የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 16



"አንተን የሚመስል ሰው አውቃለሁ ፣ አንተን የሚመስል ዘመድ አለኝ ፣ እኛ ሰፈር አንተን የሚመስል ልጅ አለ ፣ ወዘተ" ነገሮችን ብዙ ሰዎች ሲሉኝ 'ይሆናል እንግዲህ የፈጣሪ ጥበቡ ብዙ ነው' ከሚል መልስ ውጪ ብዙም ትኩረት አልሰጠዋቸውም ነበር ። science እንደ ሚለው በአለማችን ላይ ከ #4 በላይ በመልክ የሚመሳሰሉ ሰዎች አሉ ። እኔን የሚመስል ሰው እስካሁን ባካል ባይገጥመኝም ፡ ከብዙ ሰዎች ግን እሰማ ነበር ። በዚህ ዓመት ብቻ #4 ሰዎች በቁምነገር እንደዛ ብለውኛል ። አንዱ ልጅ እንደውም መንገድ ላይ አስቁሞኝ "ባህር ዳር አውቅሀለሁ እኮ እንዴት ነህ ...?" ብሎኛል ። እኔ ግን ባህርዳርን በስም እንጂ በአካል አላውቃትም ። ከሁሉ ነገር ግን ያስገረመኝ ፡ እኔን የሚመስሉ #4ቱ ሰዎች የተገኙት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ። ቆይ ግን እንዴት እኔን የሚመስል ሰው ህንድ ወይንም ደግሞ Spain ውስጥ አልተገኘም ...? ሌላው ቢቀር ቢጠፋ ቢጠፋ እኔን የሚመስል ሰው ቱርክና brazil ውስጥ ይጠፋል ...? science እኮ ያለው በአለማችን ላይ እንጂ በአንድ ሀገር ውስጥ ብቻ አላለም ። anyways ምናልባት የኔ ሌላ የቀረ high copy ሰው ካለ ግን ባልኳቸው ሀገራት ውስጥ ባይገኙም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለበዛሁ ቻይና ወይ Nigeria ውስጥ ቢገኙ አይከፋኝም ። (ደግሞ ስቀልድ ነው ...) ። ሳሉት እስኪ እኔን የሚመስል ቻይናዊ ። (በናታችሁ አትሳሉት ...) ። ከከንቲባው ልጅ ጋር ያንን ሰውዬ አይተን አጣድፋኝ መኪና ውስጥ ገብተን ወደ ኩሪፍቱ ማረፊያ ክፍላችን ገብተን አረጋግቻት ሁሉን ነገር ከነገረችኝ በዋላ በሰጠችኝ ፎቶግራፍ ላይ ፈዝዤ ቀርቻለሁ ። እኔን የሚመስል ልጅ በአካል አይቼ ባላውቅም ዛሬ ግን በፎቶ አየሁኝ ። ሰው እንዴት በተለያየ ቦታና ከተለያየ ሰው ተወልዶ እንዲህ ሊመሳሰል ይችላል ...? አልኩኝ ለራሴ ። እውነትም የፈጣሪ ጥበቡ ብዙ ነው ። የከንቲባው ልጅ አንዴ ፎቶውን ፡ አንዴ ደግሞ እኔን እያየች ማውራቷን ቀጠለች ። "ለመጀመሪያ ጊዜ በመኪናዬ ውስጥ ሆኜ ሳይክ አቤልን ያገኘሁ ፤ በቃ ፈጣሪ የኔን ዕምባ አይቶልኝ ወደ ምድር የመለሰው ነበር የመሠለኝ ። ወርጄ ተጠመጠምኩብህ ፣ ሳምኩህ ፣ እጅህን ያዝኩህ ፣ አይኖችህን ጎበኘሁ ፣ አለቀስኩብህ ፣ አስጨነኩህ ፣ አዝነህልኝ እቤት ድረስ ይዘኸኝ መጣህ ፣ አወራሁክ ፣ አብረን ተመገብን ፣ ሳታውቀኝ ሳላውቅህ እቤት አሳደርኩህ ፣ ሀሳቤን ጭንቀቴን ነገርኩክ ፣ ሰማኸኝ ፣ ትምህርቴን ብለክ ብቻዬን አልተውከኝም ፣ ከአባቴም በላይ ቀርበኸኝ ለኔ ደስታ ስትል እዚህ ድረስ አብረኸኝ መጣህ ። አየህ ካየውክ ሰዓት ጀምሮ እንደ አቤል ስለማይክ መጥፎ ነገሮችን ማሰብ አልፈለኩም ። አላውቀውም ፣ ይጎዳኛል ፣ እንዴት ልመነው የሚሉ ነገሮች ውስጥ አልገባውም ። በቃ እንዳየውክ አመንኩህ ። የሚፈጠረው ነገር ሁሉ ይፈጠር ብዬ እራሴን አሳመንኩኝ ። እምነቴ ገደል አልገባም ፤ ካሰብኩህና ከጠበኩህ በላይ ሆነኽልኛል ። ይሄን ሁሉ ደግሞ የደበኩህ ማስታወስ የማልፈልገው ታሪኬ ስለሆነ ነው ። አሁንም የነገርኩህ ልክ እኔን ለመግደል አስበው አቤልን እንደ ገደሉት አንተንም እንዳይ ነጥቁኝ ስለፈራሁ ነው እሺ የኔ ጌታ" አለችኝና አሁኑኑ መተው የሚገድሉን ይመስል ተጠምጥማብኝ "ከዚህ ቤት ውስጥ አኖጣም እሺ ...?" ትለኛለች ። ነገሩ ትንሽም ቢሆን ቢያስፈራም ለማፅናናት ብዬ 'አንቺን እንደገደሉ ነው የሚያውቁት ፣ በዛላይ ከቤት ወተሽም ስለማታውቂና እዚህም በለሊት ስለሆነ ከድሬ የመጣነው በምንም ተዐምር ስላንቺ ሊያውቁ አይችሉም አይዞሽ' አልኳትና ተረጋጋች ።
.....
ሞትን ባልፈራም ፡ በዚህ ሰዓት ግን መሞት አልፈልግም ። ቁጥሩ ይብዛም ይነስም ወደፊት መኖር እፈልጋለሁ ፤ ግን ዛሬ መሞት አልፈልግም ፡ ነገም እንደዛው ። ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ከሞት አምልጫለሁ ። (ደግሞ በሩጫ አይደለም...😜) ። እናቴ እንደ ነገረችኝ ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞትን የተጋፈጥኩት ልጅ እያለሁ ነፍስ ሳላውቅ በሁለት ዓመቴ ነበር ። ታሪኩም እንዲህ ነው "የጠዋት ፀሀይ ለልጆች ጥሩ እንደሆነ የትኛውም ዶክተር ሳይነግራቸዉ እናቶች በራሳቸው ጥበብ ስለሚያውቁት ፡ እናቴም ጠዋት ከአልጋ ላይ አንስታኝ ግቢ ውስጥ ወደሚበራው የማለዳ ብርሃን አውጥታኝ እሷ ደግሞ እቤት ውስጥ ምሳ እየሰራች ነበር ። ቆሜም ፣ በዳዴም መሄድ አልጀመርኩም ። እንደዛ ለመሄድ ብዙ ዓመት እንደ ፈጀብኝ እናቴ ነግራኛለች ። እናቴ ምሳ እየሰራች ፡ በመሀል ደግሞ ደህንነቴን ለማረጋገጥ እየወጣች ታየኛለች ። አይኔ ተከድኗል ፣ ተኝቼ እንደሆነ ለማረጋገጥ ጠጋ ብላ በጆሮዋ ትንፋሼን ለመስማት ስትሞክር ምንም አይነት የመተንፈስ ነገር አልነበረም ። ልብ ምቴንም ስታዳምጠው ቆሟል ። ይሄኔ ነበር እናቴ ብቻዋን ማንም በሌለበት ሰፈር እምቧዋን ወደላይ መርጨት የጀመረችው ። የደም እምባ አለቀሰች ። እንዴት አሳይተኸኝ ትነሳኛለህ ብላ የፈጣሪ ልብስ ይመስል የመሬቱን ሳር ጭምድድ አርጋ ይዛ አነባች ። ምነው እመቤቴ ፡ የልጅን ፍቅር ካንቺ በላይ የሚያውቅ የለ ፤ ልጄን እኮ ባንቺ ቤት ክርስትና ማስነሳቴ በፍቅርሽ እንድታኖሪልኝ ነበር ፤ ምነው ታድያ ሳልጠግበው ነጠቅሽኝ እያለች አምርራ አለቀሰች ። በዚህ መሀል ግን እናቴ ከሷ ለቅሶ በተጨማሪ የሌላ ሰው የለቅሶ ድምፅ ሰምታ ዝም አለች ። ወደኔ ስታይ እኔ ነበርኩ የማለቅሰዉ ። ያቺ ቀን ለኔ ለደቂቃዎች ምድርን ለቅቄ ሰማይን ነክቼ ፡ ፈጣሪ ከእናቱ ጋር የእናቴን እምባ አይቶላት ድጋሜ ወደ ምድር የመለሰኝ እለት ነበረች" ። ተወልጄ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በጣም እታመም ነበር ። እንደውም ሀኪም ቤት በየቀኑ ከመመላለሴ የተነሳ ቂጤ በመርፌ ብዛት ወንፊት ይመስል ነበር አሉ ። በሽታው በግልፅ ባይታወቅም ፡ ለማስታገሻ ተብሎ ሁሌም መርፌ እወጋ ነበር ። በዚያ ምክንያት እንደውም ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ካየሁ ዶክተር ስለሚመስለኝ ኡ ኡ ታውን እንደ ምለቅ እናቴ ነግራኛለች ። ያን ቀን ግን ሞቼ ከተነሳሁ በዋላ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ አሞኝ ሀኪም ቤት ስሄድ ትዝ አይለኝም ። ያቺ እለት ለኔ ከሞት ወደ ህይወት ብቻ ሳይሆን ከህመም ወደ ሙሉ ጤንነት የተመለስኩባትም ናት ። ለ #2ኛ ጊዜ ደግሞ ከሞት አፋፍ ላይ የተመለስኩት ከ #5 ዓመት በፊት የጥምቀት በዓል ላይ ነበር ። በዓሉን ለማክበር ከጎረቤት ልጅ ቤቲ ጋር ተያይዘን ወደ ጥምቀተ ባህሩ ወረድን ። ቤቲ ለትምህርት እንዲያመቻት ወላጆቿ ጋር ሳይሆን ለት/ቤቱ ቅርብ በነበሩ ዘመዶቿ (ጎረቤታችን) ጋር ነው የምትኖረው ። በወቅቱ ደግሞ እሷ ኢዶ የሚባል ፍቅረኛ ነበራት ። ምክንያቱን ባላውቅም ወላጅ አባቷ ደግሞ ይሄን ነገር ሰምቶ ልጁን ሊገድለው ይፈልግ ነበር ። ሆኖም ግን የልጁን መልክ ለይቶ ስለማያውቅ የጥምቀት ቀን እኔንና ቤቲን አንድላይ አይቶን ኢዶ መስዬው ሽጉጡን አወጣና ሊገድለኝ ወደኛ አመራ ። ይሄኔ ነበር የቤቲ አሳዳጊ ጎረቤታችን ኡኡኡ እያለች እግሩ ስር ወድቃ "እሱ አይደለም ፣ ይሄ የአበቡ ልጅ ነው ፣ ይሄ የጎረቤት ልጅ ነው" ብላው ከሞት ያስጣለችኝ ።