Paradise
662 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
#ሰካራሙ_ክፍል_፰_{8}

#ታዲያ ደስታ ለኔ ጠላቴ አይደለም ሲለኝ
በጣም መጥፎ አጋጣሚዎች ናቸው
ይቅርታ ግን ይሄ አጋጣሚ ነው እንጅ ደስታ ላንተ ጠላት ስለሆነ አይደለም
አንድአንድ ጊዜ ነገሮች እንደዚህ ተመሳስለው ይመጣሉ ስለዚህ አጋጣሚ ላይ ለሆነ
ነገሮች ሌላ ስም እየሰጠን ማሸበር መፍራት መጨነቅ የለብንም የምትወዳቸዉን
ሰዎች የወሰደ ሞት ነው እንጅ ደስታ በፍጹም ጠላትህ ሊሆን አይችልም
ህይወት ሁልጊዜም አዲስ ናት
አውቃለሁ ትላንትን መርሳት መጥፋት ወይንም ወደኋላ ተመልሶ መቀየር
መስተካከል አይቻልም ነገር ግን ትላንትን በፀጋ ተቀብለኋው የለ ? ,ያለ እግዚአብሔር
ፍቀድ ምንም ነገር አይሆንም ከትላንቱ ስህተት ትምህርት ወስደን ዛሬን
በደስታ መኖር የተሻለ ነው
ምናልባት ትላንት በአጋጣሚ ምክንያት አጣሁ የምትለውን ደስታ ዛሬ አጋጣሚ
መልሶ በሌላ ነገር ሊሰጥህ ይችላል
ህይወት ብዙ መንገድ አላት አንዱ ቢጨልም በሌላ መንገድ መሄድ ትችላለህ
ደስታም እንደዚሁ ናት በአንድ በኩል ማግኘት ባትችል እንኩዋን በሌላ ነገር
መልሰህ ታገኘዋለህ ዋናው ነገር አንተ በሁኔታዎች ላይ ሁሉም ነገር በፈጣሪ ፍቀድ
እንደሚሆን ማወቁ ነው አልኩት
ምናልባት እንቺ ትክክል ልትሆኚ ትችያለሽ በእኔ ቦታ ሆነሽ እንደዚህ ማሳብ ግን
በጣም ከበድ ነው አለኝ
አውቃለሁ ህመምን ክብደት ስቀይ ከባለቤቱ በስተቀር ማንም ሊያውቅ አይችልም
ነገር ግን የህመም ማስታገሻ ህመም እራሱ ሳይሆን መድኃኒት ነው
ላንተም ለጉዳትህ መፍትሔ ጉዳት እራሱ ሳይሆን ደስታ ነው ስለዚህ ደስተኛ
ለመሆን ሞክር አልኩት
ስለ ምክሩ አመሰግናለሁ ሲለኝ
ምንም አይደለም ግን ነገ አብረን ነን አይደል አልኩት
ይቅርታ አልችልም አለኝ
ነገርኩ ነገ ልደቴ ነው ስለዚህ መምጣት አለብህ ካልመጣህ ደስተኛ ሆኜ መክበር
እንደማልችል እወቅ ብዬ ጥዬ ቤት ገባሁ
እቤት ገብቼ ስለ ልጁ ማሰብ ጀመርኩ በእውነት በጣም አሳዛናኝ ለካ ከሁሉም
ሰው ድርጊቶቹ በስተጀርባ የራሱ የሆነ ምክንያት አለ
ሌሊቱን በሙሉ የለ እንቅልፍ አደርኩ ጥዋት ላይ እንቅልፍ ወሰደኝ እስከ ቀኑ አራት
ተኛሁ እና ቅድስት ልጀቴን ለመክበር ኬክ መጠጥ ምናምን ይዘው እንቅልፍ ላይ
እያለሁ መጡ
አንቺ በዛሬው ቀን እስከ አራት ሰአት መተኛት ምን የሚሉት ነው አሉና እየሳቁ ውሃ
አምጥተው ደፍብኝ ጥሩ feeling ላይ አይደለሁም ግን የነሱን ስሜት ለመጠበቅ
ብዬ እኔም ደስተኛ ለመምሰል ሞከርኩ
ሰባት ሰአት አከባቢ ቤቱን ሞቅ ማድረግ ጀመረን ከእኔና ሄለን በተጨማሪ ሌላ
የትምህርት ቤት ልጆችም ልደቴን ለመክበር መምጣት ጀመሩ
ልደቴን ለማክበር ብዙ ሰዎች እየመጡ ቢሆንም አንድ የሚ
ምጠብቀው ሰው ግን
እስካሁንም አልመጣም
የልደት ኬክ እንድቆረስ ሁሉም እየጠበቁኝ ነው ልቤ ግን አሁንም ተስፍ
አልቆረጥኩም ግን ጓደኞቼ እየጠበቁኝ ስለሆነ የግድ ኬኩን መቁረስ ነበረብኝ
በጣም ክፍት ብሎኛል ልጁ አለመምጣቱ ለኔ ምንም አይነት ስሜት አለመኖሩን እኔን እንደማይወደኝ መሳያ ነው አልኩኝ የራሱ ጉዳይ ብዬ ኬኩን ለመቁረስ ስል ልጁ ስጦታ ይዞ ቤት ገባ
ዋውውውው ልቤ በደስታ ተሞላ ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ከራሱ ደስታ
ይልቅ ለኔ ደስታ ብሎ መምጣቱ ይበልጥ ደስተኛ አደረገኝ እንደዛሬ ደስተኛ ሆኜ ልደቴን አክብሬ አላውቅም
ኬኩን ተቆረሰ ሁሉም ሰው መጫወት መደሰት መቀለድ ጀመረ
ከፍቅኛቸው ጋር የመጡት አብረው መደነስ ጀመሩ ሌሎችም ለሁለት ሆነው መደነስ
መጫወት ጀመሩ
ቅድስት ልጁን ይዛ አንስታ መስደነስ ጀመረች
ጥሩ ሙድ ላይ የነበርኩ ልጅ እንደገና በቅናት እርር ድብን አልኩኝ
ቅድስትን በጥሩ አይን እያየኋት አይደለም በዚህ አጋጣሚ ሮዛ ቅድስት ወደ ወጪ
አወጣች ልጁ መጣና እጄን ይዛው አስነሳ
እኔ እኮ መደነስ አልችልም አልኩት
ችግር የለም እኔ አስለምድሻለሁ ብሎ አብረን መደነስ ጀመረን ልቤ ከደስታ
ብዛት የተነሣ ቀለጠ
ቅድስት እቤት ስትገባ ከልጁ ጋር አብረን እየደነሰን ነበረ እሷም ቁጭ ብለ
በተራዋ ማየት ጀመረች
እኔ በልቤ እስክ የኔን ህመም በኔ ቦታ ሆናሽ በተራ ታመሚ ብዬ የበለጠ ከልጁ ጋር
መተሻሸት ጀመርኩ
.
.
ይቀጥላል

http://t.me/USA2A
#የታክሲ 🚎 ረዳቶች ግን #ወራጅ ስንላቹ "እዚ ጋ"? 🙄 ብላቹ የምጠይቁን 😠
#ታዲያ ወራጅ የሚል ሱስ ይዞን ነው ☹️☹️


😂😂

#Stay_Safe

@USA2A