የኛ ግጥም
44 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
​የከንቲባው ልጅ

ክፍል 1


.
.
:- እውነተኛ ታሪክ ነው!
.
.
እለተ ረቡዕ : ሚያዚያ 30, 2011 ዓ.ም ፡ ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፡ 11:00 ሰዓት አካባቢ ከሶስቱ የጊቢው በሮች ታዋቂ በሆነው በቶኒ በር ስፖርት ቤት ለመሄድ እየወጣሁ ነው ። ስፖርተኛ አይደለሁም ፡ ሰሞኑን እየተሰጠኝ ባለው አስተያየት ምክንያት መከራ እያየሁ ያለሁ ሚስኪን የ #2ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ እንጂ ። ሰው እንዴት ሳይጠየቅ comment ይሰጣል ...? ስትወፍር ፡ ምን አገኘህ ደግሞ ...? እያለ ያሽሟጥጣል ። ስትከሳ ፡ ጎዶሎህን ይሞላ ይመስል ምን ጎደለህ ደግሞ ...? ይልሀል ። ምንም ነገር ብትሆን የሰው ልጅ comment ከመስጠት ወደ ዋላ አይልም ። ምን አለበት Like ብቻ አርጎ ቢቀየስ ። ሰሞኑን "ምነው ከሳክ" ብሎ ያልጠየቀኝ ሰው ካለ ለዘላለም ይኑር ፣ የተባረከም ይሁን ። በነሱ አይን ምከንያት እነደከሳሁ ማን በነገራቸው ። እኔማ የሰው አይን እና አስተያየት ሲበዛብኝ ፈርቼ ንሰሐ ገባሁ ። (አቤት ውሸት ...) አንዳንዴማ አይናቸው ተጎልጉሎ እስኪወጣ ድረስ ስለሚያዩኝ አካሄድ እራሱ ይጠፋብኛል ። (ውይ ማጋነን ስንወድ ግን ...) የሆነ ቀን ብልጭ አለብኝና ፡ ለምን ስፖርት አልጀምርም ብዬ ከራሴ ጋር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስብሰባ ተቀመጥኩ ። ውሳኔውም ፡ በርታ ፣ ጠንክር ፣ አይዞህ ፣ ከጎንህ ነን ጀምር የሚል ነበር ። ለዚህም ውሳኔ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል ። (አቤት መበጥረቅ...) ይኸው ጠንክሬ ተፍ ተፍ ማለት ከጀመርኩ ቀናቶች እየተቆጠሩ ነው ። ወደ ስፖርት ቤቱ እያቀናሁ እያለ ፡ ፊትለፊት መንገድ ላይ በኔ street በጣም የምታምር የቤት መኪና መጣች ። መንገድ ልልቀቅ ብዬ ትንሽ ወደ ጫፍ ፈቀቅ አልኩኝ ። መኪናዋ ግን እኔ ወደ ሄድኩበት ቦታ መጥታ ጭራሽ እግሬ ስር ደርሳ ቆመች ። በሁኔታው በጣም ተናድጃለው ፤ በዛላይ ተደናግጫለሁ ። የመኪናው ሞተር ሲጠፋ ይሰማኛል ። ወዲያው ከመኪናው ውስጥ በግምት በኔ እድሜ የምትገኝ በጣሙን የምታምር ልጅ ወርዳ ፊትለፊቴ ቆመች ። አይኔ ሲደነግጥ ፡ ልቤ በምት ሲያጅበው ፡ ያስታውቅብኝ ነበር ። መኪናዋን በአይኔ ቃኝቼ ብቻዋን እንደሆነች አረጋግጫለሁ ። አይን አይኔን ካየች በዋላ እስኪጨንቀኝ ጥብቅ አርጋ አቀፈችኝ ። ያልጠበኩት ስለነበር "የኔ እህት ፡ ችግር አለ ...? ሰው ተሳስተሽ እንዳይሆን" ስላት በድጋሜ አየችኝ እና ጭራሽ ጉንጬን ሳመችኝ ። በድርጊቷ ስለተገረምኩኝ ፡ ይቺ ልጅ ግን ጤነኛ ነች ...? እያልኩኝ ልብ ብዬ ማየት ጀመርኩ ። ደግሞኮ ከዛሬ ውጪ አይቻት አላውቅም ። ቀጥላ በእጆቿ እጆቼን ስትይዘኝ ፡ በቃ ይቺ ልጅ እኔን የሚመስል ፍቅረኛ አላት ብዬ አሰብኩ ። አይኖቿ ውስጥ የሚታየኝ የፍቅር ስሜት አይኔ ውስጥ ገብቶ እምባዬን አመጣው ። ሚስኪን ነገር ትመስላለች ። ቢሆንም ግን እጄን ለማላቀቅ ሞከርኩኝ ፡ እሷ ግን ይበልጥ ግጥም አርጋ ያዘችኝ ። ግራ ሲገባኝ ፡ ይሄ ነገር prank ነው እንዴ ...? ብዬ ካሜራ ለማፈላለግ በአንገቴ ዞር ዞር አልኩኝ ። ሰፈሩ ግን ያለወትሮው ጭር ብሎ ስለነበር ማንም አልነበረም ። ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወኩም ፡ ግን በጣም ጨንቆኛል ። እሷ እስካሁን አፍ አውጥታ አልተናገረችም ፡ ካይኔ ላይ ግን አይኗን ለሴኮንድ እንኳን አልነቀለችም ።
እጆቼ በእጆቿ እንደታሰሩ ፡ አይኖቼ ካይኖቿ እንደተፋጠጡ ፡ ስሜቶቿ ጭምር ሰውነቴን ሙሉ እንደወረሩ ፡ ሁለታችንም ግትር ብለን ከቆምን ብዙ ደቂቃዎች ተቆጠሩ ። እንደ ዛሬ ሲጨንቀኝ ትዝ አይለኝም ። ሀሳቤ ለሁለት ተከፍሏል ። አንደኛው ፡ 'ይሄ ነገር አላማረኝም ፡ እንደምንም ብለህ ብታመልጣት ይሻልሃል' በሚለው እና 'ግዴለህም ማውራቷ አይቀርም ፡ ትንሽ ብቻ ታገስ' በሚለው መሀከል ። ምን ቀን ይሁን በዚህ ሰፈር እንዳልፍ የፈረደብኝ ...? እጆቼን ከእጆቿ በጉልበት መንትፌ መሮጥ አልከበደኝም ። ግን ምን ሆና እነደሆነ ማወቅ ስለፈለኩ ነው ። ማንኛውም ጤነኛ ሰው መንገድ ላይ የማያውቀውን ሰው ፡ የሆነ ነገር ካልሆነ በስተቀር መቼም እንዲህ አያደርግም ። ልጅቷም የሆነ ነገር ብትሆን እንጂ ፡ ከመሬት ተነስታ ፡ በሰላም ሀገር ለምን እነዲህ ታስጨንቀኛለች ...? መፋጠጡ ሲደክመኝ ፡ 'የኔ እህት ፡ ስምሽ ማነው ...? እንተዋወቃለን ወይ ...? ከኔ ምንድነው የምትፈልጊው ...?' የሚሉትን ጥያቄዎች አከታትዬ አቀረብኩላት ። የደነገጠች ትመስላለች ፤ እንደውም ከፊቷ ላይ ያነበብኩት ነገር ቢኖር ፡ "እንዴት እንዲህ ትለኛለህ ...? ስንቱን አብረን እንዳላሳለፍን ...?" አይነት ነበር ። እስካሁን አፏ አልተከፈተም ፡ ነገረ ስራዋ ሁሉ ግን ፍቅረኛዋ እንደሆንኩ አይነት ሆነብኝ ። አንዴ ስታቅፈኝ ፣ አንዴ ስትስመኝ ፣ ከዛን ጉንጬን ስትዳብሰኝ ፣ ሌላ ጊዜ ሸሚዜን ስታስተካክልልኝ ፣ አይን አይኔን በፍቅር ስትመለከተኝ ፣ በቃ ባጠቃላይ ኤሊፍ ለኦማር የምትሆነውን እየሆነችልኝ ነው ። እኔ ደግሞ በጭንቀት ልፈነዳ ምንም አልቀረኝም ። እስካሁን ስላልተነፈሰች ፡ 'ይቺ ልጅ ማውራት ስለማትችል ፡ ፍቅሯን በ acting እየገለፀችልኝ ይሁን እንዴ ...?' እያልኩ አሰብኩ ። ብቻ ምን ያላሰብኩት አለ ...? እሷ ግን እኔን በማግኘቷ ደስ ያላት ትመስላለች ። ልክ የእናቱን ጡት እንዳገኘ ጨቅላ ህፃን እያየችኝ ትቦርቃለች ። በማላውቀው ነገር ፡ ከማላውቃት ልጅ ጋር ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ #10 ደቂቃ በላይ ፡ ለዚያውም ድምጿን ሳልሰማ ቆምኩኝ ። ዝምታዋ አስፈራኝ ፡ ብታሳዝነኝም ምንም ማድረግ ስላልቻልኩኝ ፡ 'በቃ የኔ እህት ፡ ሰዓት ረፍዶብኛል ፡ መሄድ አለብኝ" አልኳት እና እጆቼን ከእጆቿ እንደምንም አላቅቄ ፡ አንድ እርምጃ ሳነሳ ፡ ይሄን ሁሉ ደቂቃ ሳታሰማኝ የቆየችውን ድምጿን እንደ ቴዲ አፍሮ አልበም ልክ በቃ ይሄ ሰውዬ ሙዚቃ አቁሞ ገዳም ገብቷል ብለን ተስፋ ስንቆርጥ እንደሚያሰማን እሷም በስተመጨረሻ ያንን ሰምቼውም ማላውቀውን ድምጿን ተስፋ ቆርጬ ስሄድ አሰማችኝ ። እውነት ለመናገር ድምጿን ስሰማ ልቤ ለሁለት ነበር የተሰነጠቀው ። በጣም በሚያሳዝን እና ልብን በሚነካ ዜማ "ጥለኸኝ አትሂድ ፡ ማንም ሰው የለኝም" አለችኝ ። ዞር ብዬ ሳያት እምባዋ ከነዚያ ፀሀይ ከሚመስሉ አይኖቿ ፡ እንደ ዶፍ ዝናብ እየወረዱ ነው ። አማራጭ አልነበረኝም ፡ ያነሳሁትን አንድ እርምጃ ወደ ቦታው መልሼ እቅፌ ውስጥ ሸጎጥኳት ። እንደውም ቅድም እሷ ካስጨነቀችኝ በላይ ነው እቅፍ አድርጌ ያስጨነኳት ።
ለ አስተያየት @babusem
✎ ክፍል ሁለት በኋላ ይለቀቃል....
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል................
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 4


.
.
.
ከእንቅልፌ ሳይሆን ከሶፋው ላይ ተነሳሁ ። ደግነቱ እሷም ተነስታ ኩሺና ውስጥ ሽር ጉድ እያለች ነው ። ሲመስለኝ እንቁላል ነገር እየተሰራልኝ ነው ። አፍንጫዬ ነው ሹክ ያለኝ ። ከጥቂት ደቂቃ በዋላ ድሬዳዋ ከመጣሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ልክ እናቴ ወይንም እህቴ ቤት እያለሁ እንደምትለኝ "ቁርስ ቀርቧል" የሚል የድግስ ጥሪ ከጆሮዬ ገባ ። ስላልተኛሁ ፊቴን ልታጠብ ...? አልታጠብ ...? በሚለው ሀሳብ አየተወዛገብኩ በስተመጨረሻ ታጥቤ ወደ ቁርሱ አቀናሁ ። ልክ እንደ ትናንት ማታው ተጎራርሰን ጀመርነው ። (የቤቱ ህግም አይደል ...) እውነት ለመናገር ልጅቷ ባለሞያ ናት ። የምትሰራው ምግብ ልክ እንደሷ ጣፋጭ ነገር ነው ። (እሷን ደግሞ መች ቀመስካት ...?) ምን እንደ ነካን አላውቅም ፡ ሁለታችንም ተስገብግበን ሳልፈልግ ጨረስነው ። ከቁርስ በዋላ ልክ እንደ ትናንቱ ሶፋው ላይ face to face ተቀምጠን መፋጠጥ ጀመርን ። እሷም እንደኔው ብዙም እንዳልተኛች አይኗ ይናገራል ። የግድግዳ ሰዓቱን ዞር ብላ አየችና "ዛሬ እንኳን እንደማታው አትሂድ ብዬ አላስጨንቅህም ። ማታም በዚያ ሰዓት ወተህ በኔ ምክንያት ችግር ላይ እንድትወድቅ ስላልፈለኩ ነበር ። አሁን ግን ነግቷል ፡ ከኔጋር እዚህ ብትቆይ ደስ ይለኛል ፡ መሄድ ከፈለክ ግን አላስጨንቅህም በሩ ክፍት ነው" አለችኝና ተነስታ በሩን ከፈተችው ። ቢሆንም ግን ቅር እያላት እንደሆነ ፊቷ በደምብ ያስታውቃል ። እኔም ተነሳሁና ወደ ተከፈተልኝ በር አመራሁ ። እሷ ደግሞ በሩን እንደከፈተች የበሩን መክፈቻ ሳትለቅ እዛው ቆማ ወደ መሬት አቀርቅራ ታያለች ። በሩጋ እስክደርስ ለመሄድ አስቤ ነበር ፤ ግን እሷን አልፌ የምሄድበትን ጉልበት አጣሁ ። እጇን ከበሩ መዝጊያ ላይ አንስቺ በራሴ እጅ ዘጋሁትና እጇን እንደያስኩ ወደ ሶፋው ተመለስን ። ጎበዝ ተማሪ ባለመሆኔ ዛሬ ገና ኮራሁ ። ጎበዝማ ብሆን ኖሮ ፡ "ኧረ ትምህርት ያመልጠኛል ፡ በዛላይ ብዙ assignment አስቀምጬ ነው የመጣሁት" እላት ነበር ። በዚች ምድር ላይ ካሉት ነገሮች ቁጥር #1 የምጠላው ትምህርትን ነው ። ጥናት አልተደረገም እንጂ በአለማችንም ለትምህርት ጥላቻ ካላቸው ሰዎች መካከል ቁጥር #1 እኔ ልሆን እችላለሁ ። ለትምህርት ብዙም ትኩረት አልሰጥም ። እሱ ላይ ጊዜዬን ሳጠፋ በጣም ያናድደኛል ። በተለይ የዩኒቨርስቲ ትምህርት ፡ final ፈተና ወሩን ሙሉ አንብበህም የማትሰራው ጉድ የንዴቴን መጠን ከፍ ያደርገዋል ። ከተሳካ አቋራጭ መንገድ ይመቸኛል ። እንደዚህ ስላችሁ ደግሞ የምኮርጅ እንዳይመስላችሁ ። ምን በወጣኝና ፤ የሚኮርጅ ጓደኛ አለኝ ፡ ከሱላይ ነው የምሰራው ። በዚች ምድር ላይ ከሰይጣን ውጪ የምጠላው ነገር ስለሌለ ፡ የሚያስጠሉኝን ነገሮች የሰይጣን ማህበርተኛ አድርጌያቸዋለው ። ለምሣሌ በኔ አይን illuminate የሆኑ ነገሮች እነዚህ ናቸው ፦ #1-ትምህርት ፣ #2-ትምህርት ፣ #3-ትምህርት ... ትምህርትን የጠላሁበት ትክክለኛ ምክንያት አላውቅም ። ለነገሩ ስንፍናዬኮ በቂ ምክንያት ይሆናል ። anyways ለጊዜው ትምህርቱን የራስህ ጉዳይ ብዬው ፡ እልጅቷ ቤት ቀርቻለሁ ። ከጥቂት ዝምታ በዋላ "እሺ ወጣት ተስፋዬ ፡ እስኪ ስላንተ ንገረኝ ፡ በትንሹም ቢሆን ስለኔ አውቀህ የሌ ...?" አለችኝ ።

'እንዳልኩሽ ስሜ ተስፋዬ ይባላል ። እናቴ ናት ያወጣችልኝ ። የተወለድኩት ሙገር ቀበሌ ውስጥ በምትገኝ ኩባ ሰፈር በምትባል ቦታ ነው ። ምናልባት ሙገርን በሲሚንቶ ልታውቂያት ትችያለሽ ። (ሙገር ሲሚንቶ ፣ ዳንጎቴ ሲሚንቶ) የትውልድ ሰፈሬ ኩባ የተባለው ፡ ያን ጊዜ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን የሰሩት ሰዎች ኩባውያን ስለነበሩ ነው ። ኩባ ሰፈር ደግሞ በፋብሪካው አጥር አጠገብ በታችኛው በኩል የተመሠረተ ሲሆን ፡ ያን ጊዜ የኩባውያን ፡ አሁን ደግሞ የፋብሪካው ሰራተኞችና ቤተሰቦች መኖሪያ ስፍራ ነው ። ሁለተኛ ክፍል እስክደርስ እዛው ነው ጥርሴን ነቅዬ ያደኩት ። #2ኛ ክፍል #2ኛ ሴሚስተር ላይ አባቴ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ውስጥ የስራ እድገት አገኘና ቤታችንን ከኩባ ሰፈር ወደ ሙገር መኮዳ ቀየርን ። መኮዳ ከኩባ ሰፈር በእግር ከ #30-40 ደቂቃ የሚፈጅ መንገድ ሲሆን በመኪና ደግሞ ከ #5 ደቂቃ አያልፍም ። ሰፈሩም መኮዳ የተባለው በድሮ ጊዜ እዚህ አካባቢ የኦዳ ዛፍ እንደነበር ይነገራል ። ለዛም ነው ሰፈሩ በአፋን ኦሮሞ Muka odaa /ሙከ ኦዳ (የኦዳ ዛፍ) የተባለው ። ከዛን ቀስ በቀስ ስሙ ከልጅ ልጅ ሲያልፍና ሲቆላመጥ መኮዳ ሆኖ ቀረ ። እና እዚህ ድሬዳዋ እስክመጣ ድረስ ለ #10 አመታት እዛው ነው ከቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ጋር ያሳለፍኩት ። መኮዳም ኩባ ሰፈርም ካምፕ ናቸው ። የፋብሪካው ሰራተኞችና ቤተሰቦች ብቻ የሚኖሩበት ሰፈር ። አብዛኛው የሙገር ሰው ግን የሚኖረው ሬጂ በሚባል የሙገር ከተማ ውስጥ ነው ። አስተዳደጌ ያንቺ ተቃራኒ ነው ። እቤት ውስጥ አባቴ ፣ እናቴ ፣ #3ቱ እህቶቼ እና አጎቴ ሆነን ነው የኖርነው ። እንዳንቺ ብቻዬን ለአመታት ይቅርና ለሰዓታትም አሳልፌ አላውቅም ። ቤተሰብ ፣ ዘመድ ፣ ጎረቤት ፣ ጓደኛ ፣ ሁሉንም አለኝ ። ሰፈር መንደሩ ያውቁኛል ፤ እኔም እንደዛው ። ምናልባት እኔና አንቺን የሚያመሳስለን ነገር ቢኖር የሲሚንቶ ሀገር ልጆች መሆናችን ነው ። ለነገሩ ምናችንም ሲሚንቶ አይመስልም ። ከአፈር እንደተሰራን እናስፎግራለን ። ባይሆን ግን ነጮቹ ከሲሚንቶ የተሰሩ ይመስሉኛል ። anyways ብዙም ባያኮራም ፣ ደስ የሚሉ ብዙ ታሪኮችን አሳልፌ አሁን ላይ ደርሻለሁ ። እንደ ምታዪኝ አሁን የግቢ ተማሪ ነኝ ። በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ #2ኛ ዓመት የመካኒካል እንጂኔሪንግ ተማሪ ነኝ' አልኳት እና ብዙ እንዳወራሁ ስለተሰማኝ ዝም አልኩ ። ቀጥላም "ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በመሆንህ ደስተኛ ነህ ...?" አለችኝ ። አኔም 'መጀመሪያ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ እንደደረሰን ስናውቅ በደስታ አብደን ነበር ። ከ #1 ክፍል ውስጥ #10 ተማሪ ነበር አንድላይ እዚህ የደረሰን ። እዛ ሆነን የጠበቅነው ነገርና ፡ እዚህ መጥተን ያየነው ምንም አይገናኝም ። ባጠቃላይ ስለ ድሬ ባጭሩ ሙዚቃዋ ሸወደን ማለት ይቻላል ። anyways አማራጭ ስለሌለኝና "ነገር ሁሉ ለበጎ ናቸው" በሚለው ቃል ስለማምን አሜን ብዬ ተቀብየዋለሁ' አልኳት ። መጠየቅ ትወዳለች መሠለኝ ፡ ጥያቄው ቀጥሏል ። "ይቅርታ ግን ፡ መጠየቅ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላውቅም ። እእእ ... ፍቅረኛ አለህ ...?"

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል...............
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 16



"አንተን የሚመስል ሰው አውቃለሁ ፣ አንተን የሚመስል ዘመድ አለኝ ፣ እኛ ሰፈር አንተን የሚመስል ልጅ አለ ፣ ወዘተ" ነገሮችን ብዙ ሰዎች ሲሉኝ 'ይሆናል እንግዲህ የፈጣሪ ጥበቡ ብዙ ነው' ከሚል መልስ ውጪ ብዙም ትኩረት አልሰጠዋቸውም ነበር ። science እንደ ሚለው በአለማችን ላይ ከ #4 በላይ በመልክ የሚመሳሰሉ ሰዎች አሉ ። እኔን የሚመስል ሰው እስካሁን ባካል ባይገጥመኝም ፡ ከብዙ ሰዎች ግን እሰማ ነበር ። በዚህ ዓመት ብቻ #4 ሰዎች በቁምነገር እንደዛ ብለውኛል ። አንዱ ልጅ እንደውም መንገድ ላይ አስቁሞኝ "ባህር ዳር አውቅሀለሁ እኮ እንዴት ነህ ...?" ብሎኛል ። እኔ ግን ባህርዳርን በስም እንጂ በአካል አላውቃትም ። ከሁሉ ነገር ግን ያስገረመኝ ፡ እኔን የሚመስሉ #4ቱ ሰዎች የተገኙት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ። ቆይ ግን እንዴት እኔን የሚመስል ሰው ህንድ ወይንም ደግሞ Spain ውስጥ አልተገኘም ...? ሌላው ቢቀር ቢጠፋ ቢጠፋ እኔን የሚመስል ሰው ቱርክና brazil ውስጥ ይጠፋል ...? science እኮ ያለው በአለማችን ላይ እንጂ በአንድ ሀገር ውስጥ ብቻ አላለም ። anyways ምናልባት የኔ ሌላ የቀረ high copy ሰው ካለ ግን ባልኳቸው ሀገራት ውስጥ ባይገኙም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለበዛሁ ቻይና ወይ Nigeria ውስጥ ቢገኙ አይከፋኝም ። (ደግሞ ስቀልድ ነው ...) ። ሳሉት እስኪ እኔን የሚመስል ቻይናዊ ። (በናታችሁ አትሳሉት ...) ። ከከንቲባው ልጅ ጋር ያንን ሰውዬ አይተን አጣድፋኝ መኪና ውስጥ ገብተን ወደ ኩሪፍቱ ማረፊያ ክፍላችን ገብተን አረጋግቻት ሁሉን ነገር ከነገረችኝ በዋላ በሰጠችኝ ፎቶግራፍ ላይ ፈዝዤ ቀርቻለሁ ። እኔን የሚመስል ልጅ በአካል አይቼ ባላውቅም ዛሬ ግን በፎቶ አየሁኝ ። ሰው እንዴት በተለያየ ቦታና ከተለያየ ሰው ተወልዶ እንዲህ ሊመሳሰል ይችላል ...? አልኩኝ ለራሴ ። እውነትም የፈጣሪ ጥበቡ ብዙ ነው ። የከንቲባው ልጅ አንዴ ፎቶውን ፡ አንዴ ደግሞ እኔን እያየች ማውራቷን ቀጠለች ። "ለመጀመሪያ ጊዜ በመኪናዬ ውስጥ ሆኜ ሳይክ አቤልን ያገኘሁ ፤ በቃ ፈጣሪ የኔን ዕምባ አይቶልኝ ወደ ምድር የመለሰው ነበር የመሠለኝ ። ወርጄ ተጠመጠምኩብህ ፣ ሳምኩህ ፣ እጅህን ያዝኩህ ፣ አይኖችህን ጎበኘሁ ፣ አለቀስኩብህ ፣ አስጨነኩህ ፣ አዝነህልኝ እቤት ድረስ ይዘኸኝ መጣህ ፣ አወራሁክ ፣ አብረን ተመገብን ፣ ሳታውቀኝ ሳላውቅህ እቤት አሳደርኩህ ፣ ሀሳቤን ጭንቀቴን ነገርኩክ ፣ ሰማኸኝ ፣ ትምህርቴን ብለክ ብቻዬን አልተውከኝም ፣ ከአባቴም በላይ ቀርበኸኝ ለኔ ደስታ ስትል እዚህ ድረስ አብረኸኝ መጣህ ። አየህ ካየውክ ሰዓት ጀምሮ እንደ አቤል ስለማይክ መጥፎ ነገሮችን ማሰብ አልፈለኩም ። አላውቀውም ፣ ይጎዳኛል ፣ እንዴት ልመነው የሚሉ ነገሮች ውስጥ አልገባውም ። በቃ እንዳየውክ አመንኩህ ። የሚፈጠረው ነገር ሁሉ ይፈጠር ብዬ እራሴን አሳመንኩኝ ። እምነቴ ገደል አልገባም ፤ ካሰብኩህና ከጠበኩህ በላይ ሆነኽልኛል ። ይሄን ሁሉ ደግሞ የደበኩህ ማስታወስ የማልፈልገው ታሪኬ ስለሆነ ነው ። አሁንም የነገርኩህ ልክ እኔን ለመግደል አስበው አቤልን እንደ ገደሉት አንተንም እንዳይ ነጥቁኝ ስለፈራሁ ነው እሺ የኔ ጌታ" አለችኝና አሁኑኑ መተው የሚገድሉን ይመስል ተጠምጥማብኝ "ከዚህ ቤት ውስጥ አኖጣም እሺ ...?" ትለኛለች ። ነገሩ ትንሽም ቢሆን ቢያስፈራም ለማፅናናት ብዬ 'አንቺን እንደገደሉ ነው የሚያውቁት ፣ በዛላይ ከቤት ወተሽም ስለማታውቂና እዚህም በለሊት ስለሆነ ከድሬ የመጣነው በምንም ተዐምር ስላንቺ ሊያውቁ አይችሉም አይዞሽ' አልኳትና ተረጋጋች ።
.....
ሞትን ባልፈራም ፡ በዚህ ሰዓት ግን መሞት አልፈልግም ። ቁጥሩ ይብዛም ይነስም ወደፊት መኖር እፈልጋለሁ ፤ ግን ዛሬ መሞት አልፈልግም ፡ ነገም እንደዛው ። ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ከሞት አምልጫለሁ ። (ደግሞ በሩጫ አይደለም...😜) ። እናቴ እንደ ነገረችኝ ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞትን የተጋፈጥኩት ልጅ እያለሁ ነፍስ ሳላውቅ በሁለት ዓመቴ ነበር ። ታሪኩም እንዲህ ነው "የጠዋት ፀሀይ ለልጆች ጥሩ እንደሆነ የትኛውም ዶክተር ሳይነግራቸዉ እናቶች በራሳቸው ጥበብ ስለሚያውቁት ፡ እናቴም ጠዋት ከአልጋ ላይ አንስታኝ ግቢ ውስጥ ወደሚበራው የማለዳ ብርሃን አውጥታኝ እሷ ደግሞ እቤት ውስጥ ምሳ እየሰራች ነበር ። ቆሜም ፣ በዳዴም መሄድ አልጀመርኩም ። እንደዛ ለመሄድ ብዙ ዓመት እንደ ፈጀብኝ እናቴ ነግራኛለች ። እናቴ ምሳ እየሰራች ፡ በመሀል ደግሞ ደህንነቴን ለማረጋገጥ እየወጣች ታየኛለች ። አይኔ ተከድኗል ፣ ተኝቼ እንደሆነ ለማረጋገጥ ጠጋ ብላ በጆሮዋ ትንፋሼን ለመስማት ስትሞክር ምንም አይነት የመተንፈስ ነገር አልነበረም ። ልብ ምቴንም ስታዳምጠው ቆሟል ። ይሄኔ ነበር እናቴ ብቻዋን ማንም በሌለበት ሰፈር እምቧዋን ወደላይ መርጨት የጀመረችው ። የደም እምባ አለቀሰች ። እንዴት አሳይተኸኝ ትነሳኛለህ ብላ የፈጣሪ ልብስ ይመስል የመሬቱን ሳር ጭምድድ አርጋ ይዛ አነባች ። ምነው እመቤቴ ፡ የልጅን ፍቅር ካንቺ በላይ የሚያውቅ የለ ፤ ልጄን እኮ ባንቺ ቤት ክርስትና ማስነሳቴ በፍቅርሽ እንድታኖሪልኝ ነበር ፤ ምነው ታድያ ሳልጠግበው ነጠቅሽኝ እያለች አምርራ አለቀሰች ። በዚህ መሀል ግን እናቴ ከሷ ለቅሶ በተጨማሪ የሌላ ሰው የለቅሶ ድምፅ ሰምታ ዝም አለች ። ወደኔ ስታይ እኔ ነበርኩ የማለቅሰዉ ። ያቺ ቀን ለኔ ለደቂቃዎች ምድርን ለቅቄ ሰማይን ነክቼ ፡ ፈጣሪ ከእናቱ ጋር የእናቴን እምባ አይቶላት ድጋሜ ወደ ምድር የመለሰኝ እለት ነበረች" ። ተወልጄ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በጣም እታመም ነበር ። እንደውም ሀኪም ቤት በየቀኑ ከመመላለሴ የተነሳ ቂጤ በመርፌ ብዛት ወንፊት ይመስል ነበር አሉ ። በሽታው በግልፅ ባይታወቅም ፡ ለማስታገሻ ተብሎ ሁሌም መርፌ እወጋ ነበር ። በዚያ ምክንያት እንደውም ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ካየሁ ዶክተር ስለሚመስለኝ ኡ ኡ ታውን እንደ ምለቅ እናቴ ነግራኛለች ። ያን ቀን ግን ሞቼ ከተነሳሁ በዋላ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ አሞኝ ሀኪም ቤት ስሄድ ትዝ አይለኝም ። ያቺ እለት ለኔ ከሞት ወደ ህይወት ብቻ ሳይሆን ከህመም ወደ ሙሉ ጤንነት የተመለስኩባትም ናት ። ለ #2ኛ ጊዜ ደግሞ ከሞት አፋፍ ላይ የተመለስኩት ከ #5 ዓመት በፊት የጥምቀት በዓል ላይ ነበር ። በዓሉን ለማክበር ከጎረቤት ልጅ ቤቲ ጋር ተያይዘን ወደ ጥምቀተ ባህሩ ወረድን ። ቤቲ ለትምህርት እንዲያመቻት ወላጆቿ ጋር ሳይሆን ለት/ቤቱ ቅርብ በነበሩ ዘመዶቿ (ጎረቤታችን) ጋር ነው የምትኖረው ። በወቅቱ ደግሞ እሷ ኢዶ የሚባል ፍቅረኛ ነበራት ። ምክንያቱን ባላውቅም ወላጅ አባቷ ደግሞ ይሄን ነገር ሰምቶ ልጁን ሊገድለው ይፈልግ ነበር ። ሆኖም ግን የልጁን መልክ ለይቶ ስለማያውቅ የጥምቀት ቀን እኔንና ቤቲን አንድላይ አይቶን ኢዶ መስዬው ሽጉጡን አወጣና ሊገድለኝ ወደኛ አመራ ። ይሄኔ ነበር የቤቲ አሳዳጊ ጎረቤታችን ኡኡኡ እያለች እግሩ ስር ወድቃ "እሱ አይደለም ፣ ይሄ የአበቡ ልጅ ነው ፣ ይሄ የጎረቤት ልጅ ነው" ብላው ከሞት ያስጣለችኝ ።
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 30


.
.
.
ድሬዳዋ በሰላም ገብተ

​​ናል ። ህይወት "ከልደትህ ቀን ላይ አንድ ሰዓት ሰጥተኸኝ ለትንሽ ጊዜ እንኳን አብረኸኝ አትሆንም ...?" አለችኝ ወደ ጊቢ እንደምሄድ ስነግራት ። ያንን አሳዛኝ ፊቷን እያሳየችኝ ስትለምነኝ ጥያት የመሄድ ምንም አቅሙም አይኖረኝም ። የድሬ ከተማ መግቢያ ላይ ወደ ሚገኘው #CCECC ሆቴል አመራን ። የቻይናዊ ሰው ሆቴል ነው ። "ከዚህ በፊት እዚህ መጥተህ ታውቃለህ እንዴ ...?" አለችኝ አየመራዃት ወደ ውስጥ ስንገባ ። 'አዎ' ስላት "መቼም የቻይና ምግብ አምሮህ እንዳልመጣህ ተስፋ አለኝ" አለችኝ እያሾፈችብኝ ። 'አይደለም ፤ ፊልም ለመስራት ነው የመጣሁት' አልኳት ። "የድሬ ልጅ ነች የከዚራ ፤ ስለ ውበቷ ስንቱን ላውራ የሚል ፊልም መሆን አለበት" አለችኝ በድጋሜ እየቀለደችብኝ ። 'ርዕሱን ለጊዜው አላውቅም' ስላት "እንዴዬ ፡ አንተ የምርህን ነው እንዴ አለችኝ" ኮስተር ስላልኩባት ። 'አዎ የምሬን ነው ። እንደውም አምስት ወር ሊሆነው #4 ቀን ይቀረዋል ። ታህሳስ #22 ነበር ። እዚሁ ሆቴል ውስጥ በአክተሮች ፣ ካሜራ ማኖች እና ሜክ አፕ አርቲስት ተከብቤ ነበር ። ቃልኪዳን ጥበቡ (የባባ ሚስት) ፣ ከዘመን ድራማ ተዋናዮቹ እነ አዩ ግርማ ፣ ሄኖክ ድንቁ ፣ እና የመሳሰሉት ነበሩ የፊልሙ ተዋናዮች ። ለካ ፊልም እንደዚህ ተቀርፆ ነው እኛ ጋር የሚደርሰው ። ብታይ የአምስት ደቂቃ ትዕይንት ለመቅረጽ ከሃያ ጊዜ በላይ ነው Cut ፣ action የተባለው ። ከስምንት ሰዓት እስከ #11 ሰዓት ቁጭ ብዬ ሲቀረፅ ያየሁት የ #10 ደቂቃ ትዕይንት አትሆንም ። ፊልሙ ድሬ ብቻ ሳይሆን ሀረርም እንደሚቀረፅ ነግረውኛል' አልኳት ። "መቼም የፊልሙ አክተር አንተ መሆን አለብህ" እያለች ትስቃለች ። 'በመጀመሪያ ደረጃ በዘመድ ነው famous የሆንከው እንዳትይኝ እንጂ ፤ የፊልሙ producer የዶርሜ ልጅ ጓደኛ በመሆኑ ነው እዛ የመሄድ እድል ያገኘሁት ። በመቀጠል ደግሞ እኔን የፈለጉኝ ፊልሙ እዚህ ሆቴል ውስጥ ሲቀረፅ በአክተሮቹ ጀርባ ከሆነች ልጅ ጋር ቁጭ ብዬ ሻይ እንድጠጣ ነው' ስላት ሳቋን በሀይል ለቀቀችውና አስተናጋጁ ሳንጠራው ደንግጦ መጣ ። ምሳ ሰዓት እስኪደርስ እስከዚያው ለስላሳ አምጣልን አልኩትና ተመልሶ ሄደ ። ማፌዟን አላቆመችም ። "እና ይሄን ሁሉ part ሸፍነህላቸው ስንት ብር ከፈሉክ ...?" አለችኝ ። 'እኔ ከጥበብ ገንዘብ አልቀበልም' ስላት "owk የፊልሙ ፕሮዲዩሰር ስም መሆኑ ነው ጥበብ" አለችኝ ። ህይወት በመሆኗ ነው ዕድለኛ የሆነችው እንጂ ሌላ ሰው ፤ በተለይ ደግሞ ወንድ ቢሆን እንደዚህ የሚመልስልኝ እዚሁ ነበር ሰይፌው የምሄደው ። (ወንድ ልጅ አይኑር ያለው ማነው ...?😳) ። በኔ ላይ የመቀለድ ፣ የማሾፍና የማፌዝ መብት ያላት ብቸኛዋ ሴት እሷ ሆናለች ። እሷን የመቀየም ፣ የማኩረፍና በሷ ላይ የመናደድ አቅም የለኝም ። እራሷ ናት ያሳጣችኝ ። ስትስቅ ፣ ስትደሰት ፣ ሁሉን ነገር ረስታ ቀልቧን ሁሉ ስትጥልብኝ በህይወት በመኖሬ እደሰታለሁ ። ፈገግ ባለች ቁጥር የሷን ብቻ ሳይሆን የኔንም ዕድሜ በዕጥፍ ትጨምራለች ። በተለይ ደግሞ "የኔ ጌታ" እያለች ስታቆለጳጵሰኝ ሰማይና ምድሩን እኔው እራሴ በእጄ ጠፍጥፌ የሰራሁላት ነው የሚመስለኝ ። ስታዝን ፣ ስትጨነቅ ፣ ስታለቅስ ፣ ስታኮርፍ ፣ ህይወት ግልብጥብጥ ስትልባት ፣ በቃ ያኔ ነው በህይወት መኖሬን የምጠላው ። ከእሷ አይን የምትፈስ እያንዳንዷ የዕምባ ዘለላ ከእሳተ ገሞራ በላይ ውስጤን የማቃጠል ሀይል አላቸው ።

'ፊልም መስራት የልጅነት ህልሜ ነው ። ትዝ ይለኛል የ #1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ እያለሁ ነበር የወሰወሰኝ ። ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ተማሪ እያለሁና በትምህርት ቤትም ብዙ የመድረክ ድራማዎችን ሰርቼ ነበር ። አሁንም ድረስ የኔ የወደፊቱ ህልሜ በመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተመርቄ ስራ መስራት ይቅርታ ስራ ማፈላለግ አይደለም ። የፊልም አክተር መሆንና መሆን ብቻ ነው እቅዴ ። ከፊልም ውጪ plan B እራሱ የለኝም ። ፍላጎቴ ብሩና ዝናው አይደለም ። ፊልም መስራቱን ብቻ ነው የምፈልገው ። መንገድ ላይ የፊልም director ባገኝ እግሩ ላይ ወድቄ ከፈለክ በነፃ #10 ፊልም እሰራልሀለው ማለቴ አይቀርም' ስላት "እሺ የኛ shah rhuk Khan" አለችኝ ህይወት ትኩር ብላ ካዳመጠችኝ በዋላ ። በነገራችን ላይ የፊልም አፍቃሪ እንድሆን ያደረገኝ የህንዱ አክተር ሻህሩካን ነው ። የሱን ታሪክ በጣም ስለምወደው አጠር አርጌ ልንገርሽ አልኳትና ለትረካው ተሰናዳሁ ። "በልጅነቱ ጎበዝ ተማሪ ነበር ። ስፖርት በተለይ ደግሞ ኳስ መጫወት በጣም ይወዳል ። በልጅነቱ ትምህርት ቤት እያለ አንድ ቀን አስተማሪያቸው ወደ ፊት አወጣውና ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ ብሎ ጠየቀው ። እሱም አፉን ሞልቶ በኩራት የቦሊውድ ምርጥ አክተር እሆናለሁ አለው ። ክፍል ውስጥ የነበሩ ሁሉም ተማሪዎች ሳቁበት ። አስተማሪውም የማይሆን ህልም እንደሆነና ሀሳቡን ቀይሮ ትምህርቱ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ነገረው ። ለሻህሩክ ግን ይህ አልተዋጠለትም ። ህልሙን እውን ለማድረግ የ #2ኛ ዲግሪ ትምህርቱን አቋረጠና ወደ ፊልም ጉዞ ጀመረ ። ነገር ግን በዛ ሰዓት ሁለት ነገሮች ፈተና ሆኑበት ። የመጀመሪያው ወላጆቹን በሞት ማጣቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ታላቅ እህቱ የአይምሮ ህመምተኛ መሆኗ ነበር ። በዛ ምክንያት ቤተሰቦቹን የማስተዳደር ሀላፊነት እሱ ላይ ወደቀ ። ከድህነት ጋር ትግል ገጠመ ። ስራ ለመፈለግ ወደ ሙምባይ ከተማ ሄደ ። የቤት ኪራይ የሚከፍለውን አጥቶ ከቤት ተባሮ ሁለት ቀን ጎዳና ያደረበት ቀን ነበር ። የሰዎች ሱቅ ስር ያደረበት ቀን ደግሞ ስፍር ቁጥር የላቸውም ። ሆኖም ግን በዚሁ ችግር ውስጥ ሆኖ ተዋናዮች የማይደፍሩትን ትወናዎች ይሞክር ነበር ። የሆነ ቀን ለመወዳደር ሄዶ የፊልሙ director "አንተ አርቲስት የምትሆን ሰው አይደለህም" አለው ። እሱ ግን ምንም ሳይመስለው ትቶት ሄደ ። ግን ተስፋ አልቆረጠም ፤ ወደዋላም አልተመለሰም ። ሁልጊዜ ወደ ህልሙ በሚወስደው መንገድ ላይ ይረማመድ ነበር ። ያለምንም ክፍያ ሲኒማ በር ላይ ቆሞ የመግቢያ ticket ይሸጥ ነበር ። በወረደ ሂሳብ እንደ ካሜራና መብራት ያሉ የፊልም መሳሪያዎችን ተሸክሞ ከአርቲስቶች ዋላ ይሄድ ነበር ። ነገር ግን አንድ ቀን መጣ ። የሱ ቀን ። የለውጥ ቀን ። ትንሽ ብር ተከፍሎት አንድ ፊልም (#Deewana) እንዲሰራ ተነገረው ። ከዛው ላይ ተነሳ ፣ ቀጠለበት ፣ ድህነትን ማሸነፍ ጀመረ ፣ እውቅና ትከተለው ጀመር ፣ ህልሙም እውን ይሆን ጀመር ። ለአርት አትሆንም የተባለው ሰው ምርጥ አክተር መሆን ጀመረ ። ዛሬ እንደ ህንድ ብቻ ሳይሆን እንደ አለም በጣም ታዋቂና ዝነኛ አክተር ነው ። በድህነት የሰዎች ቤት ስር ያድር የነበረው ዛሬ ላይ ከአለማችን ሀብታም አክተሮች መሀል አንዱ ነው ። ከብዙ ተቋማት ብዙ ሽልማት ያገኘ ፣ ከራሱም ተርፎ ለህዝቡ የደረሰ ጀግና ነው" ። እናም የኔ ህይወት ሰው ትሆኛለሽ ፣ አትሆኝም ስላለሽ አይደለም ። እሆናለሁ ካልሽ የማትሆኝው የለም ። ዋናው ለምንፈልገው ነገር እስከመጨረሻው ድረስ መስዋዕትነት መክፈል ነው ። ትግልሽን አሪፍ ካደረግሽ ብትወድቂ እራሱ አንድ ቀን ከላይ መሆንሽ አይቀርም ።

ይቀጥላል...