Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
549 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉ለግንባታ 4 ዓመታትን የፈጀውና 1 ቢሊዮን ብር እንደወጣበት የተነገረው ቦረና የሚገኘው የያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ያቤሎ የሚደረገውን በረራ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

በያቤሎ የመጀመሪያው አውሮፕላን ማረፊያ እንደሆነ የገለጸው አየር መንገዱ 3 ሳምንታዊ በረራዎች እንደሚኖሩት አሳውቋል። አሁን የሀገር ውስጥ መዳረሻዎቹም 23 ደርሰዋል።

አውሮፕላን ማረፊያው ለአካባቢው ህዝብ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ፦

- የቦረናን ባህል፣
- የቦረናን ታሪክ፣
- የገዳ ሥርዓት፣
- የያቤሎን የአዕዋፍ መናኸሪያ፣
- የቦረናን ፓርክ ለማየት ለሚመጡ ዕድል እንደሚሰጥ ዛሬ በነበረው ይፋዊ የማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የገኙት ም/ጠሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል።

Via Ethiopian Airlines

@etconp
❤9🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉ከመስቀል አደባባይ - መገናኛ - ሳውዝ ጌት የተከናወነውን የኮሪደር ልማት በውስጡ ለነዋሪዎች በቂ እና አመቺ የሆኑ የአገልግሎት መስጫ አሚኒቲዎችን፣ ፕላዛዎችና አረንጓዴ ስፍራዎችን አካትቷል ።

🚧ፕሮጀክቱ የመንገድና ተያያዥ መሰረት ልማቶች በስፋት የተከናወኑበት ሲሆን ከ51 እስከ 60 ሜትር ስፋት ያለው የ8 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን የዋና መንገድ፣16 ኪ.ሜ ኮንክሪት የእግረኛ መንገድ፥የድጋፍ ግንብ (Retaining wall)፥የ ITS ዳክት ዝርጋታ እና ፣ የመንገድ ዳር ስማርት ፖሎች ተገንብተውለታል።

💫በተጨማሪም የዘመናዊ የኤሌክትሪክ መስመር፣የባቡር ሀዲድ ላይ የተሽከርካሪና የእግረኞች ማቋረጫዎች፣ አመቺ የእግረኛና የሳይክል መጋለቢያ መንገድን ይዟል ተባለ።

@etconp
❤4🔥1
ADVERTISMENT

ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤4
👉4ቱ የሥራ አመራር ፍልስፍናዎች

💫1. አውቶክራቲክ (Autocratic) አስተዳደር

ሥራ አስኪያጅ ማንኛውንም ውሳኔዎች ሙሉ በሙሉ ራሱ ይወስዳል፣ ሰራተኞችም ትዕዛዙን ይከተላሉ።

🏷ባህሪያት
*ትዕዛዝ ከላይ ወደታች ብቻ ነው።
*የሰራተኞች  ሃሳብ ዋጋው አነስተኛ ነው።
*ግልጽ ደንብና ጥብቅ ክትትል።

⏺ጥቅም፡ በአደጋ ጊዜ፣ በጦር መስክ ወይም ፈጣን ውሳኔ ሲያስፈልግ።

⏺ድክመት፡ የሰራተኞችን ፈጠራና ሀሳብን ከንቱ ያደርጋል።

💫2. ፓተርናሊስቲክ (Paternalistic)

ሥራ አስኪያጅ እንደ “ወላጅ” ይሰራል፤ ውሳኔዎቹ ለሰራተኞች የሚያደላ ቢሆንም ቁጥጥሩ በእሱ ነው።

🏷ባህሪያት:
*የሰራተኞችን ደህንነት የሚጠብቅ ነው።
*ምክርና መመሪያ መስጠት።

⏺ጥቅም፡ ታማኝ ሰራተኞችና ዘላቂ ተቋም ይፈጥራል።

⏺ድክመት፡ ሰራተኞችን በሥራ አስኪያጅ ውሳኔ ላይ ሀሳብ መስጠት ይከለክላል።

💫3. ዲሞክራቲክ (Democratic/Participative) አስተዳደር

የሥራ አስኪያጅ ውሳኔ የብዙሃኑን ሃሳብ ያካትታል ።

🏷ባህሪያት:
*ለቡድኑ ስራና እድል የሚሰጥ ግንኙነት።
*የጋራ ኃላፊነት።
*አዳዲስ ሃሳቦችን ያከብራል።

⏺ጥቅም፡ ለችግር መፍትሄ የጋራ ሃሳብ ትብብር፣ በተለይ የባለሙያ  ሠራተኞች ቁጥር ብዛት ሲኖረው

⏺ድክመት፡ ውሳኔ ለመወሰን ሊዘገይ ይችላል።

💫4. ላይዘ-ፌር (Laissez-faire)

ሥራ አስኪያጅ አነስተኛ መመሪያ ይሰጣል፣ ሰራተኞችም ራሳቸው በጋራ ውሳኔ ይወስናሉ እና ሥራቸውን በሃላፊነት ይቆጣጠራሉ።

🏷ባህሪያት:
*ለሰራተኞች ከፍተኛ የሃሳብና የውሳኔ ነፃነት።
*በእምነት ላይ የተመሰረተ አቀራረብ።
*ሥራ አስኪያጅ እንደ አስተካካይ ይሰራል።

⏺ጥቅም፡ በከፍተኛ ብቃት፣ በራስ-ማነቃቂያ እና በልምድ የተሞላ ቡድን።

⏺ድክመት፡ የቡድኑ ተግባራዊ ሥራ በትክክል አይሄድም።

@etconp
❤18
👉ሕዳሴ ግድብን ለመገንባት ጥቅም ላይ የዋለው ኮንክሪት ከ110 በላይ የዌምብሌይ ስታዲየሞችን መገንባት የሚያስችል እንደሆነ ያውቃሉ?

💫90 ሺህ ተመልካቾችን የሚይዘውና በእንግሊዝ ለንደን የሚገኘው የዌምብሌይ ስታዲየምን ለመገንባት 90 ሺህ ሜትር ኩብ ኮንክሪት እንደፈጀ ይገመታል።

🚧ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የዋለው ኮንክሪት ደግሞ ከ10 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ነው።

⏺በዚህ ስሌት መሰረት የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የዋለው ኮንክሪት ከ110 በላይ የዌምብሌይ ስታዲየሞችን ለመገንባት በቂ ነው ማለት ነው።

⏺እንዲሁም የአሜሪካውን ሁቨር ግድብን የሚያህሉ ሦስት ትላልቅ ግድቦችን መገንባት ይችላል።

⏺በግዝፈቱ ካሊፎርኒያ ከሚገኘው ኦርቪል ግድብ በመቀጠል በአሜሪካ በሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው ሁቨር ግድብን ለመገንባት ወደ 3.3 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የሚገመት ኮንክሪት አስፈልጓል።

⏺ይህ ቁጥር በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ለመሥራት በጥቅም ላይ ከዋለው የኮንክሪት መጠን ጋር ሲነጻጸር፣ የሕዳሴው ግድብ በጥቅም ላይ ያዋለው የኮንክሪት መጠን ወደ  ሦስት እጥፍ ይበልጣል።

⏺ይህም ማለት ሦስት የሁቨር ግድብን መገንባት ይችላል ማለት ነው።

🏷በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የመርከብ መስመር የሆነውን የካሪቢያን ባሕር እና ፓሲፊክ ውቅያኖስን የሚያገናኘውን የፓናማ ቦይ ለመገንባት ወደ 3.8 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ኮንክሪት እንደፈጀ ይገመታል።

⏺ይህ ኮንክሪት የሕዳሴውን ግድብ ለመገንባት ጥቅም ላይ ከዋለው ኮንክሪት መጠን አንድ ሦስተኛ ያህሉ ብቻ ነው።

Via EBC

#GERD #concretework #iconic #Ethiopia #hooverdam

@etconp
❤13👍1
👉Vacancy Announcement - Junior Highway Engineer

💫Company: Smart Consulting Engineers PLC

📜Smart Consulting Engineers PLC is seeking a Junior Highway Engineer to join our dynamic team.

⭐️Requirements

▶️Education: BSc in Civil Engineering or related field

▶️Experience: Minimum of 3 years' experience in highway design and drafting

💥Salary: Negotiable

🔏Technical Skills

▶️Proficiency in Civil 3D and other design software
▶️Strong knowledge of quantity computation
▶️Ability to prepare detailed technical reports

📌Other Skills

⏺Excellent communication and management skills
⏺Strong teamwork spirit with willingness to collaborate
⏺Prior design consultancy experience is an advantage
⏺Encouragement: Female applicants are highly encouraged to apply

⚡️Deadline: September 16

📩How to Apply: Send your CV and relevant documents to
hrsmartconsultingengineerssce@gmail.com

🕹Note: Only shortlisted candidates will be contacted

@etconp
❤6🙏1
👉ለሁሉም የዓባይ መገደብ የጋራ ደስታ ነው። በዛሬ ስሜት ብቻ ሳይሆን በነገም ግምት የሚለካ ዘመን ተሻጋሪ ደስታ❤️

💚💛❤️ኢትዮጵያውያን ወገኖች፤ እንኳን ደስ ያላችሁ! እንኳን ደስ ያለን💚💛❤️

@etconp
❤10
#ADVERTISEMENT

🏭🏠TSEGAYE and YOHANNES J-Bolt & PLATE 🏚🏗 🌁🌆

🧿 OUR SERVICES ⤵️

🔲Plate

⚙️  J-Bolt

⚓Anchor Bolt

➽Tie Rod

Phone : 🤳0938494506 
              đŸ¤ł 0951087077
              🤳 0929044037

👉አድራሻ፦  መርካቶ ምንአለሽ ተራ ከጭድ ተራ ከፍ ብሎ

https://t.me/tsegaye2016Jbolt
❤2
👉ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምን አሉ

🚧የኢትዮጵያውያን ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ ለምረቃ መብቃቱ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል፡፡

⭐️ሁነቱን ከዘገቡት መገናኛ ብዙሃን መካከል ቢቢሲ፣ ሮይተርስ፣ አሶሺየትድ ፕሬስ፣ አልጀዚራ፣ ፍራንስ-24፣ ዴይሊ ኔሽንን ይጠቀሳሉ፡፡

💫ቢቢሲ "የኢትዮጵያውያን ኩራት" ሲል የገለጸው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በይፋ መመረቁን ዘግቧል፡፡

💫ፍራንስ-24 "ኢትዮጵያ ሚሊዮኖችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደርገውን ግዙፍ ግድብ ገንብታ አጠናቀቀች" ሲል ዘግቧል፡፡

"ኢትዮጵያ ለሚሊዮኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ማዳረስ የሚያስችላትን በአፍሪካ ግዙፍ የሆነ የኃይል ማመንጫ ግድብ መረቀች" ሲል የዘገበው ደግሞ ሮይተርስ ነው፡፡

💫አሶሺየትድ ፕሬስ በበኩሉ "ኢትዮጵያውያን ተስፋን የሰነቁበት በአፍሪካ ግዙፍ ግድብ ተገንብቶ ተጠናቀቀ" ሲል አስነብቧል፡፡

💫ዴይሊ ኔሽን የግድቡን መመረቅ በተመለከተ ባወጣው ዘገባ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት ስጦታ ሲል ገልጾታል፡፡

⏺ዴይሊ ኔሽን የግድቡን መመረቅ በተመለከተ ባወጣው ዘገባ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ "የኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት ስጦታ" ሲል ገልጾታል፡፡

💫በተመሳሳይ አልጄዚራ፣ ሲኤንቢሲ አፍሪካ፣ የቱርኩ አናዶሉ ኤጀንሲን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ምረቃ ዘግበዋል፡፡

@etconp
❤13