Paradise
662 subscribers
933 photos
864 videos
75 files
147 links
╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼🙊🧐😆
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭😳😜
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲ @USA2A
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔ 😡😂
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕ ❤️💋😆
#Welcome_to_ur_home_of_jokes
#አማረኛ ና በ #English ቀልዶች, #videoዎች,በ #ዘፈኖች🎶,በ #Meme, #በጥያቄዎች ና በብዙ ነገር ለመዝናናት
እኛን ለማግኝት በዚ @Galaxy1bot ተጠቀሙ
Download Telegram
#ገምሃልያ_የመጨረሻ_ክፍል😫😫😫

#ፅናት ብትጠራኝም መልስ አልሰጠኃትም ዝም ብዬ መምገዴን ቀጠልኩ እውነቱን ለመናገር መልሷን ለማወቅ ስለፈራው ነበር ምንም እንድትናገር እድል ሳልሰጣት የሄድኩት። ቤቴ ከገባው በኃላ አምላኬ ፅናት ላይ ያሳየኝን ፅናት ጨምሮ ከአስተዋይነት ጋር ይሰጣት ዘንድ ፀሎት አደረኩ።

ግዜያት ነጎዱ.... እኔም የፅናትን በህይወት መኖር ወይም መሞት ሳላውቅ እዛው ፓርክ አልፎ አልፎ መሄዴን ቀጠልኩ በሄድኩባቸው ግዜያት ሁሉ በአይኔ ፅናትን ቦታዋ ላይ እፈልጋት ነበር አንድ ቀን እንደማገኛት ተስፋ አደርግ ነበር። ፅናት ይህንን ታሪክ ከነገረችኝና ከተገናኘን አንድ አመት ከመንፈቅ አለፈ...
ይህንን የሚያሳዝን ታሪክ እንድፅፈው ያነሳሳኝ ከጥቂት ወራት በፊት ያየሁት ነገር ነበር።

ከጥቂት ወራት በፊት እንደለመድኩት ከስራ ውጥረት ነፃ በሆንኩበት በአንዱ ቅዳሜ ቦሌ ማተሚያ ጋር ወዳለው ፓርክ ልሄድ ወሰንኩ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ስራ በዝቶብኝ ተጨናንቄ ስለነበር ከሄድኩ ቆይቻለው። እንደለመድኩት ከመደርደሪያዬ ላይ የሲድኒ ሼልደን "የፍርድ ቀን ዘመቻ" የሚለውን መፅሃፍ አንስቼ እሱን ላነበ ወጣው። እንደሁልግዜውም ቦሌ ድልድይ አከባቢ ቆሜ ወደ ሸዋ ዳቦ፣ ሜክሲኮ የሚሄዱትን ታክሲዎች መጠባበቅ ጀመርኩ ምሳ ሰአት ስልሆነ ፀሃይዋ በጣም ከራለች ራሴን በያዝኩት መፅሃፍ ከልዬ አዲስ የሚሰራውን የአየርመንግድ ሞልቃቃ ሆቴል ኪነ ህንፃ እያየው መጠባበቄን ቀጠልኩ። ታክሲው ሲመጣ መሰስ ብዬ ገብቼ ጉዞዬን ቀጠልኩ ማተሚያ ጋር ስደርስ ወርጄ በእግር ያንን ቀልቀለት እየወረድኩ ወደ ፓርኩ አቀናው እነኛ ጥጃ የሚያካክሉ ፍየሎች ዛሬም አሉ! እያየኃቸው እየሳቅኩ አይ እነኚ ፍየሎች ምን ቢያበሏቸው ነው እያልኩ እየሳቅኩ ወደ ፓርኩ ገባው እንደቀድሞዬ ቦታዬ እንዳትያዝ እየቋጠርኩ ወደቦታዬ ስሄድ ሁለት ጥንዶች እኔ ከምወዳት ቦታ ላይ ተቀምጠው እየተሳሳቁ ነው ቦታዬ መያዟን ሳውቅ እየተናደድኩ በልቤ ብሽቆች!!! ከዚ ሁሉ ፓርክ የኔ ቦታ ነው ሚታያቹ አልኩና ፊቴን አዙሬ ሌላ ቦታ ፍለጋ መራመድ ስጀምር ረምሃ...ይይይ! የሚል የሴት ድምፅ ሰማው ደንገጥ ብዬ ስሜ ወደተጠራበት አቅጣጫ ዞርኩ እነኛ ቅድም ሲሳሳቁ ከነበሩት ጥንዶች ሴቷ ነበርች የጠራችኝ። አቤት አልኳት ወይኔ ጉዴ..... አንተ አለህ አለችና እየሮጠች ወደኔ መጣች ልጅቷን ስላላወቅኳት ደነገጥኩ ኮስተር ብዬ ማን ልበል ስላት እየሳቀች አላወቅከኝም ፅናት ነኝ እኮ ከአመት ከምናምን በፊት እዚ ተገናኝተን ያወራኀኝ ልጅ እኮ ነኝ አለችኝ ገምሃልያ! አለችኝ ወዲያው መልኳት እየመጣልኝ እንዴ!! ሰላም ነው ፅናት እንዴት ነሽ መልክሽ ተቀየረብኝ ወፈርፈር ብለሻል በጣም ጠፋሽ እኔማ.... መስሎኝ ነበር። ፍልቅልቅ እያለች እረ... በጭራሽ አላደረኩትም እንደውም የዛኔ በጣም አናደኀኝ ነበር ሳታስጨርሰኝ ነበር የሄድከው አለችኝ አው አልሰማ ስትይኝ ታዲያ ምን ላድርግሽ አልኳት እየሳቅኩ። የምር ግን በጣም አመሰግንሃለው የዛኔ ለመከርከኝ ምክር ከዛኔ ጀምሮ በጣም ብዙ ግዜ እየመጣው እዚ ብጠብቅህም አላገኘሁህም በጣም ላገኝህ እፈልግ ነበር ስልክህን ስላልሰጠኀኝ ላገኝህ አልቻልኩም ፌስቡክ ላይም ስፈልግህ አጣሁህ አለችኝ። አው እኔም እየፈለኩሽ ነበር ምናልባት አለመግጣጠም ይሆናል እኔ ፌስቡክ ስለማልጠቀም ለዛ ነው ከቅርብ ግዜ ወዲ ትንሽ ስራ እየበዛብኝ ስለሆነ እዚ ፓርክ መጥቼ አላውቅም ለዛ ይሆናል ያልተገናኘነው አሁን በህይወት ስላገኘሁሽ በጣም ደስ ብሎኛል ምን ተገኘ በህይወት እሚያቆይ ነገር አልኳት። አንተ! አንተና ዳኒ አለችኝ ዳኒ አልኳት? ግራ እየገባኝ ፅናት ደንገጥ እያለች ውይ የኔ ነገር ና ላስተዋውቅህ አለችኝና አብሯት ተቀምጦ ወደነበረው ጓደኛዋ ወሰደችኝ። ልክ ስንደርስ ዳኔዬ ረሚ ማለት እሱ ነው ተዋወቀው አለችው እሱም ብድግ እያለ ሰላም ነው ዳንኤል እባላለው ፅናት ብዙ ግዜ እስላንተ ብዙ ነገር ነግራኛለች በጣም አመሰግናለው ላደረክላት ነገር እውነት ፈጣሪ ውለታህን ይክፈልህ አለኝ። ልቤ በደስታ ተሞላ ትንሽ እንደማስታወስ አልኩና ዳንኤል ዳንኤል ...? ዶክተር ዳንኤል ነው አልኳት ወዘናው ዶክተር ስለመሰለኝ። አዎዎዎ... አለች ፅናት በደስታ እየዘለለች ኦው አሪፍ ነው በጣም! ደስ ይላል እውነት በጣም ደስ ብሎኛል ፅናት ያንን ከባድ ግዜ አልፈሽ ለዚ በመድረስሽ ደስ ብሎኛል ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም አልኳት ልቤ ሃሴት እያደረገች። በአንድ አጋጣሚ ተሰብሮ ያየኀው ሰው አሁን ላይ ደህና ሆኖ ሲደሰት ማየት በጣም ደስ ይላል። ፅናት የእጇን ጣቶች እያሳየችኝ ልንጋባ ነው ቀለበት አድርገናል አለችኝ ደስ ይላል አምላክ ትዳራቹን ይባርክ ለሰርጋቹ እንደምትጠሩኝ ተስፋ አደርጋለው አልኩ ፈገግ እያልኩ በደምብ ነዋ! አለ ዳኒ። ትንሽ ካወራን በኃላ በቃ አልረብሻቹ እናንተም ጨዋታችሁን ቀጥሉ እኔ ሌላ ቦታ ልሂድና ላንብብ አደራ ለሌላ ግዜ ግን ፅኑዬ ቦታዬን ለቀቅ በጣም ነው ምወዳት አልኩ ቆጣ ብዬ እንደቀልድ። አረ... ዛሬማ ከእኛ ጋር ነህ ስንት ግዜ ስፈልግህ ዛሬ ባገኝህ ልሂድ ትላለህ እንዴ አልሰማህም አለችኝና ወደ ዳኒ እያየች ዳኒዬ በናትህ እንውጣና ውጪ አንድ ካፌ ቁጭ ብለን እናጫውተው አለችው ደስ እንደሚለው ገለፀልኝ። አረ... አያስፈልግም እኔ ላነብ ነው የመጣሁት እዚ አልኳት ሌላ ግዜ ታነባለህ ባክህ አለችና መፅሃፉን ቀምታኝ እጄን ይዛ ዳኒንም እየጎተተች ከፓርኩ ወጥተን በቅርብ ያለ ካፌ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን ፅናት አሁን ስላለችበት ሁኔታና ማንነት በደምብ አጫወተችኝ ከዳኒ ጋር እንዴት የፍቅር ህይወት እንደጀመሩም ረጅም ታሪክ ተረከችልኝ ከሰአቱን ሙሉ ስንጨዋወት ዋልን መሸ! ፅናት አሁን ባላት ህይወት ፍፁም ደስተኛ ናት ዳኒ ከማንም በላይ የሚያከብራት እጮኛዋ ነው ሱሶቿን እንዳለ አቁማለች ዳኒ ቀስ በቀስ እንዳስተዋት ነገረችኝ። ራሷን ማጥፋት የሚለው ነገር ፈፅሞ እምታስበው ነገር አይደለም ሌሎች በሷ ጫማ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ስታገኝ ትረዳለች ታሪኳን አጫውታ ታበረታታቸዋለች እሷ እንድትሆን የምመኛቸውን ነገሮች በሙሉ ሆናለች እሷ ላይ ያየሁትን ጥንካሬ ራሷም ማየት ችላለች በጣም ሲመሽ መሄድ ስለነበረብኝ ስላገኘኃቸው ደስ እንዳለኝ ነግሪያቸው መልካም ትዳር ተመኝቼላቸው ልሄድ ተነሳው ትንሽ እንደሄድኩ ጠራችኝና እየሮጠች መጥታ ስልክህን አልሰጠኀኝም አሁንም ጠፍተህ ስፈልግህ አልገኝም ካላስቸገርኩህ ስልክህን ስጠኝ አለችኝ ፈገግ አልኩና ስልክ ቁጥሬን ሰጠኃትና የመጨረሻ ምክር? አልኳት ደስ ይለኛል አለችኝ። እሺ ያ የማይነጋ የመሰለሽ የመከራ ለሊት ነግቶ አይተሽዋል እኔ ላንቺ እንዳደረኩልሽ አንቺም ለሌሎች በጨለማ ውስጥ ላሉ ሰዎች ሃላፊነት አለብሽ አሁን አንቺ እምትኖሪው ላንቺ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ሰዎችም ጭምር ነው በጨለማ ውስጥ ላሉ በህይወትሽ ምሳሌነት ብርሃን ሁኚላቸው ህይወት ሁሌም በፈተና የተሞላች ናት ሁሌም በጥሩ መልኩ አይተሽ ፈተናሽን ለመወጣት የሚያበቃ አላማና ፅናት ይኑርሽ አልኳት ፅናት ፍልቅልቅ እያለች እሺሺ... አለችኝ ያ በለቅሶ እማውቀው ፊቷ ዛሬ ማስታወስ ከበደኝ ስትስቅ ታምራለች! ቻው ተባብለን ወደቤት ሄድኩ።