Paradise
662 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
#አዲስ_ትረካ_ዛሬ_ይጀመራል_በጣም_ገራሚ_ትረካ_ነዉ_ምንጀምረዉ <<ገምሃልያ>> መልካም የምንባብ ጊዜ ይሁንልን፡፡

#ክፍል_1_ገምሃልያ

#እንደወትሮዬ ሁልግዜ ቅዳሜ ወይ እሁድ ከሰአት እምሰራው ስራ ከሌለኝ ከመፅሃፍ መደርደሪያዬ ላይ ውድ ጓደኞቼ በስጦታ መልክ ከሰጡኝ መፅሃፎች አንዱን አነሳና ቦሌ ማተሚያ አከባቢ ትንሽ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኝ ደስ እሚል በዛፎች የተሞላ ፓርክ አለ።
ብዙ ግዜ እዛ ሄጄ መፅሃፍ ማንበብ እወዳለው። ዛሬ እለቱ ቅዳሜ ነው እዛ ሄጄ ለማንበብ የመረጥኩት ብርቅርቃ እሚለውን መፅሃፍ ነበር አሜን እምትባል ጓደኛዬ የሰጠችኝ መፅሃፍ ነው እሚገርመው ብርቅርቅታን የመሰለ አሪፍ መፅሃፍ እስከዛሬ አላነበብኩትም ነበር ከመደርደሪያው ላይ ስቤ ጠቅለል አድርጌው ይዤ ወጣው።
መንገዴን ከቦሌ ድልድይ ጫፍ ወደ ስታዲየምና ሚክሲኮ በሚወስደው መስመር ታክሲ ተሳፍሬ ወደ ማተሚያ ቤት ሄድኩ። ማተሚያ ቤት ጋር ስደርስ ወርጄ በእግር መንገድ ወደ ውስጥ ወደፓርኩ ገሰገስኩ መንገዱ ቁልቁለት ስለሆነ ሳልወድ በግድ ያሯሩጠኛል። እዛ ሰፈር ያሉት ፍየሎች ሁሌም ሳያቸው ያስቁኛል በጣም ትልልቅ ጥጃ ነው እሚያክሉት ምን እንደሚቀልቧቸው እንጃላቸው።
እነሱን በአይበሉባ እየታዘብኩ ፓርኩ ጋር ደረስኩ ለመቀመጥ ሁለት ብር ከከፈልኩ በኃላ ሁሌም ወደምቀመጥባት ሰላማዊ ቦታ አቀናው ቦታዋ ጥግ ላይ ሁና ከሁሉም እይታ ገንጠል ብላ ጀርባዋን ሰጥታ ያለች ቦታ ናት ከፊትለፊቷ እሚያምር፤ ትንሽ ራቅ ብሎ የሚገኝ የሙዝ እና የበቆሎ እርሻ ማሳ ይታያል። እናም ወደቦታዬ እየሄድኩ በልቤ ሌላ ሰው እንዳይቀመጥባት እየቋጠርኩ ሄድኩ ቦታዬ ላይ ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ ከጀርባ ከሚታዩት ክብ መቀመጫዎች ላይ አንዲት በግምት በእኔ እድሜ አከባቢ እምትሆን ሴት ሲጋራ እያጨሰች አየኃት ለሽራፊ ሰከንዶች ቆም ብዬ ካየኃት በኃላ ወደቦታዬ ሄድኩ ማንም አልተቀመጠባትም ደስ አለኝ።
በሸክላ ጡብ እና በሲሚንቶ የተሰራችውን መቀመጫ በሶፍት ጠረግኩና ተቀመጥኩ ቦታዋ ደስ ትላለች ሙሽሮች ሲጋቡ ለመድረክነት የሚጠቀሙባት ባለግርማሞገስ የድንጋይ ዙፋን ትመስላለች መደገፊያዋ ረጅም ስለሆነ ካልቆምኩ በስተቀር ከኃላዬ ምን እንዳለ አይታይም ያውም በኔ መለሎ ቁመት።

ቦታዬ ላይ ተረጋግቼ ከተቀመጥኩ በኃላ መፅሃፌን ከፈትኩና ሀ ብዬ ማንበብ ጀመርኩ.... ግን ቅድም ሲጋራ እያጨሰች የነበረችው ሴት በአእምሮዬ ተመላለሰች ፊቷ የተከፋ ይመስላል ሲጋራውን በብሽቀት እየማገች ጭሱን ሽቅብ ትለቀዋለች ሄጄ ምን እንደሆነች ልጠይቃት አሰብኩና ምን አገባኝ ብዬ መልሼ ተውኩት መፅሃፌን ማንበብ ቀጠልኩ።
ግን የልጅቷ ሁኔታ አእምሮዬ ውስጥ እየተመላለሰ ሰላም ነሳኝ በመጨረሻም ሄጄ ምን እንደሆነች ልጠይቃት ወሰንኩና መፅሃፉን ከድኜ አስቀመጥኩት። ወደሷ ሄድኩ እሷ የተቀመጠችበት ቦታ ከኔ ጀርባ ሆኖ ቅርብ ርቀት ላይ ነው ሄጄ ሰላም አልኳት የደረቀ ሰላምታ ሰጠችኝ። ሲጋራ ማጨስ እችላለው አልኳት ገልመጥ እያለች በእጇ መሃል የሚጤሰውን ሲጋራ ሰጠችኝ ተቀበልኳትና በጣቶቼ መሃል አድርጌ ጭሱ ሲበን ትንሽ ተከዝ ብዬ አየሁት በጎን በኩል የሸክላው ጡብ ወንበር መደገፊያ ላይ ወጥቼ እግሬን ደግሞ መቀመጫው ላይ አድርጌ ተቀመጥኩ።
እሷን ምንም ሳልናገራት ሲጋራውን ዝም ማየት ቀጠልኩ ውስጡ የሷን ጭንቀት ይሁን ሃሳብ ይነግረኝ ይመስል ከጭሱ ውስጥ መልስ ፍለጋ ገባው። ልጅቷ ከሁኔታዋ ማውራት እምትፈልግ አትመስልም እንዲያ ባይሆን ኖሮ እንደዚ አይነት በብቸኝነት ሰላም እሚሰጥ ቦታ ባልመጣች ነበር። እሷ ማውራት ባትፈልግም እኔ ግን ማውራት ነበረብኝ። ሲጋራውን ትንሽ ካየሁት በኃላ ወደታች ዘቀዘቅኩት እሳቱ ሲጋራውን በፍጥነት ወደላይ ይበላው ጀመር ጭሱ ወደላይ ይበናል አመዱ ደግሞ ወደመሬት ይወድቃል።
ልጅቷ እማደርግውን ዝምብላ እያየችኝ እንደሆነ ሳውቅ ምን ይታይሻል አልኳት ሲጋራ አለችኝ። እኔ ግን ህይወት ይታየኛል ምስቅልቅሉ የወጣ ህይወት ከላይ ወደታች የተገለበጠች ህይወት አመድ እና ጭስ የሆነ ህይወት እሳት የሆነ ፈተና። ህይወት እንደሲጋራው ቀጥ ተደርጋ በምቾት ስትያዝ እኛ የህይወትን ትርጉም አናውቅም እሳቱ ቀስ እያለ ሲጋራውን ይጨርሰዋል ነገር ግን ሲጋራው ሲገለበጥ መከራ ሲበዛብን እሳቱ ቶሎ ሲጋራውን ይበላዋል በመከራ ውስጥ ሆነን የህይወት ትርጉም ይገባናል ህይወታችችንን አጣጥመን ቶሎ ቶሎ እንኖራታለን እዚች ምድር ላይ ያለን ግዜ ውስን ስለሆነ ሲጋራው ወደታች ቢዘቀዘቅም ጭሱ ግን ወደላይ ነበር የሚጨሰው ፈተናውን የሚያልፍ ሰውም እንደዛ ነው ግን...... አልኳትና ዝም አልኩ ሲጋራውን ለልጅቷ መለስኩላት እና ተነስቼ ወደቦታዬ ለመመለስ ስዘጋጅ ግን ምን? #አለችኝ🤔 🤔

#ቀጣይ_ክፋል_እንዲቀጥል_ከፈለጋቹ

#likes #share #forward #invite! እና ብዙ like ግድ ነዉ:
#ትረካዉ #ይቀጥል👍
#ይቅር 👎🏼
http://t.me/usa2a
#የጨጓራ_ህመም_gastritis)

@USA2A ጤና #ክፍል_1

#የጨጓራ_ህመም_ምልክቶች

↪️ምግብ ከተመገብን በኋላ ጡሩ ስሜት አለመሰማት ለምሳሌ ልብ ላይ የማቃጠል ስሜት
↪️ማቅለሽለሽ
↪️ማስመለስ
↪️የምግብ ፍላጎት መቀነስ
↪️በቂ ምግብ ሳይመገቡ የጥጋብ ስሜት
↪️የሆድ መንፋት ጸባይ
↪️የሆድ መጮህ (ድምፅ መፍጠር) ጸባይ
↪️አንዳንዴ ሽንት ማቃጠል እና የመሳሰሉት

የጨጓራ ህመምን ምን ሊያመጣው ወይንም ሊያባብሰው ይችላል?
የጨጓራ ህመምን ብዙ ነገሮች ሊያስነሱ ወይም ሊያባብሱ ይችላሉ ነገር ግን ከሰው ሰው ሊለያዩ ይችላሉ ማለት ነው ለምሳሌ አንዱ ተስማምቶት የተመገበው ምግብ ለሌላኛው ላይስማማ ይችላል።
በአብዛኛው ሰዎች ላይ የሚከተሉት እንደ ምክንያት ሊጠቀስ ይችላሉ

↪️በሆነ ባልሆነው መበሳጨት
↪️ብዙ ጊዜ ለነገሮች መጨነቅ
↪️ቡና እና ሻይ ማብዛት/በተለይ ትኩሱን
↪️ምግብ በጊዜ ሰአቱን ጠብቆ አለመመገብ
↪️ከመጠን በላይ መመገብሸ
↪️መድሀኒት አብዝቶ መውሰድ
↪️ህመምን በስርአቱ አለመታከም በተለይ የሆድ፥የስኳር የጉበት ኩላሊት የልብ ህመም እና የመሳሰሉት ምክንያቱም እነኚህ ህመሞች ጭንቀት ይፈጥሩና ብዙ አሲድ ወደ ጨጓራ ተለቆ ጨጓራ እንዲላጥ ስለሚያደርጉ ነው።
እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን የጨጓራ በሽታ ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ መታከም የሚገባቸውን ህመሞች ነው ለምሳሌ የጉበት መቁሰል፥የጉበት ካንሰር፥የጨጓራ ካንሰር፥የጨጓራ ነቀርሳ/ቲቢ እና የመሳሰሉትን ነው ከዚያ በተጨማሪ የጨጓራ በሽታ የተለያዩ ደረጃ ሲኖረው ከትንሽ መቆጣት እስከ መላጥ ደረጃ ሊደርስ ይችላል መላጡን ማወቅ የሚቻለው በአፍ በኩል ተደርጎ በሚከተት #ኢንዶስኮፒ መሳሪያ ነው።

#የጨጓራ_ህመም_እንዴት_ይታከማል?

የጨጓራ ህመም በአብዛኛው ከህይወት ማሻሻል ለውጥ ጋር ቢሆን በቶሎ ወደ ጤንነት መመለሱን ያፋጥናል።

ወደ ሀኪም ቤት በመሄድ ደግሞ የተለያዩ መድሀኒቶችን(የአሲድ መመረትን የሚቀንሱ ኪኒኖች፥ከቆሰለው የጨጓራ ክፍል ላይ በመጣበቅ የማቃጠል ስሜት የሚቀንሱ ሺሮፖች፥ኤች.ፓይሎሪ የተባለውን ጀርም የሚከላክል ኪኒን በተናጠል ወይንም በተጣምሮ እንደ አስፈላጊነቱ በመውሰድ የጨጓራ ህመም ከመባባስና መጥፎ የሚባልደረጃ ሳይደርስ ለመከላከል ይረዳናል)

ከምርመራ በኋላ ሀኪም ሊያዝልን ይችላል።ለምሳሌ የሰገራ ምርመራ በጨጓራችን ውስጥ ኤች.ፓይሎሪ የሚባል ጀርም ካለ ይኸ ጀርም የአብዛኛው ሰዎችን ጨጓራ በሽታ የሚያመጣ ነው።

በተጨማሪ እነዚህ የታዩት ምልክቶች በርግጥ ከጨጓራ ነው ወይስ ከሌላ የሚለውን ለመለየት ሀኪሙ ይኸ ሊሆን ይችላል ብሎ ያሰበውን ምርመራ ያዛል
ኢንዶስኮፒ ምርመራ ደግሞ የጨጓራ ህመሙን ደረጃ ሊነግረን ይችላል።

እንደ አጠቃላይ ግን የጨጓራ ህመም ከመከሰቱ በፊት ህይወትን በማስተካከል መከላከሉ ወደር የለለው ምርጫ ነው:ታሞ ከመማመቅ አስቀድም መጠንቀቅ አይደል ሚባለዉ::

ለ አስተያየት ና በቀጣይ እንዲቀርብላቹ ምትፈልጉት በሽታ መንስኤዉ ና መፍትሄዉ ካለ በ @Galaxy1bot ተጠቅማቹ ዘድርሱን

ለጨጓራ በሽተኛ ምታዉቁዋቸዉ ሰዎች #share #forward

http://t.me/USA2A
Forwarded from Paradise