Co.Market / ኮ-ገበያ
541 subscribers
5.06K photos
81 videos
3 files
2.47K links
  📲+251 9 11 81 16 72
https://ermitheethiopia.com

👉
Download Telegram
አሁን ባለው የኢትዮጵያ የንብረት መብት ህግ የመሬት ይዞታ መብት የሚገኝባቸው መንገዶች መሬት የማይሸጥ እና የማይለወጥ የመንግስት እና የኢትዮጵያ ህዝቦች ንብረት ነው የሚለውን መርህ የጣሰ ስለመሆኑ፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች እና ብሄረሰቦች (አርሶ አደሮች፣ ዘላኖች እና የከተማ ኗሪዎች) በእኩልነት የመሬት ባለቤቶች እንደሆኑ ህገመንግስቱ በማያሻማ ሁኔታ ደንግጓል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ዜጋ እኩል የሆነ የመሬት ባለቤትነት እና ተጠቃሚነት መብት ያለው ስለመሆኑ ተረጋግቷል ማለት ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የመሬት ስሪት በገጠር እና በከተማ በልዩነት ሊታይ የሚችል አይደለም፡፡ በገጠር እና በከተማ የመሬት ስሪት ልዩነት አለው ከተባለም ልዩነቱ መምጣት ያለበት አርሶ አደሩ ወይም ዘላኑ የገጠር የእርሻ መሬትና የግጦሽ መሬት ፍላጎት ያለው መሆኑ ሲሆን የከተማው ነዋሪ ደግሞ የመኖርያ ቤት መስርያ ወይም ለተሰማረበት የንግድ ስራ የሚመጥን የድርጅት ቤት መገንቢያ መሬት የማግኘት ፍላጎት ያላቸው መሆኑ ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም ከፍ ሲል እንደገለጽነው ህገመንግስቱ በመርህ ደረጃ መሬት የህዝብ እና የመንግስት ነው ካለ በገጠር ያለውን የእርሻ መሬት እና የግጦሽ መሬት ለአርሶ አደሩ እና ለዘላኑ በነጻ እንዲተላለፍ ከፈቀደ በከተማ ለሚኖረው ነዋሪ እና ነጋዴም የቤት መስርያ ቦታ እና ለንግድ ድርጅቱ የሚያስፈልገውን የመስርያ ቦታ በነጻ ወይም ያለክፍያ ሊያገኝ ይገባው ነበር፡፡

እዚህ ላይ በአትኩሮት ልንመለከተው የሚገባው ጉዳይ በአሁኑ ስዓት በሃገራችን በተለይም በከተሞች አካባቢ የኗሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና አዳዲስ ከተሞች ሳይቀር እየተፈጠሩ የመጡበት ጊዜ ላይ የምንገኝ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የመኖርያ ቤት እጥረት አለ፡፡ ይህንን ችግር በመገንዘብ መንግስት በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ ፖሊሲዎችን እና የከተማ የመሬት ስሪት አዋጆችን በማውጣት ወደስራ ገብቶ የነበር ቢሆነም የመኖርያ ቤት ችግሩን ለመቅረፍ አልቻለም፡፡ መጠለያ የማግኘት መብት ደግሞ መሰረታዊ መብት በመሆኑ በማንኛውም ምክንያት ሊገደብ የሚችል አይደለም፡፡ በመሆኑም ሁሉም ዜጋ በሃገሪቱ ሁሉም ክልሎች ተዘዋውሮ የመስራት እና በሚሰራበት አካባቢ የመኖርያ ቤት መስርረያ ቦታ የማግኘት መብቱ ሊከበርለት ይገባ ነበር፡፡

ነገር ግን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የገጠር ኗሪው አርሶ አደር ወይም ዘላን መሬትን በነጻ የማግኘት እና በዚሁ መሬቱ ላይ የመኖርያ ቤት የመገንባት እና የቤት ባለቤት የመሆን እንዲሁም በመሬቱ ላይ የግብርና ስራዎችን የማከናወን ኢኮነሚያዊ መብቱ የተረጋገጠለት ሲሆን የከተማው ነዋሪ በተቃራኒው ግን መሬትን ለመኖርያ ቤት መስርያም ይሁን ለንግድ ስራው ማካሄጃ የሚያገኘው በክፍያ ነው፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊሉት የሚገባው ጉዳይ የገጠሩ ኗሪ መሬትን በነጻ የሚያገኘው ቢሆነም ከዚህ ይዞታው ሲነሳም መንግስት ወይም የከተማው ነዋሪ ተገቢው ካሳ የሚከፈለው መሆኑ ሲሆን በመሬቱ ላይ እኩል መብት ያለው የከተማው ነዋሪ በገጠር ለሚኖርው ካሳ እንዲከፍል መደረጉ የፍትሃዊነት ጥያቄን ከማስነሳቱ ባሻገር በከተማ የሚኖሩ ዜጎችን በሃገሪቱ ኢኮነሚ እኩል ተጠቃሚ የመሆንን እና ንብረት የማፍራት መብታቸውን የሚገድብ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህም ባሻገር አሁን ያለው የገጠር መሬትን ለማስተዳደር የወጡ አዋጆች በከተማ ገቢ በሚያስገኝ ስራ ላይ የተሰማራ ማንኛውም የከተማ ነዋሪ ስራውን ትቶ አርሶ አደር ስካልሆነ ድረስ የገጠር መሬት ተጠቃሚ መሆን እንደማይችል የሚደነግግ ሲሆን ከዚህ በተቃራኒ በገጠር የመኖርያ ቤት ሰርቶ የቤት ባለቤት የሆነው እና በእርሻ ስራ የሚተዳደረው አርሶ አደር ግን እንደከተማው ኗሪ በከተማ የመኖርያም ይሁን የንግድ ድርጅት መስርያ ቦታን በህግ በተወሰነ ክፍያ በእኩልነት የማግኘት መብቱ ተረጋግቷል፡፡

🇪🇹
#በሰው_መሬት_ላይ_ለተሰራ_ቤት_ሕጉ_ምን_ይላል

✔️አንድ ሰው የራሱ ይዞታ ባልሆነ መሬት ላይ ወይም በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት ከሰራ ከህግ አንፃር እንዴት ይታያል ለሚለው የፍትሀ ብሔር ሕጉን ቁጥር 1170 ና 1179 እናያለን።

✔️የአንድ የመሬት ይዞታ ባለቤት በይዞታው ላይ የመጠቀም መብቱ የራሱ ነው፡፡ ሌላ ሰው በዚያ መሬት ላይ ህንፃ ወይም ቤት ሊሰራ አይችልም።ልስራ ካለም ባለይዞታውን በማስፈቀድ መስራት አለበት አለበለዚያ ባለይዞታው በመሬቴ ላይ ቤት መስራት አትችልም ብሎ መቃወም ይችላል።

✔️ነገር ግን መሬቴ ላይ ቤት መስራት አትችልም እየተባለና ባለይዞታው እየተቃወመ በእምቢተኝነት በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሰራ ሰው በሰው መሬት ላይ በሰራው ቤቱ አንዳችም መብት የለውም። ባለይ ዞታው በመሬቱ ላይ እየተቃወመው ቤት የሰራው ሰው ሁለት አማራጭ የህገ መፍቴዎች አሉት

1. ለቤቱን መስሪያ ያወጣውን ወጪ ሳይመልስለት ቤቱን ለቆ እንዲሄድ ማድረግ ይችላል።

2. ቤቱን የሰራው ሰው በራሡ ወጪ ቤቱን አፍርሶ እንዲሄድ ለመፍቀድ ይችላል፡፡ ባለመሬቱ በይዞታው ላይ ባለመኖሩ ወይም በሌላ ምክንያት በመሬቱ ላይ ቤት የሚሰራውን ሰው በወቅቱ መቃወም ባይችልም ቤቱ መሰራቱን እንዳወቀ ቤቱን ማስለቀቅ ወይም ማስፈረስ ይችላል።

➥ስለዚህ የራስ ያልሆነ ይዞታ ላይ ቤት መስራት አይቻልም። ይቻላልም ከተባለ ባለመሬቱ ፍቃደኝነቱን መግለፅ አለበት።በመሬቱ ላይ ሌላ ሰው ቤት ቢሰራ እንደማይቃወም በግልፅ ወይም በዝምታ መፍቀድ ይችላል።

በግልፅ ወይም በዝምታ በመፍቀድ (ተቃውሞ ሳያቀርብ) በመሬቱ ላይ ሌላ ሰው ቤት ሲሰራ ያልተቃወመ ወይም የተስማማ ባለይዞታ እንደ ፌደራል ሰበር.በመዝገብ.ቁጥር 30101.ቅፅ 6 እና በመዝገብ.ቁጥር.105125.ቅፅ 20 በተወሰነው ውሳኔ መሰረት ቤቱን የሰራው ሰው ባለቤት ይሆናል። የመሬቱ ባለይዞታም በእንዲ አይነት ሁኔታ ቤቱን ለሰራው ሰው የቤቱን ግምት ከፍዬ ላስለቅቅ ማለት አይችልም።
https://ermitheethiopia.com/listing/new-villa-house-for-sale-code-jb-357/
New villa house for sale code-JB- 357
▪️አዲስ ቪላ▪️
▪️እንግዳ ማረፍያ▪️https://ermitheethiopia.com/listing/g1-guest-house-for-rent-around-ayat/
G+1 Guest House for Rent around ayat
https://ermitheethiopia.com/listing/apartments-guest-house-for-rent-code-ab-349/
apartments Guest House for Rent code -AB- 349
እንግዳ ማረፍያ