Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.58K photos
56 videos
536 files
3.8K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
#GERD

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ በትናንትናው ዕለት 3ኛው እና 4ኛው ተርባይኖች ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታወቁ።

ሌሎቹ ዩኒቶች በተቀመጠላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ነው የጠቀሱት።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፈው በጀት ዓመት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የኃይል አቅርቦት 17 በመቶ የሚሆነውን አስተዋፅኦ ማድረጉን ማስታወቁ ይታወሳል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀደም ብለው ሥራ የጀመሩት 2 ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት መቻላቸው የተበሰረው ከሁለት ዓመት በፊት በ2014 በዚሁ በያዝነው ወር ውስጥ ነው።

@etconp
👏4👍2❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA #GERD 🇪🇹

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ መስሪያ ቤት ምን አለ ?

(ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት / አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የሰጠው ቃል)

- በቅርቡ 2 የግድቡ ተጨማሪ ተርባይኖች አገልግሎት በመጀመራቸው ከግድቡ የሚመረተው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 1 ሺሕ 550 ሜጋዋት ከፍ ብሏል።

- ከዚሕ ቀደም ብሎ ሥራ የጀመሩ ሁለት ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 375 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ።

- ከሰሞኑን የተመረቁት ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 400 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫሉ።

- ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ከ5 ሺሕ ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።

- የግድቡ ግንባታ አሁን ወደ መጠናቀቁ ነው።

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለበት እና ብዙ ቢሊዮን ዶላር ያፈሰሰበት ግድብ ከአፍሪቃ ትልቁ የኃይል ማመነጫ ነው።

ቪድዮ ፦ PM OFFICE

#Ethiopia #AFP

@etconp
👍6❤4
👉ሕዳሴ ግድብን ለመገንባት ጥቅም ላይ የዋለው ኮንክሪት ከ110 በላይ የዌምብሌይ ስታዲየሞችን መገንባት የሚያስችል እንደሆነ ያውቃሉ?

💫90 ሺህ ተመልካቾችን የሚይዘውና በእንግሊዝ ለንደን የሚገኘው የዌምብሌይ ስታዲየምን ለመገንባት 90 ሺህ ሜትር ኩብ ኮንክሪት እንደፈጀ ይገመታል።

🚧ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የዋለው ኮንክሪት ደግሞ ከ10 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ነው።

⏺በዚህ ስሌት መሰረት የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የዋለው ኮንክሪት ከ110 በላይ የዌምብሌይ ስታዲየሞችን ለመገንባት በቂ ነው ማለት ነው።

⏺እንዲሁም የአሜሪካውን ሁቨር ግድብን የሚያህሉ ሦስት ትላልቅ ግድቦችን መገንባት ይችላል።

⏺በግዝፈቱ ካሊፎርኒያ ከሚገኘው ኦርቪል ግድብ በመቀጠል በአሜሪካ በሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው ሁቨር ግድብን ለመገንባት ወደ 3.3 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የሚገመት ኮንክሪት አስፈልጓል።

⏺ይህ ቁጥር በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ለመሥራት በጥቅም ላይ ከዋለው የኮንክሪት መጠን ጋር ሲነጻጸር፣ የሕዳሴው ግድብ በጥቅም ላይ ያዋለው የኮንክሪት መጠን ወደ  ሦስት እጥፍ ይበልጣል።

⏺ይህም ማለት ሦስት የሁቨር ግድብን መገንባት ይችላል ማለት ነው።

🏷በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የመርከብ መስመር የሆነውን የካሪቢያን ባሕር እና ፓሲፊክ ውቅያኖስን የሚያገናኘውን የፓናማ ቦይ ለመገንባት ወደ 3.8 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ኮንክሪት እንደፈጀ ይገመታል።

⏺ይህ ኮንክሪት የሕዳሴውን ግድብ ለመገንባት ጥቅም ላይ ከዋለው ኮንክሪት መጠን አንድ ሦስተኛ ያህሉ ብቻ ነው።

Via EBC

#GERD #concretework #iconic #Ethiopia #hooverdam

@etconp
❤13👍1
👉ዊ ቢውልድ (የቀድሞ ሳሊኒ ኢምፕሬጊሎ) ስለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምን አለ ?

" ፕሮጀክቱ ከሦስት መካከለኛ መጠን ካላቸው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ጋር የሚስተካከል ነው ! "

" ዊ ቢውልድ " በይፋዊ ኤክስ ገጹ ባስተላለፈው አጭር ጹሑፍ " የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሦስት መካከለኛ መጠን ካላቸው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ጋር የሚስተካከል ነው " ሲል ገልጾታል።

ኩባንያው ፦

" ታላቁ የህዳሴ ግድብ በአፍሪካ ትልቁ እና በዓለም ላይ ካሉ 10 ግዙፍ ግድቦች ተርታ አንዱ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የኃይል ስትራቴጂ ዋነኛ መሠረት ነው።

ፕሮጀክቱ በውስብስብ የግንባታ ጥበብ  የጥቁር አባይን ውሃ በመጠቀም 5,150 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም የፈጠረ ሲሆን ይህም ከሦስት መካከለኛ መጠን ካላቸው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ጋር የሚስተካከል ነው።

ሪከርድ ስለሰበረው ፕሮጀክት ቁጥሮችን ይመልከቱ [ቪዲዮው ከላይ ተያይዟል] " ሲል መልዕክቱን አጋርቷል።

" ዊ ቢውልድ " ማነው ?

ዊቢውልድ (የቀድሞው ሳሊኒ ኢምፕሬጊሎ) እ.ኤ.አ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የውሃ ኃይል እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ግልገል ጊቤ አንድ፤ ግልገል ጊቤ ሁለት፤ ግልገል ጊቤ ሦስት ፕሮጀክቶችኝ ገንብቷል። የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ግድብ እንዲሁም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በዚሁ ኩባንያ ሥር ግንባታቸው የተከናወነ ነው።

#Ethiopia
#GERD 💪

Via Tikvah Magazine

@etconp
❤12