Paradise
662 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
#ሰካራሙ_ክፍል_፬{4}

#ቡናው ከመቼው እንደለቀ አላወኩም ምናለ ሁሌም እንደዚህ አፍልቶ በጠራን እያልኩ ነው ባለፈዉ ያቆምነዉ
ብዙ ሰአታትን አብረን ከተጫወተን በሓላ እኔና ቅድስት እኛ ቤት ገብታን የሆነዉ ነገር ሁሉ እያነሳን መሳቅ መገረም ጀመረን
በሁለተኛ ቀን ሮዛ እና ሄለን መጡ እኔና ቅድስት የሆነውን ነገር ሁሉ ነገርናቸዉ ነገር
ግን በፍጹም ማመን አልቻሉም አብሶ ሄለን ውሸት ነው እሱ መቼም እንደዚህ
አይነት ሰው አይሆንም ምናልባት በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ የተናገረዉ ነገር ይሆናል
አለች ሮዛ ግን እኔ መጀመሪያውኑ ብያችሁ ነበረ እኮ ሰካራም ሁሉ ባለጌ አይደለም
ሰካራም ሁሉ አላማ የሌለዉ ሰው አይደለም ብያችሁ ነበረ እናንተ እኔን አትሰሙኝም
እንጅ አለች
ቅድስት በአንዲህማ እ ጨዋ ነው ብለን መደምደም የለብንም እሱን በዚህ አንድ ወር ውስጥ በቁጥጥር ውስጥ ማስገባት ካልቻልኩ ያኔ ጨዋ ነው ማለት እንችላለን አለች
ሮዛ እኔን ከአሁኑ ከልጁ ጋር ፍቅር ያዘኝ ብለ ሳቀች
እንዴ አንቺ ፍቅረኛ አለሽ አይደል አልኩኝ
ምነው ቀናሽብኝ እንዴ እኔ ስቀልድ ነው እንጅ አይደለም እንደዚህ አይነቱን ሰካራም
ለምርጡ አማኑኤል እንኩዋን እምቢ ብዬ የል እኔ ሮዛ በቀላሉ ለወንዶች እጅ አልሰጥም ባይሆን ቅድስትን ነው መፍራት እሷ ሰካራም አትል አጭር አትል ቀጭን
አትል ትልቅ ትንሽ አትል ሁሉንም በጅምላ ማፍቀር ነው ብላ ሳቀች
ቅድስት እንኳንም አደረኩ እኔ እንደናንተ ጭንቅ አልወድም ከሁሉ ጋር ደስ እያለኝ ማሳለፍ ነው አለች
ሮዛ የዛሬ ደስታ ነገ እምባ እንዳይሆንብሽ ወንዶች እንደሆኑ ጥሩ ደም እስካለሽና ቆንጆ እስከሆንሽ
ድረስ ካንቺ ሌላ የለም ይሉሻል በጀርባቸው አዝሎ እቤት ወስደው የሚፈልጉትን
ከጨረሱ በሓላ በጠረባ እቤት ይመልሱሻል አለች
ቅድስት ት ሽ ሽ ሽ ምን አይነት ሟርተኛ ነሽ መቼም ሺህ ዓመት አልኖር ዛሬ መደሰት
ነው ስትል ሮዛ አንቺ እኮ አሁን ደስተኛ አይደለሽም ሰው ደስተኛ መሆን የሚችለው
አላማ ሲኖረው ነው አለች
ሄለን ውይይይይ እስኪ ዝም በሉ እናንተ እኮ አንዴ ጭቅጭቅ ከጀመረችሁ መቆም
የሚባል ነገር አታውቁም በሉ አሁን ናይት ክለብ ሄደን ዘና እንበል ብላ ተነሳች
እኔም አባዬ ቤት ውስጥ ባለመኖሩ ከነሱ ጋር አብሬ ሄድኩኝ
ዋውውውው በጣም ደስ ይላል የነጻነት ቦታ ነው ሁሉም ደስ እንዳለው ይሆናል
በዚህ አጋጣሚ የቤታችን ተከራይ መጣ መጥቶ ሰላም ካለን በሓላ በጆሮዬ ቀስ ብሎ ትልቅ ሰዎችም እዚህ ይመጣሉ ወይ አለኝ
እፍረት ቢሰማኝም በቀልዱ ሳኩኝ
በሉ ተጫወቱ ብሎ ሌላ መጠጥ ጨምሮ አዘዘ ከዛም ከእኛ ጋር አብሮ
መጠጣትና መጫወት ጀመረ
በፊት እኮ ዝምታኛ ነበረ ዛሬ ወረኛ ሆኖል በቃ የሚናገረው ነገሮች ሁሉ አስቂኝ ናቸው
ከትንሽ ቆይታ በሓላ ቅድስት ሞቅ ማለት ጀመረች ከዛም ልጁን በእናትህ እንጨፍር
ብለ እየተዉረገረገች ተነሳች
እውነት ለመናገር ደስ አላለኝም
ከዛም አብረው መጨፈር ጀመሩ ዋውውውው ጭፍራዉ ይመቻል ይችላል
ወይንስ እኔ ስለማልችል ነው?
ሄለንን አንድ ልጅ መጥቶ በእናትሽ እንጨፍር ብሎ አስነሳት
ሮዛ ሽንት ቤት ደርሼ መጣሁ ብለ ሄደች
እኔ ብቻዬን ቀረሁ
ቅድስት ጭፍራ ብቻ ሳይሆን ሌላ አለም ውስጥ የገባች ትመስላለች ቆይ ግን
እነሱን ማየት ለምን አስፈለገ ብዬ ዝም ብዬ መጠጥ ለመጠጣት ብሞክርም አይኔ ግን እምቢ አለኝ
አይኔ እነሱን ባዬ ቁጥር አንጀቴ መቃጠል ጀመረ
ምን ሆኜ ነው ግን?
ከዛም ሮዛ ከሽንት ቤት መጣች ሄለንም ጭፍራ አቁመ መጣች በእናታሁ እቤት
እንሂድ አልኩኝ ለምን አሉኝ በቃ እንሂድ አልኩኝ
.

ይቀጥላል

ለ አስተያየት @Galaxy1bot

http://t.me/USA2A