Paradise
660 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
4 u by @USA2A

#ገምሃልያ_ክፍል_8

#መንገድ ላይ እየሄድኩ ታድኤልን እንዴት የኔ ማድረግ እንዳለብኝ እያወጣው እያወረድኩ እያለ ጓደኛዬ ሃናን ደወለችልኝ ሰላም ከተባባልን በኃላ አመሻሽ ላይ እምትችል ከሆነ እንድንገናኝ ጠየቅኳት። ስለታዲ ልነግራት እምችለው ብቸኛ ሰው እሷ ብቻ ነበረች ማታ ላይ ተቀጣጠርን።
ከሃኒ ጋር የተቀጣጠርንበት ቦታ ቀደም ብዬ ሄድኩ።
ከሃኒ ጋር ለተወሰነ ግዜ የጋራ ጉዳያችንን ከተጨዋወትን በኃላ ዛሬ እሷን የቀጠርኩበትን ዋና ምክንያት እነግራት ጀመር እንዴት ትናንት ከታዲ ጋር እንደተዋወቅ ሁሉንም ነገር ስነግራት ከት ብላ ሳቀች አንቺ ያምሻል እንዴ ቆይ ከተዋወቅሽው 24 ሰአት እንኳን በቅጡ ያልሞላሽን ሰው እንዴት መውደድ ትችያለሽ አትቀልጂ ባክሽ አለች እየቀለድኩ እንዳልሆነ የምሬን እንደሆነ አስረግጬ ነገርኳት እንዴት እሱም እኔን እንዲወደኝ ማድረግ እንደምችል ጠየቅኳት። ሃኒም ኮስተር እያለች አረ... ፂ ይሄማ የአይን ፍቅር ነው አለ አይደል እንዳንዴ እንዲው አይተሽው እምትወጂው ሰው እንዲው በግርድፉ እንደዛ ነው ሚሆነው ግዜ ስጪው ምን አለ በይኝ ትረሺዋለሽ አሁን አለችኝ። ተበሳጨው ሃናን እኔ እሱን መርሳት አልፈልግም አውቃለው ትናንት ነው ያወቅኩት ስለሱ እማቀው በጣም ጥቂት ነገር ነው እሱን አፈቀርኩት ስልሽ ላንቺ ቀልድ ሊመስልሽ ይችላል ግን ፍቅር እንዴት እና በየት በኩል እንደሚመጣ ማነው እሚያወቀው እስኪ ንገሪኝ አንቺ ራህመትን እንዴት ተዋውቀሽው እንደወደድሽው ታስታውሻለሻ ምንም ትርጉም እሚሰጥ ነገር ወይደለም ታዲያ መቼ ነው ፍቅር ትርጉም ኖሮት እሚያወቀው እኔ ለማንም ወንድ እንዲ ተሰምቶኝ እንደማያውቅ አንቺም እኔም እናውቃለን ታዲያ እንዴት ነው ይህንን ልዩ ስሜት እንዲሰማኝ ያደረገውን ሰው እርሺው እምትዪኝ ከመፈቀር በላይ ማፍቀር ፀጋ ነው እሺ። እሱ እኔን ባያፈቅረኝ እንኳን እኔ እሱን እያፈቀርኩት እኔራለው ከሱ እማገኘው ነገር ባይኖር እንኳን እሚያሳጣኝ ምንም ነገር የለም እና እባክሽ እርሺው አትበይኝ በራህመት ይሁንብሽ አልኳት ንዴቴ ወደ ሃዘን እየተቀየረ። ሃኒም አዘነችልኝ እሺ እሺ አልልሽው ፂ እና አሁን ምንድነው መፍትሄ...ውውው.. አለች እሷም እያሰላሰለች። ትንሽ ካሰበች በኃላ እስኪ ስለ ታድኤል ባህሪ እምታውቂውን ንገሪኝ አለችኝ። እኔም መለስ ብዬ ስለሱ አሰብኩ.... ደግ ነው ግን ደግሞ ቁጡ እና ዝግ ነው ማለት የውስጡን ለማንም አያሳይም ስለራሱ ማውራት አይፈልግም ጥሩ ሰው እንደሆነ አውቃለው ግን የሆነ እሚያስፈራ ነገርም አለው ብቻ ብዙም አላውቀውም ዝምታ የበዛበት ቦታ ይመቸዋል ወከባ ግርግር ምናምን ብዙም ደስ አይለውም ይሄእ ነው እማውቀው አልኳት ብዙ አምጬ ስለሱ የማውቀውን ነገርኳት። እእእ ከበድ ያለ ሰው ይመስላል እንደነገርሽኝ ከሆነ ጭምት የሚሆንበት የራሱ ምክንያት ይኖረዋል መናገር እማይፈልግ ከሆነ አታጨናንቂው አንቺን ደግሞ አቅሻለው በጣም ለነገሮች ችኩል ነሽ የሁለታቹ ባህሪ በጣ..ም ይለያያ... ሃናን እምታወራውን ሳላስጨርሳት አይገርምሽም ታዲም ችኩል ነሽ ብሎኛል አልኳት። አዪ.... አንቺ ልጅ እንደው ምን ይሻልሻል እስኪ ሰከን በይ እንደሱ አይነት ያለ የተረጋጋ ሰው እንዳንቺ ችኩል ችኩል ጥድፍ ጥድፍ የሚልስ አው አይመቻቸውም እመኚኝ ስለማውቅ ነው በጣም ነው ሚያበሳጫቸው ራህሚም እንደዛ ስለነበር ነው አንቺም እሱን ማግኘት ከፈለግሽ ረጋ.... በይ አለበዚያ ህፃን ነው መስለሽ እምትታያቸው እና ባህሪሽን አስተካክይ ማውራት እማይፈልገውን ነገር አትጠይቂው እና ስትቃርቢው እንደምታፈቅሪው ሰው ሆነሽ ሳይሆን እንደ እህት እንደ ጓደኛ ቅረቢው ከዛ ቀስ በቀስ እየተግባባችው ስትሄዱ ማወቅ እምትፈልጊውን ነገር አንቺ ሳትጠይቂው እራሱ ይነግርሻል እንደነገርሽኝ ከሆነ እንደታድኤል ያሉ አይነት ሰዎች ግዜ የሚፈታቸው የሚስጥር ሰዎች ናቸው ችኮላ አይመቸው ደጋግሜ ነግሬሻለው ፂ እሱን ማግኘት እምትፈልጊ ከሆነ አትሩጪ ሰከን ብለሽ ጠብቂው እሺ... እና ደሞ ወከባ ጫጫታ እማይመቸው ከሆነ ስትገናኙ ፀጥ ያለ ቦታ ተገናኙ ለሱ ነፃነት የሚሰማው ቦታ ማለት ነው በሱ ምርጫ ይሁን አለችኝ። ሃኒ የመከረችኝ ምክር አሪፍ ነበር ብዙ ግዜ ለነገሮች እንደምቸኩል አውቃለው ግን ባህሪዬ ነው ብዬ ተቀብዬው ነበር ታዲን ማግኘት ካለብኝ እኔም ባህሪዬን ማስተካከል እንዳለብኝ አሰብኩ። የታዲን ጨዋታ ከጨረስን በኃላ ራህመት እንዴት ነው በእናትሽ አልኳት እየሳቅኩ ራህመት ማለት የሃናን እጮኛ ነው በቅርቡ ነበር በቤተሰብ ኒካ ያደረጉት። ራህሚ ደህና ነው ባክሽ ምን ይሆናል ብለሽ ነው አለችኝ እሷም እየሳቀች ሃናን እና ራህመት ያላቸውን ፍቅር ሳይ ያስቀኑኛል ምናለ እኔም እንደሷ በሆንኩ እላለው ትዝ ይለኛል ሃናን ራህመትን የወደደችው ሰሞን እንዴት መከራችንን ስታበላን እንደነበር እሱም ኩሩ ልጅ ነበር አሁን ነገሮች ተገለባንጠው እኔ በሷ ቦታ ሆኜው እርፍ...

ከሃናን ጋር ምሽቱን የሆድ የሆዳችንን ስናወራ አመሸን እንዴት ታዲምመድ እንዳለብኝ ብዙ ነገር እየነገረችኝ ነበር ከሃኒ እምወድላት ባህሪዋ ብልጥ እና አስተዋይነቷን ነው። ግዜው ሲገፋ ተለያይተን ወደቤት ሄድኩ። ታዲ ዛሬ ቤተሰቦቹ ቤት ምሳ ግብዣ እንደነበረበት ትዝ ሲለኝ ልደውልለት አሰብኩና ስልኬን አወጣው።

#ይቀጥላል.......
👍👍የተመቸው እስኪ እጁን ያሳየን👍👍 እና ቶሎ ቶሎ እንፖስትዋለን።👍👍

#ክፍል_9_ቶሎ_እንዲለቀቅ_ብዙ
#like 👍 #share #forward #invite! እና ብዙ ብዙ like ግድ ነዉ:
http://t.me/usa2a