Paradise
662 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
#ሰካራሙ_ክፍል_፲፪(12)

#ለነገሩ ይሄን ሦስት ቀን ልጆችን ፍለጋ አንወጣም ምክንያቱም ፈተና አለብን ለኔ
ግን ምቹ ነው ምክንያቱም ሰካራሙ ቤት ውስጥ ነው
እንደውም ዛሬ የልብ የልቤን ፍርጥ አድርጌ ለመናገር ወስኛለሁ ዛሬ ደግሞ ምን
አይነት trouble ይፍጠር ይሁን?
ምንም ይምጣ ምንም ዛሬ አውነታውን ፍርጥ
ማድረጌ አይቀሬ ነው እንደውም ለድፍረት ከአሁኑ መጠጥ መጠጣት ጀምሬያለሁ
ምን ብዬ እንደምጀምር እያሰብኩ ቤለሁበት ወቅት
ልጁ ከበፊቱ ትንሽ ቆይቶ አንዲት ዉብ የሆናች ሴት ይዞ ሲመጣ
ቆሽቴ ነደደ ስሜቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ቆይ እኔስ አልኩት? እኔ እኮ
እወድሃለሁ ላንተ ብዬ ሰካራም ሆኜ ስጠብቅ አልኩት
ብቻ የለ ምንም ፍራቻ በመጠጣት ስሜት ውስጥ ሆኜ ልቤ ውስጥ ያለውን ነገር
ሁሉንም ተናገርኩ
ጥዋት ላይ ከእንቅልፍ ስናቀ አልጋ ላይ ነኝ
ምን? ማታ ወጪ አልነበረኩም እንዴ? እኮ እንዴት አልጋ ላይ ተገኘሁ? በጣም
ጠጥቼ ስለነበረ የድካም ስሜት አለቅ አለኝ በዛ ላይ ጭንቀቱ ተጨምሮ ጭንቅላቴ
ልፈናዳ ነው
ማስታገሻ እንዲሆን ለምን ጨምሬ አልጣጠም አልኩና እንደገና መጠጣት
ጀመርኩኝ
እንደዛሬ free ሆኜ አላውቅም የእውነት freedom ተሰማኝ በዚህ አጋጣሚ ጓደኞቼ
ለጥናት ብለው እኔጋ መጡ ለኔ ለራሴ Universe ላይ ወጥቼ ስለ Jupiter
ምናምን እያጠናሁ ነው
ሮዛ በጣም እየሳቀች እኔ እኮ መጀመሪያውኑ አውቄ ነበረ ሰካራሙ ልብሽንም
ጨምሮ አሰከራሽ አይደል አይዞሽ ጓደኛዬ የት አባቱ አሁን ሄጄ እናገራለሁ አንቺን
የመሰለች ልጅ እንደዚህ በሱ ፍቅር ስክር ስትል ማየት አልፈልግም አለች
ቅድስት ምን አልሽ ሮዛ? ሶስና ሰካራሙን ልጅ ትወዳለች ማለት ነው አለቻት
አዎ ባክሽ ካልሆነ ታዲያ ምን እንደዚህ ሰካራም አደረጋት ብለ ሳቀች
ቅድስት ሮዛ አንቺ ደግሞ ቀልድና ቁም ነገር እንኩዋን ለይታሽ አታውቂም አይደል
የእውነት ሶስና በጣም ተጎድታለች ማለት እኔ እኮ እስካዛሬ ከልጁ ጋር እንደዛ
ስሆን ለካ እሷ እየተጎዳች ነበረ ማለት ነው ብላ አይዞሽ ሶስ ስለ ሁሉም ነገር
ይቅርታ አለችኝ
ሄለንም አይዞሽ ሶስ እኔም ችዬ እኮ ነው ዝም ያልኩት አለችና እንደውም ለምን
ልጁ ጋር ሄደን እዉነቱን አንነግረዉም አለች
No No አትናገሩ ማታ እኮ ልጁ ሌላ ሴት ይዞ ሲመጣ በቅናት መንፈስ ውስጥ
ሆኜ ሁሉንም ነገር ነገርኩት አልኳት
ሮዛ አሁንም እየሳቀች ነው
ጥርስሽ ይወለቅ አሁን ይሄ ነገር ያስቃል ወይ ብዬ ትራስ ወረወርኩባት
እህህህህ ለዚህ ሰካራም ብለሽ በኔ ላይ ትራስ? እንኩዋንም ሴት ይዞ መጣ
ምናለ ዛሬም ሌላ ሴት ይዞ በመጣ ለነገሩ ወንዶች አንዴ ከጀመሩ በጅምላ ነው
መጨፍጭፍ የሚቀጥሉት ጉድሽ ነው ብላ የበለጠ አቃጠለችኝ
ቅድስት እና ሄለን ባክሽ እሷን ተያት እሷ ከቀልድ ወጪ ሌላ ቁም ነገር የላት
ብለው በሮዛ ላይ ተቆጡ
ሮዛ ለክፋት ብላ ሳይሆን እኔ ከሀሳብ እንድወጣ ፍልጋ ነው ስለዚህ በእሷ ምንም
ቅር አልልም
ዛሬ ጥናት የለም
በወሬ ብቻ ቀኑ አሳለፍን
ዛሬ ቅድስት እና ሮዛ እኛ ቤት ከኔ ጋር ለማደር ወስኖዋል ሄለን አባቷ ስለሚቆጣ
ቤቷ ሄደች
ልጁ ዛሬም ከትላንቷ ልጅ ጋር በፕላስቲክ ብዙ ነገሮችን ይዘዉ መጡ ጭራሽ
ሚስቱ አደረጋት አልኩኝ
ልቤ ተስፍ ቆረጠ
ከአንድ ሰአት በሓላ ወጪ ቁጭ ብለን እያለ ልጁ መጣና ኑ ቡና አንጣጣ አለን
እኔ ለቅድስት እና ሮዛ እናንተ ሂዱ እኔ መሄድ አልፈልግም አልኩኝ
ሮዛ እቦ ባክሽ እንዴ ሕፃን አትሁኝ እሱ እኮ እኛን አይቶ ሳይሆን አንቺን ብሎ
ነው ለብና የጠራው መሄድ አለብሽ አለችኝ
ደስተኛ አይደለሁም ግን ለጓደኞቼ ስሜት ስል አብረን ሄደን
ልጁም እቤት ስንገባ ልጅቷን እሙዬ ብሎ ጠራና ጓደኛቼ ናቸው ተዋወቁ አለ
ለኛም እህቴ ናት ተዋውቁ አለን
አይኔ እንደገና እንዴ ጥዋት ንጋት አበራ
ትሺሺሺ ግን ምን አይነት ችኩል ነኝ?
ደንባረ ነገር ነኝ ለካ እውነት ህጻን ነኝ አልኩኝ
ለነገሩ የወደደ ሰው ምን ቀልብ አለዉ በትንሽ በትልቁ መቅናት ማልቀስ ይወዳል
.
.
.
.
ይቀጥላል
http://t.me/USA2A
እርጉዝ ቁንጫ ለይቼ የማውቅ አራዳ ነኝ ይለኛል እንዴ..

#ለነገሩ_አይገርምም ያስረገዝካት እራስህ
ስ ለ ሆ ን ክ 😜😂