❗#የንብረት መብት : የመሬት ይዞታ መብት እና የቤት ባለቤትነት መብት
#የንብርት መብት
ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረት የማፍራት መብት እንዳለው፣ ይህ መብትም ንብረትን የመያዝ፣ በንብረቱ የመጠቀም፣ ንብረቱን በስጦታ፣ በውርስ ወይም በሽያጭ ወይም በሌላ ማኛውም መንገድ የማስተላለፍ መብቶችን የሚያጎናጽፍ ሰፊ መብት ሲሆን በህግም ጥበቃ የሚደረግለት መብት ነው፡፡
ይሁን እንጅ ይህ በህግ ጥበቃ የሚደረግለት ንብረት የማፍራት መብት የአብዛኛውን ህዝብ መብት ወይም ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል በህግ ሊገደብ አንደሚችል ከህገመንግስቱ አንቀጽ 40 በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ የግል ንብረት ባለቤትነት መብት የሚመነጨው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም ህጋው ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች በጉልበታቸው፣ በመፍጠር ችሎታቸው ወይም በካፒታላቸው ያፈሩት ሲሆን የንብረት መብት ይኖራቸዋል፡፡ ንበረት ግዙፍነት ያለው ሁኖ የሚንቀሳቀስና፣ የማይንቀሳቀስ ተብሎ ሊከፈል ይችላል(የፍ/ህ/ቁ 1127)፡፡
የመሬት ይዞታ መብት እና የቤት ባለቤትነት የንብረት መብቶች ግዙፍነት ያላቸው የንብረት መብቶች ሲሆኑ ከማይነቀሳቀሱ የንብረት መብቶች ውስጥ የሚመደቡ ናቸው (የፍ/ህ/ቁ 1030)፡፡ ይህም ሁለቱን መብቶች አንድ የሚያደርጋቸው የመጀመርያው ጉዳይ ነው፡፡
የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት ባለቤት መንግስት እና ህዘብ ብቻ እንደሆነ እና መሬትን መሸጥ በህግ የተከለከለ ስለመሆኑ በህገመንግስቱ ተደነግጓል፡፡ ዜጎች በመሬት ላይ ያላቸው መብት የመሬት ይዞታ መብት ሲሆን ከሽያጭ በስተቀር በመሬቱ ላይ የመጠቀም፣ የይዞታ መብታቸውን በስጦታ፣ በውርስና በኪራይ ለማስተላለፍ ይችላሉ፡፡ ይህ የመሬት ይዞታ መብትም እንደማንኛውም ግዙፍነት ያለው የንብረት መብት በህግ ጥበቃ የሚደረግለት ሰፊ መብት ነው፡፡
በሌላ በኩል የግል የቤት ባለቤትነት መብት ደግሞ ለሁሉም ዜጎች እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅቶች በእኩልነት የተሰጠ መብት ሲሆን የቤት በለንብረት የሆነ ግለሰቦች ወይም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች በቤቱ ላይ የመጠቀም፣ በስጦታ ወይም በውርስ የማስተላለፍ፣ የመሸጥ እና በሌላ ማንኛውም መንገድ ንብረቱን ለሌላ ወገን የማስተላለፍ መብት የሚሰጥ ነው፡፡
የመሬት ይዞታ መብት እና የቤት ባለቤትነት መብቶች መካከል ምን አይነት ግንኙነት ሊኖር ይችላል?
ቤት የሚገነባው በመሬት ላይ ነው፡፡ መሬት ደግሞ የመንግስት እና የህዝብ ነው፡፡ መንግስት እና ህዝብ ባለቤት በሆኑበት መሬት ላይ የተገነባ ቤት እንዴት ዜጎችን የግል የንብረት መብት ሊያጎናጽፋቸው ይችላል የሚሉት ነጥቦች በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የሚዳሰሱ ነጥቦች በመሆናቸው እንደሚከተለው ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡
#በመሬት ይዞታ መብት እና በቤት ባለቤትነት መብቶች መካከል ምን አይነት ግንኙነት ሊኖር ይችላል?
የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና ዘላኖች መሬትን ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ በነጻ የማግኘት እና ከርስታቸው ያለመነቀል ወይም ያለመፈናቀል መብት እናዳለቸው እንዲሁም የግል ባለሃብቶች በህግ በሚወሰን ክፍያ ከመንግስት መሬት ማግኘት እንደሚችሉ በህገመንግስቱ ተደንግጓል (አንቀጽ 40(4፣5፣6))፡፡ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና ዘላኖች መሬትን በነጻ ከመንግስት የሚያገኙ ስሆን ሌላው ዘጋ ወይም ህዝብ ግን የመሬት ይዞታ መብቱን የሚያገኘው በክፍያ ነው፡፡ ይህ የህገመንግስቱ ክፍል ከአርሶአደሮች እና ዘላኖች በስተቀር ያሉትን ዜጎች በሃገሪቱ ማንኛውም የኢኮነሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የመሳተፍን እና በሃገሪቱ ሃብት እኩል የመጠቀም እና በእኩልነት የመልማት ህገመንግስታዊ መባታቸውን የሚገድብ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል፡፡
ሆኖም ግን የመሬት ይዞታ መብት በነጻ ወይም በህግ በሚወሰን ክፍያ ከመንግስት የሚገኝ ሲሆን የቤት ባለቤትነት መብት ግን በግዥ፣ በስጦታ፣ በውርስ፣ ወይም በሌላ መንኛውም መንገድ የሚገኘ ሊሆን ይችላል፡፡ እዚህ ላይ ሊተኮርበት የሚገባው ጉዳይ ቤቱ የተገነባው መንግስት እና ህዝብ ባለቤት በሆኑበት መሬት ላይ መሆኑ እና የተገነባውን ቤት ከመሬቱ ተነጥሎ ሊታይ የሚችል ንብረት አለመሆኑ ነው፡፡ ግንባታው ከመሬቱ ተነጥሎ ሊታይ የሚችል ካልሆነ ደግሞ የመሬት ይዞታ መብትን በህግ በተወሰነ ክፍያ ከመንግስት ተረክቦ ቤት የገነባ የቤት ባለቤት ባለቤት ያልሆነበትን መሬት ወይም በመሬቱ ጨምሮ በሽያጭ ማስተላለፍ እንደሚችል ለመገንዘብ የሚከብድ ጉዳይ አይደለም፡፡ ስለሆነም የመሬት ይዞታ መብትን እና የቤት ባለቤትነትን አንድ የሚያደርጋቸው ሁለተኛው ምክንያት የመሬት ይዞታ መብት ቤት ከተገነባበት በኋላ በሽያጭ ለሌላ ወገን ሊተላለፍ መቻሉ ነው፡፡ እዚህ ላይ መሬትን በሽያጭ ማስተላለፍ እና የመሬት ይዞታ መብትን በሽያጭ ማስተላለፍ ግን ተመሳሳይ ትርጉም ሊሰጣቸው እንደማይችል ልብ ሊሉ ይገባል፡፡
መንግስት እና ህዝብ ባለቤት በሆኑበት መሬት ላይ የተገነባ ቤት እንዴት ዜጎችን የግል የንብረት መብት ሊያጎናጽፋቸው ይችላል?
ከፍ ሲል እንደገለጽሁት መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የመንግስት እና የኢትዮጵያ ህዝቦች ንብረት ነው፡፡ ይህም ማለት መንግስት ከሽያጭ በስተቀር መሬትን በሌላ ማንኛውም መንገድ ማስተላለፍ የሚችል ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስለሆነም ዜጎች መሬትን ከመንግስት በነጻ ወይም በክፍያ የሚያገኙት ቢሆነም በዚሁ መሬት ላይ ያላቸው መብት ግን የመሬት ይዞታ መብት ብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት ማንኛውም የመሬት ይዞታ መብት ያለው (Possessor) ሁሉ መሬቱን ከመሸጥ በስተቀር መሬቱን የመያዝ፣ በመሬቱ የመጠቀም፣ መሬቱን በስጦታ፣ በውርስ ወይም በኪራይ የማስተላለፍ መብቶች ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡
አንድ የመሬት ይዞታ መብት ያለው ባለይዞታ (Possessor) በመሬቱ ላይ ቤት ቢገነባ ወይም አትክልት ተክሎ መሬቱን ቢያለማው ይህ ባለይዞታ ለገነባው ቤት ወይም ለተከለው አትክልት ባለሃብት (owner) ይሆናል፡፡ ስለሆነም መንግስት እና ህዝብ ባለቤት በሆኑበት መሬት ላይ የተገነባ ቤት እንዴት ዜጎችን የግል የንብረት መብት ሊያጎናጽፋቸው ይችላል የሚለው ጥያቄም ሊመለስ የሚገባው ከዚሁ አንጻር ሊሆን ይገባል፡፡ የቤት የግል ንብረት ባለቤትነት ባለቤቱ ቤቱን በሽያጭ ማስተላለፍን ጨምሮ ሌሎች የንብረት መብቶችን የሚሰጥ ሰፊ መብት ነው፡፡ እዚህ ላይ ልንመለከተው የሚገባው ጉዳይ አንድ የቤት ባለቤት የሆነ ሰው ሁለት መብቶችን አጣምሮ የያዘ ስለመሆኑ ነው፡፡ የመጀመርያው ቤቱን የገነባበት የመሬት ይዞታ መብቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በመሬቱ ላይ የተገነባው ቤት ባለቤትነት መብቶች ናቸው፡፡ እነዚህን ሁለት የንብረት መብቶች ለየብቻ ተነጣጥለው ሊታዩ የሚችሉ ባይሆንም የመሬቱ ባለቤት መንግስት እና ህዝብ ሲሆን የቤቱ ባለቤት ደግሞ ቤቱን የገነባው የመሬት ባለይዞታ ግለሰብ ወይም ድርጅት ነው፡፡ ስለሆነም አንድ የቤት ባለቤት በይዞታ መሬቱ ላይ ቤት ሰርቶ ሲሸጥ ቤቱ እና ቤቱ የተሰራበት ይዞታ ተነጣጥለው ሊታዩ የሚችሉ ባለመሆናቸው (intrinsic element) በመሆናቸው የይዞታ መብቱንም ጭምር በሽያጭ እንዳስተላለፈ ይቆጣራል፡፡