Paradise
662 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
#ሰካራሙ_ክፍል_{3}

#የሚያደርጉትን ሁሉ በመስኮ ት እየተከታተልኩ ነው
ምን ነክቶኝ ነው? አሁን እነሱን መከታተሉ ለምን አሰፈለገ? ብቻ ትኩረቴን እነሱ ላይ
አድርጌ መከታተል ጀመርኩ
ትንሽ አብረው ከተጫወቱ በኋላ እቤት ገቡ
እኔ እኮ ነግሬያችሁ ነበረ ከቅድስት እጅ ማንም ማምለጥ አይችልም ብዬ
ውስጤ ብዙም ደስተኛ አይደለም ዝም ብዬ ፊልም ማየት ጀመርኩ ከትንሽ
ደቂቃዎች በሓላ ቅድስት እኔጋ መጣች አንቺ እንደተናገርሽው አደረግሽ አይደል ?
አልኩኝ
እ..እ..እ..እ ምነው እንደዚህ ሆንሽ አቦ ልጁ ፍሬሽ ነገር ነው እኔ እሱን ፈልጌ ሄዳለሁ
እሱ ቡና አፍልቶ እኮ ነው አንቺንም እንድጠራ እዚህ የለከኝ ብለ ሳቀች
ለምን እንደሆነ አላውቅም ብቻ ደስ አለኝ ለካ ነገሮችን በአንዴ እንደዚህ ነው
ብለው መወሰን ስህተት ነው እኔ ወደቤት አብረው ሲገቡ በሌላ ነገር ነበረ
የተረጎምኩት እኔ የቅድስትን ባህርይ ስላማውቅ ሌላ ነገር አስቤ ነበረ ለካ እኔ
የቅድስትን ባህርይ ብቻ እንጅ የልጁን ባህርይ አላውቅም ነበረ
ብዙም ጊዜ የእኛ የሰዎች ችግር ይሄ ነው አንድን በፊት የምናውቀውን ሰው ከሌላ
ሰው ጋር ካየን ነገሮችን በቶሎ ትክክል ነው ብለን እንወስናለን ነገር ግን ስለ
ሌላው ሰው ምንም አይነት ነገር አናውቅም ለምሳሌ አንድ ሰው ከሴተኛ አዳሪ ጋር
ካያን ወዲያውኑ ለምን ከሷ ጋር እንደሆነ ለመገመት መሮጥ እንወዳለን ልጁ ለሷ
ወንድም ይሁን ጓደኛ ይሁን በቃ ምንም አናውቅም ከሷ ጋር ስለሆነ ብቻ ነገሩን
በአራት ነጥብ እንደመድማለን
እኔና ቅድስት አብረን ልጁ ቤት ገባን ቁጭ በሉ አለና የተፈላዉን ቡና ቁርስ ጨምሮ አምጥቶ ሰጠን
ዋውውውው ይሄን ቡና ጠጥቶ ሙያውን አለማድነቅ አይቻልም መቼም ይሄ
ሰካራም እንደዚህ አይነት ቡና አፍልቶ ጠጣን ብንል ማንም አያምንም እውነቴን እኮ ነው አሁን ለእና ሄለን እራሱ እንደዚህ ብለን ብንናግራቸው መቼም በቀላሉ
አያምኑም
ለካ የሰው ልጅ ማለት የማያውቁትን መጽሐፉ ማንበብ እንደማለት ነው ምንም
አይገባሽም በቃ ዝም ብሎ ማንበብ
እንደዚህ ነው ብለሽ ለመረዳት ስትሞክሪ ሌላ ይሆናል በቃ ሙሉ በሙሉ የሰውን
ልጅ ማወቅ ከባድ ነው አሁን ይሄን ልጅ ከውጪ የያ ሰው በቃ ባለጌ ጠጪ ክቡር
የሌላ ስራ የሌላ እውቀት የሌላ ዝም ብሎ የሚኖር ሰው ይመስላል
ምንም አይናገርም ቅድስት ለጠየቀችዉን ጥያቄ ብቻ መልስ ይሰጣል
እዚህ በምን ምክንያት መጣህ አለች በስራ ምክንያት ነው አለን
በልቤ እንዴ ስራ ይሰራል እንዴ እኛ እኮ ማታ ጠጥቶ ሲመጣ ቀኑን ሙሉ እየጠጣ
የሚውል ይመስለን ነበረ
ምንድነው የምትሰራው አለች
አይ አንድ ትልቅ ድርጅት ውስጥ ማናጀር ሆኜ እሰራለሁ አለ
ምን? በመሃል ገብቼ ታዲያ እንደዚህ ትልቅ ሰው ሆነህ ለምን እንደዚህ እራስህን
ትጠላለህ አልኩኝ
ትንሽ ከሳቀ በሓላ መጠጥ የሚጠጡት ትንንሽ ሰዎች ናቸው እያልሽኝ ነው አለኝ
አይይይ እንደዛ ማለቴ አይደለም ግን አንተ ከልክ በላይ ትጠጣለህ አልኩት
ሰው ከልክ በላይ ጠጣ የሚባለው ምን ሲሆን ነው አለኝ
አለ አይደል አንተ አሁን እቤት ስትመጣ እየወደክ እየተነሳህ ነው እቤት
የምትመጣው ከልክ በላይ ጠጣ የሚባሉ ሰዎች ወድቀው መነሳት የማይችሉ ናቸው ብሎ ሳቀ
ቅድስት አንተ ግን እንደዚህ ሰክረህ እንኩዋን አንድም ቀን ሴት ይዘህ አትመጣም
እኮ ብለ ሳቀች
ማነው ሴት ልጅ የሰካራሞች ስካሪ ማብረጃ ነች ያለሽ?
ሰው መጀመሪያውኑ ልብ ውስጥ ያለውን ነገር ከፈጸመ በሓላ ጠጥቼ ነው ይላል
ልብ ውስጥ የሌለውን ነገር መጠጥ እንዴት አድርጎ ያመጣል?
ይሄ ሰዎች ስህተቱውን አሜን ብለው ላለመቀበል የሚያመጡት ምክንያት ነው እኛ
የሰው ልጆች በተፈጥሮ ስህተትን አሜን ብለን ከመቀበል ይልቅ አንዱን ስህተት
ለመደበቅ ብለን ሌላ ስህተት እንሰራለን አንድ ስህተት ሌላ ስህተት እየወለደ
ለዚህም ነው ዛሬ ሰው ከመሆን ይልቅ እንስሳ ለመሆን የበቃነው እንስሳ እንኩዋን
ከስህተት ይማራል እኛ ሰዎች ግን ለስህተት መሸፈኛ ሌላ ስህተት እንጨምራለን
አለ
ዋ..ው..ው..ው..ው ከልቤ ደስ ያሰኘኝ ንግግር ነው አልኩኝ
እስካዛሬ እንደዚህ አይነት ሰዎችን አንድም ቀን ቀርቤ አላማወቄ ቆጨኝ ለካ እውነትም የሰው ልጅ መጽሐፉ ነው ማንበብ ብንፈልግ ብዙ ትምህርቶችን ከሰው ልጅ መማር ይቻላል።
እይን አይኑን እያየሁት ቡናው ከመቼ እንዳለቀ አላወኩም ምናለ ሁሌም እንደዚህ ቡና አፍልቶ በጠራን
አልኩኝ
.
.
.
ይቀጥላል
አስተያየት መስጠት ይቻላል

@Galaxy1bot

http://t.me/USA2A