Эдвард Чесноков
12.2K subscribers
6.4K photos
657 videos
89 files
7.91K links
→ Журналист Эдвард Чесноков. @chesnokoveo Рекламу не даю!
Регистрация в РКН: https://clck.ru/3F3v5C
Download Telegram
Forwarded from Esleman Abay የዓባይ ልጅ (Esleman)
ጠቅላይ ምኒስትር ዓብይ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር በቆስጠንጢኖስ ቤተ መንግስት ዛሬ ባደረጉት ቆይታ ላይ ስትራቴጂክ የሁለትዮሽና ዓለማቀፋዊ የትብብር ሰነዶች በቅርበት ምክክር ተደርጎባቸዋል። በተለይም በፕሬዝዳንት ፑቲን አፅንኦት ከሰጡባቸው ነጥቦች መካከል ተከታዩቹን ላጋራችሁ..።

"በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የረጅም ጊዜ ወዳጃዊ ግንኙነት በእርስ በርስ መከባበርና የጋራ ጥቅምን ከግምት ያስገባ በመሆኑ ከፍተኛ ዋጋ እንደሰጠነው መናገር እፈልጋለሁ" በማለት ሀሳባቸውን የጀመሩት ፕሬዝደንት ፑቲን ሀገራቸው በአፍሪካ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የመሰረተችባት ቀዳሚ ሀገር ኢትዮጵያ ነበረች ሲል አውስተዋል። ይህ የዲፕሎማሲ ታሪክ ከ 125 ዓመታት በፊት መሆኑ በመጠቆምም የኢዩቤልዩ በአሉንም በቅርቡ ማክበራቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

ይህ ስብሰባችን በሁለትዮሽ እና አለምአቀፋዊ  ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ዝርዝር ውይይት ለማድረግ እድል ይሰጠናል ያሉት ፕሬዝደንት ፑቲን ጠ/ሚ ዓብይ ጥሪያቸውን ተቀብለው በሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ለመገኘት ስለወሰኑ ምስጋናቸውን ገልፀውላቸዋል።

ሩስያና ኢትዮጵያ በንግድ ረገድ በአንጻራዊነት አነስ ያለ ደረጃ ላይ ቢሆኑም አሁናዊ ሂደቱ ግን የተፋጠነ መሻሻል ላይ መሆኑን የጠቆሙት ፑቲን አሁን ላይ የንግድ ግንኙነቱ የ56 በመቶ እድገት መሳየቱን፤ እንዲቱም ባለፈው ሰኔ ወር በአዲስ አበባ የተከፈተው የንግድ ልዑካቸው የዘርፉን ዕድገት ይበልጥ ለማሳደግ ወሳኝ ነው ብለውታል።

"ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በተገኙበት በዚህ ጉብኝት ወቅት፣ ሩሲያ በመረጃ ደህንነትና በአየር ትራንስፖርት ላይ ያሉትን የበይነ መንግስታት ስምምነቶች ጨምሮ አጠቃላይ የሰነዶች ፓኬጅችን አዘጋጅተናል።" በማለትም ጠቅላይ ምኒስትር አብይ በሰነዶቹ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩ ዘንድ እነሆ ብለዋል - ፕሬዝደምት ፑቲን። ከዚህ በተጨማሪም የኑክሌር ኢነርጂ ትብብር ፍኖተ ካርታው ስለመቅረቡን የሩሲያው መሪ አያይዘው ገልፀዋል።

ጓደኞቻችን ለሆኑት ለኢትዮጵያዊ ባለሙያዎች የሚሰጡትን ስልጠና መቀጠላቸውን የሚገልፁት የክረምሊኑ አለቃ ባለፉት ዓመታት ከ 20,000 በላይ ኢትዮጵያውያን በሩሲያ የትምህርትና የጥናት መርሃ ግብሮቻቸውን አጠናቀዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን ጓደኞቻችን ባቀረቡልን ጥያቄ መሰረትም በ 2023–2024 የትምህርት ዘመን በሩሲያ በጀት የሚደገፈውን የኢትዮጵያ ተማሪዎቾን ኮታ ከሦስት እጥፍ በላይ አሳድገናልም ብለዋል።

ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በብዙ የአለምአቀፍ አጀንዳ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ አቋም አላቸው ያሉት ፑቲን በነዚሁ ጉዳዮች ላይ ዘላቂ ትብብሮች ለማድረግ ይህ ጉባዔ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

#የዓባይልጅ #russiaafrica2023 #Roscongress #ChinaAfrica #BRICS
🤔62👍23👎2😢1