የኛ ግጥም
44 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
​​😘የከንቲባው ልጅ😘
🔥ክፍል 40
ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
#ሊጠናቀቅ 1 የመጨረሻ ክፍል ብቻ ይቀረዋል..
ህይወት ለጊዜው ሆቴል ይዤ መረጋጋት ይኖርብኛል ብላኝ ነበር ። እኔ ግን ለብቻዋ እንድትሆን ስላልፈለኩኝ ከሷ ጋር ተቀራራቢ መልክ ካላት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ልጅ ID card ለምኜ ወደ ጊቢ ይዣት ገባሁ ። በር ላይ መታወቂያውን ልብ ብለው ስለማያዩት ማንም በማንም ሰው ID መግባት ይችላል ። በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትገባ ደንግጣ ነበር ። እንደ high school ጠባብ አይደለም ። በዛላይ ከ #15 ሺህ በላይ ተማሪዎች በአንድ ጊቢ ውስጥ ስለሚኖሩ ብዛታቸው ትንሽ ግር ይላል ። ሰዓቱም ወደ ምሽት እየተጠጋ በመሆኑ አብዛኛው ተማሪ ለእራት ከጊቢ እየወጣ ነበር ። ለተባበረችን ልጅ Id መልሼ ፡ እኛ እንደነገሩ ጊቢ ውስጥ ካለው ላውንጅ እራት በልተን ከዚህ በፊት ብቻዬን አዘውትሬ የምቀመጥባት ፣ ከማራኪዬ ጋርም ስልክ የማወራባት የነበረው ቦታ ወሰድኳት ። ቦታው ጨረቃን ወለል አድርጎ ከማሳየቱም በተጨማሪ ጭር ያለና ፀጥታ የሰፈነበት ፣ በዛላይ ደግሞ እራስን ለማዳመጥ በጣም አመቺ ነው ። "ሳልማር ዩኒቨርሲቲ ገባሁ አይደል...?" አለችኝ ህይወት በተከፋ ድምፅ ። እንዳይሰማት ብዬ 'እኛ ተምረን ይመስልሻል እዚህ የደረስነው ...? ዩኒቨርስቲ ከገባ ውስጥ #10% አይሆንም ተምሮና በራሱ ጥረት እዚህ የገባው ። አብዛኛው ኮርጆ ፣ አንዳንዱ ደግሞ ሳያስበው ነው እራሱን እዚህ ቦታ ላይ ያገኘው ። ዞረሽ ብትጠይቂያቸው "እኔ ለቤተሰቦቼ ብዬ ነው የምማረው ፡ እኔ ላይፉን ለማየት ነው የመጣሁት ፣ እኔ ከ famly ርቄ ነፃነቴን ለማግኘት ነው የመጣሁት ፣ ወዘተ ይሉሻል ። አላማ አለኝ ፣ ትምህርቴን ጠንክሬ ጨርሼ ለሀገሬና ለወገኔ እንደዚህ ላደርግ ነው የመጣሁት የሚልሽ በጣት የሚቆጠሩ ልጆች ብቻ ናቸው ። ታዲያ አንቺስ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ባለመግባትሽ ማመስገን እንጂ ማማረር ነበረብሽ ...?' አልኳት ። ደግሞም የምሬን ነው ። የከሰረ ትውልድ ይዛ ፣ ትርፍ ለማግኘት የምትሯሯጥ ሀገር ላይ ነን ። ይሄንን ትውልድ ማስተማር ያለብን physics ፣ chemistry ፣ biology ሳይሆን ትምህርት ምን እንደሆነ ፣ ምን ምን ጥቅም እንዳለው ፣ በወሬ ብቻ ሳይሆን በተግባር ጭምር ማሳየት አለብን ። ከሁሉ ነገር መቅደም ያለበት ለትምህርት ያለን ፍቅርና ፍላጎት ነው ። እሱ ላይ ከተሰራ ሌላው ሁሉ በራሱ ጊዜ ይመጣል ። ይሄ ትውልድ ትምህርት የሚለውን ቃል እራሱ መስማት አይፈልግም ። በቃ ከሰይጣን በላይ ጠልቶታል ። ስለዚህ የጠላውን ነገር በግድ ተማር ከምንለው ፡ ለምን እንደጠላ መርምረን ፣ ምን ብናደርግ ደግሞ መውደድ እንደሚችል አስበን ወደ ቀልቡ መመለስ የተሻለ ይሆናል ። እንዲሁ ስለ ዩኒቨርስቲ እያወራን እያለ #01:30 ላይ የህይወት አባት እቤት ገብተው አጧት መሠለኝ ስልኳ ላይ ደወሉ ። አንስታው እንድሰማቸው ነው መሠለኝ loud speaker ላይ አደረገች ። "የኔ ህይወት ፡ የት ሄደሽ ነው ፣ ከቤት አጣውሽ እኮ ...?" ሲሏት "አያይ ብዙም አልራኩም ፡ ባሌንና ልጄን አይቼ ለመመለስ ብዬ ነው" አለቻቸው ፈርጠም ብላ ። "ስለምን ባልና ልጅ ነው የምታወሪው ልጄ ...?" አሏት መልሰው ። ህይወትም ትንሽ የፌዝ ሳቅ እንደመሳቅ አለችና "ለካ አልነገርኩህም ፡ ባል አለኝ እኮ ፣ ለዛውም አንድ ቆንጂዬ ህፃን ልጅ ከሶስት ዓመት በፊት ወልደናል" አለቻቸው ። ምንም መልስ የለም ፣ ፀጥ ፡ ሴኮንዱ ይቆጥራል ፡ አሁንም ግን ምንም አይነት መልስ ከህይወት አባት አልመጣም ። ህይወት ዝምታው ሲበዛባት "አየህ ፡ ምንም መልስ የለህም ። ቆይ ግን እስከመች ነበር እኔን ለመደበቅ ያሰብከው ፣ እስከዘላለም ...? ንገረኛ ...? ለማንኛውም ከኔጋር ከምታሳልፈው ቅዳሜና እሁድ ይልቅ ከነሱ ጋር የምታሳልፋቸው አምስት ቀናት የተሻሉ ስለሆኑ እነሱ ይሻሉሀል ። ቆይ ግን ልጅ አለኝ ፣ ሚስት አለኝ ብትል የምቃወምህ መስሎህ ነበር ...?" ስትላቸው "የኔ ልጅ እቤት ተመለሺና እናውራ" ብለው ይማፀኗት ጀመር ። "ሶስት ዓመት ሙሉ እኮ እቤት ነበርኩ ። ያኔ የት ነበርክ ። ለማንኛውም አትፈልገኝ ፣ የተሻለ ቦታ ላይ ነው ያለሁት ። መገናኘት ሲያስፈልገን እራሴው እቤት እመጣለሁ" ብላ ስልኩን ዘጋችው ።ምንድነው ሰው ሁሉ ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ መላክ የመሰለው ፣ እንዴት ነው ሰማዩ እንዲህ ተጠቅልሎ በእጄ የምይዘው መሀረብ ያከለው ፣ ኧረ ምን ተዓምር ነው ፡ መሬት መዞር ትታ በእፎይታ ያቆማት ፣ ምንድነው ጨረቃን ከሰማይ አውርዶ ምድር ያሳረፋት...? እያልኩ አስባለሁ ። ደግሞም አላቆምም መልሼ መላልሼ አሁንም አስባለሁ ። ማነው በመንገዴ ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ ፣ ማንስ ነው ግማሽ ልቤን ሸርፎ የወሰደው ፡ በትልቁ ቆርሶ ፣ መንገደኛው ሁሉ የተከፋ ፊቱን በማን ተነጠቀ ፣ ከጨፍጋጋ ፊት ላይ እንዲህ ያለ ብርሃን እንዴት ፈነጠቀ ፣ ሚሊዮን ህፃናት ከልብ በሚነሳ ስርቅርቅ ድምፃቸው ፡ የት ቢዘምሩ ነው ልቤ ሚሰማቸው ፣ እኮ በምን ምክንያት ይህ ሁሉ ተቀየረ ፣ ያልነበረ ወደነበረ እንዴት ተመለሰ ...? እያልኩ አስባለሁ ። አሁንም አስባለሁ ። ምንድነው እንደዚህ ፊቴን በብርሃን ፡ ከንፈሬን በውብ ሳቅ የሚያጥለቀልቀው ፣ እንዴትስ ነው ከልቤ ኮለል ያለ ሰላም በጠዋት የሚፈልቀው ፣ የጠሉኝን ሁሉ ድንገት መውደዴ ፡ መሬቱን ለቅቄ አየር ላይ መንጎዴ ፡ ምንድነው ምስጢሩ ፣ ቆይ ውስጤን ምን ነካው ...? አለም እንዲህ ጠቦ በእርምጃ የሚለካው ፣ ውቅያኖስ በእፍኝ ተጨልፎ የሚደርቅ ፣ ተራራው በክንዴ ተጎሽሞ የሚደቅ ፣ ኧረ ምን ተዓምር ነው እያልኩ አስባለሁ ። እኔ ደግሞ ቤሳቤስቲን ሳንቲም ኪሴ ሳይጨመር ፣ ዓመት የለበስኩት ልብሴ ሳይቀየር ፣ የዘውትር ጉርሴ ጣዕሙ ሳይነካ ፣ እኔነት እኔ ውስጥ ተቀይሯል ለካ ። እኮ በምን ምክንያት እኔ ተቀየርኩኝ ፣ እንዴት እኔ ነኝ ስል ፡ እኔ ሌላ ሆንኩኝ እያልኩ አስባለሁ ። ለካስ ከህይወት ጋር ስለሆንኩኝ ነው ። ያውም ከአባቷ ተለይታ ከድሬዳዋ ለቃ ከዩኒቨርስቲ የዚህን ዓመት ትምህርት ጨርሼ ስመለስ አብራኝ ወደ ትውልድ ቦታዬ ወደ ሙገር መጥታ ። አሜሪካ እንደማትሄድ ለአባቷ አሳውቃ በሰላምና በዕንባ ተለያይተዋል

✎ የመጨረሻ ክፍል ይለቀቃል....
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................