የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 4


.
.
.
ከእንቅልፌ ሳይሆን ከሶፋው ላይ ተነሳሁ ። ደግነቱ እሷም ተነስታ ኩሺና ውስጥ ሽር ጉድ እያለች ነው ። ሲመስለኝ እንቁላል ነገር እየተሰራልኝ ነው ። አፍንጫዬ ነው ሹክ ያለኝ ። ከጥቂት ደቂቃ በዋላ ድሬዳዋ ከመጣሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ልክ እናቴ ወይንም እህቴ ቤት እያለሁ እንደምትለኝ "ቁርስ ቀርቧል" የሚል የድግስ ጥሪ ከጆሮዬ ገባ ። ስላልተኛሁ ፊቴን ልታጠብ ...? አልታጠብ ...? በሚለው ሀሳብ አየተወዛገብኩ በስተመጨረሻ ታጥቤ ወደ ቁርሱ አቀናሁ ። ልክ እንደ ትናንት ማታው ተጎራርሰን ጀመርነው ። (የቤቱ ህግም አይደል ...) እውነት ለመናገር ልጅቷ ባለሞያ ናት ። የምትሰራው ምግብ ልክ እንደሷ ጣፋጭ ነገር ነው ። (እሷን ደግሞ መች ቀመስካት ...?) ምን እንደ ነካን አላውቅም ፡ ሁለታችንም ተስገብግበን ሳልፈልግ ጨረስነው ። ከቁርስ በዋላ ልክ እንደ ትናንቱ ሶፋው ላይ face to face ተቀምጠን መፋጠጥ ጀመርን ። እሷም እንደኔው ብዙም እንዳልተኛች አይኗ ይናገራል ። የግድግዳ ሰዓቱን ዞር ብላ አየችና "ዛሬ እንኳን እንደማታው አትሂድ ብዬ አላስጨንቅህም ። ማታም በዚያ ሰዓት ወተህ በኔ ምክንያት ችግር ላይ እንድትወድቅ ስላልፈለኩ ነበር ። አሁን ግን ነግቷል ፡ ከኔጋር እዚህ ብትቆይ ደስ ይለኛል ፡ መሄድ ከፈለክ ግን አላስጨንቅህም በሩ ክፍት ነው" አለችኝና ተነስታ በሩን ከፈተችው ። ቢሆንም ግን ቅር እያላት እንደሆነ ፊቷ በደምብ ያስታውቃል ። እኔም ተነሳሁና ወደ ተከፈተልኝ በር አመራሁ ። እሷ ደግሞ በሩን እንደከፈተች የበሩን መክፈቻ ሳትለቅ እዛው ቆማ ወደ መሬት አቀርቅራ ታያለች ። በሩጋ እስክደርስ ለመሄድ አስቤ ነበር ፤ ግን እሷን አልፌ የምሄድበትን ጉልበት አጣሁ ። እጇን ከበሩ መዝጊያ ላይ አንስቺ በራሴ እጅ ዘጋሁትና እጇን እንደያስኩ ወደ ሶፋው ተመለስን ። ጎበዝ ተማሪ ባለመሆኔ ዛሬ ገና ኮራሁ ። ጎበዝማ ብሆን ኖሮ ፡ "ኧረ ትምህርት ያመልጠኛል ፡ በዛላይ ብዙ assignment አስቀምጬ ነው የመጣሁት" እላት ነበር ። በዚች ምድር ላይ ካሉት ነገሮች ቁጥር #1 የምጠላው ትምህርትን ነው ። ጥናት አልተደረገም እንጂ በአለማችንም ለትምህርት ጥላቻ ካላቸው ሰዎች መካከል ቁጥር #1 እኔ ልሆን እችላለሁ ። ለትምህርት ብዙም ትኩረት አልሰጥም ። እሱ ላይ ጊዜዬን ሳጠፋ በጣም ያናድደኛል ። በተለይ የዩኒቨርስቲ ትምህርት ፡ final ፈተና ወሩን ሙሉ አንብበህም የማትሰራው ጉድ የንዴቴን መጠን ከፍ ያደርገዋል ። ከተሳካ አቋራጭ መንገድ ይመቸኛል ። እንደዚህ ስላችሁ ደግሞ የምኮርጅ እንዳይመስላችሁ ። ምን በወጣኝና ፤ የሚኮርጅ ጓደኛ አለኝ ፡ ከሱላይ ነው የምሰራው ። በዚች ምድር ላይ ከሰይጣን ውጪ የምጠላው ነገር ስለሌለ ፡ የሚያስጠሉኝን ነገሮች የሰይጣን ማህበርተኛ አድርጌያቸዋለው ። ለምሣሌ በኔ አይን illuminate የሆኑ ነገሮች እነዚህ ናቸው ፦ #1-ትምህርት ፣ #2-ትምህርት ፣ #3-ትምህርት ... ትምህርትን የጠላሁበት ትክክለኛ ምክንያት አላውቅም ። ለነገሩ ስንፍናዬኮ በቂ ምክንያት ይሆናል ። anyways ለጊዜው ትምህርቱን የራስህ ጉዳይ ብዬው ፡ እልጅቷ ቤት ቀርቻለሁ ። ከጥቂት ዝምታ በዋላ "እሺ ወጣት ተስፋዬ ፡ እስኪ ስላንተ ንገረኝ ፡ በትንሹም ቢሆን ስለኔ አውቀህ የሌ ...?" አለችኝ ።

'እንዳልኩሽ ስሜ ተስፋዬ ይባላል ። እናቴ ናት ያወጣችልኝ ። የተወለድኩት ሙገር ቀበሌ ውስጥ በምትገኝ ኩባ ሰፈር በምትባል ቦታ ነው ። ምናልባት ሙገርን በሲሚንቶ ልታውቂያት ትችያለሽ ። (ሙገር ሲሚንቶ ፣ ዳንጎቴ ሲሚንቶ) የትውልድ ሰፈሬ ኩባ የተባለው ፡ ያን ጊዜ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን የሰሩት ሰዎች ኩባውያን ስለነበሩ ነው ። ኩባ ሰፈር ደግሞ በፋብሪካው አጥር አጠገብ በታችኛው በኩል የተመሠረተ ሲሆን ፡ ያን ጊዜ የኩባውያን ፡ አሁን ደግሞ የፋብሪካው ሰራተኞችና ቤተሰቦች መኖሪያ ስፍራ ነው ። ሁለተኛ ክፍል እስክደርስ እዛው ነው ጥርሴን ነቅዬ ያደኩት ። #2ኛ ክፍል #2ኛ ሴሚስተር ላይ አባቴ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ውስጥ የስራ እድገት አገኘና ቤታችንን ከኩባ ሰፈር ወደ ሙገር መኮዳ ቀየርን ። መኮዳ ከኩባ ሰፈር በእግር ከ #30-40 ደቂቃ የሚፈጅ መንገድ ሲሆን በመኪና ደግሞ ከ #5 ደቂቃ አያልፍም ። ሰፈሩም መኮዳ የተባለው በድሮ ጊዜ እዚህ አካባቢ የኦዳ ዛፍ እንደነበር ይነገራል ። ለዛም ነው ሰፈሩ በአፋን ኦሮሞ Muka odaa /ሙከ ኦዳ (የኦዳ ዛፍ) የተባለው ። ከዛን ቀስ በቀስ ስሙ ከልጅ ልጅ ሲያልፍና ሲቆላመጥ መኮዳ ሆኖ ቀረ ። እና እዚህ ድሬዳዋ እስክመጣ ድረስ ለ #10 አመታት እዛው ነው ከቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ጋር ያሳለፍኩት ። መኮዳም ኩባ ሰፈርም ካምፕ ናቸው ። የፋብሪካው ሰራተኞችና ቤተሰቦች ብቻ የሚኖሩበት ሰፈር ። አብዛኛው የሙገር ሰው ግን የሚኖረው ሬጂ በሚባል የሙገር ከተማ ውስጥ ነው ። አስተዳደጌ ያንቺ ተቃራኒ ነው ። እቤት ውስጥ አባቴ ፣ እናቴ ፣ #3ቱ እህቶቼ እና አጎቴ ሆነን ነው የኖርነው ። እንዳንቺ ብቻዬን ለአመታት ይቅርና ለሰዓታትም አሳልፌ አላውቅም ። ቤተሰብ ፣ ዘመድ ፣ ጎረቤት ፣ ጓደኛ ፣ ሁሉንም አለኝ ። ሰፈር መንደሩ ያውቁኛል ፤ እኔም እንደዛው ። ምናልባት እኔና አንቺን የሚያመሳስለን ነገር ቢኖር የሲሚንቶ ሀገር ልጆች መሆናችን ነው ። ለነገሩ ምናችንም ሲሚንቶ አይመስልም ። ከአፈር እንደተሰራን እናስፎግራለን ። ባይሆን ግን ነጮቹ ከሲሚንቶ የተሰሩ ይመስሉኛል ። anyways ብዙም ባያኮራም ፣ ደስ የሚሉ ብዙ ታሪኮችን አሳልፌ አሁን ላይ ደርሻለሁ ። እንደ ምታዪኝ አሁን የግቢ ተማሪ ነኝ ። በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ #2ኛ ዓመት የመካኒካል እንጂኔሪንግ ተማሪ ነኝ' አልኳት እና ብዙ እንዳወራሁ ስለተሰማኝ ዝም አልኩ ። ቀጥላም "ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በመሆንህ ደስተኛ ነህ ...?" አለችኝ ። አኔም 'መጀመሪያ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ እንደደረሰን ስናውቅ በደስታ አብደን ነበር ። ከ #1 ክፍል ውስጥ #10 ተማሪ ነበር አንድላይ እዚህ የደረሰን ። እዛ ሆነን የጠበቅነው ነገርና ፡ እዚህ መጥተን ያየነው ምንም አይገናኝም ። ባጠቃላይ ስለ ድሬ ባጭሩ ሙዚቃዋ ሸወደን ማለት ይቻላል ። anyways አማራጭ ስለሌለኝና "ነገር ሁሉ ለበጎ ናቸው" በሚለው ቃል ስለማምን አሜን ብዬ ተቀብየዋለሁ' አልኳት ። መጠየቅ ትወዳለች መሠለኝ ፡ ጥያቄው ቀጥሏል ። "ይቅርታ ግን ፡ መጠየቅ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላውቅም ። እእእ ... ፍቅረኛ አለህ ...?"

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል...............