የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ስሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 228002 በሰጠ ውሳኔ መሰረት መንግስት/ቀበሌ ቤትን ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት አያጎናጽፍም አንድን ቤት ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት የማያጎናጽፍ በመሆኑ እንዲሁም ቤቱ የመንግስት መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌሉበትሁኔታ በተቋሙ የመረጃ ስርአት ቅጽ 008 በቀበሌ ቤትነት መመዝገቡ ብቻ ቤቱ በመንግስትየተወረሰ የቀበሌ /የመንግስት ቤት ነው ሊያስብለው አይችልም።
በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለረጅም ግዜ በመንግስት እጅ የነበረ ቤትን በሚመለከት በስህተት አላግባብ ያለህጋዊ ምክንያት ተሰጥቷል የተባለው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመከነና በመንግሰት ባለቤትነት የሚታወቅ ስለመሆኑ በተገለጸበት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት መንግስት የወረሰው መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌለበት ቤቱን የመንግስት ንብረት አያሰኘውም።

ሰላም!
የደንብ መተላለፍ ድርጊቶችን የሚከላከል፣ እርምጃ የሚወስድና የሚያስወስድ ባለሙያ (ፓራሚሊተሪ ኦፊሰር) ነዎት?
እንግዲያውስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣንን አደረጃጀት፣ አሰራር እና የፓራሚሊተሪ ሠራተኞች አስተዳደርን ለመወሰን በወጣው ደንብ ቁጥር 150/2015 አንቀጽ 45 መሰረት መቼና ለምን ኃይል መጠቀም እንደሚችሉ የተደነገገውን ልናጋራዎት ወድደናልና ያንብቡን!
1/ ኃይል መጠቀም የሚቻለው መቼ ነው?
ኦፊሰሩ ኃላፊነቱን በሚወጣበት ወቅት፥-
ሀ) ኃላፊነቱን እንዳይወጣ የሚያደርግ ግልጽ ተቃውሞ ካጋጠመው፤
ለ) ሌሎች አማራጮችን ሲያጣ፤ እና
ሐ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣንን በማሳወቅ
ብቻ ተመጣጣኝ ኃይል ሊጠቀም ይችላል።
2/ ሀይል መጠቀም የሚቻለው ምን ሲያጋጥም ነው?
ሀ) በራሱ ወይም በስራ ባልደረባ ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለመከላከል፤
ለ) የተወረሰ ንብረትን ከደንብ መተላለፍ እርምጃ አወሳሰድ ኦፊሰሩ ወይም ህገ-ወጡን ከሚቀለብሰው ግብረ-ሀይል በመንጠቅ ለማምለጥ የሚሞክረዉን፣ ንብረቱን ነጥቆ በመያዝ በማምለጥ ላይ ያለን ህገወጥ ድርጊት ፈጻሚ ለማስቆም ነው።
3/ ሀይልን ከሕግ ውጪ መጠቀም ምን ያስከትላል?
የተሰጠውን ሥልጣን ካላአግባብ በመጠቀም በግለሰብ አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ኦፊሰር ከባድ የዲስፕሊን ጥፋት እንደፈጸመ ተቆጥሮ፥-
ሀ) እስከ አራት ወር የሚደርስ ደመወዙን ሊቀጣ፣
ለ) እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ለሚደርስ ጊዜ ከሥራ ደረጃው እና ደመወዙ ዝቅ ሊደረግ፣
ሐ) ከሥራው ሊሰናበት ይችላል።
መውጫ፥- ኦፊሰሩ የሚጠቀመው ተመጣጣኝ ሀይል ኃላፊነቱን እንዳይወጣ የሚያደርገውን መሰናክል ለማስቀረት ብቻ መሆን አለበት!
የዲሲፕሊን እርምጃ የፓራ-ሚሊተሪ ሠራተኛውን የወንጀልና የፍትሐብሔር ተጠያቂነት አያስቀርም!
መስከረም 18 ቀን 2016 ኣ.ም
ፋሲካ አጌና (የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት አቃቤ-ሕግ)

የዉል ህግ
የዉል ምንነት
ዉል ማለት አንድ ሰዉ፣ተፈጥሮአዊ ሆነ በህግ ሰዉነት የተሰጠዉ፣ አንድን ተግባር ለመፈጸም ወይም ከመፈጸም ለመቆጠብ የሚገባዉን ግዴታ የሚያስርበት የስምምነት አይነት ነዉ፡፡ ይህ ዉል እቃዎችን ለመግዛት፣ ለመሸጥ ወይም አገልግሎት ለመስጠት፣ መብት ለመስጠት ወይም መብት ለማስቀረት፣ ስጦታ ለመስጠት፣ የስራ ቅጥር ለመፈጸም እንዲሁም የተለያዩ ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ ተመስርቶ ሊፈጸም ይችላል፡፡
አንድ ዉል ምን አይነት ሁኔታዎችን ማሟላት አለበት?
የዉል ህግ የሚገዛዉ በሀገራችን የፍትሐብሔር ህግ ስር ነዉ፤ የተለያዩ ልዩ ሁኔታዎች እሚያስቀምጡ ህጎች ካሉ የእነሱ ተፈጻሚነት እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡ ይህም የሆነዉ ከጠቅላላ ህግ ልዩ ህግ ቅድሚያ ስለሚሰጠዉ ነዉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአገራችን ዉል ህግ በአራተኛዉ መጽሃፍ ስር ከአንቀጽ 1675 ጀምሮ ባለዉ ይገዛል፡፡ አንቀጽ 1675 ዉልን ሲተረጉም “ዉል ማለት ንብረታቸዉን የሚመለከቱ ግዴታዎችን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸዉ ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መካከል የሚደረግ ስምምነት ነዉ፡፡” በማለት ያስቀምጠዋል፡፡ ከዚህ ትርጉም መረዳት እንደምንችለዉ ዉል አንዱ ንብረት መፍጠሪያ መንገድ ነዉ፡፡ ይህም መብት የሚፈጠረዉ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ በሆኑ ሰዎች ሆኖ ግዴታዎች ላይ በመመርኮዝ ነዉ፡፡ ግዴታ ተቋቋመ ፣ተለወጠ ወይም ቀረ የሚባለዉ እነዚህ ሰዎች በሚገቡት ዉል ላይ በሚያስቀምጡት መዘርዝር ነዉ፡፡ በመሆኑም አንድ ዉል እነዚህን መብቶች መፍጠሩን በግልጽ ማሳየት አለበት፡፡
አንድ ዉልም ዉል ለመባል፡-
1. ዉሉ ችሎታ ባላቸዉ ሰዎች የተፈጸመ መሆን አለበት፡፡ አንድ ሰዉ ችሎታ አለዉ የሚባለዉ በህጉ የተቀመጠዉን የእድሜ ገደብ ሲሞላ ወይም ምንም አይነት የአእምሮ እክል ከሌለበት፣ ወይም በህግ የተከለከለ ካልሆነ ነዉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎችም ተሟልተዉ ቢሆን ዉሉን የሚገባዉ ሰዉ ሙሉ ፈቃዱን የሰጠ መሆን አለበት፡፡ ማንም ሰዉ ቢሆን በማስፈራራት፣ በመደለል፣ በማታለል ሆነ በማስገደድ የዉል ግዴታ ዉስጥ ማስገባት አይቻልም፡፡
2. በዉሉ ላይ እንዲፈጸም የተቀመጠዉ ጉዳይ በአግባቡ ትርጉም የተሰጠዉ ወይም እርግጠኝነት ያለዉ፣ ሊፈጸም የሚቻልና ህጋዊ የሆነ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ አለም ዉጪ የሆነ ወይም ለመፈጸም በማንኛዉም መልኩ ቢሆን አዳጋች የሆነ እንዲሁም ህገ-ወጥ ተግባር ለመፈጸም ዉል መግባት አይቻልም፡፡
3. በህጉ በአንድ በተለየ ፎርም እንዲፈጸም የተቀመጠ ዉል ከሆነና ይህንም ፎርም ያልተከተለ ከሆነ የሚጸና ዉል አይሆንም፡፡ ህጎች ብዙ ግዜ አንድን ዉል በጽሁፍ መሆን አለበት ካሉ በኋላ መልሰዉ የተለየ ሁኔታ የሚያስቀምጡበት ሁኔታ አለ፡፡ ለምሳሌ አንድ ዉል በጽሁፍ የሰፈረ መሆን አለበት ካለ በኋላ መልሶ ደግሞ ዉሉ መፈጸሙን በምስክር ማስረዳት ይቻላል ሲል ሊያስቀምጥ ይችላል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ህጉ የተለየ ፎርም አስቀምጦ ከሆነ በዛዉ መልኩ መፈጸሙ ወደፊት ሊነሱ የሚችሉ ክርክሮች ሊያስቀርና የህግም ድጋፍ ያገኛል።
ውብአለም መስፍን
የቦሌ/ክ/ከ/የህ/ስ/ም/መ ዳይሬክቶሬት ዐ/ህግ

👍2
የቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ለሰው ሀይል አስተዳደር ባለሙያዎች በአዋጅ ቁጥር 56/2010 እና በዲሲፒሊን አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 26/2002 ላይ የተሰጠ ስልጠና።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ.ም
የመንግስት ሰራተኛ ምን ማለት ነዉ?
“የመንግሥት ሠራተኛ” ማለት በአስተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው። ነገር ግን በአስተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ የተቀጠሩ ቢሆንም በዚህ አዋጅ የማይገዙ ተቀጣሪዎች አሉ።
የመንግስት ሰራተኛ ለመሆን መሟላት ያለባቸዉ ሁኔታዎች
አንድ ሰዉ በአስተዳደሩ ስር የሚገኝ መስሪያ ቤት ዉስጥ ተቀጥሮ ለመስራት፦
• ዕዴሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው፤ ነገር ግን ከ 14 አመት በላይ የሆናቸዉ ልጆችን ለመቅጠር በመመሪያ ሊወሰን ይችላል
• በሙስና፣ እምነት ማጉደል፣ የስርቆት፣ የማጭበርበር ወይም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተፈረደበት ማንኛውም ሰው ሆኖ ነገር ግን ቅጣቱ ከተፈጸመ፣ በይርጋ ከታገደ ወይም በይቅርታ ከተሰረዘ 5 አመት ያለፈው እና ከነዚህ ወንጀሎች ነፃ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት። ከዚህ ወንጀል ዉጪ በዚህ አዋጅ አንቀፅ 88 መሰረት በዲሲፒሊን ከመንግሥት መስሪያ ቤት ከስራ ተሰናብቶ አምስት አመት የሞላዉ ሰው።
• የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
• በዚህ አዋጅ አንቀጽ 17 መሠረት ቃለ-መሀላ ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ ሰው፡፡
• ከኤች አይ ቪ ውጪ ማንኛውንም ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ የሆነ
• ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ። ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ለተፈለገዉ ስራ ማግኘት ካልተቻለና የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ አገራቸው በተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 270/1994 አንቀፅ 5(2) በተደነገገው በጊዚያዊነት መቅጠር ይቻላል።
የመንግስት መስሪያ ቤት ያለበት ግዴታ
• ግንዛቤ ፈጠራ
• የስራ ቦታ ከሃይማኖት የጸዳ ማድረግ
• ለሰራተኛው የስራ ሃላፊነቱን በዝርዝር ማሳወቅ
• ስራን በእቅድ እንዲመራ በማድረግ አፈጻጸሙንም በዚሁ መሰረት መገምገም
• የስራ ቦታን ለሰራተኛዉ መቹ እንዲሆን ማድረግ
• ለስራዉ የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን ማቅረብ አገልግሎቱንም ማሳወቅ በማለት በአጭሩ ያስቀምጠዋል
የመንግስት ሰራተኛዉ ያለበት ግዴታ
• አንድ የመንግስት ሰራተኛ፦
• ህገ-መንግስቱን የማክበር እና የማስከበር
• ህግ እና ፖሊሲዎችን የመተግበር
• ስራን በታማኝነት እና በትጋት መፈጸም
• በስራ መዘርዝሩ እና በቅርብ ሃላፊዉ የሚሰጡትን ስራዎች የመተግበር የግል እምነቱን በስራ ቦታ አለማንጸባረቅ
• ያለ አድሎ መስራት
• በስራዉ አጋጣሚ ያገኘዉን መረጃ በሚስጥር መያዝ
• ከስራዉ ጋር የሚቃረን ወይም የሚያጓድል ሌላ ሰራ መስራት
• ስራን ለፖለቲካ ጥቅም አለማዋል
• ለሰጠዉ አገልግሎት ጥቅም ያለው ነገር በምትኩ አለመጠየቅ
• የተሰጠዉን ማንኛዉም አይነት ንብረት በአግባቡ የመያዝ።በንብረቶቹ ላይም ጉዳት ቢደርስ ተጠያቂ የሚሆነዉ በቸልተኝንት ወይም ሆን ብሎ ከሆነ ብቻ ነው።
• ከኤች አይ ቪ ምርመራ ዉጪ ያሉ ምርመራዎች ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን
• ስለሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ የወጡ መመሪያዎችን የማክበር ግዴታዎች አሉበት።
የስራ ሰአትና ፍቃድ (አንቀጽ 33-47)
የአመት ፈቃድ
ይህ ፈቃድ የሚሰጠዉ አንድ ሰራተኛ በተሰጠዉ የእረፍት ግዜ እራሱን አነቃቅቶ እና በቂ እረፍት አግኝቶ ወደስራዉ በመመለስ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም እንዲኖረዉ ነዉ። እረፍት መዉሰዱም ለአሰሪዉም ሆነ ለሰራተኛው ብዙ ጥቅም ያለዉ ነዉ።
አንድ የመንግስት ሰራተኛ የአመት እረፍት ለማግኘት 11 ወራት ማገልገል አለበት። ፍቃዱም 20 ቀን ብሎ ይጀምራል በየአመቱም 1 ቀን ይጨምራል። ነገር ግን ይህ ጭማሪ 30 ቀን ላይ ሲደርስ ያቆማል።
የአመት እረፍትም ወደ ብር የሚቀየረዉ አገልግሎት ሲቋረጥ ብቻ ነዉ። ከዛ ዉጪ ባለዉ ባስገዳጅ ሁኔታዎች ብቻ በበላይ ሃላፊዉ ተዕዛዝ መሰረት የአመት እረፍት ለ 2 የበጀት አመት ሊራዘም ይችላል።
የአመት ፈቃድ ወደብር የሚለወጠዉ አገልግሎት ሲቀር ብቻ ቢሆንም በበላይ ሃላፊ ለ 2 በጀት አመት እንዲዛወር ከተደረገ እረፍት ዉስጥ የአንዱ በጀት አመት በብር ተለውጦ እንዲሰጥ ለሚቀርብ ጥያቄ መስተንግዶ መሰጠት አለበት።
የቀን ደሞዙም የሚታሰበዉም ያልተጣራዉ ደሞዝ ለ 30 ተካፍሎ ነዉ።
የወሊድ ፍቃድ
- ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚሰጥ ማንኛዉም የሃኪም የእረፍት ትዕዛዝ እንደህመም ፍቃድ ሳይቆጠር ተፈጻሚ ይሆናል።
- የወሊድ ፍቃድ በጠቅላላዉ 120 ቀናት ናቸዉ። 30 ቀናት ግን ከወሊድ በፊት ሊወሰድ ይችላል።
ጽንስ በመቋረጥ የሚሰጥ ፈቃድ
እርግዝናዉ፡-
• 6 ወር ከሞላው — 60 ቀን
• ቅድመ ወሊድ ፍቃድ ሞልታ ከነበር — ተቋርጦ 90 ቀን
• ከ 3-6 ወር እርግዝና — 30 ቀናት
• የአባቶች ፍቃድ 10 የስራ ቀን
የህመም ፍቃድ
- አንድ የመንግስት ሰራተኛ ሃኪም በሚሰጠዉ የእረፍት ትዕዛዝ መሰረት ከክፍያ ጋር እረፍት እንዲወስድ ይፈቀድለታል።
- ጠቅላላ እረፍቱም በአመት ከ 8 ወር በ 4 አመት ከ 12 ወር መብለጥ አይችልም። ለመጀመሪያ 6 ወራትም ከሙሉ ደሞዝ ጋር ለተቀሩት 2 ወራት ከግማሽ ደመወዝ ጋር እረፍቱ ይሰጣል።
- ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ሰራተኛዉ የሙከራ ግዜዉን ያጠናቀቀ መሆን አለበት።
- ሙከራዉን ያላጠናቀቀ ሰራተኛ ከሆነ ከ 1 ወር ላልበለጠ ግዜ ከደመወዝ ጋር ፍቃድ ይሰጠዋል።
- የህመም ፍቃድ የአመት ፍቃድን ያቋርጣል።
ልዩ ልዩ ፍቃዶች
አንድ የምንግስት ሰራትኛ በአንድ የበጀት አመት ዉስጥ፦
• 7 ቀናት ለግል ጉዳዩ ሊወስድ ይችላል።
• ለፍርድ ቤት ቀጠሮ
• ለህዝባዊ ምርጫ
ያለደመወዝ የሚሰጥ እረፍት ፍቃድ
ይህ ፍቃድ በቂ ምክንያት ላቀረበ፣ የምርጫ ተወዳዳሪ ሲሆንና በልዩ የመንግስት ፕሮጀክት ተሳታፊ ሲሆንና ለዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ሥራ የሰራተኛ ባል/ሚስት በውጭ ሀገር መመደብ ምክንያት ያለደመወዝ ፍቃድ ይሰጣል፡፡
የስራ ዉል ማቋረጥ እና ማራዘም
- የስራ ዉል በሰራተኛዉ አነሳሽነት ወይም በመንግስት መስሪያ ቤቱ አነሳሽነት ሊቋረጥ ይችላል፡፡
- በመንግስት በኩል በህመም ምክንያት፣ በስራ ፍቃድ ብቃት ማነስ፣ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት፣ በእድሜ እና በሞት ሊቋረጥ ይችላል፡፡
በቦሌ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የሕ/ስ/ም/መ/ዳ ዐቃቤ ሕግ ዉብአለም መስፍን

👍2❤1
152.pdf
1.1 MB
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ስራዎች ድርጅት ለማቋቋም የወጣው ደንብ ስራ ላይ ዋለ፡፡
።።።።።።።።።
የንግድ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እና የነዋሪው ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም ሌሎች በአለም አቀፍ እና በሀገሪቱ ውስጥ በተፈጠሩ የተለያዩ ምክንያቶችን ተከትሎ የግብርና እና የኢንዲስቱሪ ምርቶች ዋጋ እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ለኑሮ ውድነት የተጋለጠ ሲሆን መንግስት በከተማው የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ የንግድ ስራዎችን ለማቋቋም ደንብ አውጥቷል፡፡
የከተማው አስተዳደር ለከተማ ነዋሪው በተፈጠረው የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም እየጨመረ የመጣውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር እና በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ህብረተሰብ ክፍሎች የግብርና እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምርቶችን እና የንግድ ዕቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በቀጥታ ከአርሶ አደሩ በመግዛት የሚያቀርብ ደንብ ቁጥር 152 /2015 በከተማው ካቢኔ ፀድቆ ወደ ስራ የተገባ መሆኑን ከህግ ጥናት ምርምርና ረቂቅ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ለማወቅ ተችሏል፡፡

👍2👏1
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 358
በመዝገብ ላይ ተከራካሪ መሆን የሚገባቸው ሰዎች በተለያየ ምክንያት ተሳታፊ ሳይሆኑ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል። ለዚህ መፍትሄ እንዲሆኑም የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግ የተለያዩ የመፍትሄ አንቀጾች አስቀምጧል። ከነዚህ ውስጥ አንዱም አንቀፅ 358 ነው። የዚህ አንቀጽ ተጠቃሚ ለመሆንም :-
1. ጣልቃ ለመግባት አቤቱታ የሚያቀርበው ሰዉ በክርክሩ ተሳታፊ መሆን የሚገባው/የሚችል
2. የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካው ሰው መሆን ያለበት ሲሆን በዋነኝነት መቃወሚያው መቅረብ የሚችለው መብቴን ይነካዋል ያለው ፍርድ ከመፈጸሙ በፊት ነው።

👍1
የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 78
በመዝገብ ላይ ተከሳሽ የነበረ ሰው(የተፈጥሮ/በህግ ሰውነት የተሰጠው) ለቀረበበት ክስ መልስ ሳይሰጥ ወይም ተገቢውን ክርክር ሳያደርግ ቀርቶ በሌለበት ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ የተሰጠበት እንደሆነ እነዚህ እንዲነሱለት ማመልከቻ ማቅረብ ወይም ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው:-
1. ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ እንደተሰጠ ባወቀ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ከሆነ
2. የፍርድ ቤት መጥሪያ በአግባቡ እንዳልደረሰው ካስረዳ
3. ወይም ቀርቦ መከራከር ያልቻለው በበቂ ምክንያት መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳት ከቻለ ብቻ ነው።
ይህ አንቀፅ ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ ሲነበብ ብቻ ላልተገኘ ሰው ተፈፃሚ አይሆንም።

የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 418
አንድ ሰው የመዝገብ ተካፋይ/ተከራካሪ ባይሆንም በክርክሩ ምክንያት የሱ የሆነ ንብረት እንደመያዣ/ ማስከበሪያ በተከራካሪ ወገኖች ቀርቦበት ሊሆን ይችላል። በዚህ ንብረት ላይ ያለውንም መብት ለማስጠበቅ የሚያቀርበው አቤቱታም:-
1. መዝገቡ አፈፃፀም እስኪደርስ የዘገየው በበቂ ምክንያት መሆኑን ማስረዳት
2. በፅሁፍ ሆኖ ፍርዱን ለሚያስፈጽመው ፍርድ ቤት መቅረብ
3. በንብረቱ ላይ ያለውን የተቀዳሚነት መብት ወይም ባለይዞታነቱን የሚያረጋግጥ የፅሁፍ ማስረጃ አብሮ ማያያዝ አለበት።
አቤቱታውን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ቢያደርገው አቤት ባዩን በንብረቱ ላይ አዲስ ክስ ከመመስረት አያግደውም።

👍3
Forwarded from ሕግ አገልግሎት Legal Service
ለአዲሱ ቦሌ ምድብ ችሎት ተገልጋዮች በሙሉ
**********
በቀድሞ ቦሌ (በአሁኑ ለሚ ኩራ ምድብ ችሎት) ጉዳያችሁን ስተከታተሉ የነበራችሁ እና በአዲሱ ቦሌ ምድበ ችሎት አዲስ ስያሜ የተሰጣቸው ችሎቶች በቀድሞ ሲስተናገዱ የነበሩበት ችሎቶች ስያሜ መግለጫ እንደሚከተለው የተገለጸ ሲሆን ከህዳር 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ ጉዳያችሁን የተመደበበት ችሎት በማረጋገጥ እንድታቀርቡ እና እንድትስተናገዱ በአክብሮት እናሳውቃለን ፡፡
ፍርድ ቤቱ

የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 39-43
አንድ ችሎት በክርክሩ ውስጥ መካተት የነበረበት ወይም መካተት ያልነበረበት ወገን በክሱ ላይ አልተካተተም ወይም ተካቷል በማለት መዝገብ መዝጋት አይችልም። ተካፋይ ያልነበረው ወገንም
1. ክሱ በክፉ ልቦና የቀረበ እስካልሆነ ድረስ በፍርድ ቤቱ ወይም በተከራካሪ ወገን አነሳሽነት መካተት ያልነበረበት ከክርክሩ እንዲወጣ ወይም ያልተካተተ ወደክርክሩ እንዲካተት ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል። አንቀፅ 40 & 43
2. ማንኛውም ጉዳዩ ያገባኛል የሚል ሰዉ ዉሳኔ ከመሰጠቱ በፊት በክርክሩ ጣልቃ ልግባ ሲል ምክንያቱን ዘርዝሮ ሊያመለክት ይችላል። አንቀፅ 41
3. ዐ/ህግ ህጉ በሚፈቅድለት ሁኔታ ሁሉም (በሰብአዊ መብት ጥሰት፣ስለኪሳራ የመሳሰሉት) ጣልቃ ልግባ ሲል ሊጠይ ይችላል ። አንቀፅ 42

👍3👏1
Forwarded from ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️ (Daniel Fikadu)
በፍርድ ቤት በማስረጃነት ሲቀርቡ ቴምብር ቀረጥ ለሚከፈልባቸው ሰነዶች ተገልጋዮች ክፍያ መፈጸም የሚችሉባቸው የገቢዎች ማዕከላት፡፡
************************************************************
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ በፍርድ ቤት በማስረጃነት በሚቀርቡ ሠነዶች ላይ የቴምብር ቀረጥ ለማስለጠፍ እና ቀረጥ በተመን ለማስከፈል ባለጉዳዮች ክርክራቸውን በሚያቀርቡበት ምድብ ችሎቶች አቅራቢያ አገልግሎቱን ለመስጠት ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት በምድብ ችሎቶች አቅራቢያ የተደራጁ የቴምብር ቀረጥ ክፍያ የሚፈፀምባቸው የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና የወረዳ ቢሮዎች ከዚህ በታች የተመለከቱት መሆናቸውን እናሳውቃለን፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት