Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
57 videos
549 files
3.88K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Itoophiyaa‍❤️)
👉በመዲናዋ 3 ሠራተኞችን ለህልፈት የዳረገው የሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ እንዲቆም ተደረገ

🚧ባሳለፍነው ዓርብ የሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ 3 ሠራተኞች ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የሕንጻው ግንባታ እንዲቆም መደረጉን የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

🚧የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ባሳለፍነው ዓርብ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 6 በጅምር ግንባታ ላይ የሚገኝ ባለ 9 ወለል የአርሂቡ ሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ 3 ሠራተኞች  ሕይወት አልፏል፡፡

🚧ሠራተኞቹ ሲሚንቶ ወደ ላይ የሚያወጡበት ጋሪ የተሸከመው የብረት ገመድ በመታጠፉ  የብረት ገመዱን  ለማስተካከል በእጃቸው ይዘው በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት በአቅራቢያው ከነበረ የኤሌክትሪክ ገመድ ጋር በመገናኘቱ  ከሕንጻው ወደ መሬት ወድቀው ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

🚧ተጨማሪ አንድ ሰራተኛ ወደ ሕክምና ተቋም መወሰዱን ያብራሩት አቶ ገዛኸኝ ሶስቱ  ሠራተኞች ግን ወዲያውኑ ሕወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

🚧የደረሰውን አደጋ ተከትሎም ሕንጻው የግንባታ እንቅስቃሴውን እንዲያቆም መደረጉን ነው ያስታወቁት፡፡

🚧ከዚህ ባለፈም የሕንጻው ባለቤት፣ የአማካሪውንና የተቋራጩን የግንባታ ፈቃድ በመያዝ  ከአደጋው ጋር በተያያዘ ማብራሪያ እንዲሰጡ መታዘዛቸውን ገልጸዋል።

🚧በሕንጻ አዋጅና መመሪያ መሰረት ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመው ለጠፋው ሕይወትም በሕግ እንደሚጠየቁ አክለዋል ፡፡

Via FBC

#FirstSafety

@etconp
Forwarded from Ethio Construction Engineering (Itoophiyaa‍❤️)
👉በአዲስ አበባ በግንባታ ስራ ላይ በነበሩ ሰራተኞች ድንጋይ ተንዶ የ1 ሰው ህይወት ሲያልፍ 3 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

⚡️በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ህንጻ ጀርባ በግንባታ ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች በስራ ላይ እንዳሉ ድንጋይ ተንዶባቸዉ የ1 ሰዉ ህይወት ሲያልፍ 3 ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

🚧አደጋዉ በዛሬው እለት የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:52 ሰዓት ላይ የተከሰተ ሲሆን ሰራተኞቹ ለመሰረት በተቆፈረዉ አስር  ሜትር ጥልቀት ባለው ጉድጓድ ዉስጥ በስራ ላይ እንዳሉ ድንጋይ ተንዶባቸዉ አደጋው ስለመከሰቱ ተገልጿል።

🖱ጉዳት የደረሰባቸዉ ተጎጂዎች ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን አደጋ የደረሰበት ቦታ አሁንም ለአደጋ የተጋለጠ ነው ተብሏል።

▶️በአዲስ አበባ በግንባታ የስራ ላይ አደጋ በ20 ቀናት ዉስጥ  የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ  ስድስት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱንም ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

#FirstSafety

@etconp
👍1
👉አዳማ‼

🚧በአዳማ ከተማ ለሕንፃ ግንባታ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ በነበሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ የሁለት ሰራተኞች ህይወት ማለፉን የከተማው ዋና ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

✳️በመምሪያው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለጹት አደጋው ትናንት በከተማው ደጋጋ ወረዳ ልዩ ቦታው ቀጠና አራት አካባቢ የደረሰ ነው፡፡

❇️በአደጋው ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪም ሌሎች ሁለት የጉልበት ሰራተኞች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

⏺ሕንፃ አሰሪዎች ለሚያሰሯቸው ሰራተኞች የስራ ደህንነት ሊጠብቁና ዋስትና ሊሰጡ እንደሚገባም አሳስበዋል ብሎ የዘገበው ፋና ሬድዮ ነው።

#FirstSafety

@etconp
👍6😭3
#አሳዛኝ_ዜና

ኢዩኤል ታዬወርቅ ሸዋታጠቅ ይባላል ተወልዶ ያደገው አዲስአበባ ኬንያ ኢምባሲ ከፍ ብሎ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው።

እዩኤል (አቢቲ) በጎንደር ዩኒቨርስቲ የኪነህንፃ ኢንጅነሪንግ 5ኛ ዓመት ተማሪ ነበር።

የፋሲካ በዓልን አያቱ ጋር አክብሮና እዛው ሲጫወት አድሮ በማግስቱ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከመጣ ታናሽ ወንድሙ ጋር ወደቤተሰቦቹ ቤት ሲመለስ ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝና 14 ፎቅ እርዝመት ካለው ፎቅ ላይ ተወርውሮ የወረደ ብረት ጭንቅላቱ ላይ መቶት በአበባነት እድሜው በአሳዛኝ ሁኔታ ተቀጥፏል።

#FirstSafety

@etconp
😭8👍6❤2