውስጥ አለልሽ እሺ እኔ አሁን ወደ ስራ ልሄድ ነው ማታ ስመጣ ወደውጪ ወጥተን በሰፊው እናከብራለን አለችኝ ድስ እያለኝ እሺ አልኳት። ከታዲ ጋር የተቀጣጠርነው ከሰአት ነበር።

#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_11_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:
http://t.me/usa2a
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_11

#ዳግም እማልነቃ እስኪሆን ድረስ ከማልነሳበት ዘላለማዊ እንቅልፍ ከሚመስል ቦታ ቀስ በቀስ አይኔን ገለጥኩ ሁሉም ነገር በብዥታ ይታየኝ ጀመረ እኔ ያለሁበት ክፍል ውስጥ የተቀመጠ ሰው ይታየኛል ትኩረቴን ወደሱ አደረኩ ማንነቱን በደምብ መለየት ባልችልም ፊት ለፊት ካለው ሶፋ መሰል ወንበር ላይ ተቀምጦ አቀርቅሮ የሆነ ነገር እየፃፈ ነው። አይኔ የእይታው አድማስ ቀስበቀስ እየተስተካከለ እየጠራ እየጠራ ሄደ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ የሚፅፈው ሰው ታድኤል ነበር ከዚ ቀደም የማውቀውን ታድኤል አልመስልሽ አለኝ ፊቱ ጠቋቁሯል ፂማም ሆኗል በመጠኑም ቢሆን የከሳ ይመስላል አላየኝም አሁንም አቀርቅሮ ወረቀቱን ጉልበቱ ላይ አስደግፎ እየፃፈ ነበር። ወደራሴ መመለስ ስጀምር የተፈጠረውን ነገር ማስታወስ ጀመርኩ የመጨረሻ ትውስታዬ ነጭ የቤት መኪና ሲገጨኝና ታድኤል ተንበርክኮ እያለቀ ሲያየኝ ነበር! ልቤ መደንገጥ ጀመረ አእምሮዬ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች መምጣት ጀመሩ... ምኔን ነው የተጎዳሁት? አካል ጉዳተኛ ነኝ? ምን ያህል ግዜ ነው ሆስፒታል የተኛሁት ወዲያው ታድኤልን ለመጨረሻ ግዜ የነበረውን መልክ እና አሁን ያለውን አስታውሼ ረጅም ግዜ ሳልነቃ እንደተኛው ገባኝ። ልቤ ከቅድሙ የበለጠ ይመታ ጀመር። ከተኛሁበት አልጋ ለመነሳ ስጣጣር ታዲ ድምፅ ሰምቶ ካቀረቀረበት ቀና አለ ሲያየኝ ነቅቻለው ድብልቅልቅ ያለ ስሜት አየሁበት እየሮጠ መጥቶ አልጋው ስር ተንበርክኮ እጄን ጭብጥ አድርጎ ያዘኝ። ፂ... ፂ... ነቃሽ ....ነቃሽ ፂ... በእውንህ ነው በይኝ በህልሜ እንዳይሆን እእእ ነቃሽ ፂ አለኝ አይኖቹ መንታ መንታ እንባ እያፈሰሱ። እንባዎቹን ሳይ እኔም እያለቀስኩ አው ታዲ ነቃው አልኩት ቀልቤ ለብዙ ግዜ ተኝቼ እንደነበር ይነግረኛል። የታዲ እንባዎች ችምችም ብለው ለብዙ ግዜ እንዳልተቆረጠቅ ከሚያስታውቅበት ፂሙ ውስጥ እየገቡ ይሰወራሉ ፊቱ በጣም ገርጥቷል። ታዲ በደስታ ብዛት እጄን እየሳመ እንባውን አዘራው ወዲው እንባውን እየጠራረገ ዶክተሮቹን ጠርቻቸው መጣው ብሎ እየሮጠ ሄደ...።

ብዙም ሳይቆይ ታዲ ከሁለት ዶክተሮች ጋር ወደ ክፍሉ ገባ ሁለቱም ዶክተሮች በመገረም ነበር ነበር የሚያዩኝ። አንደኛው ዶክተር ወደኔ ቀረብ ብሎ ቀለል ያሉ ምርመራዎችን ካደረገልኝ በኃላ ምን እየተሰማኝ እንደሆነ ጠየቀኝ ነገርኩት እግሬን እንዳንቀሳቅሰው ጠየቀኝ ሁለቲንም እግሮቼን አወዛወዝኳቸው እጆቼንም እንደዛው። ዶክተሮቹ በጣም ተገረሙ ቀላ ያለው ዶክተር በደስታ ስሜት እያየኝ ፅናት! በእውነት እስከዛሬ ድረስ እንዳቺ ከባድ የመኪና አደጋ ደርሶበት በአምላክ ተአምር የዳነ ሰው አይቼ አላውቅም እኛ ብዙ ግዜ በጣም ተስፋ ቆርጠን ነበር አንቺ ግን ምንም ፓራላይዝ ሳትሆኚ ነቃሽ ትልቁ ስጋታችን እሱ ነበር እውነትም እንደስምሽ ፅናት ያለሽ ሴት ነሽ በርቺ አምላክ ከጎንሽ አለ! አለኝ ሌላኛው ዶክተር ደግሞ አልጋው ጎን ላይ ያለውን ዶሴ ወረቀቶቹን አገላብጦ ካየ በኃላ ብዙ ምርመራ እናደርግልሻለን አሁን ያለሽበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ነው.... ብሎ የሚያወራውን ሳይጨርስ እህቴ... ምን ሆነች የሚል ጩኀት ከበሩ ተሰማ የሊና ድምፅ እንደነበር መለየት አልከበደኝም ዶክተሮቹን እየገፈታተረች ወደኔ ስትመጣ እማላውቃት ሴት ሆነችብኝ ሊናን አይቼ በጣም ደነገጥኩ በኔ ምክንያት ብዙ መከራ እንዳየች ብዙ እንደተሰቃየች ህይወቷን እንደጣለች ገባኝ በጣም በጣም ከስታለች እሷም እንደ ታዲ ፊቷ ጠቋቁሮ አጥንታ ጎልቶ ይታያል የዚህ ምክንያት እኔ እንደሆንኩ ሲገባኝ ደም እንባ ማልቀስ ጀመርኩ። ሊና በድንጋጤ ምን እንደተፈጠረ ሳይገባት በእጇ የያዘችውን ፌስታል እያውለበለበች ክፍሉን በአንድ እግሩ አቆመችው ዶክተሮቹ እና ታዲ ሊያረጋጓት ሞከሩ ታዲ አቅፏት ተረጋጊ ሊና መጥፎ ነገር አይደለም ፅኑ ነቅታለች አላት። ሊና ሁሉም ነገር ከአቅሟና ከአእምሮዋ በላይ ሆኖ እኔ መንቃቴን እንኳን ማስተዋል እንደተሳናት እና ያበደች መስሎ ተሰማኝ ሃዘኔ ይበልጥ በረታ። ታዲ እንደነቃው ሲነግራት እየሮጠች መጥታ አቀፈችኝ እኔም አቅፊያት ለረጅም ግዜ ተላቀስን ዶክተሮቹ የተወሰነ ግዜ ለብቻችን እንድናገኝ ብለው ትተውን ሄዱ። ሁለታችንም ተላቅሰን ስናበቃ ሊኑ አስር ግዜ ግንባሬን ትስመኛለች የእህትነትና እናታዊ ፍቅሯ ይበልጥ ሲጨምር ተሰማኝ። ታዲ እሚሆነውን ሁሉ አይኑ እንባ እንዳቀረረ እያየን ነበር ሁለታችንም እንደተቃቀፍን መጥቶ ሁለታችንንም አቀፈን።
ሊናና ታዲ እንዳቀፉኝ ምን ያህል ግዜ ሆነኝ ሆስፒታል ከገባው አልኳቸው ሁለቱም ደንገጥ አሉና ለቀውኝ እርስ በእርስ ተያዩ ፊታቸው ላይ እንንገራት አንንገራት የሚል የማንገራገር ስሜት ይነበብ ነበር። ሊኑ እንባዋን እየጠራረገች እእእ ፂዬ እሱ ችግር የለውም ዋናው አንቺ አሁን በሰላም መመለስሽ ነው አለችኝ እኮ ስንት ግዜ አልኳት ሊኑ እንደማመንታት እያለች ወደ ሰባት ወር ሊሞላሽ ነው መሰለኝ አለችኝ በጣም ደነገጥኩ ሰ..ባ..ት ወ..ርርር! ሰባት ወር 7 ሙሉ ሳልነቃ!
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_12_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:
http://t.me/USA2A
4 u by @USA2A
#ገምሃልያ_ክፍል_12

#ሊኑ ልታረጋጋኝ ሞከረች.. አይዞሽ ፅኑዬ ዋናው አንቺ መንቃትሽ ነው እንጂ የፈጀውን ግዜ ይፍጅ ደሞ ምንም ነገር አላመጠጠሽም ትንሽ ግዜ ናት አይዞ..ሽ አይዞሽ እያለች ታባብለኝ ጀመር ራሴን ለማረጋጋጥ ጣርኩ ግን አልሆነልኝም ላለፉት ሰባት ወራት ምን እንደተፈጠረ ባላውቅም ለሊና እና ታድኤል ቀላል ግዜ እንዳልነበር አልጠፋኝም ሁለመናቸው ለኔ ለኔ ሲሉ በጣም ብዙ እንደተሰቃዩ እና እንደተሸገሩ ገብቶኛል ፀፀተኝ ከታድኤል ጋር የተገናኘንባትን ቀን ረገምኳት ግና ምን ያደርጋል የነሱ ስቃይ ሲያቆም የኔ የስቃይ እና የመከራ ህይወት ሊጀምር ነበር። በደምብ ከተረጋጉ በኃላ ታድኤል ቅድም ሲፅፍባቸው የነበሩትን ወረቀቶች ከመሬት ላይ ሰብስቦ እያስተካከለ ወንበሩ ላይ ተቀመጠ ለምን እንደሆነ ባላውቅም እዚች ወንበር ላይ በጣም ብዙ ግዜ እኔን እየጠበቀ ያሳልፍ እንደነበር ተሰማኝ። እግሩን አጣምሮ ተቀምጦ ወረቀቶቹን አስተካከለና መፃፍ ጀመረ የለበሰው ጥቁር ሰማያዊ ሹራብ አንገቱ ድረስ ሸፍኖታል ከታች የለበሰው ብኒ ሱሪ ጎልቶ ይታያል የሆነ የድሮ ደራሲዎች አለባበ መሰለኝ ወረቀቱን ይዞ ሳየው። ሁሉንም ወረቀቶች ካስተካከላቸው በኃላ ከኪሱ ውስጥ ፖስታ አውጥቶ አጣጥፎ ከተትታቸውና ፖስታው ላይ የሆነ ነገር ፅፎ ከወንበሩ ስር ያለ ካርቶን ውስጥ ከተተው ካርቶኑ ውስጥ ብዙ እንዳሁኑ አይነት ያሉ ደብዳቤዎች እንዳሉ አየው ብዙ ናቸው እሚያደርገውን በጥሞና እየተከታተልኩት ነበር ለማን ነው ይሄንን ሁሉ ደብዳቤ የሚፅፈው አልኩ ለራሴ።
ሊና ድንገት የሆነ ነገር ትዝ ያላት ይመስል ውይ... ብላ ተነሳች ታዲ ደንገጥ ብሎ ምነው አላት ቅድም ዶክተሮቹ እዚ ተሰብስበው ሳያቸው ደንግጬ ላንተ ያመጣሁልህን ምግብ ውጪ ላይ ደፍቼው ነበር አለችውና ወደበሩ አመራች ነገር ግን ውጪው ላይ ምንም ነገር አልነበረም አይ... ፅዳቶቹ ወይም ነርሶቹ አንስተውት ይሆናል አለችና ወደ ታዲ እያየች እራት በልተሃል ይዤልህ ልምጣ አለችው አይ እበላለው ትንሽ ቆይቼ አረፍ በይ አንቺ እኔ ሄጄ አመጣለው ዛሬ የኔ ተራ አይደል አላት። እውነት ታዲ አይሆንም ዛሬ እኔ ላምጣ ደሞ ከነጋ ጀምሮ አልበላህም ብላ መልሱን እንኳን ሳትጠብቅ ሄደች። እኔ እህቷ ከነቃው ጥቂት ሰአታት ሆኖኝ እንዴት አስችላት እንደሄደች አስቤ ገረመኝ ግን ብዙም ሃሳብ አልሰጠሁትም ሃሳቤ ዳግም ወደምወደው ሰው ሆነ ታዲ! አልኩት አይኑን ከበሩ እየመለሰ ወዬ ፂ አለኝ። ለማነው ግን ያንን ሁሉ ደብዳቤ የምትፅፈው እእእ በጣም ብዙ ነው ቅድም ካርቶኑ ውስጥ ስትከት እያየሁህ ነበር አልኩት። ትንሽ አሰብ ካረገ በኃላ እእእ... ላንቺ ነበር የምፅፍልሽ የዛኔ የመኪና አደጋ የደረሰብሽ ቀን ከኔጋ ልንገናኝ የነበረበት ቀን ነበር እና ከዛን ግዜ ጀምሮ እስካሁን እኔና ሊና ሆነን ከዛሬ ነገ ትነቂያለሽ ትድኛለሽ እያልን ስናስብ እና ስንጨነቅ ነበር እህትሽ ሙሉ የህክምናሽን ወጪ መሸፈን ስላልቻለች እኔ በቻልኩት ሁሉ አግዛት ነበር በብርም በሁሉም ነገር አግዛታለው ላንቺ እንዲ መሆን እኔ ምክንያት እንደሆንኩ ይሰማኛል ዘውትር እዚች ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ከአሁን አሁን ትነቂያለሽ እያልኩ እጠብቅሽ ነበር አምላኬን ከገባሽበት ረጅም እንቅልፍ ይቀሰቅስሽ ዘንድ እለምነው ነበር እና ሁሌም እጆችሽን ይዤ አንቺ ባትሰሚኝም ውሎዬን ስለኔ እነግርሽ ነበር እናም አንድ ቀን ምናልባት ወደፊት ስትነቂ እምታነቢው ደብዳቤ ብዬ መፃፍ ጀመርኩልሽ በዛው ቀጠለ አንቺም አልነሳ አልሽ እኔም የዚች ክፍል ብቸኛ ፀሃፊ ሆንኩልሽ አለኝ ፈገግ እያለ። ታዲ ይህንን ሲነግረኝ ምን ያህል የጭንቀት ግዜ እንዳሳለፈ አስቤ ሳላውቀው ከአይኖቼ እንባ ፈሰሰ ታዲ በእጆቹ ዳብሶ ጠረገልኝ እጆቹን በእጄ ይዤ በተማፅኖ እያየሁት ታዲ! አልኩት ወዬ አለኝ አንዱን ደብዳቤ አንብብልኝ ደስ የሚልህን አልኩት። ፈገግ እያለ እውነት? እሺ አለና ወደ ካርቶኑ ሄዶ ካሉት ደብዳቤዎች ውስጥ ፍፕለግ ፈለግ አድርጎ አንዱን አወጣውና ወደኔ ተመለሰ እኔም ለማዳመጥ ዝግጁ ሆንኩ።
ደብዳቤውን ከፈተውና ውስጡ ያለውን ወረቀት አወጣው ለማንበብ ዝግጁ ሆኖ ጉሮሮውን ጠራረገ....
የታድኤል ደብዳቤ ቁጥር አንድ መቶ ሃያ
ጨለማ ውስጥ ያለ ሰው ስለ ብርሃን መስማት አይፈልግም ብርሃንን ማየት እንጂ፣ የከፋው ሰው ስለደስታ መስማት አያስፈልግም ደስታን ማግኘት እንጂ አውቃለው የሄድሽበት የህልም አለም እሩቅ ቢሆንም አንድ ቀን እንደምትነቂ አውቃለው። ታውቂያለሽ ብዙ ሰዎች ብቻቸውን ነው የሚኖሩት ለምን ይመስልሻል? እነሱም በደጉ ዘመን የኔ የሚሉት ሰው ነበራቸው ነገር ግን በአንድ የቀን ጎዶሎ ያንን ሰው ይነጠቃሉ የዛኔ ዳግም ሰው መቅረብ ዳግም ማፍቀር ይፈራሉ። ይገርምሻል አሁን እየዘነበ ነው ሰሞኑን ሸገር ሆዷን ባር ባር እያላት ነው መሰለኝ ለቅሶዎን ቀንን ከለሊት ታሽጎደጉድብናለች ምናልባት ያንቺን ሁኔታ ሰምታ ይሆን። ፂዬ ቅድም ስትናፍቂኝ የተገናኘንበት እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ደርሼ መጣው አምላኬን ያነቃሽ ዘንድ እያለቀስኩ ለመንኩት ፂዬ ባሁን ሰአት ብዙ ስዎች ሆስፒታል ናቸው እነሱም ግን ድነው ተሽሏቸው ዳግም እንደሚራመዱ ተስፋ አላቸው ሲነሱ ማስተካከል የሚፈልጒቸው ብዙ ነገሮች አሏቸው... እያለ ታዲ ሲያነብኝ የሚያነብልኝን ነገር በአእምሮዬ እየሳልኩ ተመስጬ አዳምጠዋለው። ድንገት ሊኑ ስትገባ ማንበቡን አቆመ እእእ ደራሲው እያነበብክላት ነው የፃፍከውን አለችው እየሳቀ አው አላት በል እራት አምጥቼልሃለው እንብላ እኔም አልበላሁም ነበር አለችው እሱም ቆይ አንዴ ፂ እእእ እርቦኛል አለኝና ወደ ምግቡ ሄደ። ታዲና ሊና ሲበሉ ታዲ ያነበበልኝን ደብዳቤ አስቤ ተደሰትኩ ይሄ ሁሉ ደብዳቤ ለኔ ነው! ታዲ እኔን ወዶኛል! እንኳንም መኪና ገጨኝ አልኩና ለራሴው ፈገግ አልኩ እኔና ታዲ በፍቅር ማእበል ስንዋኝ ስንደሰት ስንጋባ... ሁሉም በአእምሮዬ ተሳሉ ደስታዬ ለከት አጣ!። በልተው ከጨረሱ በኃላ ላለፉት ወራት ያመለጡኝን አዳዲስ ነገሮች እየነገሩኝ አመሹ ናፍቆታችንን ተወጥተን እንቅልፍ ሲይዘኝ ተኛው ታዲ ወንበሯ ላይ ኩርምትምት ብሎ ተኛ ሊኒም እኔ የተኛሁበትን አልጋ ተደግፋ ተኛች።
ጠዋት ላይ ኮሽታ እና ሹክሹክታ ሰምቼ ከእንቅልፌ ነቃው። ሊናና ታዲ እየተንሾካሸኩ ነበር እኔ እንዳልነቃ ድምፃቸውን ቀንሰው ያወራሉ። በቃ እኔ ወደስራ ልሂድ አንተ ጠብቃት ከሰአት እመለሳለው ምሳ ምን ላምጣልህ አለችው እሱም እያንሾካሾከ ድምፅሽን ቀነስ አድርጊ እንዳትነሳ ቆይ እንደውም ልሸኝሽ እታች ድረስ አላትና ተያይዘው ወጡ እኔም ከአልጋዬ ቀና ብዬ ወደ በሩ አየው የሉም የኮቴያቸው የዳና ድምፅ ይሰማል ደረጃውን ሲወርዱ ተሰማኝ። ትንሽ ቆይተው እታች የሆስፒታሉ በር ጋር ቆመው ያወራሉ መስኮቱ ክፍት ስለነበር ሁለቱንም በቀላሉ እያየኃቸው ነበር። ትንሽ ካወሩ በኃላ ሊና ታዲን አቀፈችው አስተቃቀፏ ከወትሮው ለየት ያለ መበር ግራ ገባኝ ታዲም አቀፋትና እጁን አንገቷ ስር አድርጎ ከንፈሯን ሲስማት አየው እንደ በኃ ድንጋይ ደርቄ ቀረው እኔ ይህንን ማመን አልችልም አልልችልም አልችልልልልልልም! አይሆንም ታዲ የኔ ነው የኔ ብቻ! ጮህኩ።
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍
ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_13_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_13

#ምን እንደሚሰማኝ ማወቅ ተሳነኝ አስበኀዋል ከራስህ ህይወት በላይ አስበልጠህ የምትወደው ሰው ካንተ እጅ ሲወጣ እና የሌላ ሲሆን የሌላም ብቻ ሲሆን አይደለም የእህቴ ፍቅረኛ ሲሆን....
ያ... በኮማ ውስጥ ሆኜ ያሳለፍኩት ሰባት ወር በህይወቴ ትልቅ ነገር እንደቀማኝ የገባኝ አሁን ነበር ታዲ የኔ ሳይሆን የእህቴ ሆነ! በጣም ከልቤ አዘንኩ። ታዲ ሊናን ግንባሯን ሳማት እና ድጋሚ እቅፍ አድርጓት ወደኃላ መመለስ ጀመረ። ሳይታወቀኝ ብዙ እንዳለቀስኩ የገባኝ ድንገት የለበስኩትን አንሶላ ስነካው ሲቀዘቅዘኝ ነበር። ደንገጥ ብዬ ምንም እንደማያውቅ ለማስመሰል እንባዬን ጠራርጌ ተመልሼ ተኛድ። የዳኔ የኮቴው ድምፅ ከውጪ እየቀረበ ሲመጣ ባላየውም አይኔን ጨፍኜ ይሰማኛል። ታዲ ቀስ ብሎ በሩን ክፍት አድርጎ ገባና ከውጥ ዘጋው እንደለመደው ሄዶ ወንበሩ ላይ ቁጭ ሲሊ አሮጌዋ ሶፋ መሰል ወንበር ተንፃፃች ከዛም ከወንበሩ ስር ያለውን ካርቶን ስቦ በለሆሳ ወረቀት ሲየንኮሻኩሽ ቆየና ዝምምም... አለ። ከዝምታው እየፃፈ እንደሆነ ገባኝ። ለታዲ የተኛው ብመስልም ግን ነበርኩ እሚደረገውን ሁሉ ዝም ብዬ እ ሰማ ነበር
ዝምምም.. ብዬ ስለ ታዲና ሊና ማሰብ ማስላሰል ጀመርኩ። በዚ አለም ላይ እንደ ሊና እምወዳት እህት አልተፈጠረችም ከማንም በላይ ወዳታለው ከልጅነታችን ጀምሮ ለኔ ብላ ብዙ ስቃይና መከራን እንደተቀበለች አውቃለው ታድኤል ከማንም በላይ ለሷ ይገባታል ግን እኔስ? የኔስ ፍቅር? የኔስ መውደድ ታዲን ማንንም ወንድ ወድጄ በማላውቀው ስሜት እወደዋለው ግን የእህቴ ሆነ! ወሰንኩ! መውደዴን ደብቄ የሊና እንዲሆን ወሰንኩ! ልቤ እያረረ እየተቃጠለም ቢሆን ወሰንኩ እኔ ለሊና የምመኝላት ፍፁም ደስታ እና ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ፍቅር ነው ያንን ደሞ ከታዲ እንደምታገኝ እርግጠኛ ነኝ። እህቴ እኔ ታዲን እንደማፈቅረው ብታውቅ ግንኙነታቸውን እንደምታቆመው በደምብ አውቃለው ምክንያቱም ለኔ የነሱ ደስታ የስቃይ ኑሮ እንደሚሆንብኝ ታውቃለችና ስለዚ ዝምታን መረጥኩ ታዲን ለመርሳት! ፍቅርን ለመርሳት ዝምምም... ለማለት አምላክ እኔን ለፍቅር ያልታደልኩ አድርጎ እንደፈጠረኝ ተሰማኝ ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም... እንደዚ የህሊና ህመም ሆኖ እንዲጠዘጥዘኝ ያደረገኝን ታዲን የተዋወቅኩበትን ቀን ረገምኳት ታዲን ያገኘሁበትን ቀን ረገምኳት ያለፉትን ሰባት ወር በሙሉ ረገምኩ!።
ብቻ ከራሴ ጋር ብዙ ከተጨቃጨቅኩ በኃላ በስተመጨረሻ የብቸኝነቱን ጎዳና መርጬ እነሱ የጀመሩት የፍቅር ህይወት እንዲሰምር እኔ ደሞ ውስጤ እያረረ የዝምታን መንገድ ይዤ ሁለቱም ደስተኛ ሆነው እንዲቀጥሉ ወሰንኩ በውሳኔው ደስተኛ ባልሆንም ግን ትክክለኛው ውሳኔ መስሎ የታየኝ ይህ ነበር ለኔ የእህቴ ደስታ ከኔ ደስታ ይበልጥብኛል እኔን እየከፋኝም ቢሆን እህቴን ብቻ ደስ ይበላት!
ሁሉንም ነገር በልቤ ወስኜ ከጨረስኩ በኃላ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ቀስ እያልኩ አይኔን እያስለመለምኩ ገለጥኳቸው እየተንጠራራው ታዱ አልኩት። አቀርቅሮ ከነባረበት ድንገት ቀና እያለ አተኝና ውይ ፅኑ ነቃሽ አለኝ አው አልኩት ፈገግ እያለ ሰባት ወር የተኛሽው ሳያንስሽ አሁንም ትተኛለሽ አይደል አለኝ ተሳሳቅን ትንሽ ዝም ከተባባልን በኃላ እየፃፈ የነበረውን ወረቀት ቀጥ እያደረገ አሁን የፃፍኩት ነው ላንብብልሽ አለኝ ደስ እያለኝ አው አልኩት። ለማንበብ ተስተካክሎ ከተቀመጠ....
የታድኤል ደብዳቤ ቁጥር 134
ፅኑዬ እንደምን አለሽ ዛሬም ዳግም በሌላ ደብዳቤ መጥቼልሻለው ትናንት በህይወቴ በጣም የተደሰትኩባት ቀን ነበረች አንቺ አትነቂም ብለው ሁሉም ተስፋ በቆረጡብሽ ግዜ ከረጅሙ እንቅልፍሽ ተነሳሽ እኔ ግን ባንቺ አንድም ቀን ተስፋ አልቆረጥኩም ነበር ሁሌም ለሊኑዬ ስነግራት ዛሬ ባይሆን ነገ ትነሳለች እርግጠኛ ሆኜ እላት ነበር ይኀው ተነሳሽ ደስ አለኝ። ብዙ ግዜ ለዚ ሁሉ ምክንያት እኔ እንደሆንኩ አስባለው ግን ደግሞ አንቺ ብትጎጂም አምላክ አንቺን እና ሊናን የመሰለ ቤተሰብ ሰጠኝ በማጣት ውስጥ ትልቅ ማግኘት እንዳለ አምናለው ሁሌም ሁሉንም ነገር በተለያየ መንገድ ማየት አለብን ብዬ አስባለው አንዱ ሲወሰድብን ሌላው እየተሰጠን እንደሆነ ማሰብ አለብን!... ታዲ ይህችን ቃል ከወረቀቱ ላይ ሲያነብ በአእምሮዬ ምን እንዳጣ እና ምን እንዳገኘ ስላወቅኩ በጣም ተሰማኝ በልቤ ታዲ የኔ ነው አንተ የኔ ነህ አልኩ እንባ ከአይኔ ፈሰሰ። አሁንም ታዲ አንገቱን ደፍቶ እያነበበ ስለነበር ሳያየኝ እንባዬን ጠረግኩ ከዛ በኃላ እኔም በሌላ የሃዛብ ዥረት ተሳፍሬ በሃሳብ ማእበል መዋኘት ጀመርኩ የታዲ ንባብ ቢሰማኝም የማስተውልበት አቅም ግን አልነበረኝም ብቻ መጨረሻ ላይ እእእ ፅኑ እንዴት አገኘሽው ሲለኝ ደንግጬ አሪፍ ነው አልኩት......

#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_14_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

http://t.me/usa2a
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_16

#እኔ እኮ አፈቅርሃለው.... ቃለ አፌ ላይ ተንጠልሎ ቀረ አፌን እንደከፈትኩ እኔኔኔ.... አልኩ ስቆይበት ግዜ አንቺ ምን አለኝ። ልተፋት የነበረችውን ቃል መልሼ ዋጥኳት ምንም ተወው በቃ አልኩት እንዴ ለምን ንገሪኝ እንጂ አለኝ ምን እንደሆነ ለማወቅ የጓጓ ይመስላል ድንገት ሌላ ጥያቄ መጣልኝ። እእእ እሺ እንትን ሊናን እንደወደድካት እንዴት እና መቼ እንዳወቅክ ልትነግረኝ ትችላለህ አልኩት ታዲ ከት ብሎ ሳቀና ቀስበቀስ ወደ ሰመመን ውስጥ ገባ ረዘም ላለ ግዜ ዝም ካለ በኃላ አው አስታውሳለው ሊናን የወደድኳት አንቺን ምን ያህል እንደምትወድሽ ካየው በኃላ ነው አንቺ ከምታስቢውና ከምታውቂው በላይ ትወድሻለች ታስብልሻለች። አስታውሳለው አንቺ ሆስፒታል የነበርሽ ግዜ ምን ያክል ስቃይ እንዳየች እኔ አውቃለው ደምሽ በጣም ከመፍሰሱ የተነሳ ደም ያስፈልግሽ ስለነበር የሷና ያንቺ ደም ደሞ ማች ስለሚያደርግ እሷ እንድትሰጥሽ ይደረጋል ሆኖም ግን በቂ አልነበረም እናም ድጋሚ ከሷ እንዲወስዱ ትጠይቃቸዋለች ዶክተሮቹ ግን ከልክ በላይ ስለወሰዱ ከዚ በላይ ደም ከሰጠች የሷም ህይወት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ይነግሯትና ያስተዋታል። ታውቂ ከሆነ ያንቺ ደም እና የሷ ደም ኦ ማይነስ ነው ይህ ደም ለማግኘት በጣም ከባድ ነው
ከመቶ ሰው አንድ ሰው ብቻ ነው ኦ ማይነስ የሚገኘው ታዲያ ዶክተሮቹ ከእህትሽ ሌላ ኦ ማይነስ የደም አይነት ያለው ሰው ለማግኘት በሚሯሯጡበት ግዜ እሷ ውጪ ወጥታ ማንነቷ እንዳይታወቅ ልብስ ቀይራ እንዳለ ራሷን ቀይራ መጣች የደም አይነቷ ኦ ማይነስ እንደሆነ ተናግራ ዶክተሮቹ ሳያውቁ ከሷ ደሙ ተወስዶ ላንቺ እንዲሰጥሽ ተደረገ እሷ ግን ከመጠን በላይ ስለሰጠች ራሷን ስታ መሬት ላይ ወደቀች ነርሶቹ ሊና እንደሆነች ያወቁት ከተዘረዘችበት ሲያነሷት ነበር ለሷም በስንት መከራ የናንተ የደም አይነት ተፈልጎ ተለገሳት በህይወት ተረፈች እኔ በጣም ነበር የተገረምኩት እንደዚህ አይነት ለራስ ሳያስቡ ለሰው ማሰብ በጣም ይከብዳል ብቻ ከዛም በኃላ እኔም እሷም ላንቺ ህይወት ስንል እዛው ሆስፒታል ውስጥ ሆነን አንቺን መንከባከብ እና እምትነቂበትን ቀን በተስፋ መጠበቅ ጀመርን ብዙ ግዜ አናወራም ነበር ግን በጊዜ ሂደት ማውራት ጀመርን እየተቀራረብን መጣን ስላንቺ እምታወራልኝ ነገሮች እንድወዳት አደረገኝ ሊና በጣም እምትገርም በሳል ሴት ናት አለኝ አስቀናኝ!!

ቀናት ቀናትን እየወለዱ ሄዱ አዲስ አመት መጣ። ከሊና እና ታዲ ጋር አንድ ላይ መኖሩ እየከበደኝ መጣ በሁለቱ የፍቅር ኑሮ ሁሌም እንደቀናው ነው ልደቷን እንዴት ደስ በሚል ሁኔታ እንዳከበረላት ሳስብ፣ አውደአመት መጥቶ በተለየ ሁኔታ እንዳከበሩት ሳስብ በሊና ፋንታ እኔ ልሆን እችል ነበር የሚለው ሃሳብ ሁሌም አእምሮዬ ይመላለሳል ፍቅር ምን ያህል እንደሆነ ዳግም ከማፈቅረው ሰው መማር ከበደኝ። ይህንን ቁጭትና መብሰልሰል እማካፍላት ሃናን ብቻ ነበረች ብቻ በብዙ ምክንያቶች ከሁለቱም መራቅ እንዳለብኝ ተሰማኝ ጓደኛዬ ሃናንን አናግሪያት ከእሷ ጋር ልኖር ወሰንኩ እሷ ሁሉንም ነገር ስለምታውቅ ከሷ ጋር መኖር ይቀለኛል ግን ትልቅ ጭንቀት የሆነብኝ ነገር ለታዲና ሊና እንዴት መንገር እንዳለብኝ ነው በጣም ጨነቀኝ እነሱ ለኔ ብለው ስንት ነገር ከፍለው ስንት ስቃይ አይተው እኔ ከቤት ወጥቼ ሌላ ቤት ልኖር አስቢያለው ስላቸው ምን ሊሰማቸው እንደሚችል መገመት ከበደኝ በጣም የሚበሳጩብኝ መስሎ ተሰማኝ። ብዙ ካሰብኩበት በኃላ መጀመሪያ ከሊና በፊት ለታዲ ልነግረው አሰብኩ የዛን ቀን ሁለቱም ስራ ሄደው ብቻዬን ስለነበርኩ ለታዲ ደውዬ ላገኘው እንደምፈልግ ነገርኩት እሱም በሊና ጉዳይ የሚያማክረኝ አንድ ጉዳይ ስላለ እዛው የለመድነው ፓርክ እንድንገናኝ ቀጠረኝ። ምን ሊነግረኝ ፈልጎ ነው ብዬ ተብሰለሰልኩ ስለሊና ምን ሊነግረኝ ፈልጎ ነው ሳወራው ትንሽ የተጨነቀ አይነት መስሎ ተሰምቶኛል ምን እንደሆነ ለማወቅ እየቸኮልኩ ተነስቼ ወደዚህ ፓርክ መጣው ስደርስ ታዲ ሁሌ የምንቀመጥበት ቦታ ላይ ተቀምጦ አገኘሁት። ትንሽ ሃሳብ የገባው ይመስላል ሄጄ ሰላም አልኩትና ተቀመጥኩ ትንሽ ዝም ከተባባልን በኃላ ታዲ ምነው ሰላም አይደለህም እንዴ አልኩት። ከሰመመን እንደመንቃት እያለ እእእ... ደና ነኝ ደና ነኝ ፅኑዬ አለኝ። እሺ አልኩትና እስከሚያወራ ድረስ በዝምታ መጠበቅ ጀመርኩ። ያንቺን ፍቃድ መጠየቅ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላውቅም ግን... ግ... ግን.... አለና በፍጥነት ወደጉልበቴ እየተንበረከከ ከኪሱ ውስጥ የሆነች ቀይ ትንሽዬ ሳጥን ነገር አወጣ ሁኔታው አስደነገጠኝ ፍፁም ያልጠበቅኩት ነገር ነበር ታዲ ሳጥኗን ከፈታት ሳጥና ውስጥ የብር የቃልኪዳን ቀለበት ነበር!!! በጣም ደነገጥኩ ለኔ ነው ለሊና?።
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_17_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

http://t.me/usa2a
@USA2A የቀረበ
4 u @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_17


#እማየውን ማመን አቅቶኝ ም..ምን ምን..!!! ብዬ ተንተባተብኩበት በጣም ደንግጫለው ታዲ ከእግሬ ላይ ተነሳና ፅኑዬ ሊናን በጣም ነው እማፈቅራት ለኔ ከማንምና ከምንም በላይ ናት ያለፈው አመተ ከባድ ግዜ ቢሆንም ከእሷ ጋር ስሆን ግን ሁሉንም ነገር እረሳና ደስተኛ እሆናለው በህይወቴ እንደዚ ደስተኛ እምሆን አይመስለኝም ነበር ግን ለዚህ ሁሉ ሰላሜ እና ደስታዬ ምንጭ ነች ሊና እህትሽን ከምንም በላይ አፈቅራታለው ስለዚህም በህግ ላገባት ሚስቴ ላደርጋት አስቢያለው ከዚ በላይ ግዜ ማቃጠል አልፈልግም ይህ ሁሉ እንዲሆን ግን ያንቺን መልካም ፍቃድ እፈልጋለው እንደምታውቂው እህትሽ ካንቺ ፍቃድ ውጪ ምንም ነገር እንደማታደርግ አውቃለው ለዛም ነው ከሷ በፊት አንቺን መጠየቅና ማስፈቀድ የፈለግኩት አንቺ እሺ ያልሽውን ነገር እሷ ፈፅሞ እንቢ ልትል አትችልም ደሞ ታውቂያለሽ አሁን ምን ያህል ደስተኛ እንደሆነች እእእ እና ፅኑዬ ምን ትይኛለሽ አለኝ እንደመለማመጥ እንደመቁነጥነጥ እያደረገው ታዲ እንዲ ሲጨነቅ አይቼው አላውቅም እኔም በጣም ደንግጬ እምለው ነገር ጠፋብኝ እ...እ...እ ብዬ ዝም አልኩ ሁሉም በእጄ ሆነ ሊናን ማግባት ከፈለገ የኔን ፍቃድ ማግኘት አለበት! ኣታግባት ብዬ የኔ ባደርገው ደስ ባለኝ ነበር ግን አልችልም የግድ እሷን ማግባት አለበት በሆነ ምክንያት በሆነ ተአምር ከኔ ጋር ቢሆን ምንኛ ደስ ባለኝ አውቃለው ረምሃይ እብድ ነሽ ልትለኝ ትችላለህ ግን እብድም ሆኜ ታዲን ባገኘው ምንኛ ደስ ባለኝ ግን በቃ ውስጤ ያለው ፍም እሳት ይፍለቀለቅ ጀመረ እህቴ ታዲን የነጠቀችኝ መስሎ ታየኝ በጣም ጠላኃት ሳላስበው እዛው ቁጭ እንዳልን አፌን በእጄ እንደያዝኩ በእንባ ታጠብኩ ታዲ ሲያየኝ በጣም ደነገጠ! ምነው ፅኑ ምነው... ምነው? ምን አጠፋው እሚያስቀይምሽ ነገር ተናገርኩ እንዴ እእእ ፅኑ ምን አደረኩሽ .... እሺ ይቅርታ አለኝ አንደበቱ እየተሳሰረ። በለቅሶ ብዛት እሱን መስማት አልቻልኩም መላ ህይወቴ ሲገለባበጥ ተሰማኝ ታዲ ሊናን ሲያገባት ልጅ ሲወልዱ ልጃቸውን ትምህርት ቤት ይዘው ሲሄ አብረው በደስታ ሲኖሩ ሁሉም በህሊናዬ ተሳለ ያኔ አደጋ ባይደርስብኝ ሊና ሳትሆን እኔ ነበር እምሆነው የሚለው ክፉ ሃሳብ መጣብኝ ይበልጥ አለቀስኩ! ታዲ ምን እንደሚለኝ ግራ ገብቶት ደንግጧል። ከቆይታ በኃላ ራሴን አረጋግቼ እንባዬን ጠርጌ ተቀመጥኩ ትዝ ሲለኝ ታዲ ለምን እንዳለቀስኩ ትልቅ ማብራሪያ እንደሚያስፈልገው አወቅኩ በጣም ደነገጥኩ ለምንድነው ያለቀስሺው ሲለኝ ምን ልበለው እውነቱን አልነግረው ነገር አልችልም ትልቅ ችግር ይፈጠራል ሁሉንም በውስጤ አፍኜ ሽምጥጥ አድርጌ ልዋሸው ወሰንኩ። እንባዬን ጠራርጌ ወደታዲ ፈገግ ብዬ ዞርኩ ይቅርታ ታዲ አስደነገጥኩህ አይደል በጣም ደስ ስላለኝ ነው እሺ ያለቀስኩት ይቅርታ ስሜታዊ ሆንኩብህ ይህንን ቀን በጣም ስጠብቀው ነበር ሊና እንዳንተ አይነት ውድ ባል እንድታገባ እፈልጋለው እንድታገባት ስትጠይቀኝ ማመን አቅቶኝ በደስታ ብዛት አለቀስኩ እኔና ሊናዬ ያሳለፍነውን ህይወት ታውቀዋለ ቀላል አልነበረም እናም አሁን አጋሯ ስትሆን ስትጋቡ እሚያማምሩ ልጆች ስትወልዱ እያሰብኩ ተደሰትኩ ታዲዬ እኔ ሙሉ ፍቃዴን በደስታ ሰጥሃለው ግን እህቴን አደራ ጥላ ከለላ ሁናት ጋሻዋ ነህ በጤናም ሆነ በህመም በመልካም ሆነ በችግርህም ግዜ መቼም እንዳትታዋት ይህንን ቃል ግባልኝ አልኩት። ታዲ ይህንን ስነግረው ማመን አልቻለም ቅድም ደንግጦ የነበረው ፊቱ ተቀይሮ ፌሽታ በፌሽታ ሆኗል። እኔ አላምን....ም ፅኑዬ ቅድም እንደዛ ስታለቅሽ እምቢ እምትይ መስሎኝ በጣም ተጨንቄ ነበር እኔ.... አላ...ምን...ም!!! እና ፈቀድሽ ፅኑ አለኝ በእጆቹ ትከሻዬን እየወዘወዘ። አው ታዲ ፈቅጃለው አልኩት በዚህ አለም ላይ እማፈቅረውን ብቸኛ ሰው በገዛ ፍቃዴ እህቴን እንደያገባ ፍቃድ ሰጠሁት!!!🎁
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_18_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

http://t.me/usa2a
@USA2A የቀረበ
4u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_18
........የታድኤል ደብዳቤ........
ቁጥር አንድ

#ሊናዬ እስከዛሬ ለፅኑ 146 ደብዳቤዎችን ፅፌላታለው ይህ ደሞ ላንቺ መፃፍ የምጀምረው አዲስ ደብዳቤ ነው አውቃለው አንቺ ደብዳቤ ማንበብ እንደምትወጂ እስከዛሬ ለምን ላንቺ እንዳልፃፍኩልሽ ሳስበው ቆጨኝ! ሊናዬ እኔ አንቺን ከሚባለው በላይ አከብርሻለው፣ አምንሻለው፣ አስብልሻለው፣ እወድሻለው አፈቅርሻለው በቅደም ተከተል። ከመውደድ በፊት ክብር ይቀድማል ከማፍቀር በፊት ማመን ይቀድማል። እኔ አንቺን ሳፈቅርሽ በነኚ ነገሮች ሁሉ ውስጥ አልፌ ነው መጀመሪያ ስንተዋወቅ ለሰው ያለሽን ክብር አይቼ አከበርኩሽ ከዛም ለአምላክሽ ያለሽን ታማኝነትሽን እምነትሽን አይቼ አመንኩሽ አምኜሽም አልቀረው ዘውትር ስላንቺ ማሰብ መጨነቅ ጀመርኩ ሳላስበው እየወደድኩሽ መጣው መውደዴ በመውደድ ብቻ አልቀረም ለእህትሽ ያለሽን ጥልቅ ፍቅር አይቼ አፈቀርኩሽ! እኛ እምቶጃቸው ዘፋኝ ነብሳቸውን ይማረውና ጋሽ ሚኒሊክ ፍቅር አያረጅም አይደል ያሉት እኔና አንቺ አብረን ሆነን ፍቅራችን ሳያረጅ አብረን እንድናረጅ እፈልጋለው ሆሌም ከእንቅልፌ ስነሳ መጀመሪያ ማየት የምፈልገው ያንቺን ፈገታ ነው ቀኑ አሳልፌም ማታ ደክሞኝ ስተኛ መጨረሻ ማየት የምፈልገው ያንቺን ገፅ ነው ሊናዬ እኔ አንቺን ምንያህል እንደማፈቅርሽ ከምነግርሽ ይልቅ ባሳይሽ እመርጣለው ፍቅር የሚነገር ሳይሆን በተግባር የሚታይ ነገር ነውና። አንቺ ለኔ አለሜ ነሽ ባዶ የነበረው ህይወቴ መጣፈጥ የጀመረው አንቺን ካወቅኩበት ቀን ጀምሮ ነው ትናንት ከዚህ በላይ ማፍቀር የለም ብዬ አስቤ ነበር ዛሬ ደግሞ ይበልጥ ሳፈቅርሽ ይበልጥ ስወድሽ እና ማንነቴን ስትቆጣጠሪ ይሰማኛል ከዚያ የብቸኝነት ህይወት ያወጣሽኝ አንቺ ነሽ ህይወቴ አንቺ እስክትመጪበት ድረስ ባዶ ነበር ያንን ባዶ ልብ ግን አንቺ በፍቅር ሞላሽው ሊናዬ በመልካሙም ሆነ በክፉ ግዜ ይበልጥ ላፈቅርሽና ከጎንሽ ልሆንልሽ ቃል እገባልሻለው። አብረን እጅ ለእጅ እንደተያያዝን ሞት መጥቶ እስኪለያየን ድረስ አንድ ላይ እንድንሆ እፈልጋለው፣ ፍቅር አያረጅም መውደድ አያረጅም እድሜ ቢጠወልግ ሰውነት ቢጃጅም እያልን ባረጀ በሰለለ ድምፃችን እንደወጣትነታችን እንድንዘምር እመኛለው፣ የምንወልዳቸው ልጆች ወግ መአረግ እንዲያሳዩን ሲያገቡ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ ማየት እናፍቃለው፣ አንቺ እርጉዝ ሆነሽ ይሄ አማረኝ ይሄን አድርግልኝ ስትይኝ ልሰማ እናፍቃለው.... ግ...ን ግን... ያ... ሁሉ እንዲሆን መጀመሪያ ለኔ አንድ ጥያቄ መመለስ አለብሽ.... ታ....ገ...ቢ...ኛ.....ለ.....ሽ?

.................................................

ሊና የታዲን ደብዳቤ ጮክ ብላ ስታነበው በደስታ ብዛት ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች እንባዋን እየጠረገች ነበር እኔም በቅናት ይሁን በደስታ ብዛት እያለቀስኩ ነበር። ሊና ወረቀቱን ወደታች ስታረገው ታዲ ቀለበቱን እንደተንበረከከ ይዞታል ሊና ይበልጥ በደስታ መንሰቅሰቅ ቀጠለች ታዲ እንደተንበረከከ ወደሷ እየተጠጋ ሊናዬ አንቺን እንድታገቢኝ ከመጠየቄ በፊት ፅናትን ጠይቂያት ደስተኛ ከመሆኗ የተነሷ ሁሉንም ነገር ያዘጋጀችው እሷ ናት ምግቡን አበባውን ሻማውን ሁሉንም ነገር... ያው እዛጋ ተደብቃ እየጠበቀች ነው አላት እየሳቀ ሊና የታዲ እጅ አደጠቆመበት ወደኔ አቅጣጫ ስትዞር መብራቱን አበራሁት እኔም ሳይታወቀኝ እንባ በእንባ ሆኜ ነበር ታዲ የፃፈው ደብዳቤ በጣም ያምር ነበር። እእእ ሊኑዬ መልስሽን እኮ እየጠበቀ ነው አልኳት ሊና በደስታ እሺ አገባሃለው የኔ ፍቅር ብላ እሷም ተንበርክካ ተጠመጠመችበት ተቃቅፈው ተላቅሰው ሲያበቁ ታዲ ቀለበቱን እጇ ላይ አደረገላት ምሽቱን በደስታ አሳለፍን። ግን ምን ያደርጋል... አየህ አንዳንዴ ትልቅ ደስታ ትልቅ ሃዘንን ከጀርባው ይዞ ይከተላል እኔ በህይወቴ ታላቅ ስብራት ያጋጠመኝ ይሄኔ ነበር አንዳንዴ ስትደሰት ደስታዬን ለበጎ አድርገው ብለህ ፀልይ ቀጥሎ ምን እንደሚያጋጥምህ አታውቅምና ታላቅ ደስታ ታላቅ ሃዘንን ይዞ መጣ!
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_19_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

http://t.me/usa2a
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A #ገምሃልያ_ክፍል_19

#ህይወት ቀጠለች.... ግዜያት ሄዱ እኔም ከቤት ወጥቼ ከሃናን ጋር አንድ ላይ መኖር ጀመርን በዚህ ወሳኔዬ ሊና መጀመሪያ ላይ ብዙም ደስ ባይላትም ግን በጊዜ ሂደት ተቀበለችው እጩዎቹ ሙሽሮች ሊና እና ታዲም አንድ ላይ ይፍቅር ህይወታቸውን ያለማንም ከልካይ ይኖራሉ ለግዜውም ቢሆን ከነሱ መሬቄ ለኔም ለነሱም አሪፍ ነበር ለነሱ የግል ግዜያቸውን ሲያገኙበት ለኔ ደሞ ወደራሴ መለስ ብዬ ተረጋግቼ ነገሮችን እንዳስብ እድል ሰጥቶኛል ሁሌም ቢሆን ሰለታዲ ማሰቤን አላቆምኩም የፈለገ ከሱ ብርቅም ስለሱ ማሰቤን ግን ማቆም አልቻልኩም ቢቸግረኝ ቤተክርስቲያን ሄጄ ይህንን አዚም ነቅሎ ይጥልልኝ ዘንድ ፀሎት አደረኩ ፍቅር በፀሎት ይተው ይመስል....
ሳምንቱን ሙሉ በስራ ተጠምጄ እውልና ቅዳሜ ወይ እሁድ እነሊናን ልጠይቃቸው ቤት እሄዳለው ስሄድ ናፍቀውኝ እንዳልሄድኩ ስመለስ ግን በቅናት ተቃጥዬ ፊቴ ጠቁሮ እመለሳለው ሁሌም ቤት ስሄድ ያላቸው የማይሰለች ፍቅር ዘውትር እየጨመረ ይበልጥ ሲዋደዱ አያቸዋለው። ቤቱ ውስጥ በትልቅ ፍሬም የተለጠፉት አብረዋቸው የተነሷቸው ፎቶዎችን ሳይ በሊና ፋንታ እኔ ልሆን እንደምችል እኔ ልሆን እንደሚገባ እያሰብኩ በቅናት እበግናለው!። ሴት እንዴት የእህቷን ባል ልትመኝ ትችላለች ብዬ እጠይቃለው መልሼ ደግሞ እኔ እኮ ነኝ መጀመሪያ ታዲን የማውቀው እኔ እኮ ነኝ መጀመሪያ የወደድኩት ብዬ ከራሴ ጋር ሙግት እየገጠምኩ ወደቤት እመለሳለው እንዲ መጨናነቁና ቅናቱ እየበዛብኝ ሲመጣ እኔም ቀስ በቀስ እነሱጋ መሄድ አቆምኩ ስጠፋባቸው እየደወሉ ይጠሩኛል ተገናኝተን ለምን እንደጠፋው ሲጠይቁኝ ስራ እያጨናነቀኝ እንደሆነ ነግራቸዋለው ታውቃለህ በዚህ አለም ላይ ከባዱ ስሜት የሚወዱት ሰው ሌላ ሰው ሲወዱ ማየት ነው ይህንን ያየው ብቻ ነው ሚያውቀው። አውቃለው ታዲ የኔ መቼም እንደማይሆን ግን በቃ የሆነ ተአምር ተፈጥሮ የኔ እንዲሆን እፀልያለው ሁሌም! ሁሌ ለሃናን ስለታዲ እያወራው ሳሰለቻት ትቆጣኛለች። አንድ ቀን ሲሰለቻት ምናልባት ታዲን እሚያስረሳኝ ከሆነ ብላ አንድ ጓደኛዋን ካላስትዋወቅኩሽ በላ ይዛኝ ሄደች ኤልሻዳይ ይባላል። ሁለታችንን አስተዋውቃን ትንሽ ካወራን በኃላ ሃናን መጣው ብላኝ በዛው ሄዳ ቀረኝ ልታጣብሰኝ እየሞከረች እንደሆነ ቆይቶ ነበር የገባኝ።
ኤልሻዳይን ትንሽ እንዳየሁት ደበረኝ ታድኤልን ባየሁበት አይን ኤልሻዳይን ሳየው በጣም አስጠላኝ ምናቸውም አይገናኝም ኤልሻዳይ ማለት የዘመኑ አይነት ወጠጤ ወንዶች ማለት ነው ችኩል በሱ ቤት ማጨስ ማቃም መጠጣት በየመሸታ ቤቱ መዋል አሪፍነት ነው የአውሮፓ እና የአሜሪካ መጢቃ ወይኔ እንዴት እንዳስጠላኝ... በዛላ ላይ ደግሞ በዛ ኮሳሳ ሰውነቱ ላይ ጥብቅ ያለ ብጭቅጭቁ የወጣ ቡተቱ ሱሪ አድርጎ ሲመጣ... እኔ ከወንድ እሚያስጠላኝ ነገር ቢኖር ሴታሴት ወንድ ነው በእድሜ እኩል ብንሆንም ግን በጣም መብሰል የሚቀረው የከተማ ጥሬ መስሎ ታየኝ። በኔ አመለካከት አሪፍ ወንድ ማለት እንደወንድ ስነስርአት ያለው አለባበስ የሚለብስ የተረጋጋ ሲናገር በማስተዋል እና በእርጋታ የሚናገር ከጊዜያዊ ነገሮች ይልቅ የወደፊቱን አርቆ እሚያይ ማለት ነው። ማንም ሴት እንዲ አይነት ወንድ ባትወደው እንኳን ታከብረዋለች "gentle" ስለሆነ ደግሞ አንድ እውነት ልንገርህ ሴቶች እንደኤልሻዳይ አይነት ያሉ የዘመኑ ወጣቶችን አብረው ግዜ ለማሳለፊያነት ሊጠቀሙበት ይችላሉ እንጂ መቼም ለቁምነገር አያስበትም ነገርግን እንደታዲ ያሉ አስተዋዮችን ግን ለብዙ ነገር ያስቧቸዋል ይህንን ማንንም ሴት ብትጠይቅ ትነግርሃለች አለችኝና ፈገግ አለች እኔም አሁን ያለውን ትውልድ አስተውዬ ፈገግ አልኩ ፅናት የምትጠላቸውን ነገሮች እኔም ብዙም አይመቹኝም በግሌ አሁን ያሉትን ወንዶች ሳያቸው ከወንድነታችው ይልቅ ሴታሴትነታቸው ጎልቶ ይታየኛል ልክ እንደሴት ሰውነት ላይ ልጥጥጥጥ...ፍ የሚል ሱሪ፣ ፀጉራቸውን እንደሴት ተቆርጦ ቀለም መቀባት ሎቲ ማንጠልጠል፣ አውራራቸው እንደሴት ሁሉ ነገራቸው እንደሴት የወንድነት ለዛው ይኑረን!። ወዴት እየሄድን ነው? ብዬ እያሰብኩ እንዳለ ፅናት ቆይማ የኤልሻዳይን ፎቶ ላሳይህ ብላ ስልኳን ከፍታ አሳየችኝ ከት ብዬ ሳቅኩ ከፅናት ጋር ይህንን እያወራን ከት ብለን ተሳሳቅን ስናበቃ ታሪኳን ካቆመችልኝ ቦታ ቀጠለችልኝ...
እና እልሃለው ከእንደዚ አይነት ፎዞ ጋር ነበር ሃናን ልታጣብሰኝ የፈለገችው የተወሰነ ቀን ሃናን በግድ እየጨቀጨቀችኝ በግድ እየሄድኩ ኤልሻዳይን አገኘሁት ይበልጥ እያስጠላኝ መጣ እሚያወራቸው ነገሮች በሙሉ ገና ልጅነቱን ያልጨረስ ህፃን ነው። ሁሌ እስከዛሬ ስለጠበሳቸው ቆንጆ ቆንጆ ሴቶች፣ ስለቤተሰቦቹ ሃብት፣ ስለሚለብሳቸው ብራንድ ልብሶች ሲበጠረቅ ይውላል የሆነ ቀን ምርር ሲለኝ እንዴ አንተ አይሰለችህም እንዴ እንዲ አይነት ወሬ ማውራት ስታየኝ ያንተን ሃብት ልመዘግብ የመጣው ማዘጋጃ ቤት መስልሃለው አልገባህም እንጂ እምታወራው ወሬ ሆድ ይነፋል ህፃን ሁለተኛ እንዳትደውልልኝ ብዬ ሰድቤው ሄድኩ። ፅናት በብሽቀት ይህንን ስትነግረኝ የሰደበችው ስድብ በጣም አስቆኝ በሳቅ ሞትኩ ፅናትም አብራኝ ሳቀች።
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_20_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

http://t.me/usa2a
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A
#ገምሃልያ_ክፍል_21

#በኔ ጩኀት ኦና የነበረው ሰፈር በሽርፍራፊ ሰከምዶች በሰው ተሞላ ጎረቤት ተከራዮች ሁኔታውን ሲያዩ ተሯሩጠው አምፑላንስ ደውለው ጠሩ እኔ ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩብ በጩኀት ሰፈሩን ድብልቅልቁን አውጣሁት። እኔና ሃናንን ያከራዩን ሴትዮ ከሌሎች የሰፈሩ እናቶች ጋር ሆነው ለሊና የተቻላቸውን እያደረጉላት እያለ አምፑላንሱ ከተፍ አለ! ጎረምሳዎች ሊናን ወዲያው ስትሬቸር ላይ አስተኝተውአምፑላንሱ ውስጥ አስገቧት እኔም ተከትዬ ገባው አምፑላንሱ በፍጥነት ተነስቶ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል መገስገስ ጀመረ... እንባዬን እያዘራው እባክህን በፍጥነት ንዳው አልኩት... ሊና እያቃሰተች ለ...ለ..ምን... ሳ..ትነ..ግሪኝ ፅኑ እእእእ ለ..ምን.... ታዲን አደ...ራ... ድምፃ እየደከመ መጣ ልቤን ፍርሃት ፍርሃት አለው እምትሞት መሰለኝ ይበልጥ እያለቀስኩ ሊኑ.... ሊኑዬ ጥለሽኝ እ.ዳትሄጂ.... ብ...ቻዬን ነኝ... ሊኑዬ ቃል ግ..ቢ..ልኝ... እጇን ጭምቅ አድርጌ ያዝኳት አይኔን እንባ ሞልቶት ሁሉም ነገር ብዥ አለብኝ... ፅ...ኑ... ታዲ...ን አደ..ራ እሱ..ንንንን አግ..ብተሽው .. በደ..ስታ...ኑሪ ታ...ታ...ታዲን... አ..ደ...... እጇ ከእጄ ላይ አምልጦ ወለሉ ላይ ተጎዘጎዘ የተኛች እየመሰለኝ ትከሻዋ እየናጥኩ ሊ....ና.... ሊሊሊና እያልኩ እየጮህኩ ልቀሰቅሳት ሞከርኩ እ... እሷ... እሷ... ግን አልነቃ...ችም.... ሊናዬ ሞተችችች!

ፅናት ከዚ በላይ ታሪኳን ልትቀጥልልኝ አቻለችም በጊዜው የነበረው ሁኔታ ትዝ ብሏት በጣም አምርራ አለቀሰች ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም ወደሷ ጠጋ አልኩና አይዞሽ ፅናት አውቃለው ከባድ ነው የሚወዱትን ሰው.ማጣት ከባድ ነው ባሁን ሰአት ሊና ጠንካራ ሆነሽ እንድትኖሪላት ነው እንጂ እንድታዝኚ አትፈልግም ለሷ ብለሽ ጠንክሪላት እሺ አይዞሽ እያልኩ ያቅሜን ያህል ላፅናናት ሞከርኩ። አልቅሳ ስታበቃ የያዝኩትን ሃይላን ውሃ ሰጠኃት ፊቷን ታጥባ ስትመለስ የቀይ ፊቷ በጣም ቀልቶ ቲማቲም መስሏል ውስጧ በጣም እንደተከፋ እንዳዘነች ገብቶኛል በዚህ ሁኔታ ታሪኳን እንድትቀጥልልኝ አልፈለኩም እስካሁን እሷ አውርታለች ደክሟታል እኔ ደግሞ በተራዬ የኔን አንድ ታሪክ ልነግራት አሰብኩ።
ተረጋግታ ከተቀመጠች በኃላ አንቺ እሚያሳዝን ታሪክ ነግረሽኛል አንቺ ተረጋግተሽ እስከምትቀጥይልኝ ድረስ እኔ በሂወቴ ካጋጠሙኝ ከባድ ግዜያት ውስጥ አንዱን ልንገርሽ አልኳት ፅናት በግድ ፈገግ እያለች እሺ አለችኝ።
ታሪኩ እሚጀምረው ከሃይስኩል ነው በጣም እምወዳት ጓደኛ ነበረችኝ ቢታንያ ትባላለች በጣም እምወዳት ፍቅሬ ነበረች ሁሌ ከትምህርትቤት ስንመለስ አብረን በእግር ወክ እያደረግን እንመለሳለን በየቀኑ እንገናኛለን አብርን እንውላለን አብረን እናጠናለን የልጅነት ፍቅር ታቂያለሻ እንደዛ ነበረ ብዬ ፈገግ ብዬ ፅናትን ፈገግ ላስብላት ሞከርኩ። ከሃይስኩል ጀምሮ አንድ ላይ የሆንን ወደ ማትሪክ ተፈትነን ካለፍን በኃላ የዩኒቨርስቲ ምደባ ሲደረግ ሁለታችንም መቀሌ ዩኒቨርስቲ ደረሰን አንድ ላይ ስለነበርን በጣም ደስተኛ ነበርኩ እሷም እንደዛው እውነት እልሻለው ፅናት በህይወቴ እንደሷ በንፁህ ልብ ያፈቀርኳት ሴት የለችም አትኖርምም። ግን ምን ያደርጋል ግቢ እና ሃይስኩል አንድ አይደሉም ሁለታችንም ዩንቨርስቲ ከገባን በኃላ ቀስበቀስ በመኃላችን ክፍተት እየተፈጠረ መጣ እኔ ከሷ ይልቅ ለትምህርቴ ግዜ እሰጥ ነበር ይህ ነገር እየተደጋገመ ሲመጣ ተጣላን ብዙም ሳንቆይ ታረቅን አመቱ ሊገባደድ ሲል ድጋሚ በማይረቡ ምክንያቶች ተጣላን አሁን ላይ ምን ያክል እንደሚፀፅቱኝ አይገባሽም!። ሁለተኛ አመት መቀሌ ስመለስ ቢታንያ ግን አልተመለሰችም በዛው ቀርታ ነበር ለዚህም ምክንያቱ እኔ እንደነበርኩ በጣም አውቃለው ክረምቱን በሙሉ ሆስፒታል ነበረች ከተለያየን በኃላ መርዝ ጠጥታ ራሷን ልታጠፋ ሞክራ ነበር ጓደኞቼ ይህንን ሲነግሩኝ የተሰማኝን ስሜት እኔ አውቃለው ያለችበት ሆስፒታል ድረስ ሄጄ እግሯ ስር ተደፍቼ እያለቀስኩ ይቅርታ ብጠይቃትም ይቅርታዋን ግን የማገኝበት ግዜ አላገኘሁም ቤተሰቦቿ በሴኪዩሪቲ አስወጡኝ.... ግዜያት አለፉ ሁለተኛ አመት... ሶስተኛ አመት... አራተኛ አመት... አምስተኛ አመት ግዜያት ነጎዱ እኔም ከግዜው ጋር በጣም ተቀያየርኩ ከሴትሴት ስዘል ስንዘላዘል ኖርኩ እንደቢታ አይነት ሴት ፍለጋ ተንከራተትኩ ግን አንድም እሷ አጠገብ የምትደርስ ሴት አልነበረችም ተስፋ ቆርጬ ብቸኝነትን መርጬ በተቀመጥኩበት ሰአት ከ አምስት አመት በኃላ ቢታንያ ከየት መጣች ሳትባል ደወለች ስልኲን በቃሌ አውቀዋለው እሷ መሆኗን ማመን አቃተኝ ገና አንስቼው ማውራት እንደጀመርኩ አይኖቼ በእንባ ተሞሉ ማውራት አቃተኝ የሷ ፍቅር ከአምስት አመት በኃላ ከተቀበረበት ተነሳ! እያለቀስኩ ይቅርታ እልኳት እሷም ይቅርታ አደረገችልኝ ለሊቱን ሙሉ እስከ ንጋት 11:00 ድረስ ብዙ ነገር አወራን ላለፉት አመታት የነበሩትን አዲስ ነገሮች በስተመጨረሻም እንዳዲስ ፍቅራችንን እንድንጀምር ተስማማን በህይወቴ በጣም የተደሰትኩባት ቀን ነበረች አምስት አመት የስጠብቃት የነበረችው ፍቅሬ ተመለሰች እኔ የዛኔ ተመራቂ ተማሪ ሪሰርች የምሰራበት ሰአት ነበር አጉል ሰአት!አልኩና በሃሳብ ሰመመን ወደዛች ቀን ሄድኩ.... ረምሃይ ብላ ፅናት ነቃ አደረገችኝ እእእ አልኳትና ታሪኩን ቀጠልኩላት።
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_21_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

http://t.me/usa2a
@USA2A የቀረበ
4u by @USA2A
#ገምሀልያ_ክፍል_22

ከዛ በቃ ለሊቱን ሙሉ የፍቅር ቃላት ስንለዋወጥ አደርን እንደድሮዬ ሰላማዊ እና የተረጋጋው ስሆን ተሰማኝ እሷ ሰላሜ ነበረች። ከሷ በኃላ በጣም ብዙ ሴቶች ጠብሻለው ግቢ እያለው ሴት ላይ ጥሩ ስም አልነበረኝም አጫዋች ነበርኩ ግን ሁሉንም ትቼ መስተካከል ስጀምር ቢታ ተመለሰች ገረመኝ። እያወራን ሊነጋጋ ሲል ነገ ማታ ደውዬ ከአዲሶቹ ጓደኞቼ ጋር እምደማስተዋውቃት ቃልገብቼላት ተሰነባበትን እንዳነጋው በዛው ቀኑን ሙሉ ስራ ስለነበረብኝ ስሰራ ዋልኩ ቀኑን ሙሉ ሰለቢታንያ እያሰብኩ ደስ ብሎኝ ዋለ ለጓደኞቼ እስካስተዋውቃት ቸኮልኩ ማታ ከስራ ወደግቢ ስመለስ ጓደኜቼን ጠርቻቸው ወደ አርክ ጣራ ላይ ሄድን የአርክ ጣራ ማለት ባለ አምስት ፎቅ እምንማርበት ህንፃ ነው ብዙ ግዜ ጣራው ላይ ተቀምጠን መቀሌን ማየት እናዘወትራለን እና እያቻኮልኩ እዛ ወስጃቸው ስለ ቢታንያ ነገርኳቸው በጣም ደስ አላቸው ስለሷ ብዙ ነገር ያውቃሉ እና ላስተዋውቃቸው ስልኳን ስደውል አይሰራም ብዙም ሳይቆይ አንድ የሃይሰኩል ጓደኛዬ ደውሎ ቢታንያ ቀን ላይ የመኪና አደጋ ደርሶባት እንደሞተች ነገረኝ ከትልቅ ደስታ ወደ ትልቅ ሃዘን ማመን አልቻልኩም... እንግዲ አስቢው በዚ አለም ላይ የምታፈቅጊያት ብቸኛ ሴት ተለያይተሽ ከአራት እና ከአምስት አመት በኃላ አጊኝተሻት ታርቀሻት በማግስቱ ሞተች ስትባይ ምን ይሰማሻል...
ከአምተኛ ፎቅ ላይ ራሴን ላጠፋ ልዘል ስል ጓደኜቼ በግድ ይዘው አስቀሩኝ ያቺ ቀን እኔን እስከዘልአለሙ ቀየረችኝ። ጓደኞቼ ለሳምንት ያክል ሆቴል ውስጥ ቆልፈውብኝ እጅና እግሬን ታስሬ ሳለቅስ ነበር የከረምኩት በህይወቴ ገባዱ ግዜ ነበር ለወራት ከሰው እንደሸሸው እምሰራበት ቢሮዬ ውስጥ ወንበር ላይ እንደተቀመጥኩ ይነጋል ይመሻል ግን የግዜ ነገር ይደንቃል በጊዜ ሂደት መፅናናትን አገኘው ራሴን አጠንክሬ ወደ ትምህርቴ ወደ ስራዬም ተመለስኩ ቢታ እንደዚ እንዳዘንኩ እንድቀር እንደማትፈልግ ለራሴ ነገርኩት እሷ የተሻለ ቦታ ሄዳለች ግዜ የማይሽረው ጠባሳ የለም ሁሉም በግዜው ይሆናል ግዜ ለኩሉ በቢታ ሞት እጅግ ባዝንም ትልቅ ትምህርትን ግን አስተምሮኝ ይህቺ የተሰጠችን ህይወት አጭር ናት በሚገባ ልንጠቀምባት እንደሚገባ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር መኖር እንዳለብኝ አስተማረኝ። ያው አሁን ከቢታ ሞት ከሁለት አመት በኃላ አሁን እንደምታዪኝ አለው እንደድሮዬ እስቃለው እጫወታለው መዝናናት ባለብኝ ሰአት ዘና እላለው በስራ ሰአት ደግሞ ስራዬን በሚገባ እሰራለው በህይወቴ ብዙ ስህተቶችን ብሰራም በነኛ ስህተቶቼ ግን ምንም ፀፀት የለብኝም አሁን ላለሁበት ማንነት ዋና መሰረት ናቸው እና ምን ልልሽ ፈልጌ ነው በእህትሽ ሞት ብታዝኚኝ ተፅናንተሽ እንደድሮሽ የምትሆኚበት ነገር ይመጣል the only way out is through ብርሃን እምታገኚው በዋሻው መጨረሻ ላይ ነው እርግጥ ነው የሊና ሞት ቢያሳዝንም ግን በሷ ህልፈት ትልቅ ትምህርት አስተምሮሽ ሊያልፍ ይገባል የማይገድልሽ ነገር ያጠነክርሻል እሺ... አልኩና ሳቅኩ ፅናት ተመስጣ እያዳመጠችኝ ነበር ዋይ ይገርማል እንዲ አይነት ነገር አልጠበቅኩም ነበር ሁሌ እኔ ብቻ በጣም ነበር በጣም የተጎዳው የሚመስለኝ አለችኝ። መልካም አሁን ታሪክሽን መቀጠል ትችያለች ወይስ ሌላ ግዜ ይሁን። አይ እቀጥላለው ችግር የለውም አለችኝ ፈገግ እያለች።

#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_23_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

http://t.me/usa2a
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_23

#ፅናት እያለቀሰች ታድኤል ሊና መስላው እንደተኛት ስትነግረኝ በጣም አዘንኩ በልቤ ምን አይነት ጠንካራ ሴት ናት አልኩ! የፅናት ታሪክ ቀጠለ...

እያለቀስኩ ሊና እንዳልሆንኩ ብነግረውም ታዲ ግን... አሳዘነኝ... ምንም አልጮህኩ ድምፅ አላወጣው ዝም ብዬ እንዳረገኝ ሆንኩ።
ጥዋት ስነሳ ታዲ አልጋው ላይ አልነበረም እንደለመደው ወደ ሊና ጋር እንደሄደ ገመትኩ ታዲ እኔን ስለተኛኝ ምንም አልመሰለኝም እሱ በጤናው እንዲ እሚያደርግ ስብእና እንደሌለው በሚገባ አውቃለው። ቀኑን ሙሉ ተኝቼ ዋልኩ ማታ ላይ ታዲ ድጋሚ ስክሮ መጣ በሩ ተንኳኳ ከፈትኩለት ምንም ሳይነካኝ ገብቶ ተኛ።

ይህ ነገር ቀን በቀን እየተደጋገመ መጣ ውሎውን ከሊና መቃብር ወደ ባር ቀየረ በየቀኑ ከልክ በላይ ጠጥቶ ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ ይመጣል ያንኳኳል እከፍትልታለው ገብቶ ይተኛል ምንም ነገር አይናገር አይጋገር። ቀናት እያለፉ በሳምንት ተተኩ ሳምንታተም አንድ ላይ እየተያያዙ ወራትን አስቆጠሩ ታዲ ከዛሬ ነገ ይሻሻላል እያልኩ ብጠብቅም ጭራሽ እየባሰበት ሄደ በየቀኑ እየጠጣ ይመጣል ሰፈር ውስጥ ወድቆ አገኘዋለው ይዤው ገባለው። ከፈለገም በዛው ያድራል ለሊቱን ሙሉ በሰላም ይመጣ ይሆን እያልኩ ስጨነቅ አድራለው ጭንቀቴ ሲብስብኝ በዛ ድቅድቅ ለሊት ወጥቼ እሱን ፍለጋ በየባሩ ስዞር አድራለው በቃ ህይወት አስጠላችኝ መኖር አስጠላኝ ድሮ አፈቅረው የነበረው ታድኤል አሁን ላይ የለም ፍፁም ሌላ ሰው ሆኗል የሊና ሞት ሃዘኑ ከቀን ወደቀን እየባሰበት ሄደ እንጂ ምንም መፅናናትን ማግኘት አልቻለም። ሁሌም ሲያመሽ ካለበት ባር ላመጣው ስሄድ መንገድ ዳር ተደፍቶ እያለቀሰ አገኘዋለው ልቤ ክፉኛ ይሰበራል ሊናን ከኔ ይበልጥ ይወዳት ነበር።

በእደዚ አይነት ሁኔታ ሁለት አመት አለፈ...
አንድ ቀን ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ታዲ መሬት ላይ ወድቆ ደም ሲያስመልስ አየው ደንግጬ ከአልጋው ተነሳውና አጠገቡ ሄድኩና ደረቱን በእጄ ደገፍ አደረግኩለት። ትንሽ ሲረጋጋ ውሃ እንዲጠጣ ሰጠሁት አቅሙ በጣም ደክሟል! ደግፌው ወደ አልጋው ወሰድኩና አስተኛሁት አጠገቡ ሆኜ እቅፍ አድርጌው ተኛው ምንም አላለኝም ዝምምም... ውስጤ ከረጅም ግዜ በኃላ ሰላም ተሰማው መልሶ ደሞ ልቤ ይሸበር ጀመረ ታዲን እማጣው እማጣው መሰለኝ እጁ ላይ ጥምጥምም እንዳልኩበት ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ። ታዲ እባክህ እንደዚ አትሁን ራስህን በጣም እየጎዳህ ነው አንተ ለኔ ከማንም በላይ ታስፈልገኛለህ በዚ አለም ላይ ያለኀኝ ሰው አንተ ብቻ ነህ እባክህን ራስህን ጠብቅ እባክህን በሊና ይዤሃለው እራስህን አትጉዳ። ታዲ አንተ ባታፈቅረኝም እኔ ግን አፈቅርሃለው እባክህ ልለምንህ እንደዚህ አትሁን ያ... ጨዋታክ እና ቁጣህ ናፈቀኝ... አምርሬ አለቀስኩ ታዲ ከሁለት ድፍን አመት በኃላ አናገረኝ በእጆቹ አቀፈኝና ሳም አድርጎ ፅናት! እኔ የተሰበረ ልብ ነው ያለኝ የተሰበረ ልብ ለማንም አይጠቅምም ምን ያደርግልሻል!? አለኝ ከረጅም ግዜ በኃላ ስላናገረኝ በጣም ደስ ብሎኝ ስላለኝ ነገር እንኳን በቅጡ አልሰማሁትም እኔን እያናገረኝ መሆኑ ብቻ እንኳን በቂዬ ነበር። ጨጓራዬን በጣም እያመመኝ ነው አለኝ ደንገጥ እያልኩ ሆስፒታል እንሂድ ህክምና ያስፈልግሃል በጣም ተጎድተሃል ሰውነትህ ደክሟል አልኩት ታዲ ምንም መልስ አልሰጠኝም ዝም አለ! ዝምታውን እንደ እሺታ ቆጥሬ በፍጥነት ተነሳውና ልብስ ቀያይሬ ታዲም የለበሰውን ልብስ ቀይሬለት ወደሆስፒታል ሄድን።
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_24_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

http://t.me/usa2a
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A
#ገምሃልያ_ክፍል_24
#ታዲ በዶክተሩ ትእዛዝ መሰረት ላብራቶሪ ምርመራ ካደረጉለት በኃላ ውጤቱ ወደ ዶክረተሩ ተመለሰ። ዶክተሩ ራሱን እየወዘወዘ የታዲ ጉበቱ እና ጨጓራው በሚጠጣው አልኮሆል ምክንያት በጣም እንደተጎዳ ነገረን እናም ከዚህ በኃላ መጠጥ በደረሰበት እንዳይደርስ አስጠንቅቆ መክሮት ለኔም እንድጠብቀው አስጠንቅቆኝ ለህመሙ የሚሆን መድሃኒት ሰጥቶት ሸኘን።
ወደቤት ስንመለስ ታዲ ወደኔ ዞረና እንባ እያቀረረ ሊና ናፈ..ቀችኝ!! አለኝ አንጀቴ ተላወሰ ውስጤ ድብልቅል ያለ ስሜት ቱማኝ ታዲ ቢያሳዝነኝም በስንት አመት አድርጎት እማያውቀውን ሲያዋራኝ በጣም ደስ አለኝ። እንባ ያቀረሩ አይኖቹን እየጠረግኩለት እሷ ጋር ደርሰን እንምጣ ሄደህ ካየሃት እኮ በጣም ቆየህ አልኩት። ምንም ሳያመነታ አዎ እንሂድ አለኝ መንገዳችንን ቀየርንና ታክሲ ያዝን።
የሊና መቃብር ቦታ ስንደርስ ታዲ እንባ አውጥቶ ማልቀስ ጀመረ። እሱን ለማፅናናት አልሞከርኩም ሊና ማረፏን መቶ በመቶ እስከዛሬ ድረስ አምኖ አልተቀበለም ነበር... አስታውሳለው የዛን ቀን ያለቀሰው ለቅሶ ከሁሉም ይለይ ነበር ለምን እንደሆነ ባላውቅም የስንብት አይነት ለቅሶ መሰለኝ እንደሌላው ግዜ ንዴት እና እልህ ጩኀት የተቀላቀለበት አይነት ለቅሶ አልነበረም መቃብሯን እቅፍ አድርጎ ይዞ በለሆሳስ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ...
ለሰአታት አልቅሶ ሲበቃው በረጅሙ ተነፈሰና እንባውን እየጠራረገ ተነስቶ ወደኔ መጣ እቀፊው የሚል ስሜት መጣብኝ ጥምጥምምም ብዬ አቀፍኩት ታዲ ከለቅሶው እንደበረደ ሃዘኑ የቀለለው ይመስል እስትንፋሱ እየተቆራረጠ አፍፍፍፍፍ... ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ። አይዞህ ታዲ አይዞ...ህህህ አውቃለው ሊናን ማጣት ከባድ ነው ለኔም ቀላል ግዜ አልነበረም ያለፈው አመት ጨለማ ነበር ለማክሰኞ ተራውን የማይለቅ ሰኞ የለም፤ ለብርሃን ተራውን የማይለቅ ጨለማ የለም ዋናው ነገር በትእግስት መጠበቅ ነው ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል። በጨለማውም ግዜ አብሬህ ነበርኩ በብርሃኑም ግዜ አብሬህ እሆናለው አልለይህም እሺ ታዴ ቃሌ ነው promise? ብዬ ፈገግ እያልኩ የማርያም ጣቴን ዘረጋሁለት በልቤ እሱም እንደዚሁን እንዲያደርግ ተመኘው። በብዙ ለቅሶ የቀረዘዙት አይኖቹ አዩኝ ከደረቁት ከናፍሮቹ መሃል ነጫጭ ጥርሶቹ በግድ ታግለው ወጥተው ታዩ... ታዲ ፈገግ አለና promise! አለኝ በጣም ደስ አለኝ ከረጅም ግዜ በሓላ ከታዲ ጋር ሁሉም ነገር መስመር ሲይዝ ተሰማኝ እንደዛው እንደተቃቀፍን ወደቤት ሄድን።
ቤት ስንደርስ ታዲ እሚወደውን ፓስታ በአትክልት ሰርቼ አብረን በላን እስከዛሬ ድረስ ብዙ ግዜ አልበላም እያለ ሲያስቸግረኝ ነበር ዛሬ ግን በራሱ እጅ መብላት ጀመረ... ታዲ ሙሉ ለሙሉ ወደጤንነቱ እንደተመለሰ አመንኩ እንደሌላ ግዜው ሾጥ እሚያረገው ነገር ምንም አላየሁበትም። እዚ ጋር ፅናትን አቋረጥካት አው ፅናት ያውልሽ አንዳንዴ ከራሳችን በላይ አስበልጠን እምንወዳቸውን ሰዎች ባልጠበቅነው ሁኔታ በሞት ስንነጠቅ እውነታውን መቀበል በጣም ከባድ ይሆናል ለስንት ነገር ያቀድሽው ሰው ጠዋት አይተሽው ከሰአት ላይ እንደጤዛ ሲረግፍ ማየት ትንሽ የአእምሮ መቃወስ ሊያመጣ ይችላል ይሞታሉ ብለሽ የማትጠብቂያቸው ሰዎች ሞተው ማየት ለማመን ይከብዳል ይመስለኛል ታድኤልም ጋር የነበረው ነገር ይህ ይመስለኛል ብዬ የተሰማኝን ድንገት ነገርኳት በሚገባ! ልክ ነህ ታዲ ጋር የነበረው ይህ ነው አለችና አረጋገጠችልኝ። ከዛ በቃ እቤት ቁጭ ብለን እያወራን ያልን ታዲ ድጋሚ እንዳዲስ እየቀረበኝ ነበር በጣም ደስ አለኝ ስሜቴ ውርር አድርጎኝ ሳላስበው ሳምኩት! ሳያስበው ስለነበር ደንገጥ አለ ትንሽ ቆይቶ እሱም ሳመኝ ወዲያው በስሜት ማእበል ተናወጥን.... አንድ ላይ ተኛን በጣም ደስ አለኝ ግን... ግን ምን ያደርጋል እኔ ለደስታ የተፈጠርኩ ሰው አይደለሁም አምላክ እኔን ለደስታ አልፈጣረኝም ዘልአለም አለሜን ከርታታ እና ሃዘንተኛ እንድሆን ፈርዶብኛል።
ጥዋት ስነቃ ራሴን ከታዲ እቅፍ አገኘሁት ደስ እያለኝ በስሱ ደረቱን ስዳብሰው ከእንቅልፉ ነቃ እንዳየኝ ግራ የመጋባት ስሜት ፊቱ ላይ አነበብኩ ትንሽ ቆይቶ ፊቱ ወደሚያስፈራ ቁጣ ተቀየረ በጣም ፈራሁት... ማነሽ አንቺቺቺቺ.... ብሎ አንቧረቀብኝ በጣም ደነገጥኩ እየተንተባተብኩ ፅ..ፅ..ፅና..ትት ነ..ኝ አልኩት።
#ይቀጥላል.......

👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_25_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

http://t.me/USA2A
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_25
#የታዲ እንዲ መቀያየር በጣም አስደነገጠኝ ፊቱ በጣም ያስፈራል ትናንት በፈቃዱ አብሮኝ አድሮ ሲነጋ እንዲ መቀየሩ ደስታዬን ወደሃዘንና ድንጋጤ ቀየረው የታዲ አእምሮ በስትክክል እየሰራ እንዳልሆነ በደምብ አረጋገጥኩ። የእንባ ዥረት እያፈሰስኩ አንሶላውን ለብሼ ማ..ማን..ም አ..ይደለ..ሁሁ...ም አልኩት በከሃዘን ባለፈ ንዴት አንሶላውን እየነከስኩ። ታዲ በፍጥነት ልብሱን ለብሶ እየገላመጠኝ ቤቱን ጥሎ ጠፋ።
የታዲ ነገር በቃኝ! ብዙ ሞከርኩ ብዙ ጣርኩ ታዲ ላይመለስ ሄደ ሁሌም በራሱ የእብደት አለም ውስጥ ሲባዝን ሳየው በጣም ያሳዝነኛል ሁሌም ከሄደበት አለም ላወጣው ሞክራለው ዛሬ ግን በቃኝ! በቃኝ.... ቀኑን ሙሉ ስቅስቅ ብዬ ሳለቅስ ዋልኩ በህይወቴ እንደዚ የተማረርኩበት ቀን አልነበረም ህይወቴ አስጠላኝ መኖር አስጠላኝኝኝ.... ራሴን ለማጥፋት ወሰንኩ። በፍጥነት ከአልጋው ተነሳውና ለታዲ የታዘዙትን መድሃኒቶች በሙሉ ሰበሰብኩና እጄ ላይ ከመርኳቸው በሌላኛው እጄ የብርጭቆ ውሃ ያዝኩ። እንደቆሎ የዘገንኳቸውን ኪኒኖች ወደአፌ አጠጋኃቸው ለተወሰነ ግዜ እንደዛ እንደቆየው እጄ መንቀጥቀ ብዙ ነገር በሃሳቤ ቢመላለሱም አንዳቸውም ለኔ በህይወት ለመቆየት ምክንያት አልነበሩም ድንገት ታዲ አስፓልት ላይ ብቻውን ሲባዝን በህሊናዬ ተሳለ ወኔዬ ከምሽሽ ብሎ ጠፋ ኣቅም ኣጣው ታዲን ጥሎ መሄድ ከበደኝ እሱን ለማን ጥዬ የመኖሬ ምክንያት እሱ ነው! በብሽቀት በእጄ የያዝኩትን ብርጭቆ ወደ ግድግዳው ወረወርኩት ኪኒኖቹንም ዘረገፍኳቸው እንባና እልህ ተናነቀኝ ባዶ ቤት ውስጥ እንደ እብድ ጮህኩ ለምን ታዲ ለምን ለምን ለምምምምንንንን! ለምን እንዲ ባንተ ልሰቃይ ለምን! ንዴቴ ወደ ለቅሶ ተቀይሮ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ።
ቀኑን ሙሉ ምግብ ሳልበላ ዋልኩ ቤት ውስጥ እሚላስ እሚቀመስ ምንም አልነበረም። ማታ ወደ 3፡00 ሰአት አከባቢ በረሃብ ኩርምትምት ብዬ ሶፋ ላይ ተቀምጬ ቲቪ እያየው እያለ የሰፈር ልጆች እየተራራጡ መጥተው በሩን ብርግድ አርገውት ገቡ በጣም ደነገጥኩ ሁሉም እየተንጫጩ ታድኤል ሌቦች ደበደቡት አሉኝ።
እንዴት እንዴት ሆኜ ከቤት እንደወጣው ኣላስታውስም ብቻ እየጮህኩ እንደነበር ትዝ ይለኛል ልጆቹ እየመሩኝ ታዲ አለ ወዳሉኝ ቦታ ስበር ሄድኩ፡፡ ስደርስ ሰዎች ከብ ሰርተው እያዩት ነው እየጮህኩ ሁሉንም አልፌ እሱ ጋር ደረስኩ። ምን ቆማችቅ ታያላች...ው አምፑላንስ ጥሩልኝ ብዬ ጮህኩባቸው በሰው ተከብቤ ሰው አጣው! ኡኡ..ኡ..ኡ...ኡ የሰው ያለህ አረ የሰው ያለህህህ....! ጮህኩ ታዲ በደም ተበክሏል ድንገት ሆዱ አከባቢ ስነጋው ደም ይበልጥ ፈሰሰው በድንጋጤ ሹራቡን ስገልጠው ጎኑ አከባቢ በጩቤ ተወግቶነበር። ይበልጥ ጩህቴን አቀለጥኩት። አምፑላንስ መጣ ቶሎ ወደሆስፒታል መሄድ ጀመርን በጣም ፈራው! ሊናዬን ያጣኃት አምፑላንስ ውስጥ ነበር ታዲንም ሆስፒታል ሳልደርስ እንዳላጣው ፈራው ተንቀጠቀጥኩ ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ በአለም ላይ ያለኝ ሰው እሱ ብቻ ነው እሱሱ... ብቻቻቻ! እሱን ማጣት አልችልም አልችልም አልችልም! ነርሶቹ አድብ እንድይዝ አስጠነቀቁኝ እነሱ የተቻላቸውን እያደረጉ የሱን ህይወት ለማትረፍ እየተረባረቡ ነበር ታዲ ጠጥቶ አልኮሆል በደሙ ውስጥ ስለነበር የደሙን ፍሰት ለማስቆም በጣም ተቸገሩ። ነበሴ በአፌ ልትወጣ ደረሰች እሚሞት መስሎ ተሰማኝ በስንት ጭንቅ ሆስፒታል ደረስን በፍጥነት ወደ ድንገተኛ ክፍል ተሯሩጠው ይዘውት ገቡ እኔን ከበሩ አስቀሩኝ! እኔንም በተራዬ ዞር ሲያረገኝ ተሰማኝ። ኮሪደሪ ላይ ከዛ ወደዚ ስመላለስ መጠበቅ ጀመርኩ። ለሊቱ ሲጋመስ ዶክተሩ ከድንገተኛው ክፍል ወጥቶ ወደኔ እየመጣ በደም የተጨማለቀ ጓንቱን ወደቆሻሻ መጣያ ውስጥ እየጨመረ የታድኤል ቤተሰብ ነሽ አለኝ አው አልኩ በፍጥነት ውጤቱን ለመስማት ቸኩዬ። እእእ የታድኤል ደም አይነት ኦ ማይነስ ነው ባሁን ሰአት በደም ባንካችን ኦ ማይነስ ደም የለንም ስለዚህ ህይወቱን ማትረፍ እምትፈልጊ ከሆነ የቅርብ ቤተሰቤቹ ወይ ተመሳሳይ የደም አይነት ያለው ሰው ማግኘት ይኖርብሻል አለኝ። በዚ ለሌሊት ኬት ነው የማመጣው እኔ ቤተሰቦቹን አላውቃቸውም አልኩት በጣም በጭንቀት ሆኜ አላውቅም አለኝ እንዴት አታውቅም ብዬ የለበሰውን ጋውን አንቄ ጮህኩበት በግድ አስለቀቀኝና የውልሽ የኔ እናት እኔ ስራዬን ነው የምሰራው ኦ ማይነስ የደም አይነት ከመቶ ሰው አንድ ሰው ነው የሚገኘው የማግኘት እድል በጣም ጠባብ ነው ብዙ ሰው ደም ስለማይለግስ ያንን ደም ብዙም አናገኝም አለኝ። ዶክተሩ የነገረኝ ነገር ተስፋ አስቆረጠኝ ሃሞቴ ፈሰሰ እያለቀስኩ በቃ ሞት ፈረድክበት! አልኩት። አላልኩም ወደውጪ ወጥተሽም ቢሆን ተመሳሳይ የደም አይነት ፈልጊ ግዜ አለሽ ከፈጠንሽ አለኝ ዶክተሩ አውርቶ እስኪጨርስ አልጠበቅኩም በሩጫ ከሆስፒታሉ ከንፍ ወጣው። አስፓልት ለአስፓልት እሚረዳኝ ሰው መለመን ጀመርኩ ኦ ማይነስ ደም ያለው! ለሰአታት በዛ ለሊት አስፓልቱ ላይ የሚሄዱትን መኪኖች መለመን ጀመርኩ እግዜር በነፃ የሰጠንን ደም! መጨረሻ ላይ ተስፋ ቆረጥኩ ተንበክኬ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ አምላኬ ታምርህን አሳየኝ ታዲን አድንልኝ ብዬ ለመንኩት።
#ይቀጥላል.......

👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_26_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

ክፍል 29 ላይ በቀርቡ ተረካው ይጠናቀቃል 😫😫😫😫😫😫

http://t.me/USA2A
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A
#ገምሃልያ_ክፍል_26

#በሁሉም ነገር ተስፋ ቆረጥኩ አምላኬ ረሳኝ! በተሰበረ ቅስም ወደሆስፒታሉ ተመለስኩ በሩ ጋር ስደርስ መራመድ አቃተኝ ሰውነቴ ተሳሰረ በረን እንደተደገፍኩ እየተንሸራተትኩ ወርጄ ዘፍ ብዬ ተቀመጥኩ ምንም ማድረግ አልቻልኩም! ዝም ብዬ ማልቀስ ብቻ! እሱን ብቻ ነበር ማድረግ እምችለው። ድንገት የሆነ ኮቴ ድምፅ ወደኔ ሲመጣ ሰማውና ካቀረቀርኩበት ቀና አልኩ። ጋውን የለበሰ ዶክተር ነበር ዶክተር እሚባል ነገር ለአይኔ አስጠልቶኛል የህይወት መድሃኒት ሳይሆን የሞት መልአክ መስለው ነው የሚታዩኝ። እህት ምን ሆነሽ ነው እምታለቅሺው አለኝ በሰለለ ድምፄ እሚረዳኝ አጣው አልኩት። ምን አይነት እርዳታ ነው ሚያስፈልግሽ አለኝ። ደም! ደም ለጓደኛዬ የሚሰጥልኝ ሰው አጣው ኦ ማይነስ ደም አልኩት። እኔ ኦ ማይነስ ነኝ አለኝ ጮክ ብሎ ከተቀመጥኩበት በብርሃን ፍጥነት ታሰብስቤ እየተነሳው እባክህ በምትወደው ሰው ልለምንህ በእመብርሃን በወላዲተ አምላክ ፍቅሬን አድንልኝ የሞት አፋፍ ላይ ነው አልኩይ። በፍጥነት ወደውስጥ ይዞኝ እየገባ የት ነው ያለው አለኝ ማመን አልቻልኩም ማንም ሰው ቸርነትን በነፈገኝ ሰአት ይህ ዶክተር ለኔ ምንም ለማያቃት ሴት ቸርነትን አደረገልኝ ታዲን ሊያድን ከሰማይ የተላከ መልአክ መስሎ ተሰማኝ። ዶክተሩ በፍጥነት ደሙን ለግሶ ለታዲ ተደረገለት ቀዶ ጥገናውም በሰላም ተጠናቀቀ! ውጥረቴ ሁሉ አለለኝ ለሊቱን ደረቅ ወንበር ላይ ከርምትምት ብዬ ስጠብቅ አነጋው እንቅልፍ ያዳፋኛል።
ጥዋት ላይ እንቅልፍ እያንገላጀጀኝ እንደተቀመጥኩ ትናምት ለሊት የረዳኝ ዶክተር ፈረቃውን ጨርሶ ነው ማሰለኝ ጋውኑን አውልቆ በእጁ እንደያዘው በኩሪደሩ ላይ ሲያልፍ አየሁት ብድግ ብዬ ወደሱ አጥኩ ማም እግሬን ወደሱ እንድሄድ እንዳዘዘው አላውቅም። ስደርስ ዶክተር... ዶክተር እያልኩ ከኃላው ጠራሁት ወደኃላ ዞረና አየኝ ፈገግ አለ። ሰላም ነው .... እእእ ብሎ ስሜን እንድነግረው እየጠበቀ እንደሆነ ሲገባኝ ፅናት! አልኩት ጠበቅ አድርጌ። ሰላም ነው ፅናት እንዴት አደርሽ ጓደኛሽስ እንዴት ነው አሁን ጤንነቱ አለኝ ደህና ነው ክብሩ ይስፋ መድሃኒ አለም አልኩት። ጥሩ ዋናው ደህና መሆኑ ነው ዶክተር ዳንኤል እባላለው አለኝ። ዶክተሩ እያወራኝ እያለ ጥሩ ያልሆነ ስሜት ተሰማኝ ያጥወለውለኝ ጀመር ራሴን ስቼ ወደቅኩ።
ስናቃ ሃኪም ቤት ውስጥ አልጋ ላይ ተኝቼ እጄ ላይ ጉሉኮስ ተሰክቶ አገኘሁት በደምብ ወደራሴ ስመለስ ዶክተር ዳንኤል ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ስልክ እየጎረጎረ ነበር። ቀና ብሎ ሲያየኝ ነቅቻለው ነቃሽ ፅናት አለኝ ረጋ ባለ አነጋገር አው ነቅቻለው አልኩት። ትንሽ እንደማሰብ እያለ ምግብ ለመጨረሻ ግዜ የበላሽው መቼ ነው አለኝ ለማስታወስ ሞከርኩ ምንም ትዝ ሊለኝ አልቻለም እኔንጃ ትዝ አይለኝም አንድ ቀን አለፈኝ መሰለኝ አልኩት። ለምን አልበላሽም አለኝ ትንሽ እንደመቆጣት እያለ። የተወሰነ ስለ ታዲና ስለ ሊና ታሪክ ነጋርኩት ባሁን ሰአት ከባድ ችግር ውስጥ እንደሆንኩ ነገርኩት ዶክተር ዳንኤል አዘነልኝ። ከካፍቴሪያ ምግብ አስመጥቶልኝ እንድበላ ካደረገኝ በኃላ መሄድ ስለነበረበት ተሰናብቶኝ ሄደ። አመሻሽ ላይ ታዲ ካሸለበበት ነቃ ደስ አለኝ ሲያየኝ ማልቀስ ጀመረ። ፅናት አስቀይሜሻለው ይቅርታ እንደምትፈልጊው አይነት ሰው አልሆንኩልሽም መፅናናትን ማግኘት አቃተኝ አሁንም ሊናን ወዳታለው መቼም ከልቤ አትወጣም አለኝ እጅግ በሰለለ ድምፅ። እኔ እሱን በማፈቅረው መጠን እሱም ሊናን በዛ መጠን ያፈቅራታል። ምንም እንዳልሆነ አድርጌ እሱን ለማፅናናት እየሞከርኩ ሳለ ዶክተር
ዳንኤል ወደ ክፍሉ ገባ ታድኤልና እኔን ሰላም ካለን በኃላ ታድኤል እንዴት ነህ አሁን ደህና ነህ? ምን እየተሰማህ ነው አለው ጮክ ብሎ ታዲ ፈገግ እያለ ደና ነኝ ዶክተር እድሜ ለናንተ አለው። ትንሽ የታዲን ጤንነት ሲከታተል ከቆየ በኃላ ወደኔ ዞሮ ፅናት ማውራት ያለብን ጉዳይ አለ ወደ ቢሮ እንሂድ? አለኝ ግራ እየገባኝ እሺ አልኩትና ተነሳው አብረን ተያይዘን
ወጥተን ወደ እሱ ቢሮ ስንገባ ያ... ትናንት ያናደደኝ ዶክተር ወንበሩ ላይ ዘብነን ብሎ ተቀምጧል ገና ሳየው አስጠላኝ። ተቀመጭ ብሎ ወደመቀመጫው ጋበዘኝ ሄጄ ተቀመጥኩ ዶክተር ዳንኤልም ከኔ ፊትለፊት ተቀመጠ። ሁለቱም በዝም ለተወሰነ ግዜ ከተቀመጡ በኃላ ዶክተር ዳንኤል በረጅሙ ተነፈና... እእእ እንዴት ብዬ መናገር እንዳለብኝ አላውቅም ፅናት እእእእ ጠዋት ላይ ስለታድኤል ታሪክ የተወሰነ ነገር ነገርሽኝ ከተለያየን በኃላ ለዶክተር ይስሃቅ ደውዬ ለታድኤል የበለጠ ከአንገት በላይ ምርመራ እንዲያደርግለት ጠይቄው ምርመራ አድርጎለት ነበር አለኝና በሃሳብ ተውጦ ዝም አለ። ልቤ መፍራት ጀመረ የሆነ መጥፎ ነገር ሊነግረኝ እንደሆነ ቀልቤ ይነግረኛል።
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_27_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

ክፍል 29 ላይ በቀርቡ ተረካው ይጠናቀቃል 😫😫😫😫😫😫

http://t.me/USA2A
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_27

#ታድኤል brain tumour(የጭንቅላት እጢ) አለበት! አለኝ ዶክተር ዳንኤል ከረጅም ግዜ በኃላ ብዙ አምጦ። ምን እንደሆነ ባላውቅም ምን! ብዬ ደንግጬ ተነሳው። ለታድኤል ከአንገት በላይ ባደረግንለት ምርመራ የx-ray ፎቶግራፍ ላይ በግራ በኩል በሚገኘው የአእምሮው ክፍል ላይ በመጠኑ ተለቅ የሚል እጢ አግኝተናል እናም ይህ እጢ የሚያመነጨው እጢ ከቀን ወደቀን አንዛኛውን የአእምሮውን ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳው ይገኛል ለታድኤል የአእምሮ መዛባት ምክንያቱም ይህ ነበር። አየሽ ከረፈደ በኃላ ስለሆነ የመጣው ህመሙ መታከም እማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ ሙሉ አእምሮውን ተቆጣጥሮታል ምናልባትም በግዜ ቀደም ብሎ መጥቶ ቢሆን ኖሮ እጢውን በግዜ በቀዶ ጥገና አስወጥተን እንደቀድሞው ጤናማ እንዲሆን ማድረግ እንችል ነበር ነገር ግን ያንን ማድረግ አንችልም ባደረግንለት ተጨማሪ ምርመራም ታድኤል ለመኖር የቀሩት የሳምንታት እድሜ ነው! ምንንንን! ብዬ ደንግጬ ተነሳው። በህይወቴ ብዙ ግዜ ደንግጬ አውቃለው ነገር ግን እንደዚ ሰውነቴ እስኪከዳኝ ድረስ የደነገጥኩበት ቀን ትዝ አይለኝም። ሁሉም ነገር ብዥ እያለ እየጨለመ ሄዶ ራሴን ስቼ ወደቅኩ።
ቀጣይ እማስታውሰው ነገር አልጋ ተይዞልኝ ተኝቼ ነበር። ስነቃ ዶክተር ዳንኤል ጋውኑን እንደለበሰ አጠገቤ ተቀምጦ ነበር። ድንገት እጁን ጭምቅ አድርጌ ስይዘው ደነገጠ መንቃቴን አላየም ነበር። እጁን ይዤ ስቅስቅ ብዬ እያለቀስኩ እባክህን ዶክተር ታዲን አድንልኝ በዚ አለም ላይ ያለሱ ማንም የለኝም የምኖረው ለሱ ስል ነው እባክህን ዶክተር እባክህህህ..ን የሆነ ተአምር ፋጥረህም ቢሆን ታዲን አድንልኝ የመኖሬ ምክንያት እሱ ነው እኔ ያለሱ መኖር አልችልም ይከብደኛል! ብዙ ግዜ ራሴን ላጠፋ ሞክሬ አውቃለው ግን እንዳላደርገው የሚይዘኝ አንድ ምክንያት ነበር ታዲ! እሱ ከሞተ እኔም እከተለዋለው እንዳትጠራጠር! አልኩት እጁን በእንባ እያራስኩት። ዳንኤል ከእጆቹ ላይ ቀና አድርጎ እንባዬን በእጆቹ እያበሰ አዝናለው ፅናት ይህ ከአቅማችን በላይ ነው እመኚኝ እኔ ታድኤልን ማዳን ብችል ሁሉንም ነገር አድርጌ አድንልሽ ነበር ላንቺ ስል ግን.... ጉዳቱ ከመጠን አልፏል ማንኛውም እሱን ለማትረፍ የምናደርገው ቀዶ ጥገና ህይወቱን ሊያሳጣው ይችላል ከኛ አቅም በላይ ነው በድጋሚ አዝናለው ፅናት! አለኝ እጅግ በለዘበ አንደበት ይበልጥ ማልቀስ ጀመርኩ ዶክተር ዳንኤል ሊያፅናናኝ ቢሞክርም አልተሳካለትም በመጨረሻ ቢቸግረው ቆጣ እያለ ፅናት! ጠንከር ብለሽ እሱንም አጠንክሪው እንጂ ለም እንደዚ ትሆኛለሽአለኝ እየተቆጣ።

ለሁለት ሳምንት ያክል ታዲ ህክምናውን ሆስፒታል ውስጥ እየተከታተለ ቆየ። እኔ የሱን የህክምና ወጪ የምከፍልበት አቅም ስላልነበረኝ ዶክተር ዳንኤል ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ራሱ አከመው እኔንም በቻልኩት መጠን ራሴን አረጋግቼ ታዲን እንድከታተለው እና እንድበረታ እመክረው ነበር። ሁለቷ ሳምንት ለኔ ሲኦል ነበረች እንደዛን የተጨነቅኩበት ግዜ አላስታውስም ከዛሬ ነገ ሞተ እያልኩ ስጨነቅ እውላለ አድራለው። ትዝ ሲለኝ እኔም የመኪና አደጋ የደረሰብኝ ግዜ ታዲ እና ሊና እንዲ ነበር ሲጨነቁ የነበረው ብዬ አሰብኩ እኔስ ሁለት ሳምንት ነው እነሱ ግን ለብዙ ወራት ነበር ፅናታቸው ገረመኝ እኔ በሁለት ሳምንት ገረጣው ከሳው ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲ ስለተጋረጠበት ዱብዳ ምን የሚያውቀው ነገር የለም እኔ ዶክተሮቹም ለጤንነቱ ብለን አልነገርነውም። ጤናው መለስ ብሎ ቁስሉ በደምብ ከዳነለት በኃላ ከሃኪም ቤት ይዤው ልወጣ ወሰንኩ እነሱ ከዚ በላይ ምንም ሊያደርጉለት አይችሉም ዶክተር ዳንኤልንም ከዚ በላይ ማስቸገር አልፈለኩም።
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_28_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:

ክፍል 29 ላይ በቀርቡ ተረካው ይጠናቀቃል 😫😫😫😫😫😫

http://t.me/USA2A
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A
ገምሃልያ
ክፍል 28

(ማለቂያው ደርሰዋል )

ሁሉንም ነገር ጨራርሼ ዶክተር ዳንኤልም የቀረውን የህክምና ወጪ ከሸፈነልኝ በኃላ ኮንትራት ታክሲ ጠርቶ ካሳፈረን በኃላ ገብተን ልንሄድ ስንል ከኃላ እየሮጠ መጥቶ ፅናት አለኝ አቤት ብዬው ከመኪናው ወጣው። እእእ እቺን ያዣት ለአንዳንድ ነገር ይሆንሻል ብሎ በፖስታ የታሸገ ብር ሊሰጠኝ ሲል አይሆንም ዶክተር ውለታህ በዛብኝ አመሰግናለው ላደረክልኝ ነገር ሁሉ እግዜር ያክብርልኝ በጣም አመሰግናለ ይህን ግን አልቀበልህም አልኩት። ብሩ እንደሚያስፈልገኝ ባውቅም ከዚ በላይ ላይስቸግረው አልፈለኩም። ዳንኤል በግድ ፖስታውን አስያዘኝና ከኪሱ ውስጥ የቢዝነስ ካርድ አውጥቶ እየሰጠኝ በማምኛውም ሰአት እሚያስፈልግሽ ነገር ካለ ደውይልኝ እሺ ምንም እንዳታመነቺ ልረዳሽ ዝግጁ ነኝ አለኝ። በግድ የሰጠኝን ፖስታና ቢዝነስ ካርድ ወደኖርሳዬ እየከተትኩ፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም ዶክተር ውለታህ በጣም በዛብኝ እግዜር ውለታህን ይክፈልህ አልኩትና ተሰነባብተን ሄድኩ። ላዳው ወደቤት ካደረሰን በኃላ ታዲን አስተኝቼው ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማሰላሰል ጀመርኩ። ትዝ ሲለኝ አከራያችንን ላማክራቸው አሰብኩና ወደሳቸው ጋር ሄድኩ። ሁኔታውን ለአከራያችን ስነግራቸው በጣም አዘኑ ሆስፒታል እያለ አልፎ አልፎ እየተመላለሱ ይጠይቁት ነበር። ታዲያ ሃኪምቤት መፍትሄ ከሌለው ለምን ፀበል አንወስደውም አሉኝ በሃሳባቸው ተስማማው።
በማግስቱ በጥዋት ሊናዬ ወደተቀበረችበት ቤተክርስቲያን ይዤው ሄጄ ፀበል ላስጀምረው ወሰንኩ አምላኬ አያሳፍረኝም!
ቤት ውስጥ ምንም እሚላስ እሚቀመስ ነገር ስላልነበር ታዲ ሳይነሳ ዳንኤል በሰጠኝ ብር አስቤዛ ገዛዝቼ መጣው። ታዲ ከእንቅልፉ ሲነሳ እሚወደውን ምግብ ሰርቼ አበላሁት እነድሮው ይስቃል ይጫወታል ያወራኛል ትንሽ ወደ ቀድሞ ማንነቱ የተመለሰ መሰለኝ።
በማግስቱ ታዲን በጥዋት ቀሰቀስኩት እና ቤተክርስቲያን እንሂድ አልኩት ምነው በሰላም ነው አለኝ አው እንዲው እንድንጠመቅ ነው አልኩት። እሺ አለኝና መነሳት ጀመረ ልብሱን አለባበስኩትና ተነስተን ወደ ቤተክርስቲያን ሄድን። ስንደርስ ቅዳሴ እየተቀደሰ ነበር ወደፀበል ቤቱ አከባቢ ሄደን ታዲን አስጠመቅኩት ስንመለስ የሊና መቃብር ጋር ሄድን እና ተቀመጥን ታዲ ዝም ብሎ ተቀመጠ እኔ ሊና ካለፈች በኃላ ያሳለፍኩትን ስቃይ ትዝ አለኝና ታዲ ሳያየኝ ትንሽ አለቀስኩ ወደኔ ሲዞር አየኝ። ምን ሆነሽ ነው ምታለቅሽው አለኝ እሱን እንዳይከፋው ብዬ እንባዬን ቶሎ ጠራረግኩና አይ ምንም አልኩት ትንሽ ከቆየን በኃላ ተነስተን ሄድን። በቀጣዩም ቀን እንደዛው ተነስተን ሄድን አስጠመቅኩት ስንመለስ የሊና መቃብር ጋር ሄደን ተቀመጥን። ሳምንቱን ሙሉ በጥዋት እየተነሳን ሄደን ሳስጠምቀው ከረምን በሳምንቱ ጠዋት ቲዲ ከእንቅልፉ ቀድሞኝ ተነሳና ቀስቅሶኝ ፅኑ ቤተክርስቲያን እንሂድ እንጂ አለኝና ልብሱን ይለብስ ጀመር በጣም ደስ አለኝ ዛሬ ራሱ ያለኔ እርዳታ ልብሱን ለበሰ አምላኬ ላሳየኝ ተአምር አመሰገንኩት። ምንም ሳያስቸግረኝ ሃደኝ ፀበል ተጠመቀ ስንመለስ ፅኑ አለኝ ወዬ አልኩት እስከዛሬ አንድም ቀን ብዬሽ እንደማላውቅ አውቃለው እወድሻለው በብዙ አስቸጋሪ ጊዜያት አብረሽኝ ነበር አመሰግናለው አለኝ። ልቤ በሐሴት ተሞላች አምላኬን አመሰገንኩት። ደስ እያለኝ ወደ ሊና መቃብር ጋር ሄድን። ልክ ስንደርስ ታዲ ወደ ሊና መቃብር ጋር ተጠጋና ፎቶዋን ስሞ አጠገቧ ተቀመጠ ወደኔ ዞሮ አየና ፅኑ አንዴ ብቻዬን ልሁን ከእሷ ጋር አለኝ ግራ እየገባኝ እሺ ስትጨርስ ወደቤተክርስትያኑ ተመለስ እዛ ፀሎት እያረኩ እጠብቅሃለው ብዬው ሄድኩ።

በተመስጦ ሆኜ የተወሰነ ግዜ ቆየው ፀሎት አድርጌ ከጨረስኩ በኃላ ስልኬን አውጥቼ አየው ሰአቱ እየረፋፈደ ነው ታዲ ምን ሆኖ ነው እስካሁ የቆየው ብዬ አሰብኩ ትንሽ ልጠብቀውና ካልመጣ እሄዳለው አልኩ ለራሴ። አምስት ደቂቃ ጠበቅኩት አልመጣም አይ በቃ ከዚ በላይ እንኳን ይበቃል ብዬ ወደመቃብሩ ስፍራ ሄድኩ ቦታው ላይ ስደርስ ታዲ የሊና መቃብር ላይ በፊቱ ተደፍቷል። ትንሽ ቆም ብዬ አየሁት ምንም አይንቀሳቀስም ታዲ አይበቃም እንሂድ በቃ ሰአቱ እየረፈደ ነው አልኩት መልስ የለም!

ድጋሚ ታዲ! አልኩት ጮክ ብዬ አሁንም ዝምምም... ልቤ መምታት.ጀመረ ፈጠን ብዬ ወደሱ ተጠጋውና አንተ ታዲ አልኩና ከትከሻው ቀና አደረኩት እማየውን ማመን አልቻልኩም ልቤ በአፌ ልትወጣ ደረሰች! ዋ.......ይይይይ!!! ብዬ ጮህኩ ታ...ታዲ አፍና አፍንጫው እንዳለ ድመ በደም ሆኖ ተዘርራ ምንም እየተነፈሰ አይደለም! ተለበስኩትን ነጠላ ከራሴ ላይ አውርጄ እየቀዳደድኩት ጮህኩ የሰው ያለህ አረ... የሰው ያለህ እርዱኝ ኡ..ኡ..ኡኡ..ኡ.. ጮህኩ። ወዲያው ቤተክርስቲያኑ አከባቢ ያሉ ሰዎች ተሰበሰቡ ታዲን ከሊና መቃብር ጋር አንስተውት ወደ ገላጣ መሬት ላይ አስተኙት አንድ ነጠላ የለበሱ አሮጊት መጥተው ፊቱን ገልበት ገልበጥ አድርገው፤ የልብ ምቱን ካዳመጡ በኃላ ምን ሆኖ ነው የኔ ልጅ ለኔ ያደርገው ለኔ ለኔ ወይኔ ልጄ ወይኔ ልጄ ወይኔ ልጄጄጄ!!! ቅድም ደና አልነበር ምን ሆንክብኝ ቅድም አዋርቼህ አሆን እንደጤዛ ረገፍክ ሞትክ!!! እያሉ ደረታቸውን እየደቁ እሳቸውም ማልቀስ ጀመሩ።

ፅናት ይህንን ስትነግረኝ ልቤ በጣም እየመታ ነበር ታሪኩን ልትቀጥልልኝ አልቻለችም በጣም አለቀሰች ከለቅሶዋ ታድኤል እንዳረፈ ገባኝ በጣም አዘንኩ አሳዘነችኝ! ታድኤል መሞት የነበረበት ሰው አልነበረም!
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_29_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:
በቀርቡ ተረካው ይጠናቀቃል 😫😫😫😫😫😫

http://t.me/USA2A
@USA2A የቀረበ
ገምሃል_ያክፍል_29

የመጨረሻዉ ክፍል 29 ብዙ ስለሆነ 3 ቦታ ከፍለነዉ ነዉ

#ፅናት ለሰላሳ ደቂቃ ያክል ስታለቅስ ቆየች እኔ ግን ህመሟ በለቅሶዋ ይወጣላታል ብዬ ስላሰብኩ አልቅሳ እስክትጨርስ ድረስ ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ በልቤ ምን ማለት እንዳለብኝና እሷን እንዴት ማፅናናት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ ነው።
ለቅሶዋ ትንሽ ቀዝቀዝ ሲልላት አይዞሽ እንኳን እንዳላልኳት ትዝ አላት መሰለኝ ትንፋሿ እየተቆራረጠ አ...አይዞሽ እንኳን አትለኝምምም አለችኝ። አንቺ አፍነሽ የያዝሽው ህመም እኮ አይዞሽ በሚል ቃል ብቻ የሚድን አይደለም ሲቀጥል እኔ ማውራት እምጀምረው አንቺ ሁሉንም ነግረሽኝ ከጨረሽ በኃላ ነው አልኳት።
ምን ልቀጥልልህ ከዚህ በላይ በቃ ታዲ ከሞት በኃላ ሁሉም ነገር ድብልቅልቁ ወጣ ምናልባት ጨካኝ ነሽ ብለህ ልታስበኝ ትችል ይሆናል ሊና ስትሞት ከነበረኝ ሃዘንና ስብራት በላይ ታዲ ሲሞት ነበረብኝ ይብስ ነበር ታዲን ከሊና በላይ ምን ያክል እንደምወደው የገባኝ ሲሞት ነበር። ከዛ በኃላ እኔም ለቀቅኩ ሱስ ውስጥ ገባው እሱ ለሊና እንደሆነው እኔም ለሱ እንደዛ መሆን ጀመርኩ ከሃዘኔ ለመሸሸግ ጨጓራዬ እስኪላጥ እጠጣለው ግን ይህ ቁስል በአልኮሆል እሚጠፋ ህመም አልነበረም ታዲ... አእምሮው ትክክል ባይሆን እንኳን በህይወት መኖሩ ብቻ ያኖረኝ ነበር ግን አሁን የምኖርለት ምክንያት አጣው ታዲያ ለማን ብዬ ልኑርርር... ንገረኝ እስኪ ለማን ብዬ ልኑር አለችኝ እያለቀሰች ተስፋ በቆረጠ ስሜት ከዚ በላይ ምንም ልትለኝ እንደማትችል ገባኝ።

ከትናንት ጀምሮ እስካሁን አንቺ ታሪክሽን ስትነግሪኝ ነበር ይመስለኛል ከዚህ በላይ ምንም የምትነግሪኝ ታሪክ የሚኖር አይመስለኝም ስለዚህ አሁን ደግሞ እኔን ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነሽ ብዬ ጠየቅኳት። ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች። መጀመሪያ ማልቀሷን እንድታቆምና ራሷን አረጋግታ በደምብ ማዳመጥ እስከምትጀምር ጠበቅኳት።

ታቂያለሽ ትናንት መጀመሪያ ሲጋራ እያጨስሽ አይቼሽ ካለፍኩ በኃላ አሁን ባለው ትውልድ ላይ በጣም እየተናደድኩ ነበር በቃ ሁሉም ነገር በጭስ እና በአልኮሆል እሚፈታ ይመስላችኃላ የአእምሮ ቁስል በነኚ ርካሽ ነገሮች የሚፈታ አይደለም ይህንን እወቂ ሲጋራ እና ጫት አልኮሆል ሃሽሽ... ሁሉም ለግዜው ልትደበቂባቸው ትሽያለሽ ግን ዘልአለማዊ አይደሉም የሆነ ግዜ ላይ ትነቂያለሽ አእምሮችን እያጀዘብሽ ሰውነትሽን እያገረጣሽ ነብስሽን እያቀጨጭሽ እየኖርሽ እንደሆነ ሲገባሽ መውጣት ትፈልጊያለሽ ያኔ ግን ረፍዷል! እኔም ላንቺ እምመክርሽ ሣይረፍድብሽ እንድትወጪ ነው ሱሶች ከእውነታው አለም መደበቂያ ሊሆኑ አይችሉም ብዙ ወጣቶችን አይቻለው ከጓደኞቻቸው ጋር ለመመሳሰል ብለው አራዳ ለመባል እንደዚ አይነት ማጥ ውስጥ የሚገቡ አራዳነት እንዲ ከሆነ ዘልአለም አለም ፋራ ልሁን። አውቃለው አንቺ በእንደዛ አይነት ሁኔታ ወደ ሱስ ውስጥ እንዳልገባሽ ግን የፈለገ ያክል ሃዘን ቢያጋጥምሽ እንደዚ አይነት ነገር ውስጥ መግባት መፍትሄ አይሆንም ይበልጥ ፈተናሽን ያበዛዋል። ችግሮችሽን ተጋፍጠሽ አሸንፈሽ ቀና በሽ መራመድ በሚገባሽ ሰአት በመጨረሻዋ ሰአት ያለችውን ጭላንጭል ብርሃን ያደበዝዙብሻል ብርሃንሽን ያጠፏታል እና የመጀመሪያ ምክሬ ይህ ነው ህመምሽ እንዲያበቃና ወደፊት መራመድ እምትፈልጊ ከሆነ አስረው የያዙሽን ሱሶች በሙሉ አቁሚ! አልኳት ቆጣ ብዬ።
#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_29_ሁለተኛዉ_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:
በቀርቡ ተረካው ይጠናቀቃል 😫😫😫😫😫😫

http://t.me/USA2A
@USA2A የቀረበ
4 u by @USA2A

ገምሃል_ያክፍል_29(2)

የመጨረሻዉ ክፍል 29 ብዙ ስለሆነ 3 ቦታ ከፍለነዉ ነዉ
#ምን አለኝና በህይወት እቆያለው አለችኝና ቦርሳዋን እየከፈተች የተጠቀለለ ሲባጎ ገመድ አወጣች!። አልደነገጥኩም ምን ልታደርግ እንዳሰበች አውቃለው። እኔ እዚ የመጣሁት ራሴን ላጠፋ ነው ወስኛለው አለችኝ። በጣም ተናደድኩ ከተቀመጥኩበት ተነሳው። አንቺ ማለት #ገምሃልያ ነሽ ገምሃልያ! አልኳት ቃሉ አዲስ ስለሆነባት ገ...ምን አለችኝ። ወደኃላ ዞሬ ወደሷ እያየው ገ..ም..ሃ..ል..ያ! ቃል በቃል ቆጠርኩላት። ምን ማለት ነው አለኝ ግራ እየገባት። ገምሃልያ ማለት ሞትን የመረጠ ታግሎ ታግሎ በመጨረሻዋ ሰአት እጅ የሰጠ ሊያሸንፍ ጥቂት ሲቀረው ሰልችቶት ተስፋ ቆርጦ ሞቱን የመረጠ ማለት ነው ምናልባት ትንሽሽሽ ቢታገስ ኖሮ ታላቅ ባለድል ይሆን የነበረ ማለት ነው አንቺም ታግለሽ ታግለሽ የማሸነፊያሽ ግዜ ሲቃረብ እጅሽን ለሞት ሰጠሽ ባንቺ ህይወት ውስጥ አንቺ የማታያቸው እኔ የሚታዩኝ ብዙ ነገሮች አሉ አንቺ ግን እነኛን ነገሮች ለማየት ተስኖሻል ያንቺ የድል ቀን እንደተቃረበ አውቃለው አንቺ ግን ያንን ማየት አልቻልሽም ሊነጋ ሲል እንደሚጨልም አላውቅሽም ልታሸንፊ ስትይ የመሸነፍ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እንደሚሰማሽ አታውቂም ከስምሽ በላይ ትልቅ ፅናት አለሽ ትልቅ ጥንካሬ አለሽ አንቺ ምን ያክል ጠንካራ እንደሆንሽ ግን አላወቅሽውም እስከዛሬ ካየኃቸው ሴቶች እንዳንቺ አይነት ጥንካሬ እና ፅናት ያለው ሰው አላየሁም የሚወዱትን ሰው ማጣት ምን ያክል ከባድ እንደሆነ እኔም አውቀዋለው እውነቱን ንገረኝ ካልሽኝ ዛሬም ድረስ የቢታ ሞት ውስጤን ይጠዘጥዘኛል ምን ያክል እወዳት እንደነበር ነግሬሻለው ግን የሷ ሞት ብዙ እጥፍ አጠነከረኝ እንጂ አላሰነፈኝም ታውቂየለሽ ለምትወጃቸው ሰዎች ከመሞት በላይ ለምትወጃቸው ሰዎች መኖር በጣም ከባድ ነው!። እኔና አንቺ በመጠኑም ቢሆን የሚመሳሰል ታሪክ አለኝ በምንወዳቸው ሰዎች ዙሪያ አንቺ ተስፋ ቆረጥሽ እኔ ግን ይኀው እንደምታዩኝ አለው ዛሬም ድረስ ለራሴ ብዬ መኖር ቢከብደኝ ለቢታዬ ስል እኖራለው አውቃለው የሚፈጠሩት ነገሮች ልብ ይሰብራሉ ያንቺ ስሜት ከማንም በላይ ይገባኛል ግን ራስን ማጥፋት በምንም ተአምር መፍትሄ ሊሆን አይችልም ስለዚ ይህንን እልሻለው ለራስሽ ብለሽ መኖር ቢያቅትሽ ለታዲ እና ለሊና ስትይ መኖር ጀምሪ በነሱ ትዝታ ውስጥ መኖር ጀምሪ ያኔ እነሱም ባንቺ ውስጥ መኖር ይጀምራሉ ከዛ ወደራስሽ ማንነት መመለስ ትጀምሪያለሽ እኔ አንቺን ራስሽን ከማጥፋት ላስቆምሽ አልችልም ውሃውም እሳቱም ቀርቦልሻል ምርጫው ያንቺ ነው እጅሽን ወደፈለግሽበት ስደጅ አልኩና ገመዱን ዘረጋሁላት።

ከዚ በላይ እምራመድበት ወደፊት እምቀጥልበት አቅም የለኝም አቅም ቢኖረኝ እንኳን ምክንያት የለኝም አለችኝና ገመዱን ከእጄ ላይ ተቀበለችኝ ውስጤ ተቃጠለ የነገርኳት ነገሮች ያሳምኗታል ብዬ አስቤ ነበር አልሆነም። አንድ ነገር ልጠይቅሽ ከዛ በኃላ ግን ራስሽን ማጥፋት ከፈለግሽ ትቼሽ እሄዳለው አልበጠብጥሽም አልኳት እሺ ጠይቀኝ አለችኝ። ለምን ታሪክሽን ለኔ መንገር ፈለግሽ ማለት ራስሽን እንደምታጠፊ ከቆረጥሽ ለኔ መናገሩ ምንም ጥቅም አልነበረውም ከትናንት ጀምሮ ያንን ሁላ ታሪክ ለምን መናገር ፈለግሽ?

#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

ለ አስተያየት በ @galaxy1bot በኩል መላክ ይቻላል፡፡
#ክፍል_29_ሶስተኛዉ_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:
በቀርቡ ተረካው ይጠናቀቃል 😫😫😫😫😫😫

http://t.me/USA2A
@USA2A የቀረበ
አንድ ሳምንት ቤት ቁጭ ብዬ ብውል #የቤት_እመቤት የሚል ግሩፕ ላይ #Invite አላደረጉኝም 😡 😡 😡 😡

#ከኮረና_መጠንቀቅ_እንዳይዘነጋ_ታድያ #stayhome

@USA2A