የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
Channel created
​የከንቲባው ልጅ

ክፍል 1


.
.
:- እውነተኛ ታሪክ ነው!
.
.
እለተ ረቡዕ : ሚያዚያ 30, 2011 ዓ.ም ፡ ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፡ 11:00 ሰዓት አካባቢ ከሶስቱ የጊቢው በሮች ታዋቂ በሆነው በቶኒ በር ስፖርት ቤት ለመሄድ እየወጣሁ ነው ። ስፖርተኛ አይደለሁም ፡ ሰሞኑን እየተሰጠኝ ባለው አስተያየት ምክንያት መከራ እያየሁ ያለሁ ሚስኪን የ #2ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ እንጂ ። ሰው እንዴት ሳይጠየቅ comment ይሰጣል ...? ስትወፍር ፡ ምን አገኘህ ደግሞ ...? እያለ ያሽሟጥጣል ። ስትከሳ ፡ ጎዶሎህን ይሞላ ይመስል ምን ጎደለህ ደግሞ ...? ይልሀል ። ምንም ነገር ብትሆን የሰው ልጅ comment ከመስጠት ወደ ዋላ አይልም ። ምን አለበት Like ብቻ አርጎ ቢቀየስ ። ሰሞኑን "ምነው ከሳክ" ብሎ ያልጠየቀኝ ሰው ካለ ለዘላለም ይኑር ፣ የተባረከም ይሁን ። በነሱ አይን ምከንያት እነደከሳሁ ማን በነገራቸው ። እኔማ የሰው አይን እና አስተያየት ሲበዛብኝ ፈርቼ ንሰሐ ገባሁ ። (አቤት ውሸት ...) አንዳንዴማ አይናቸው ተጎልጉሎ እስኪወጣ ድረስ ስለሚያዩኝ አካሄድ እራሱ ይጠፋብኛል ። (ውይ ማጋነን ስንወድ ግን ...) የሆነ ቀን ብልጭ አለብኝና ፡ ለምን ስፖርት አልጀምርም ብዬ ከራሴ ጋር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስብሰባ ተቀመጥኩ ። ውሳኔውም ፡ በርታ ፣ ጠንክር ፣ አይዞህ ፣ ከጎንህ ነን ጀምር የሚል ነበር ። ለዚህም ውሳኔ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል ። (አቤት መበጥረቅ...) ይኸው ጠንክሬ ተፍ ተፍ ማለት ከጀመርኩ ቀናቶች እየተቆጠሩ ነው ። ወደ ስፖርት ቤቱ እያቀናሁ እያለ ፡ ፊትለፊት መንገድ ላይ በኔ street በጣም የምታምር የቤት መኪና መጣች ። መንገድ ልልቀቅ ብዬ ትንሽ ወደ ጫፍ ፈቀቅ አልኩኝ ። መኪናዋ ግን እኔ ወደ ሄድኩበት ቦታ መጥታ ጭራሽ እግሬ ስር ደርሳ ቆመች ። በሁኔታው በጣም ተናድጃለው ፤ በዛላይ ተደናግጫለሁ ። የመኪናው ሞተር ሲጠፋ ይሰማኛል ። ወዲያው ከመኪናው ውስጥ በግምት በኔ እድሜ የምትገኝ በጣሙን የምታምር ልጅ ወርዳ ፊትለፊቴ ቆመች ። አይኔ ሲደነግጥ ፡ ልቤ በምት ሲያጅበው ፡ ያስታውቅብኝ ነበር ። መኪናዋን በአይኔ ቃኝቼ ብቻዋን እንደሆነች አረጋግጫለሁ ። አይን አይኔን ካየች በዋላ እስኪጨንቀኝ ጥብቅ አርጋ አቀፈችኝ ። ያልጠበኩት ስለነበር "የኔ እህት ፡ ችግር አለ ...? ሰው ተሳስተሽ እንዳይሆን" ስላት በድጋሜ አየችኝ እና ጭራሽ ጉንጬን ሳመችኝ ። በድርጊቷ ስለተገረምኩኝ ፡ ይቺ ልጅ ግን ጤነኛ ነች ...? እያልኩኝ ልብ ብዬ ማየት ጀመርኩ ። ደግሞኮ ከዛሬ ውጪ አይቻት አላውቅም ። ቀጥላ በእጆቿ እጆቼን ስትይዘኝ ፡ በቃ ይቺ ልጅ እኔን የሚመስል ፍቅረኛ አላት ብዬ አሰብኩ ። አይኖቿ ውስጥ የሚታየኝ የፍቅር ስሜት አይኔ ውስጥ ገብቶ እምባዬን አመጣው ። ሚስኪን ነገር ትመስላለች ። ቢሆንም ግን እጄን ለማላቀቅ ሞከርኩኝ ፡ እሷ ግን ይበልጥ ግጥም አርጋ ያዘችኝ ። ግራ ሲገባኝ ፡ ይሄ ነገር prank ነው እንዴ ...? ብዬ ካሜራ ለማፈላለግ በአንገቴ ዞር ዞር አልኩኝ ። ሰፈሩ ግን ያለወትሮው ጭር ብሎ ስለነበር ማንም አልነበረም ። ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወኩም ፡ ግን በጣም ጨንቆኛል ። እሷ እስካሁን አፍ አውጥታ አልተናገረችም ፡ ካይኔ ላይ ግን አይኗን ለሴኮንድ እንኳን አልነቀለችም ።
እጆቼ በእጆቿ እንደታሰሩ ፡ አይኖቼ ካይኖቿ እንደተፋጠጡ ፡ ስሜቶቿ ጭምር ሰውነቴን ሙሉ እንደወረሩ ፡ ሁለታችንም ግትር ብለን ከቆምን ብዙ ደቂቃዎች ተቆጠሩ ። እንደ ዛሬ ሲጨንቀኝ ትዝ አይለኝም ። ሀሳቤ ለሁለት ተከፍሏል ። አንደኛው ፡ 'ይሄ ነገር አላማረኝም ፡ እንደምንም ብለህ ብታመልጣት ይሻልሃል' በሚለው እና 'ግዴለህም ማውራቷ አይቀርም ፡ ትንሽ ብቻ ታገስ' በሚለው መሀከል ። ምን ቀን ይሁን በዚህ ሰፈር እንዳልፍ የፈረደብኝ ...? እጆቼን ከእጆቿ በጉልበት መንትፌ መሮጥ አልከበደኝም ። ግን ምን ሆና እነደሆነ ማወቅ ስለፈለኩ ነው ። ማንኛውም ጤነኛ ሰው መንገድ ላይ የማያውቀውን ሰው ፡ የሆነ ነገር ካልሆነ በስተቀር መቼም እንዲህ አያደርግም ። ልጅቷም የሆነ ነገር ብትሆን እንጂ ፡ ከመሬት ተነስታ ፡ በሰላም ሀገር ለምን እነዲህ ታስጨንቀኛለች ...? መፋጠጡ ሲደክመኝ ፡ 'የኔ እህት ፡ ስምሽ ማነው ...? እንተዋወቃለን ወይ ...? ከኔ ምንድነው የምትፈልጊው ...?' የሚሉትን ጥያቄዎች አከታትዬ አቀረብኩላት ። የደነገጠች ትመስላለች ፤ እንደውም ከፊቷ ላይ ያነበብኩት ነገር ቢኖር ፡ "እንዴት እንዲህ ትለኛለህ ...? ስንቱን አብረን እንዳላሳለፍን ...?" አይነት ነበር ። እስካሁን አፏ አልተከፈተም ፡ ነገረ ስራዋ ሁሉ ግን ፍቅረኛዋ እንደሆንኩ አይነት ሆነብኝ ። አንዴ ስታቅፈኝ ፣ አንዴ ስትስመኝ ፣ ከዛን ጉንጬን ስትዳብሰኝ ፣ ሌላ ጊዜ ሸሚዜን ስታስተካክልልኝ ፣ አይን አይኔን በፍቅር ስትመለከተኝ ፣ በቃ ባጠቃላይ ኤሊፍ ለኦማር የምትሆነውን እየሆነችልኝ ነው ። እኔ ደግሞ በጭንቀት ልፈነዳ ምንም አልቀረኝም ። እስካሁን ስላልተነፈሰች ፡ 'ይቺ ልጅ ማውራት ስለማትችል ፡ ፍቅሯን በ acting እየገለፀችልኝ ይሁን እንዴ ...?' እያልኩ አሰብኩ ። ብቻ ምን ያላሰብኩት አለ ...? እሷ ግን እኔን በማግኘቷ ደስ ያላት ትመስላለች ። ልክ የእናቱን ጡት እንዳገኘ ጨቅላ ህፃን እያየችኝ ትቦርቃለች ። በማላውቀው ነገር ፡ ከማላውቃት ልጅ ጋር ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ #10 ደቂቃ በላይ ፡ ለዚያውም ድምጿን ሳልሰማ ቆምኩኝ ። ዝምታዋ አስፈራኝ ፡ ብታሳዝነኝም ምንም ማድረግ ስላልቻልኩኝ ፡ 'በቃ የኔ እህት ፡ ሰዓት ረፍዶብኛል ፡ መሄድ አለብኝ" አልኳት እና እጆቼን ከእጆቿ እንደምንም አላቅቄ ፡ አንድ እርምጃ ሳነሳ ፡ ይሄን ሁሉ ደቂቃ ሳታሰማኝ የቆየችውን ድምጿን እንደ ቴዲ አፍሮ አልበም ልክ በቃ ይሄ ሰውዬ ሙዚቃ አቁሞ ገዳም ገብቷል ብለን ተስፋ ስንቆርጥ እንደሚያሰማን እሷም በስተመጨረሻ ያንን ሰምቼውም ማላውቀውን ድምጿን ተስፋ ቆርጬ ስሄድ አሰማችኝ ። እውነት ለመናገር ድምጿን ስሰማ ልቤ ለሁለት ነበር የተሰነጠቀው ። በጣም በሚያሳዝን እና ልብን በሚነካ ዜማ "ጥለኸኝ አትሂድ ፡ ማንም ሰው የለኝም" አለችኝ ። ዞር ብዬ ሳያት እምባዋ ከነዚያ ፀሀይ ከሚመስሉ አይኖቿ ፡ እንደ ዶፍ ዝናብ እየወረዱ ነው ። አማራጭ አልነበረኝም ፡ ያነሳሁትን አንድ እርምጃ ወደ ቦታው መልሼ እቅፌ ውስጥ ሸጎጥኳት ። እንደውም ቅድም እሷ ካስጨነቀችኝ በላይ ነው እቅፍ አድርጌ ያስጨነኳት ።
ለ አስተያየት @babusem
✎ ክፍል ሁለት በኋላ ይለቀቃል....
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል................
​የከንቲባው ልጅ

ክፍል 2


.
.
.
.
እቅፌ ውስጥ ሆና ስታለቅስ ደረቴ ላይ እምባዋ እንደ ጅረት ይፈስ ነበር ። የሷ እንደዛ ማልቀስ ሲገርመኝ ፡ የኔም እምባ ከየት መጣህ ሳይባል ጀርባዋ ላይ ዱብ ዱብ እያለ አጃዒብ አስባለኝ ። ቃል ሳታወጣ ስሜት ማጋባት ትችልበታለች ። በጣም እንደተጎዳች ታስታውቃለች ። ችግሩ ግን የማይሆን ሰው ላይ መውደቋ ነው ። እኔ እንኳን የሰውን ችግር ልቀርፍ ይቅርና ፡ የራሴንም የራሱ ጉዳይ ብዬ የተውኩ ሰው ነኝ ። ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም ፤ ብቻ እንደ ተቃቀፍን ደቂቃዎች ተቆጠሩ ። በኔ ፍቃድ ተላቀቅንና 'እሺ እቤት ላድርስሽ ...? የት ነው መሄድ የምትፈልጊው ...?' ስላት ፡ "ብቻዬን እዛ ቤት መሄድ አልፈልግም" አለችኝ እና ድጋሜ እቅፌ ውስጥ ገብታ ማልቀስ ጀመረች ። አሳዘነችኝ እና ድንገት ሳላስበው 'አያሳስብም ፡ አብረን እንሄዳለን' አልኳት ። "ያሉት ከሚጠፋ ..." ። መኪናዋ ውስጥ ገብተን ፡ መሪውን ወደ ዋላ አዙራ ፡ ሄጄ ወደ ማላውቅበት ሰፈር ወሰደችኝ ። ድሬዳዋ ከመጣሁ በዚህ በ2 ዓመት ውስጥ ፡ እንደዚህ አይነት ቤቶችን አይቼም አላውቅም ። ሲመስለኝ የሀብታሞች ወይንም የባለስልጣናት ሰፈር ይመስለኛል ። ይህን ሰፈር አልፈን ትንሽ ደቂቃ እንደሄድን ፡ ጭር ያለና ብዙም ሰው የሌለበት ፡ በዛላይ ምንም ሰፈር የሌለበት ቦታ ደረስን ። ግን መኪናው ውስጥ ሆኜ አንድ ቤት ይታየኛል ። መኪናውን በሩ ፊትለፊት አቁማ ፡ "ደርሰናል ፡ እንውረድ" አለችኝ ። የቤቱ አሰራር ኢትዮጵያ ውስጥ ካየዋቸው ለየት ያለና ያልተለመደ አይነት ነበር ። ጥበቃ የለውም መሰለኝ ፡ እራሷ የውጪውን በር ከፍታ ፡ መኪናዋን ጊቢ ውስጥ አቆመች ። እየመሸ ስለሆነ ብዙ ነገሩ እንደ ልብ አይታይም ። "ና ፡ አትፍራ ፡ እንደ ቤትህ እየው" ስትለኝ ፡ በልቤ ውስጥ 'አሜን' አልኩኝ ። እንደዚህ አይነት ቤት ስገባ የመጀመሪያዬ ነው ። ማን ያውቃል ምናልባትም የመጨረሻዬም ሊሆን ይችላል ። ወደ ሳሎን ቤቱ መራችኝና ሶፋ ላይ እንድቀመጥ በእጇ ጋበዘችኝ ። "ሚጠጣ ምን ላምጣልህ ...?" ብላኝ ፍሪጅ ከፈተች ። አይኔ በቅድሚያ ፍሪጁ ውስጥ ወዳለው ቢራ ላይ ቢያርፍም ፡ ጨዋ ለመሆን ያክል ፡ 'ኮካ አርጊልኝ' አልኳት ። ለኔም ለራሷም ኮካኮላ ከፍታ ፡ ፊትለፊቴ ባለው ሶፋ ላይ ተቀመጠች ። በሁኔታው ግራ እንደተጋባሁ ስለተረዳች ፡ በራሷ ተነሳሽነት ታሪኳን እና ቅድም እኔላይ ስላሳየችው ነገሮች ልትነግረኝ ተዘጋጀች ። "እየውልህ የኔ ወንድም ፡ በመጀመሪያ ስለ ሁሉም ነገር በጣም ይቅርታ እሺ ፤ ስሜታዊ ሆኜ ስለነበር ነው ። በዛላይ የት መሄድ እና ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ በገባኝበት ሰዓት ነው አንተን በመኪናዬ ውስጥ ያየሁክ" ብላ ታሪኳን ጀመረች ። "እናቴን አይቻት አላውቅም ፡ ያኔ ገና ስወለድ ነበር ያጣዋት ። የኔ ህይወት እንዲተርፍ ፡ የሷ ማለፍ ነበረበት ። ያኔ እንዳሁኑ በየቦታው ሆስፒታሎች ከመሠራታቸው በፊት ብዙም አልነበሩም ። እኔ ስወለድ እናቴን ብዙ ደም ፈሷት ስለነበር ፡ በአቅራቢያው ደግሞ ጤና ጣቢያ ስላልነበር ፡ በፈሰሳት ብዙ ደም ምክንያት አቅም አጥታ ህይወቷ አለፈ ። ብዙዎች አግኝተው ነው የሚያጡት ። እነደኔ አይነቱ እድለ ቢስ ግን ሳያገኝ ያጣል ። እናቴ ህይወቷን ሰውታ ህይወት ስለሰጠችኝ ፡ አባቴ ህይወት ብሎ ስም አወጣልኝ ። እስካሁን አልተዋወቅንም አይደል ...? ህይወት እባላለሁ" አለችኝ እና እጇን ለትውውቅ ዘረጋችልኝ ።
'ተስፋዬ እባላለሁ' አልኳት የዘረጋችልኝን እጅ እየጨበጥኩ ። ታሪኳን ቀጠለች ፡ "አባቴ ነው ያሳደገኝ ፡ የሚገርምህ እናት እንደሌለኝ ተሰምቶኝ አያውቅም ። እንደ እናትም ፣ እንደ አባትም ፣ ሆኖ ብቻውን ያሳደገኝ እሱ ነው ። አባቴ እንደ አባት ብቻ አይደለም ፡ እንደ ጓደኛም ጭምር ሆኖ ነው አብረን የኖርነው ። ከ 1 ነገር ውጪ አንድም ነገር ከልክሎኝ እና አጉድሎብኝ አያውቅም ። በነገራችን ላይ አባቴ ባለሥልጣን ነው ፡ ያውም የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ" ስትለኝ በሆዴ 'በቃ ተስፍሼ ቁርጥህን አወቅ ፡ ነገ ወይ ከርቸሌ ፡ ወይ ሲኦል ገብተሃል' አልኩኝ ። ስታወራ አይን አይኔን እያየች ስለነበር እንደፈራሁ ገብቷት ፡ "አይዞህ አትጨናነቅ ፡ አባቴ እነደምታስበው አስፈሪ እና ቁጡ ሰው አይደለም ፤ በተቃራኒው ደግ እና አዛኝ ነው ። ደግሞም ለጊዜው ሀገር ውስጥ ስለሌለ ማንም እዚህ ቤት አይመጣም ፈታ በል"። ስትለኝ ትንሽም ቢሆን ተረጋጋሁ እና ታሪኳን እንድትቀጥልልኝ በአይኔ ምልክት ሰጠዋት ። "እንዳልኩህ አባቴ የከተማችን ከንቲባ ነው ። በዚህም ምክንያት ብዙ ችግሮች እየደረሱበት ነው ። ለጊዜው የሱን እንተወውና የኔን ጥቂት ልንገርህ ። "እስካሁን ድረስ አባቴ ስልጣን ላይ ከወጣ በዋላ ያየሁት ዘመድ ፣ ጎረቤት ፣ ጓደኛም የለም ። ከአባቴ ውጪ ቀርቤ የማውቀው ሰው የለኝም ። ብዙ ጊዜ ከቤት ስለማልወጣ ሰውን በአካል ሳይሆን በቴሌቪዥን ነው የማየው ። በአጭሩ በብቸኝነት የምሰቃይ ሴት ነኝ ። ከአባቴ ጋር ከቅዳሜ ምሽት እስከ እሁድ ሙሉ ቀን አብረን እናሳልፋለን ። ከዚያ ውጪ ግን አምስቱንም ቀናት ስራ ላይ ነው የሚያሳልፈው ። አልፎ አልፎ ደህንነቴን ለማወቅ ካልሆነ በስተቀር እዚህ አይመጣም ። በስልክ ግን በየሰዓቱ እናወራለን ማለት ይቻላል ። ቢያንስ በቀን #5 ጊዜ እንደዋወላለን ። ሰሞኑን ግን ምን እንደሆነብኝ እንጃ ከደወለልኝ ድፍን #3 ቀን ሞላው ። አሜሪካን ሀገር አስተካክዬ የምመጣው ነገር አለኝ ብሎ ነበር ከ #5 ቀን በፊት የሄደው ። የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ቀናት ደውሎልኝ በሰላም አውርተን ነበር ። ከዛ በዋላ ግን ስለሱ የማውቀው ምንም ነገር የለም ። በዚህ ጉዳይ በጣም ስለተጨነኩ እና ቤቱ ያለወትሮው ሊበላኝ ስለደረሰ ነበር ከዚህ ቤት ለመውጣት ያሰብኩት ። ግን የት መሄድና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወኩም ። በዛ መሀል ነበር አንተን በመኪናዬ ውስጥ ያየሁክ ። ሳይክ በቃ ፡ ዘመዴን ያገኘሁ ነበር የመሰለኝ ። ለዛም ነው ቅድም እንደዛ ያለቀስኩብህ ። ብቻዬን እዚህ ቤት ውስጥ ያሳለፍኩትን የብቸኝነት ስቃይ ከኔና ከፈጣሪ ውጪ ማንም አያውቅም ። በቲቪ ብዙ ፊልሞችን ሳይ ነፃነታቸውን አይቼ እቀናባቸዋለው ። አባቴ በስራው ምከንያት ስለሚጠነቀቅልኝ ፡ ሰራተኛም ፣ ጥበቃም የለንም ። ከሱ ውጪ ይሄን ቤት የሚያውቀው ሰው ያለም አይመስለኝም ። በተረፈ መኪና መንዳት እና ምግብ ማብሰል አባቴ በስርዓት አስተምሮኛል ። ሲጀምር ብዙም የምግብ ፍላጎት ስለሌለኝ ያን ያክል አያስጨንቀኝም ። ስራዬ ሁሉ ቲቪ ማየት ፣ መፅሐፍ ማንበብ እና መተኛት ብቻ ነው ። ይሄ ሁሉ የሆነው እንግዲህ የዛሬ #4 ዓመት አካባቢ ልክ አባቴ ወደ ስልጣን እንደመጣ ነው ። ትምህርቴንም አቋርጫለሁ ፤ አሁን እንደምታየኝ በልጅነቴ የቤት እመቤት ሆኜ ቀርቻለሁ" ። ብላኝ በድንገት ከሶፋው ላይ ብድግ አለች ።

✎ ለአስተያየት @babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 3

.
.
.
እንደዛ ተስፈንጥራ በቁጭት እና ንዴት ከመነሳቷ በፊት ፡ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለን ኮካችንን እየተጎነጨን ፡ እሷ አይን አይኔን እያየች እያወራች ፡ እኔ ደግሞ አፌን ከፍቼ እያዳመጥኳት ነበር ። ተነስታ ቤት ውስጥ ወደዛ ወደዚህ ስትል አይኔ ፊትለፊቷ ወደተሰቀለው የግድግዳ ሰዓት ላይ አረፈ ። አናቱ ላይ በትክክል መገመት ባልችልም #02:05 አካባቢ ይላል ። እሷ ቅድም ከተስፈነጠረችው በላይ ነበር ደንግጬ ከሶፋው ላይ የተነሳሁት ። 'በቃ እኔ ልሂድ ፡ ሰዓቱ ሳላስበው በጣም ሄዷል ፡ ባይሆን ሌላ ቀን አገኝሻለው' ብያት ወደ በሩ ሳቀና ፊትለፊቴ ቀድማኝ ፡ በሩን ተደግፋ አትሂድ የሚል ፊቷን አሳየችኝ ። "ዛሬን ብቻ እዚህ ቤት ብታድር ትሞታለህ ...? ፡ እእእ ፡ ንገረኛ ...? በዛላይ መሽቷል ፡ በዚህ ሰዓት መሄድ ላንተም ጥሩ አይደለም" አለችኝ ። ብቻ ልጅቷ ሆዴን በልታዋለች ። ወድጄም ባይሆን ለማደር ወስኛለሁ ። ሲጀመር በዚህ ሰዓት ብቻዬን ወደ ግቢ ልመለስ ነው ወይንስ ልጅቷን ፡ 'እንዳመጣሽኝ ወደ ቦታው መልሺኝ' ልላት ነው ...! ሆኖም ግን ጥሩ ስሜት ላይ አይደለሁም ። የማላውቀው ሰፈር ፣ የማላውቀው ቤት ፣ ከማላውቃት ልጅ ጋር ...! ብቻ ደስ አይልም ። "ቆንጆ እራት ሰርቼ ፡ አብረን እንበላለን እሺ...! እስከዛ እንዳይደብርህ TV እያየህ ጠብቀኝ" አለችኝና ኩሺና ገባች ። የምወደውን ebs ቲቪ እያየሁ ጠበኳት ። እራቱም ቀረበና አጭር ፀሎት ተደረገ ። ከዛን ለራሷ ሳትጎርስ ፡ እኔን ልታጎርስ ምግብ የጠቀለለ እጇን ወደ አፌ ዘረጋች ። ሁኔታው ግር ቢለኝም እያመነታሁ ጎረስኩላት ። ቀጥላ "ከአባቴ ጋር ስንበላ መጀመሪያ ተጎራርሰን ነው" ስትለኝ ፡ እኔም የቤቱን ስርዓት ለማስቀጠል ብዬ ለራሴ ያዘጋጀሁትን ጥቅልል እንጀራ ወደ አፏ ሰደድሁ ። እውነት ለመናገር የሰራችው ምግብ ከነ ጣቷ ብሉኝ ብሉኝ ይላል ። ለጨዋታ ያህል ፡ 'አንቺ ፡ እውነትም የቤት እመቤት አይደለሽ እንዴ ...?' አልኳት ። ቅር አላላትም ፡ እንደውም "ሙት እሺ" አለችኝና በግራ እጇ ፡ እንዳልጎዳ በማሰብ ትከሻዬን መታችኝ ። እራታችንን በልተን ጨርሰን ፡ ከምግብ ጠረጴዛ ወደ ሶፋው ተመለስን ። ቲቪውን ለማየት እንዲያመቸን ፡ ሁለታችንም ከቲቪው ፊትለፊት ባለው ሶፋ ላይ ተቀምጠናል ። ሀሳባችንን እርግፍ አርገን ትተናል ። ብቻ እየተጫወትን ፡ እየተሳሳቅን ነው ። የምሽቱን ፀጥታ በሳቋ አድምቃለች ። ስቃ አታውቅም መሠለኝ ፡ ስትስቅ አታባራም ። ደግሞ ስትስቅ ደረቴ ላይ ልጥፍ ትላለች ። ኮስተር ማለት አልፈለኩም ፡ ዛሬ የደስታዋ ቀን ይሁን ብዬ እራሴን ሰጥቻታለሁ ። እስካሁን ግን እየሆነ ባለው ነገር አየተገረምኩ ነው ። ህልም እንጂ እውን አይመስልም ። የጥፋተኝነት ስሜት አልተሰማኝም ። ሲጀመር ምን አጠፋሁ ...? እንደውም "ሰውን ለመርዳት ፡ ሰው መሆን በቂ ነው" የሚለውን አባባል አየተገበርኩ ያለው ነው የመሠለኝ ። በመሀል ሰዓቱ በጣም መሄዱን ስላወኩ 'ዛሬ የመተኛት እቅድ የለሽም እንዴ ...?' አልኳት ። ከዛን "ውይ ፡ በጣም ይቅርታ እሺ ፡ እኔኮ ብዙ ጊዜ ቀን ቀን ስለምተኛ ነው" አለችኝ እና እጄን ይዛ ወደ አንድ ክፍል ወሰደችኝ ። "የአባዬ መኝታ ቤት ነው ፡ ከፈለክ እዚህ ተኛ ፤ ይሄኛው ደብሮህ ሳሎን ሶፋ ላይ ማደር ከተመቸህ ግን እዛም ማደር ትችላለህ" ስትለኝ ፤ የባለስልጣን አልጋ ላለመዳፈር ብዬ 'ኧረ ፡ ሶፋው እኮ ይበቃኛል ፡ አትጨናነቂ' አልኳት ። "እንደተመቸህ" ብላኝ ፡ ብርድ ልብስ አቀበለችኝና ቲቪውን ዘግታ ወደ መኝታ ክፍሏ አመራች ። በልብስ መተኛት ስለማልወድ ፡ ከላይ የለበስኩትን አውልቄ ልተኛ ስል ልጅቷ ድንገት ከተፍ አለች።

...በልብስ መተኛት አልወድም። ልተኛ ልብሴን ሳወልቅ ሳላስበው በድንገት መጥታብኝ ፡ ትንሽም ቢሆን አሳፈረችኝ ። መደንገጤን አይታ "ውይ በጣም ይቅርታ እሺ ፡ ልብስህን እንዳወለክ ስላላወኩ ነው ። ለማንኛውም ፡ ደና እደር ሳልልህ ሄድኩኝ አይደል ...? ፡ ደና እደር እሺ የኔ ጌታ" አለችኝና ወደመጣችበት ተመለሰች ። የሷን አላውቅም ፡ እኔን ግን በፍጹም እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም ። እኔ እንኳን ይሁን ልመናት ፡ እሷ ግን እንዴት አመነችኝ ...? ፡ ይሄን የመሠለ ቤት ውስጥ ብቻዋን የምትኖር አንዲት ፍሬ ልጅ ፡ እንዴት እንደኔ አይነቱን ጎረምሳ አምና ታሳድራለች ...? ፡ ነው ወይስ ተደብቃ ምን እንደማደርግ እያየችኝ ይሁን ...? ፡ anyways የሶፋው ምቾት ፡ ምቾቴን ነስቶኝ እንቅልፍ ባይኔ ዝር ሳትል ፡ ከመስጂድ "Allah wakbar" የሚል ድምፅ ከጆሮዬ ገባ ። በ #4 ማይክራፎን ነው ሚጠቀሙት መሠለኝ ድምፁ ከልክ በላይ ይሰማል ። ሲመስለኝ ቤታቸው ለመስጂድ ፤ ወይም ደግሞ መስጂዱ ለቤታቸው ቅርብ ነው ። ከጥቂት ደቂቃ በዋላ ከልጅቷ መኝታ ቤት ድምፅ ይሰማኝ ጀመር ። ሲመስለኝ እየቃዠች ነው ፡ ድምጿ ስለረበሸኝ ወደ ክፍሏ አመራሁ ። "አባአአአ ፡ አባዬኤኤኤ ፡ አትሂድ አባ ፡ አትሙትብኝ ፡ አይሆንም" (በሃይለኛ ድምፅ) ። የኔ በር በርግዶ መግባትና የሷ ከቅዠት መባነን clash አደረገ ። በጣም አልቧታል ፤ በዛላይ ከመጠን በላይ ቁና ቁና እየተነፈሰች ነው ። ለማረጋጋት ብዬ አቀፍኳትና እንደ ልጅ እያባበልኳት "አይዞሽ እሺ ሁሉም አልፏል ፡ ደግሞም ቅዠት እንጂ እውነት አይደለም" አልኳት ። ደረቴ ውስጥ ገብታ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች "አባዬን የሆኑ ሰዎች ጫካ ውስጥ ሲገድሉት አየሁ እኮ" አለችኝ ። በጣም ፈርታለች ፡ ሁሉ ነገርዋ ይንቀጠቀጣል ። በፍርሀት ስታቅፈኝ እራሱ እንዳለቃት ነው መሠለኝ ፡ ትንፋሽ እንኳን መውሰድ እስኪያቅተኝ ድረስ ነው ። ለተወሰኑ ደቂቃዎች በእቅፌ ውስጥ ሆና አምርራ አለቀሰች ። ቀስ በቀስ ግን ድምጿ እየቀነሰ ፡ እየቀነሰ ፡ በስተመጨረሻ silent ሆነች ። ቀስ ብዬ ሳያት ፡ አሸልባለች ። እንደምንም ብዬ ሳልቀሰቅሳት አልጋዋ ላይ አስተኛዋት ። ለደቂቃዎች አልጋዋ አጠገብ ቁጭ ብዬ አየኋት ። ቅድም ያየሁት ፡ ያ እንቡጥ ፅጌሬዳን የሚመስለው ጉንጯ አሁን ላይ በእንባዋ ታጥቦ ሌላ ሰው አስመስሏታል ። ቅድም እንተኛ ስላልኳት ሊፀፅተኝ ነው መሠለኝ ። እንደዛው እንደሳቀች ባነጋነው ። ብቻ ልጅቷ ሚስኪን ከሚባሉት ጥቂት ሴቶች መሀል አንዷ ናት ። ትቻት ወደ ሳሎን ተመለስኩኝ ። ለመጀመሪያ ጊዜ ለሊቱን ሙሉ አይኔ ሳይከደን ጀምበር ወጣች ። ቢረዝምም ይነጋል ፡ ሚያልፍ ባይመስልም ሁሉም ያልፋል ። የዛሬው ቀን አያልፍም እንዴ ብዬ የሰጋሁት ትናንት ሆነልኝ ። ያልተኛሁት ያለሁበትን ቦታ ፈርቼ አልነበረም ። በቃ እንቅልፍ እምቢ ስላለኝ ነው ። ለማንኛውም ተመስገን ማለቱ ሳይሻል አይቀርም ። ተመስገን ፈጣሪዬ ።
"ነቅቻለሁ ፡ ተርፌያለሁ ፡
ራሴን ላድን ፡ ቆርጫለሁ ...!"
Le asteyayet
@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................